02/10/2025
#እምነት
እምነት ማለት ምንም ሳይኖር በባዶ ተስፋ ያደረግነውን ነገር በተግባር እንዲናገኝ የሚያደርግ መለኮታዊ ኃይል የእግዚአብሔር ምስጢር ነው።
ኢየሱስ ክርስቶስ ሰማይንና ምድርን የሚታየውንም የማይታየውን ዓለም ሁሉ ሲፈጥር ዋው ይገርማል🤔 😳 ብሎ አልተደነቀም። ኢየሱስን ያስደነቀው ልጁ ሽባ ሆኖ የታመመበት አንድ ሮማዊ መቶ አለቃ ገዥ "ጌታ ሆይ ከቤቴ ጣራ በታች ልትገባ አይገባም ነገር ግን ቃልህን ብቻ ላኪ ልጄም ይድናል ስል የኢየሱስ ክርስቶስ ምላሽ ዋው እንዴት ያለ እምነት ነው? እንዲህ ያለ እምነት በእስራኤል እንኳን አላየሁም" ብሎ የመቶ አለቃውን እምነት ተደንቀዋል። ማቴዎስ 8:5-10 ላይ ታገኙታላችሁ 🙏
በሰው ልጆች አይን የማይታይ የማይመስል ነገር ይሆናል ብሎ በእምነት ተስፋ መጠባበቅ ያልነበረውን እንደነበረ ያደርጋል። እግዚአብሔርን ያለ እምነት ደስ ማሰኘት ስለማይቻል ምንም በሌለበት እምነታችሁ የፀና ይሁን 🙏