
07/03/2025
ፖሊስ በመስቀል አደባባይ ለሚደረገው ስብከተ ወንጌል ዝግ የሚሆኑ መንገዶችን ይፋ አደረገ
*****************
የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውንስል ከቢሊግርሃም ኢቫንጀሊስቲክ አሶሴሽን ጋር በመተባበር የካቲት 29 እና 30 ቀን 2017 ዓ/ም በመስቀል አደባባይ የስብከተ ወንጌል አገልግሎት መርሀ ግብር ይካሄዳል።
ይህንንም ተከትሎ መርሀ ግብሩ ተጀምሮ እስከሚጠናቀቅ የተወሰኑ መንገዶች ለተሽከርካሪዎች ዝግ እንደሚሆኑ የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል።
በዚህም መሠረት በሁለቱም ቀናት ከቀኑ 5:00 ሠዓት ጀምሮ ፕሮግራሙ እስኪጠናቀቅ ድረስ፦
ከኦሎምፒያ ወደ መስቀል አደባባይ (ኦሎምፒያ አደባባይ ላይ) ከጥላሁን አደባባይ ወደ ሳንጆሴፍ መብራት (ጥላሁን አደባባይ ላይ) ከለገሀር መብራት ወደ መስቀል አደባባይ (ለገሃር መብራት) ከቴሌ ማቋረጫ ወደ ስታድየም (ቴሌ ማቋረጫ ላይ) ከሀራምቤ መብራት ወደ መስቀል አደባባይ (ሀራምቤ መብራት ላይ ) ከብሔራዊ ቤተ መንግሥት ወደ መስቀል አደባባይ (ብሔራዊ ቤተመንግሥት ላይ) ከቅዱስ ዑራኤል አደባባይ ወደ መስቀል (ባምቢስ መቅረዝ ሆስፒታል መታጠፊያ) ላይ የሚዘጋ ሲሆን አሽከርካሪዎች አማራጭ መንገዶችን እንዲጠቀሙ የአዲስ አበባ ፖሊስ አሳስቧል።