
05/08/2024
እድገቴ በኢትዮጵያዊነት መንፈስ የተቃኘ ነው
የዛሬን ቀን ሀገር ውስጥ አለመኖሬ በጣም ይቆጨኛል በደስታው አብሮ መደሰት እንዳለ ሁሉ ወገን ሲያዝን አብሮ ማዘን ልቤ ላይ ያለ መርህ ነውና።
ውድ የጎፋ ቤተሰቦቼ ሆይ ኖሬ ናዳ የሸፈናቸውን ወገኖቼን አስሼ ባገኝ ሀዘኔ በጥቂቱም ቢሆን ይቆርጥልኝ ነበር።
በጣም አዝኛለው! የሀገሬ ልጆች ÷ በዚህ መሪር ሀዘን ለተጎዳችሁ ቤተሰቦች ÷ እንዲሁም ለመላው የኢትዮጵያ ህዝብ ፈጣሪ መፅናናቱን ያድል።
በድርጅታችን በወርቁ ፋውንዴሽን ስም በቦታው በመገኘት የተቻለንን እገዛ አርገን አጋርነታችንን ለማሳየት ዝግጁ ነን
#ወርቁ አይተነው