Dilla zuria worda police office

  • Home
  • Dilla zuria worda police office

Dilla zuria worda police office Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Dilla zuria worda police office, Media/News Company, .

11/01/2025
10/01/2025
10/01/2025
10/01/2025

ሳምንታዊ የትራፊክ አደጋ መረጃ

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ባሳለፍነዉ አንድ ሳምንት በበዓል ሰሞን ባጋጠሙ 8 የትራፊክ አደጋዎች የሁለት ሰው ህይወት ማለፉ ተገለፀ።

ወላይታ ሶዶ ጥር 1/2017 ዓ.ም (ደ.ኢ.ፖ.ኮ)
ባጋጠመዉ 8 የትራፊክ አደጋዎች በ6 ሰዎች ላይም ከባድ የአካል ጉዳት መድረሱን የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን የትራፊክ አደጋ መከላከልና ቁጥጥር ዳይሮክተሬት ገለፁ።

አደጋዎቹ የተመዘገቡት በክልሉ ዉስጥ ከሚገኙ 12 ዞኖች መካከል በ6ት ዞኖች ውስጥ ሲሆን በጌዴኦ በጋሞ በጎፋ በኮሬ በኮንሶና በአሪ እንደሆነም ተገልጿል።

በጌዴኦ ዞን በሁለት የተለያዩ ቀናት የትራፊክ አደጋዎች የተመዘገቡ ሲሆን የመጀመርያዉ አደጋ ከጨርሶ ወረዳ ወደ ኩራም ቀበሌ ሲጓዝ የነበረዉ ሞተር ሳይክል እግረኛ በመግጨት በ1 ሰዉ ላይ የሞት አደጋ ያደረሰ ሲሆን የአደጋዉ መንስኤ የብቃት ማነስ ነዉ ተብሏል።

ሁለተኛዉ የትራፊክ አደጋ ያጋጠመዉ በዲላ ከተማ አስተዳደር ዉስጥ ለዉስጥ ሲንቀሳቀስ የነበረዉ ሀይላክስ ደብል ገቢና ተሽከርካሪ እግረኛ በመግጨቱ የ1 ሰዉ ህይወት ያለፈ ሲሆን የአደጋዉ መንስኤ የጥንቃቄ ጉድለት መሆኑን መረዳዉ አመላክቷል።

በጋሞ ዞን ዉስጥ በአርባምንጭ ከተማ አስተዳደር ከሲቀላ ወደ ሴቻ በመጓዝ ላይ የነበረዉ ሞተር ሳይክል እግረኛ በመግጨት በ2 ሰዎች ላይ ከባድ የአካል ጉዳት ማድረሱ ሲገለፅ የአደጋዉ መንስኤ ለእግረኛ ቅድሚያ አለመስጠት ነዉ ተብሏል።

በጎፋ ዞን ኡባ ደብረ ፀሀይ ወረዳ ሻላ ትፎ ቀበሌ ዉስጥ መነሻዉን ጅንካ መዳረሻዉን ደግሞ አዲስ አበባ ያደረገዉ አይሱዙ የጭነት ተሽከርካሪ እግረኛ በመግጨት በ1 ሰዉ ላይ ከባድ የአካል ጉዳት ማድረሱ ሲመዘገብ የአደጋዉ መንስኤ የጥንቃቄ ጉድለት መሆኑን መረጃዉ አመላክቷል።

በኮሬ ዞን ኬሌ ከተማ አስተዳደር 02 ቀበሌ ዉስጥ ለዉስጥ ሲንቀሳቀስ የነበረዉ ሞተር ሳይክል እግረኛ በመግጨት በ1 ሰዉ ላይ ከባድ የአካል ጉዳት ለመድረሱ ምክንያት ሲሆን የአደጋዉ መንስኤ የብቃት ማነስ ነዉ ተብሏል።

በኮንሶ ዞንም በካራት ከተማ አስተዳደር ጋሞሌ ቀበሌ ከጃርሶ ወደ ወደ ካራት ከተማ በመጓዝ ላይ የነበረዉ ሞተር ሳይክል በመገልበጡ በ1 ሰዉ ላይ ከባድ የአካል ጉዳት የተመዘገበ ሲሆን የአደጋዉ መንስኤ የብቃት ማነስ መሆኑ ተገልጿል።

በኮሬ ዞን በዳኮ ዳዉላ ወረዳ ከፌላ ቀበሌ ወደ ገዜ ቀበሌ ሲጓዝ የነበረዉ ሞተር ሳይክል እግረኛ በመግጨቱ በ1 ሰዉ ላይ ከባድ የአካል ጉዳት ያጋጠመ ሲሆን የአደጋዉ መንስኤ የብቀት ማነስ ነዉ ተብሏል።

ባሳለፍነዉ አንድ ሳምንት ዉስጥ ካጋጠሙ 8 የትራፊክ አደጋዎች መካከል 6ቱ በባለሁለት እግር ሞተር ብስክሌት የተመዘገቡ መሆናቸዉን ዳይሮክተሬቱ ከላኩልን መረጃ ማወቅ ተችሏል።

ዘገባዉ የሪፖርተራችን ትዕግስት ከበደ ነዉ።

የህዳሴዉ  ግድብ ዋንጫ በዲላ ዙሪያ ወረዳ ፖሊስ እና ከወረዳ አመራሮች አቀባበል ተደረገ ጥር 01/05/2017 ዓ/ም(ዲ.ዙ.ወ.ፖ) የህዳሴ ግድብ ዋንጫ ከራጴ ወረዳ አስተዳደር ተረክቤን ለዲላ...
09/01/2025

የህዳሴዉ ግድብ ዋንጫ በዲላ ዙሪያ ወረዳ ፖሊስ እና ከወረዳ አመራሮች አቀባበል ተደረገ

ጥር 01/05/2017 ዓ/ም(ዲ.ዙ.ወ.ፖ)

የህዳሴ ግድብ ዋንጫ ከራጴ ወረዳ አስተዳደር ተረክቤን ለዲላ ዙሪያ ወረዳ ዋና አስተዳደር በፖሊስ አዛዥና የዲላ ዙሪያ ወረዳ ማሕበረሰብ አቀፍ ወንጀል መከላከል ኃላፍ አማካይነት እንድሁም የንግድ ማህበረሰብ በተገኙበት የርክክብ ስነስርዓት ተደረገ ።

የዲላ ዙሪያ ወረዳ ፖሊስ የ2016 በጀት ዓመት የስራ አፈፃፀም ግምገማ በማድረግ ላይ ይገኛል።      በግምገማ የወረዳ ከፍተኛ አመራሮች እና ከዞን ፖሊስ ከፍተኛ አመራሮች ተገኝተው በጋራ የ...
02/08/2024

የዲላ ዙሪያ ወረዳ ፖሊስ የ2016 በጀት ዓመት የስራ አፈፃፀም ግምገማ በማድረግ ላይ ይገኛል። በግምገማ የወረዳ ከፍተኛ አመራሮች እና ከዞን ፖሊስ ከፍተኛ አመራሮች ተገኝተው በጋራ የግምገማውን መድረክ እየመሩ እንደምገኙ ለማወቅ ተችለዋል። ዲላ ዙርያ ወረዳ ፖሊስ ጽ/ቤት

25/07/2024

02/07/2024
በገደኦ ዞን በዲላ ዙራ ወረዳ ፓሊስ ህገወጥ ኮንትሮባንድ መያዙ ተገለጸ።በቀን 24/10/2016 ዓም አሳቻ ክትትልና ቁጥጥር የዲላ ዙርያ ወረዳ ፓሊሰ በማድረግ በህገወጥ ሁነታ በባለ2/ሁለት /...
02/07/2024

በገደኦ ዞን በዲላ ዙራ ወረዳ ፓሊስ ህገወጥ ኮንትሮባንድ መያዙ ተገለጸ።

በቀን 24/10/2016 ዓም አሳቻ ክትትልና ቁጥጥር የዲላ ዙርያ ወረዳ ፓሊሰ በማድረግ
በህገወጥ ሁነታ በባለ2/ሁለት /ጎማ በምተር ሳይክል ተጭነው ስመላሌስ የነበረውን
የተለያዩ የልባሽ ጨርቅ፡የተለያዩ ጫማወች በግምት ሦስት መቶ ሺ ልሸጥ የምችል ንብረት
ተይዘው ለኢትዮጵያ ጉምርክ ለጭጩ ጣብያ
የታያዜውን ማስረከቡን የዲላ ዙርራ ወረዳ ፖሊስ
የልማት ዕቅድ አመራር የሆኑት ም/ኢ/ር ማቴዎስ ድዶ ገለጹ።

Address


Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Dilla zuria worda police office posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

  • Address
  • Alerts
  • Claim ownership or report listing
  • Want your business to be the top-listed Media Company?

Share