Rior ahmed

Rior ahmed Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Rior ahmed, Digital creator, .

05/06/2025
05/06/2025

ከማህበረሰቡ ጋር የተደረጉት ውይይቶች ስኬታማና ለቀጣይ ስራ ግብዓት የሚሆኑ ሀሳቦች የተነሱበት ነበር- አቶ ጌቱ ወዬሳ

ከማህበረሰቡ ጋር የተደረጉት ውይይቶች ስኬታማና ለቀጣይ ስራዎች ግብዓት የሚሆኑ ሀሳቦች የተነሱበት እንደነበር የሐረሪ ክልል ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ፅ/ቤት ሀላፊ አቶ ጌቱ ወዬሳ ገለፁ።

በሐረሪ ክልል ሁሉንም የህብረተሰብ ክፍሎች ባሳተፈ መልኩ ሲካሄድ የቆየውን የውይይት መድረክ አስመልክቶ በብልፅግና ፓርቲ የሐረሪ ክልል ቅ/ፅህፈት ቤት ሀላፊ አቶ ጌቱ ወዬሳ መግለጫ ሰጥተዋል።

በመግለጫውም ከህብረተሰቡ ጋር በተደረጉት የውይይት መድረኮቹ ባለፉት የለውጥ ዓመታት የተመዘገቡ ስኬቶች እና ውስንነቶች በጥልቀት ውይይት የተደረገባቸየው መሆኑን ገልፀዋል።

ውይይቱ በፖለቲካው፣ በማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ዲፕሎማሲያዊ ዘርፎች ላይ በተመዘገቡ ውጤቶችና የተስተዋሉ ውስንነቶች ላይ
ቀጣይ አቅጣጫዎች የተመላከቱበት እንደነበር ገልጸዋል።

በተለይ በኮሪደር ልማት በከተማና ገጠር የተከናወኑ የልማት ስራዎችን በተመለከተ የተሰጡ አስተያየቶች ለቀጣይ ስራዎች ግብዓት የተገኘባቸው ናቸው ብለዋል።

በውይይት መድረኮቹ ሊታረሙ ይገባል ተብለው የተነሱ የመልካም አስተዳደር፣አገልግሎት አሰጣጥ፣ የኑሮ ውድነትና ከወጣቶች ስራ እድል ፈጠራ ጋር በተገናኙ የተገመገሙ ውስንነቶችን
በዕቅድ በመያዝ ለመፍታት እንደሚሰራም ገልፀዋል።

መንግስት ከማህበረሰቡ የተነሱ ጥያቄዎችን ለመመለስ ይሰራል ያሉት አቶ ጌቱ ወዬሳ ማህበረሰቡ የጥላቻ ፖለቲካ ከሚያራምዱ ፅንፈኛ ሀይሎች ዕራሱን በማራቅ አንድነቱን ይበልጥ አጠናክሮ ሊያስቀጥል እንደሚገባ መልዕክት አስተላልፈዋል።

በተለይ ማህበረሰቡ ከመንግስት ጎን በመቆም የተጀመሩ የልማት ስራዎች በተያዘላቸው ግዜ እንዲጠናቀቁ አስፈላጊውን ድጋፍ ሊያደርግ ይገባል ብለዋል።

19/03/2025
16/06/2024
01/06/2024

"ሀረር ከተማን ዘመናዊ ከተማ ( Smart City ) የማድረግ ስራዎች ተጠናክረው ይቀጥላሉ" -አቶ ኦርዲን በድሪ

ሀረር ከተማን ስማርት ሲቲ ለማድረግ እየተከናወኑ የሚገኙ የተለያዩ ስራዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ የሀረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኦርዲን በድሪ ገለፁ፡፡

ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኦርዲን በድሪ እንዳሉት በተለይም በአሁኑ ወቅት ሀረር ከተማን የሚያዘምኑ የቴክኖሎጂ ሲስተምና መሰረተ ልማቶች እየተከናወነ ይገኛል ብለዋል።

ለዚህም ከኢትዮዽያ ስፔስ ሳይንስ እና ጂኦ ስፓሻል ኢንስቲትዩት ጋር በቅንጅት የሚሰራው የዲጂታል የአድራሻ ስርአት የኤሌክትሮኒክ ግብይትን ለማሳለጥ፣ የቱሪስት ፍሰቱን ለመጨመር፣ በአደጋ ጊዜ ፈጣን ምላሽ ለመስጠት፣ ለዘመናዊ ገቢ አሰባሰብ እና የንግድ ፈቃድ አሰጣጥ፣ ለአምቡላንስ እና እሳት አደጋ አገልግሎት መሻሻል ከፍተኛ እገዛ እንደሚያደርግ አንስተዋል።

በተጨማሪም ሀረር ከተማ ያላትን የቱሪዝም ሃብት የምታስተዋውቅበት ስማርት ሲቲ ቱሪዝም አፕሊኬሽን (መተግበሪያ) እና የቋንቋ መተርጉሚያ ሶፍትዌር ማበልፅግ መቻሉን ጠቅሰው ይህም ጎብኚው ባለበት ሆኖ በቀላሉ መረጃ እንዲያገኝ ያስችላል ነው ያሉት።

በሌላ በኩልም ከአጂፕ እስከ ደከር የሚሰራው ፕሮጀከት የመኪና፣ የሳይክል እና የእግረኛ መንገዶችን የያዘ የስማርት ሞቢሊቲ ጽንሰ ሀሳብን ማእከል ያደረገ መሆኑን ገልጸዋል።

የCCTV መሰረተ ልማት ቴክኖሎጂ የዜጎችን ደህነት እና የህግ የበላይነትን ከማረጋገጥ በተጨማሪ የአገልግሎት አሰጣጥን ለማሻሻል እና ሀረርን ተመራጭ የቱሪስት መዳራሻ ለማድረግ የሰነቅነውን ራእይ እውን ለማድረግ እገዛ ያደርጋል ሲሉም አክለዋል።

የመሬት ይዞታን በካዳስተር ስርአት መመዝገብ መሬት አስተዳደርን ለማዘመንና ከመሬት ጋር የተያያዙ ብልሹ አሰራሮችን እንዲሁም የመሬት ወረራን ለመከላከል የሚያስችል መሆኑን አብራርተዋል።

የውሃ መጠን መቆጣጠሪያ ስካዳ እና ቴሌሜትሪ እንዲሁም በየተቋሙ እየተሰሩ ያሉ አውቶሜሽን ስራዎችም ሀረር ዘመናዊ ከተማ( smart city) ለማድረግ እየተሰሩ ያሉ ተግባራት መሆናቸውን ገልፀዋል።

ከተማዋን በስትራቴጂ ልማት እቅድ በመምራት ከተማውን ሙሉ ለሙሉ ወደ ስማርት ሲቲ ለማሳደግ ወሳኝ ብለዋል።

ሀረርን ስማርት ሲቲ ለማድረግ የተጀመረው ስራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልፀው ይህም አገልግሎት አሰጣጥን የሚያሳልጥ፤ የከተማ መሠረተ ልማትን የሚያስፋፋ፤ ወጪን እና የሀብት ብክነትን የሚቀንስና የህዝብ ተጠቃሚነትን የሚያሳድግ እንዲሁም ዲጂታል ኢኮኖሚ ለመገንባት አቅም የሚፈጥር መሆኑን ጠቁመዋል።

ርእሰ መስተዳድሩ ሀረር ከተማን ስማርት ሲቲ ለማድረግ እየተከናወኑ የሚገኙ ስራዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ ጠቁመው በሚከናወኑ ስራዎችም ሁሉም ባለድርሻ አካላት በኃላፊነትና በቅንጅት መንቀሳቀስ እንዳለባቸው አሳስበዋል።

01/06/2024

የሐረር ከተማን ዘመናዊ የማድረግ ስራዎች ተጠናክረው ይቀጥላሉ -አቶ ኦርዲን በድሪ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 24፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የሐረር ከተማን ዘመናዊ ለማድረግ እየተከናወኑ የሚገኙ የተለያዩ ስራዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ የሀረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኦርዲን በድሪ ገለፁ፡፡

በተለይም በአሁኑ ወቅት ሀረር ከተማን የሚያዘምኑ የቴክኖሎጂ ስርዓቶች እና መሰረተ ልማቶች እየተከናወኑ እንደሚገኙ ርዕሰ መስተዳድሩ ተናግረዋል።

ለዚህም ከኢትዮዽያ ስፔስ ሳይንስ እና ጂኦ ስፓሻል ኢንስቲትዩት ጋር በቅንጅት የሚሰራው የዲጂታል የአድራሻ ስርዓት÷ የኤሌክትሮኒክ ግብይትን ለማሳለጥ፣ የቱሪስት ፍሰቱን ለመጨመር፣ በአደጋ ጊዜ ፈጣን ምላሽ ለመስጠት፣ ለዘመናዊ ገቢ አሰባሰብ እና ለንግድ ፈቃድ አሰጣጥ፣ ለአምቡላንስ እና እሳት አደጋ አገልግሎት መሻሻል ከፍተኛ እገዛ እንደሚያደርግ አንስተዋል።

በተጨማሪም ሐረር ከተማ ያላትን የቱሪዝም ሃብት የምታስተዋውቅበት ስማርት ሲቲ ቱሪዝም መተግበሪያ እና የቋንቋ መተርጎሚያ ሶፍትዌር ማበልፅግ መቻሉን ጠቅሰው ይህም ጎብኚው ባለበት ሆኖ በቀላሉ መረጃ እንዲያገኝ ያስችላል ነው ያሉት።

በሌላ በኩልም ከአጂፕ እስከ ደከር የሚሰራው ፕሮጀከት የመኪና፣ የሳይክል እና የእግረኛ መንገዶችን የያዘ የስማርት ሞቢሊቲ ጽንሰ ሀሳብን ማእከል ያደረገ መሆኑን ገልጸዋል።

የደህንነት ካሜራ መሰረተ ልማት ቴክኖሎጂ የዜጎችን ደህንነት እና የህግ የበላይነትን ከማረጋገጥ በተጨማሪ የአገልግሎት አሰጣጥን ለማሻሻል እና ሐረርን ተመራጭ የቱሪስት መዳራሻ ለማድረግ የሰነቅነውን ራዕይ እውን ለማድረግ እገዛ ያደርጋል ሲሉም አክለዋል።

የመሬት ይዞታን በካዳስተር ስርዓት መመዝገብ መሬት አስተዳደርን ለማዘመንና ከመሬት ጋር የተያያዙ ብልሹ አሰራሮችን እንዲሁም የመሬት ወረራን ለመከላከል የሚያስችል መሆኑን አብራርተዋል።

የውሃ መጠን መቆጣጠሪያ ስካዳ እና ቴሌሜትሪ እንዲሁም በየተቋሙ እየተሰሩ ያሉ አውቶሜሽን ስራዎችም ሐረርን ዘመናዊ ከተማ ለማድረግ እየተሰሩ ያሉ ተግባራት እንደሆኑ መግለፃቸውን የክልሉ ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመላክታል፡፡

01/06/2024

"ሀረር ከተማን ዘመናዊ ከተማ ( Smart City ) የማድረግ ስራዎች ተጠናክረው ይቀጥላሉ" -አቶ ኦርዲን በድሪ

ሀረር ከተማን ስማርት ሲቲ ለማድረግ እየተከናወኑ የሚገኙ የተለያዩ ስራዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ የሀረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኦርዲን በድሪ ገለፁ፡፡

ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኦርዲን በድሪ እንዳሉት በተለይም በአሁኑ ወቅት ሀረር ከተማን የሚያዘምኑ የቴክኖሎጂ ሲስተምና መሰረተ ልማቶች እየተከናወነ ይገኛል ብለዋል።

ለዚህም ከኢትዮዽያ ስፔስ ሳይንስ እና ጂኦ ስፓሻል ኢንስቲትዩት ጋር በቅንጅት የሚሰራው የዲጂታል የአድራሻ ስርአት የኤሌክትሮኒክ ግብይትን ለማሳለጥ፣ የቱሪስት ፍሰቱን ለመጨመር፣ በአደጋ ጊዜ ፈጣን ምላሽ ለመስጠት፣ ለዘመናዊ ገቢ አሰባሰብ እና የንግድ ፈቃድ አሰጣጥ፣ ለአምቡላንስ እና እሳት አደጋ አገልግሎት መሻሻል ከፍተኛ እገዛ እንደሚያደርግ አንስተዋል።

በተጨማሪም ሀረር ከተማ ያላትን የቱሪዝም ሃብት የምታስተዋውቅበት ስማርት ሲቲ ቱሪዝም አፕሊኬሽን (መተግበሪያ) እና የቋንቋ መተርጉሚያ ሶፍትዌር ማበልፅግ መቻሉን ጠቅሰው ይህም ጎብኚው ባለበት ሆኖ በቀላሉ መረጃ እንዲያገኝ ያስችላል ነው ያሉት።

በሌላ በኩልም ከአጂፕ እስከ ደከር የሚሰራው ፕሮጀከት የመኪና፣ የሳይክል እና የእግረኛ መንገዶችን የያዘ የስማርት ሞቢሊቲ ጽንሰ ሀሳብን ማእከል ያደረገ መሆኑን ገልጸዋል።

የCCTV መሰረተ ልማት ቴክኖሎጂ የዜጎችን ደህነት እና የህግ የበላይነትን ከማረጋገጥ በተጨማሪ የአገልግሎት አሰጣጥን ለማሻሻል እና ሀረርን ተመራጭ የቱሪስት መዳራሻ ለማድረግ የሰነቅነውን ራእይ እውን ለማድረግ እገዛ ያደርጋል ሲሉም አክለዋል።

የመሬት ይዞታን በካዳስተር ስርአት መመዝገብ መሬት አስተዳደርን ለማዘመንና ከመሬት ጋር የተያያዙ ብልሹ አሰራሮችን እንዲሁም የመሬት ወረራን ለመከላከል የሚያስችል መሆኑን አብራርተዋል።

የውሃ መጠን መቆጣጠሪያ ስካዳ እና ቴሌሜትሪ እንዲሁም በየተቋሙ እየተሰሩ ያሉ አውቶሜሽን ስራዎችም ሀረር ዘመናዊ ከተማ( smart city) ለማድረግ እየተሰሩ ያሉ ተግባራት መሆናቸውን ገልፀዋል።

ከተማዋን በስትራቴጂ ልማት እቅድ በመምራት ከተማውን ሙሉ ለሙሉ ወደ ስማርት ሲቲ ለማሳደግ ወሳኝ ብለዋል።

ሀረርን ስማርት ሲቲ ለማድረግ የተጀመረው ስራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልፀው ይህም አገልግሎት አሰጣጥን የሚያሳልጥ፤ የከተማ መሠረተ ልማትን የሚያስፋፋ፤ ወጪን እና የሀብት ብክነትን የሚቀንስና የህዝብ ተጠቃሚነትን የሚያሳድግ እንዲሁም ዲጂታል ኢኮኖሚ ለመገንባት አቅም የሚፈጥር መሆኑን ጠቁመዋል።

ርእሰ መስተዳድሩ ሀረር ከተማን ስማርት ሲቲ ለማድረግ እየተከናወኑ የሚገኙ ስራዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ ጠቁመው በሚከናወኑ ስራዎችም ሁሉም ባለድርሻ አካላት በኃላፊነትና በቅንጅት መንቀሳቀስ እንዳለባቸው አሳስበዋል።

13/05/2024

#የኢትዮጵያ #ጠቅላይ #ሚኒስትር #ክቡር #ዶ/ር

Address

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Rior ahmed posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

  • Address
  • Alerts
  • Claim ownership or report listing
  • Want your business to be the top-listed Media Company?

Share