
05/04/2025
ሰበር ዜና
ሾዴ "የመሮ ዋና ሰው ተገደለ"
የመሮ ዋናው ሰው የነበረው እንዲሁም በታንዛኒያው ድርድር ከጫካ ወጥቶ ታንዛኒያ ዳሬሰላም ድረስ ከመሮ ጋር ተጉዞ የሸኔ ሽብር ቡድን ተደራዳሪ የነበረው ሾዴ በተወሰደበት እርምጃ ሊገደል ችሏል። ሾዴ የተባለው የሽብር ቡድኑ አመራር ከታንዛኒያ መልስ የአጠቃላይ የወለጋ ዞኖች አዛዥ ተደርጎ በመሮ ተሹሞ የነበረ ነው። ሾዴ የተገደለው ምስራቅ ወለጋ ዞን ሃሮ ሊሙ ወረዳ ገንጂ አካባቢ ከኮርማ ወንዝ ወደ ሱጊ በሚወሰድ መንገድ ላይ በሞተር ሳይክል ተደብቆ ሲጓዝ የፀጥታ ኃይሎች ባገኙት መረጃ በ26/07/2017 ዓ/ም አመሻሽ ላይ እርምጃ ወስደውበት ከሱ ጋር የነበሩትን ጨምሮ በርካቶች አጅበው ሲጓጓዙ የነበሩት ተደምስሰዋል።