16/04/2025
የብርቱካን ጉዳይ ለምን ይህን ያክል ትኩረት አገኘ
ሰዎች በማወቅም ሆነ ባለማወቅ በEBS የተላለፈው የብርቱካን script እና film ለምን ይህን ያክል ትኩረት አገኘ በማለት ጥያቄ ያነሳሉ ፤ ነገር ግን ይህ ታሪክ ሲመረጥ እና እንዲሰራጭ ሲፈለግ ትልቅ ጥፋት አንግቦ እንደ ሆነ መርሳት የለብንም ። የብርቱካን ጉዳይ ፊልም መሆኑን እና ምንም እውነት እንደሌለው በመንግስት እና በሰጥታ ሃይሎች ብርቱ ስራ ተጋለተ እንጂ ፅንፈኞች ይህን ነገር ሲያዘጋጁ ታሪኩን ሲመርጡ በዘፈቀደ አይደለም ፤ ከዚህን በፊትም በወለጋ ተገደልኩ ፣ ታረድኩ ፣ ደመን ጠጡ ፤ በደራ አሮሞ እና አማራን ለማገጨት ተገደልን ፣ ተጨፈጨፍን በማለት አጸያፊ ትሪክት ለመፍጠር ተሞክሯል ።
ስለዚህ የብርቱካን ጉዳይ አንድ የውሸት ትሪክት ብቻ ሳይሆን በዚህ መልኩ የተሰሩ ሀገርን የሚረብሹ ፣ ህዝብን የሚያስቆጡ የብዙ የበሬ ወለደ ፈጠራ ማሳያ ስለ ሆነ ነው ። ህዝባችን የሆነ ነገር ሲሆን ለምን ሆነ ፣ እንዴት ሆነ ፣ ማን አደረገ ብሎ በመጠየቅ የጽንፈኞችን ሴራ እንዲያከሽፍ በብዙ ትህትና እጠይቃለው ።