Amhara Today

Amhara Today Peace for Amhara people

ሲነግሩት ያልሰማን ሲሰማ ቅበረዉ ይላል የሃገሬዉ ሰዉ!በትናንትናዉ እለት የመንግስትን ተደጋጋሚ የሰላም ጥሪ  ያልተቀበሉት ጽንፈኞች የአፈሙዝ ራት ሁነዋል።ከእነዚህ መካከል የፅንፈኛዉ ከፍያለው...
19/07/2025

ሲነግሩት ያልሰማን ሲሰማ ቅበረዉ ይላል የሃገሬዉ ሰዉ!

በትናንትናዉ እለት የመንግስትን ተደጋጋሚ የሰላም ጥሪ ያልተቀበሉት ጽንፈኞች የአፈሙዝ ራት ሁነዋል።

ከእነዚህ መካከል የፅንፈኛዉ ከፍያለው ደሴ ታነሽ ወንድም የሱን ሀላፊነት ተቀብሎ ሻለቃ በመሆነረ በታች ጋይንት ጽንፈኛዉን ሲመራ እና ሲያስተባብር በትናትነው እለት ተደምስሷል።

በታች ጋይንት ወረዳ በአቄቶ ቀጠና የሻለቃ አመራር ሆኖ ንፁሀንን የገደለ ንብረት ሲዘርፍ የነበረው ፅንፈኛ/አዝማሪ አስናቀው ትናንትናዉ እለት እርምጃ ተወስዶበታል።

ሌላኛዉ ኮማንዶ አትክልት እባቡ ትናንት በነበረው ህግ የማስከበር እርምጃ በታች ጋይንት በጥምር ጦሩ ተደምስሷል።

 #ሰበርባበይ ስጠኝ(ዋግነር )ብሎ ራሱን የሰየመው የፅንፈኛ ቡድን መሪ ተብየ ከዚህ በፊት ልዩ ኃይል የነበረና ወደ ፅንፈኛው ቡድን በመቀላቀል ህዝብን ሲያሰቃይ ሲገድል የነበረ የፅንፈኛ መሪ ...
18/07/2025

#ሰበር

ባበይ ስጠኝ(ዋግነር )ብሎ ራሱን የሰየመው የፅንፈኛ ቡድን መሪ ተብየ ከዚህ በፊት ልዩ ኃይል የነበረና ወደ ፅንፈኛው ቡድን በመቀላቀል ህዝብን ሲያሰቃይ ሲገድል የነበረ የፅንፈኛ መሪ አሰፍስፎ ሲመጣ ደልጊ ላይ ተቀንድሿል።

በትናንትናው እለት በማዕከላዊ ጎንደር ዞን በጣቁሳ ወረዳ ደልጊ ከተማን ለመዝረፍ በሶስት አቅጣጫ አሰፍስፎ የመጣው ፅንፈኛ ቡድን በሀገር መከላከያ ሰራዊቱና በክልሉ የጸጥታ ሃይል ልዩ ጥምረት ከፍተኛ ኪሳራ ደርሶበታል።

ጽንፈኛ ቡድኑ እራሱን የደረጃ በላይ ቡድን ብሎ የሚጠረው ፅንፈኛ ሃይል በሻለቃ ውበት እና ባበይ ስጠኝ(ዋግነር )ብሎ ራሱን የሚጠራው ፅንፈኛ ቡድን በአይንባ (ሰቀልት) አካባቢ ህዝብን ሲያሰቃይ ሲዘርፍ ሲገድል የነበረ ሲሆን ደልጊ ላይ ተቀንድሿል።

ጥምር ጦሩ በወሰደው የማጥቃት እርምጃም የጽንፈኛ ቡድኑ ከነ መሪያቸው እና አባላቸው ላይ ከፍተኛ ኪሳራ አድርሶበታል።

በዚህም 3 የሻለቃ መሪ ነን የሚሉ እና 15 አባላቸው እስከወዲያኛው ተሸኝተዋል። በርካቶች ቆስለዋል፤ ቀሪው ደግሞ እግሬ አውጭኝ ብሎ ወደየመጣበት ፈርጥጧል።

ጽንፈኛን የማጽዳቱ ስራ ተጠናክሮ ቀጥሏል!ጽንፈኛን የማጽዳቱ ስራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ተናግሬ ነበር!ትናንት እና ከትናንት በፊት በደጋ ዳሞት ለመርዶ ነጋር ሳይተርፍ የረገፈዉ ጽንፈኛ ቡድን ...
16/07/2025

ጽንፈኛን የማጽዳቱ ስራ ተጠናክሮ ቀጥሏል!

ጽንፈኛን የማጽዳቱ ስራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ተናግሬ ነበር!

ትናንት እና ከትናንት በፊት በደጋ ዳሞት ለመርዶ ነጋር ሳይተርፍ የረገፈዉ ጽንፈኛ ቡድን ዛሬ ደግሞ ወረፋዉ ደርሶት በእብናት እንደቅጠል እየረገፈ ነዉ።

ይህ ቡድን በቡሬ እና በላሊበላ አካባቢም በያለበት እየተለቀመ የተረፈዉ እግሬ አዉጭኝ ብሎ መፈርጠጡ የቅርብ ጊዜ ትዉስታ ነዉ።

መንግስት ስለሰላም ሲሰብክ ራሱን አቅም እንዳለዉ ቆጥሮ የራሱን ህዝብ እየዘረፈ የሚገኘዉ ይህ እኩይ ቡድን በጀግናው የመከላከያ ሰራዊትና የክልሉ የጸጥታ ሃይል በየደረሰበት እንደ እባብ እየተቀጠቀጠ ነዉ።

በጽንፈኛዉ እየደረሰበት ያለዉ ዝርፊያ፣ እገታና እንግልት ያንገበገበዉ የአማራ ህዝብ ከያሉበት እያነቀ እና እየጠቆመ ለመከላከያ ሰራዊት እያስረከባቸዉ ነዉ።

ተመሳሳይ ኦፕሬሽን በሁሉም የክልሉ አካባቢዎች ተናክሮ እንደሚቀጥልም መረጃዉ ደርሶኛል።

#ሰላም

ይህ አሳዛኝ ምስል በሰሜኑ ጦርነት ወቅት ከደረሱኝ የጦርነትን አስከፊነትና አሰቃቂነት እንድገነዘብ ካደረጉኝ ምስሎች አንዱ ነዉ።በዚህ ወቅት ትህነግ የትግራይን ህዝብ ከሊቅ እስከደቂቅ አሰልፌ ...
15/07/2025

ይህ አሳዛኝ ምስል በሰሜኑ ጦርነት ወቅት ከደረሱኝ የጦርነትን አስከፊነትና አሰቃቂነት እንድገነዘብ ካደረጉኝ ምስሎች አንዱ ነዉ።

በዚህ ወቅት ትህነግ የትግራይን ህዝብ ከሊቅ እስከደቂቅ አሰልፌ የማዕከላዊ መንግስቱን እቆጣጠራለሁ ብሎ በማሰብ በተሳቢ ጭኖ ወደ ጦር ሜዳ ይልክበት የነበረ ጊዜ ነዉ።

ታዲያ እነዚህን ወጣቶች በወቅቱ "ጦርነቱ አብቅቷል እናንተን የምንልከዉ ትግሉን ለማጠናቀቅና የግል ሃብትም እንድታገኙ ነዉ" በሚል የተሳሳተ ፕሮፓጋንዳ ነበር በተሳቢ ጭኖ የላካቸዉ።

እዉነታ ግን ይሄ ሳይሆን ጦርነትን እንደ ፖለቲካ ገበያ በሚጠቀመዉ ትህነግ የተላኩት ወጣቶቹ ጦር ሜዳ እንኳን ሳይደርሱ መንገድ ላይ ህልማቸዉ መክኖ ወደ አመድነት ተቀይረዉ ተገኙ።

ትህነግ ግትር አስተሳሰብ ያለዉ ከኔ መስመር ዉጭ ከሆነ አገር ትፍረስ የሚለዉ አቋሙ ከጫካ ጀምሮ እስከዛሬ አልተቀየረም። ይሄዉ ዛሬም እንደትናንቱ የመቀስቀሻ ፕሮፓጋንዳዉን እንኳ ሳይቀይር የትግራይ ወጣቶችን ለዳግም እልቂት እያዘጋጀ ነዉ።

በርግጥ አሁን ላይ እነሱም እንደመሰከሩት በክልሉ ዉስጥ ታይቶ በማይታወቅ መንገድ የወያኔ አረመኒያዊ ድርጊት የገባዉና የጠቅላይነትና የእኔ አዉቅልሃለሁ ሗላ ቀር የፖለቲካ አስተሳሰብ ያንገሸገሸዉ የትግራይ ወጣት ትህነግን ለመዉጋት አሰፍስፎ እየጠበቀ ነዉ።

ግን ቡድኑ ትህነግም አይደል ያለ ጦርነት ቀኑ መሽቶ አይነጋለትም ያልነቁ ወጣቶችን ማግዶ የጥይት ራት ማድረጉ አይቀሬ ነዉ።

ለዚህ ቡድን እድሜ ማራዘሚያ ሲባል ግን ስንት የትግራይ ወጣት ነዉ የሚያልቀዉ?

11/07/2025

"ትህነግ ሚባለው ሰዉ እየበላ ያደገ፤ ሰዉ እየበላ የሞተ ድርጅት ነዉ" ኮረኔል ደመቀ ዘዉዱ

ትህነግ ሞክሮ የከሸፈበትን ፕሮፓጋንዳ ጽንፈኞች አንስተዉ መጫወት ጀምረዋል፤ከሰሞኑ  ኬንያ ዉስጥ  የተቃጠሉ ሞተሮችን የመንግስት የጸጥታ አካላት በምዕራብ ጎጃም ዞን ደጋ ዳሞት ወረዳ እንደፈጸ...
02/07/2025

ትህነግ ሞክሮ የከሸፈበትን ፕሮፓጋንዳ ጽንፈኞች አንስተዉ መጫወት ጀምረዋል፤

ከሰሞኑ ኬንያ ዉስጥ የተቃጠሉ ሞተሮችን የመንግስት የጸጥታ አካላት በምዕራብ ጎጃም ዞን ደጋ ዳሞት ወረዳ እንደፈጸሙት በማስመሰል ማራገብ ከጀመሩ ሰነባብተዋል።

ይሄን መሰል ማደናገሪያ አጀንዳ ትህነግ በሰሜኑ ጦርነት ደጋግሞ ሞክሮት የከሸፈበት አጀንዳ እንደነበር አይረሳም።

ምናልባት ትህነግ ከአሮጌ መሳሪያዉ ጋር ያረጀ ፕሮፓጋንዳም አብሮ ይሸጥላቸዉ ይሆን ያስብላል።

ሲመጡ ሩጡ! በሚል የትግል መርህ የሚማረክ ወታደርስ ከወዴት ይገኛል! እየሮጡ ሱሪን መደገፍም ስራ ነዉ!

እየተዋወቅን!

ትህነግ የአማራን ህዝብ ደም ዳግም ለማፍሰስ ጦር እየደገሰ ነዉ!ትህነግ በትግራይ ህዝብ ስም ባደራጃቸዉ ምልምል ዘር መርጦ ገዳዮች(ሳምሪ) በማይካድራና በጭና ለመርዶ ነጋሪ ሳይተርፉ የንጹሀንን...
21/06/2025

ትህነግ የአማራን ህዝብ ደም ዳግም ለማፍሰስ ጦር እየደገሰ ነዉ!

ትህነግ በትግራይ ህዝብ ስም ባደራጃቸዉ ምልምል ዘር መርጦ ገዳዮች(ሳምሪ) በማይካድራና በጭና ለመርዶ ነጋሪ ሳይተርፉ የንጹሀንን ደም አፍሷል።

ይህ ታሪክ ሩቅ አይደለም ብቻ ሳይሆን በአማራነታቸዉ ዋጋ የከፈሉና የተሰዉ ወገኖቻችን መቃብር ገና ሳር አልበቀለበትም ብል ማጋነን አይሆንም።

የአማራ ህዝብ በታሪኩ በርካታ ፈተናዎች የገጠሙት ቢሆንም የማይካድራ አይነቱ የዘር ጭፍጨፋ ገጥሞት አያዉቅም። ይሄን አስከፊ ታሪክ ለግል የፖለተካ ንግድ ሊያዉሉ የሚፈልጉ እኩይ ቡድኖች የፈሰሰዉን ደም፣ የተከሰከሰዉን አጥንት ወደጎን በመተዉ ከወያኔ ጋር ያለ አቻ ጋብቻ ፈጽመዋል።

ይህ አይነቱ የፖለተካ ቁማር የወጡበትን ህዝብ መሸጥ ብቻ ሳይሆን አጋድሞ ከማረድ ያልተናነሰ የእፉኝት ባህሪ ነዉ።

እኔም እላችሗለሁ ወያኔስ አንዴ ጠላት ነዉ፤ የወያኔ ፈረስ በመሆን ግን በራሳችሁ ላይ ህዝብ ይቅር የማይለዉ ጥቁር ታሪክ አትጻፉ መልዕክቴ ነዉ።

ቀበሮ የበሬ ብልት ይወድቃል ብላ ስትከተል ዋለች አሉ:-ሊበላ😂ጽንፈኛዉ ቡድን የአማራ ክልል መሪዎችን የመብላት ህልሙ ቅዠት ሁኖ ቀርቷል። ትናንት ጎርጎራ ላይ ሂሊኮፍተር መትቸ ጣልኩ መሪዎችን...
16/06/2025

ቀበሮ የበሬ ብልት ይወድቃል ብላ ስትከተል ዋለች አሉ:-ሊበላ😂

ጽንፈኛዉ ቡድን የአማራ ክልል መሪዎችን የመብላት ህልሙ ቅዠት ሁኖ ቀርቷል። ትናንት ጎርጎራ ላይ ሂሊኮፍተር መትቸ ጣልኩ መሪዎችንም ገደልኩ እያለ መንጋዉን ጮቤ ሲያስረግጥ አምሽቷል።

ይህ ቅዠቱ መክኖ በዛሬዉ እለት መሪዎች ዉቢቷ ባህርዳር ላይ ሲጎማለሉ፤ የደከሙበትን የጣና ዳር ኮሪደር ሲጎበኙ ዉለዋል።

መንጋዉም ኩም ብሎ የሚይዘዉ የሚጨብጠዉ አጧል። መሪዎችም ከባህርዳር ህዝብ ጋር የሆድ የሆዳቸዉን እያወጉ ይገኛል።

ኑ አብረን እንፈር😂

31/05/2025

31/05/2025

ጀዋር ለምን በማይወደዉ አማረኛ ጽፎ ከማይደዉ እና ካስጨፈጨፈዉ ህዝብ ጎን ቆመ🤔

ራያና የአማራ ክልል መሪዎች!ሰላምን የናፈቀ ህዝብ፤ የሰላም አምባሳደር ከሆኑ መሪዎቹ ጋር መከረ!ህዝቡም ህግ አስከብሩልን፤ ማንነታችን አጹኑልን ሲል ለመሪዎቹ ሀሳቡን በአደባባይ ገለጸ። የዉጭ...
26/05/2025

ራያና የአማራ ክልል መሪዎች!

ሰላምን የናፈቀ ህዝብ፤ የሰላም አምባሳደር ከሆኑ መሪዎቹ ጋር መከረ!

ህዝቡም ህግ አስከብሩልን፤ ማንነታችን አጹኑልን ሲል ለመሪዎቹ ሀሳቡን በአደባባይ ገለጸ።

የዉጭ ተልዕኮ የተሸከሙ ማንነታችን ለፖለቲካ ንግድ ሊያዉሉ የሚፈልጉ አካላት አርሰን እንዳንበላ፣ ያመረትነዉን ለገበያ እንዳናቀርብ፣ ነግደን እንዳናተርፍ፣ ልጆቻችን እንዳይማሩ፣ ተዘዋዉረን እንዳንጠያየቅ አቀቡን፣ መንግስትን በአቅራቢያችን አግኝተን የልማት እና የማንነት ጥያቄያችን እንዳናነሳ ከለከሉን ሲል ደጋግሞ የራያ ህዝብ በምሬት ለመሪዎቹ ገለጸ።

መሪዎችም አዳመጡት፤ ለህዝቡ ሰላምና የማንነት ጉዳይ ላይ የቅድሚያ ቅድሚያ ሰጠዉ እንደሚሰሩ ቃል ተጋብተዉ ተለያዩ።

ህዝብና መሪ እንዲህም አይደል!!!

#ሰላም

24/05/2025

የህወሓት የፖለቲካ ግልሙትና በቴዲ አንደበት🤔

Address


Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Amhara Today posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

  • Address
  • Alerts
  • Claim ownership or report listing
  • Want your business to be the top-listed Media Company?

Share