Tsehay press

Tsehay press Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Tsehay press, Digital creator, .

26/09/2026
14/09/2026

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ እና ፕሬዚዳንት ፑቲን አንድ ላይ ተጉዘው ወደ ስብሰባ ሲገቡ

Prime Minister Abiy Ahmed and President Vladimir Putin travel together to a meeting in New Delhi

አዲስ አበባ የ2027 የብሪክስ (BRICS) ጉባኤ ለማስተናገድ አዲስ ታሪካዊ ምዕራፍ ላይ ናትኢትዮጵያ የተቀላቀለችውና በፍጥነት በማደግ ላይ ያሉ የዓለም ሀያላን ሀገራት ጥምረት የሆነው ብሪክ...
12/09/2026

አዲስ አበባ የ2027 የብሪክስ (BRICS) ጉባኤ ለማስተናገድ አዲስ ታሪካዊ ምዕራፍ ላይ ናት

ኢትዮጵያ የተቀላቀለችውና በፍጥነት በማደግ ላይ ያሉ የዓለም ሀያላን ሀገራት ጥምረት የሆነው ብሪክስ (BRICS) እ.ኤ.አ. የ2027 የመሪዎች ጉባኤውን በአፍሪካ መዲና አዲስ አበባ ለማስተናገድ መሰናዳቱ ለሀገራችን ትልቅ የዲፕሎማሲና የኢኮኖሚ ስኬት ነው። ኢትዮጵያ የሕብረቱ አባል በሆነች በአጭር ጊዜ ውስጥ ይህንን ታላቅ የዓለም አቀፍ መሪዎች ስብሰባ እንድታዘጋጅ መመረጧ በዓለም አቀፍ መድረክ ያላትን ተቀባይነት፣ ስትራቴጂካዊ ቦታና የዲፕሎማሲ ተፅዕኖ በግልጽ የሚያሳይ ነው።

በተጨማሪም የታዳጊ ሀገራትንና የአፍሪካን ኢኮኖሚያዊ ፍላጎት በዓለም አቀፍ ደረጃ በግንባር ቀደምትነት ለማስከበር የሚያስችላትን ታሪካዊ ኃላፊነትና ዕድል ያጎናጽፋታል።

ይህ አጋጣሚ ከአህጉራዊ ውክልና ባሻገር ለሀገሪቱ ዘርፈ ብዙ የኢኮኖሚ ጥቅም ይዞ ይመጣል። የዓለማችንን ግዙፍ ኢኮኖሚዎች የሚመሩ ሀገራት መሪዎች፣ የንግድ አበጋዞችና በርካታ ልዑካን ወደ አዲስ አበባ መምጣታቸው ለውጭ ኢንቨስትመንት፣ ለቱሪዝም፣ ለሆቴልና አገልግሎት ዘsector ትልቅ የገበያ መነቃቃት ይፈጥራል።

ጉባኤውን ተከተሎ የሚከናወኑ ዝግጅቶች የከተማዋን መሠረተ ልማትና የአገልግሎት አሰጣጥ አቅም ወደ ላቀ ደረጃ የሚያሸጋግሩ በመሆናቸው፣ ዝግጅቱ የአዲስ አበባን የዓለም አቀፍ ኮንፈረንስ ማዕከልነት ያረጋገጠ ሌላው ታላቅ የሀገራችን ስኬት ነው።

02/09/2026
በኢትዮጵያ የሚገኙ የአርሰናል ደጋፊዎች ክለባቸዉ ከ22 ዓመታት በኋላ የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ዋንጫ ማንሳቱን ምክንያት በማድረግ እንዲሁም የቀድሞ የአርሰናል ተጫዋች ኢማኑኤል ኢቦዬን እና የ...
06/06/2026

በኢትዮጵያ የሚገኙ የአርሰናል ደጋፊዎች ክለባቸዉ ከ22 ዓመታት በኋላ የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ዋንጫ ማንሳቱን ምክንያት በማድረግ እንዲሁም የቀድሞ የአርሰናል ተጫዋች ኢማኑኤል ኢቦዬን እና የAFTV ሚድያ አባላት በአዲስ አበባ ስታድዮም አሁን-በፎቶ!

ወንዝና ከተማ።የአካባቢያችሁን ወንዞች አስቧቸው አሁን ምን ላይ ናቸው? አዲስ አበባ ወንዟ ዳር የከተማ ሳፋሪ ዕውን አድርጋለች። ***(ተጓዡ ጋዜጠኛ ሄኖክ ስዩም - ለድሬ ቲዩብ)የት ነበር ዋ...
13/01/2026

ወንዝና ከተማ።
የአካባቢያችሁን ወንዞች አስቧቸው አሁን ምን ላይ ናቸው?
አዲስ አበባ ወንዟ ዳር የከተማ ሳፋሪ ዕውን አድርጋለች።
***
(ተጓዡ ጋዜጠኛ ሄኖክ ስዩም - ለድሬ ቲዩብ)

የት ነበር ዋኝታችሁ ያደጋችሁት? ቀበና ወይስ በሰቃ? ቦርከናዎች ናችሁ ባሮዎች? ወይስ ቀሃ የዋኛችሁ? ኩልፎ ነው ትዝታችሁ? አዌቱ? ቡልቡላ ነን የምትሉት ወይስ ደግሞ ጪጩ?

ለንደን በቴምዝ፣ ፓሪስ በሴይን፣ ካይሮ በናይል ላይ እንደ ደመቁት በዓለም ላይ ካሉት ጥንታዊ ከተሞች እና አብዛኛዎቹ ዋና ከተሞች በወንዞች ዳርቻ ያደጉ ናቸው። የእኛስ የወንዝ ዳርቻዎች ብንል እነሱም ከተማ አፍርሰዋል ከተማውም ወንዞቹን አንጥፏል።

ያም ሆኖ ባለ ወንዝ ነን። ከተሞቻችን ከወንዝ አልራቁም። ዋኝተናል፣ አዋሽ እንኳን የስንት ከተሞቻችን ጌጥ ነው። የጎርጎ ልጆችን ያዝናና እስከ አቦ ምሳ ያጌጥንበት፣ የወረር መልክ፣ የሰዲ ገፅ፣ ከዱብቲና አሳይታ የማይነጠል።

እሺ ይርጋለም ያለ ወይማ ምንድን ነው? ማርቆስስ ያለ ውትርን? ኮሶኮል የሚዛን ወዝ አይደለምን? እኮ የት ነበር ወንዛችሁ? የትስ ዋኛችሁ? ላህ ለፍኖተ ሰላም መልኳ ነው። አምቦ በሁሉቃ ጥሟን ጭምር ቆርጣለች።

እኔ አንጅሶና አቃቂ እስከ ጀሞ የዋኘሁ የአዲስ አበባ ልጅ ነኝ። የወንዝ ውበትም የወንዝ ግማትም ጣጣው ምን እንደሁ አውቃለሁ። አሜሪካዊው ፕሮዲዩሰር Ted Turne "Rivers are places that renew our spirit, connect us with our past, and link us directly with the flow and rhythm of the natural world" የሚል አባባል አለው።
እርግጥ ነው ያ ልጅነታችን መንፈሱ በወንዞቻችን ይታደስ ነበር። ካለፈው ታሪካችን ጋር የሚያገናኙን እንደሆኑ ለመረዳት መለስ ብሎ ማጤን ነው። ልጅነታችን በቀጥታ ከተፈጥሯዊው ዓለም ፍሰት ጋር የተገናኘባቸው አንድ ስፍራ የአካባቢያችን ወንዞች ነበሩ።

ወንዞችና ከተሞች ጥልቅ፣ ታሪካዊ ትስስር አላቸው፣ ብዙውን ጊዜ በውሃ አማካኝነት ለምግብ፣ ንግድ፣ ትራንስፖርት ዓላማ የሚፈጠሩ ሰፈሮች፣ የከተማ እድገትን፣ ባህልን እና ኢኮኖሚን ​​የሚቀርጹ ናቸው። ለእርሻ ልማት በሚል አዋሽ ወንዝ ዳርቻ የተፈጠሩ ከተሞች ዛሬ የዚህ ማሳያ ናቸው።

በሌላ በኩል የከተማ መስፋፋት ለወንዞች ብክለት ጦስ ነው። እኔ የዋኘሁበት የዘነበወርቁ አንጅሶ መጀመሪያ ተበከለ ቀጥሎ ደረቀ አሁን ተረት ሆነ።

ከተማና ቱሪዝም ፅንሰ ሐሳብ ነው። ከተማን ለመጠበቅ ወንዞችን መጠበቅ የሚለው ገኗል። አዲስ አበባ የወንዝ ዳርቻዋን ከጥፋት ጭቆና ነፃ አውጥታለች። እንደ አራዳ ፓርክ ያሉ ቦታዎች ቀድሞ ምን እንደነበሩ ለሚያውቅ አሁን ሲመለከታቸው ይደንቃል።

ከአምባሳደር ጀርባ የነበረውን አስታውሼ ዛሬ ቆም ብዬ እስከ ግዮን ስመለከት ወንዞችን አጥፍቶ ከመጥፋት ልማዳችን ያመለጥንበት አዲስ አብዮት ይደንቀኛል።

አዲስ አበባ የከተማ ሳፋሪ ልዩ ስፍራ ባለቤት ሆናለች። ሰሞኑን አዲስ አበባ ከምታስተዋውቀው ልማት አንዱ በወንዞች ዳርቻ የገነባችውን የከተማ ሳፋሪ ነው። አንዳንድ ሚዲያዎች የዱር ሳፋሪ ሲሉ ሰምቻለሁ። wilidlife safari "የዱር ሳፋሪ" ማለት እንስሳትን በተፈጥሮ ወይም ከፊል ተፈጥሯዊ መኖሪያዎቻቸው ውስጥ ለመመልከት የሚደረግ ጉዞ እና ዘመናዊ ኢኮ-ቱሪዝም ሀሳብ ነው። ለምሳሌ እንደ አምስቱ ትልቆች የምንላቸው የአፍሪካ ዱር እንስሳት መዳረሻዎች ዓይነት።

አዲስ አበባ ግን የከተማ ሳፋሪ city safari ወይም በሌላ መጠሪያው Urban Safari ነው የገነባችው። ሁለቱ በሳይንስም፣ በብያኔም፣ በይዘትም፣ በጠባይ

Address


Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Tsehay press posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

  • Want your business to be the top-listed media company?

Share