
17/08/2025
የመካነ ሰላም ከተማ አመሰራረት
=====================
መካነ ሰላም መካነ + ሰላም ከሚሉ ከ6 ፊደላት የተሰየመች ከተማ ስትሆን ትርጉሙም እጅግ የሰላም ቦታ /ሰላሟ የበዛ / እንደማለት ነው ፡፡
መካነ ሰላም ከተማ የምትገኘው ከደሴ በስተምእራብ አቅጣጫ 182 ኪሎሜትር እርቀት ላይ ነው፡፡መካነሰላም ከተማ አሃድ ብላ የተቆረቆረችው በደጃች ጎበና አመዴ ገዥበነበሩበት ዘመን 1941 ዓ.ም ሐምሌ 5 ቀን መካነ ሰላም ከተማ በያኔየው አጠራር አንድ(ጭቃ) መሬት (ቀበሌ) ሆና ተቆረቆረች ፡፡ የያኔየም አሮጌው ሰፈር ላይ የተቆረቆረቸው መካነ ሰላም እምብዛም እዛ ቦታ ላይ ሳትቆይ የበርካታ ሙህራንን ያፈራው የቦረና ከፍተኛ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ፊት ለፊት አለው ሰፈር ቦታ ላይ ድን ኳን ጥለው እንድመሰረት ካደረጉ በኋላም የጭቃ ሹም ደግሞ ከበደ ሙሃመድን አድርገው ሹመውም ነበር፡፡
በኋላ ላይ ደግሞ አሁንፒያሳ የሚባለው ቦታ ቴሌ ፊትለፊትላይ የመካነሰላም ከተማ የውሃ ታንከር አለበት ቦታ አካባቢ እጣፈንታዋ ተወስኖ ቤቶች እንድስሩ በማድርግ የከተማዋ ዋና ቦታ ሆኖ ተመሰረተ:: ከዘህ በኋላ ከተማይቱ እንድህ እንድህ እያለች እየሰፋች መጣች ከተማዋ ፒያሳና አራዳ ሰፈሮች ላይ በማንሰራራት አራዳና ፒያሳ ዋና የሸቀጣሸቀጥ ሶቆች ሞቅ ደመቅ በማድረግ መከፈት ጀመሩ ፡፡ ከተማዋ በፈጣን እድገት እየሰፍች ሲትሄድም ጥሩ ጥሩ ቢሮዎች አሁን አስተዳደር ግቢ የሚባለው ላይ በወቅቱ በነበረው የአውራጃ አስተዳዳሪ በአቶ እሸቱ ሰይድ ሃሳብ አፍላቂነት አማካኝነት ህብረተሰቡን በማስተባበር ቢሮዎች እንድገነቡ ሆነዋል፡፡ ለምሳሌ በወቅ ቱ አጠራር ገንዘብ ሚኒስቴር በጣም የተሻለ ቢሮ ሲሆን ሌሎችንም እንደ ፍርድቤት ፍትህ ፓሊስ እና ትምህርት ሚኒስቴር ቢሮዎችን አስገንብተው ለአገልግሎት አብቅተዋል፡፡
በኋላም ከተማዋ እየሰፍች ስትሄድ በ1981ዓ.ም መንግስት የቦታ ምሪት በመፍቀዱ ቲታኤ ሰፈር ቀላዱ /መድረሳ/ በኋላም ቄራ በሚባሉ ሰፈሮች በስፍት የመስሪያ ቦታ መሬት በመሰጠቱ የመንግስት ሰራተኞች ቤት ተሰርተዋል፡፡ ከተማዋ እንድትሰፋም በወቅቱ እድል ፍጥሮም ነበረ ፡፡ ከ2004 በኋላ ደግሞ መንግስት ለመንግስት ሰራተኞች የቦታ ምሪት እንድሰጥ በማድረጉ ግብርና ሰፈር አየር ጤና በመካነሰላም ጤና ጣቢያ በታች በላንቂሳና ደንቢ ለገአማራ አሻጋሪ አሮጌው ሶዩ ከተማይቱ የመስፍት እድል አግኝታለች አሁን ደግም ጨፌ ደንበሌ ናበጎማጣ አድስ ምራት እየተሰጠ ነዉ።
መካነሰለም አሁን ላይ በልጆቿ ጥረት በመልሶ ግንባታ በፈጣን እድገት ላይም ትገኛለች፡፡
ይች ከተማ እንድህ እንድህ እያለች እያደገች በመጣቷ የተነሳ ህብረተሰቡም የነቃ ህዝብ በመሆኑ በ2001 ዓም ራሷን ችላ የከተማ አስተዳደር እንድትሆን መስፈርቱን በማሟላቷ የከተማ አስተዳደርነት ቦታ ክልሉ ሰጥቷታል ፡፡በዚች ከተማ የሚኖረውም ህዝብ አሁን ላይ ከ85ሽ ህዝብ በላይ ህዝብ በከተማዋ ውስጥ ይኖራል፡፡ ከተማዋም በ5 ቀበሌዎች የተዋቀረች ስትሆን በከተማዋውስጥም 1 ዩኒቭርስቲ 1ቴክኒክና ሙያ ኮሌጂ 1የግል ጤና ኮሌጅ ማሰልጠኛ 1 የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል 1ጤና ኬላ 1ጤና ጣቢያ በግል ደግሞ 2 መካከለኛ ክሊኒክ 1 አስራሰባት(17 )ባንክ የመንግስትና የግል ሌላዉ የጂነአድም ባልተቤት ነች፡፡
ከተማዋን ለማሳደግም በውስጧ አቅፍ በያዘቻቸው ወጣት ባለሃብት ልጆቿ ያላሰለሰ ጥረት ከተማይቱ የመልሶ ግንባታ ለአይን ማረፊያ ህንጻዎች ተገንብተዋል፡፡ ሌላው የወደፊት የከተማዋን እጣፈንታ የሚወስን የገበያ ማእከል የከተማዋ ባለሃብቶች እየሰሩበትና እየገነቡ ነው፡፡ ሌላው የመቅደላ አምባ ዮኒቭርስቲበመከፈቱ ለከተማዋ እድገትበ ፈጥሮአል ፡፡ የግል የጤና ሳይንስ ኮሌጃም ተከፍቶየአርሶ አደሩ ልጆቹን ወደ ደሴ እና ሌሎች ቦታዎ ች ልኮ ልጆቹን በኤክስቴሽን እንዲማሩ ልኮ ያስተምር ስለነበር አሁን ላይ ደግሞ መካነሰላም ከተማ በመከፈቱ ሁሉ በደጀ ብሎማስተማር ችሎአል፡፡
ተተኳሪ ጉዳዮች
==========
የመካነሰላም ከተማ ያልተሻገረቻቸው ተግዳሮቶችንም ስናነሳ
በፌደራል መንገዶች ባለስልጣን ያሰራው ከኮምቦልቻ መካነሰላም ግንደ ወይን መንገድ ፕሮጀክት መሰራቱ ጥሩ ሆኖ እያለ የተሰራው የመሃል አገረ መስመሩን ለማገናኘትና ንግዱንም ይሁን ከወደብ የሚመጡ እቃዎችንም ለማጓጓዝ ናለማሳለጥ ታሳቢ ያደረገ ቢሆንም የኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣን ያሰራው መገድ በ1999 ዓ.ም ጨረታ በማውጣት ለቻይና መንገድ ስራ ፕሮጀክት በመስጠት በ5አመት ውስጥ እንድጠናቀቅ ወል ቢቆረጥለትም ተጨማሪ 3 አመት በመጨመር ልክ በ8 አመቱ ተጠናቆ በ2007 ዓ.ም 2ኛ ሩብ አመት ላይ በምክትል ጠቅላይ ሚኒስቴር ደመቀ መኮንንና በወቅቱም ትራንስፓርት ሚኒስቴር በነበሩት ወረቅነህ ገበየሁ (ዶ/ር )ተመርቆ በይፍ ተክፍቶአል፡፡ ይህ በፌደራል መንግስት በጀት ከኮምቦልቻ መካነ ሰላም ግንደ ወይን የተሰራው አስፓልት መንገድ ወረዳዋንም ይሁን ከተማዋን የ76 ኪ.ሜ ተጠቃሚ አድርጎ በመሀል ከተማው አቋርጦ ከማለፉም ባሻገር በአባይ ወንዝ ምክንያት ተራርቀውና ተነፋፍቀው ይኖሩ የነበሩ የምስራቅ ጎጃም ዞንና የደቡብ ወሎ ዞን ህብረተሰቦች በቀላሉ በማገናኘት በሁለቱም ዞኖች መካከል ያለውን የህብረተሰብ ትስስር ከማጠናከሩም ባሻገር ኑሮን በማሻሻል ትልቁን ሚና ይጫወታል፡፡
ለመሃል አገር እንደ ዋና መገናኛ ኮሪደር ተደረጎ እያገለገለ እና ለመንግስትም በጅንታው ጦረነት እንደዋና እስትራቴጅ ሆኖም አገልግሎል፡፡
መንገድ ግን እምብዛም አገልግሎት ሳይሰጥ ለብልሽት ተዳርጎአል ባለሃብቶችም በዚህ መስመራ ለመሄድ አዳጋች መሆኑን ለመንግስት አቤቱታ ቢያሰሙም የመንገዱ እድሳቱም ሰሚ ያጣ ይመስላል፡፡ትራንስፖርቴሽን ሲስተሙም መንገዱ ወዳው እንደተሰራ ደሴ 3.00 ሰዓት የሚገባ ሲሆን አሁን ላይ ደግሞ 7.00 ሰዓት ለዶልፊንና ለሃይ ሩፍ የሚወስድ ሲሆን ለሌሎች የጭነት መኪኖች ደግሞ ያው የዱሮው አካሄድ ውስጥ ገብተዋል፡፡ እናዚህ መኪኖችም እንደበፊቱ ተፍ ተፍ ብለው እመስመሩ ላይ ሲሰሩ አይታዩም፡፡ ለምንቢባልም መንገዱ ከጊዜ ወደጊዜ የብልሽት መጠኑ እየጨመረ ስለመጣነው ፡፡
ሌላው የከተማይቱ ትልቅ ተግዳሮት ባለፉት ተከታይ አመታት የውሃ ችግር ህብረተሰቡን እያማረረ ሲሆን ከዚህ ችግር የተነሳ ህብረተሰቡ የሰነበተ ውሃ እስከመጠጣት ተገዶአል ፡፡ አሁን ላይተስፍ የተታለበት የሆጨጨ ግድብ ዘላቂ መጠጥ ውሃ ፕሮጀክት በመንግስት በጎአሳቢነት በባለሙያዎች ና በጎ አሳቢ ሰዎች ባደረጉት እርብርብ ፕሮጀክቱ ዘላቂና አስተማማኝ ውሃ መሆኑ ቢታወቅም ወደስራ ለመግባት በተከታታይ አመታት የጥናቱ ውጤትና የመሬት ካሳ ክፍያ ሁኔታዎች ተደርገዋል። እምብዛም በ2011 ጀምሮ ወደ ስራ ያልተገባ ሲሆን አሁን ላይ ከክልሉ ባለፈ የውሀ ሀብት ሚኒስቴር በበላይነነት ይዞት 2018 ከህዳር ወር በኋላ እንደሚተገበር ታዉቋል።
የህብረተሰቡ የውሃችግር አሳሳቢ እየሆነ በመማጣቱ ለዚህ ፕሮጀክት መሳካት መንግስት ህብረተሰቡ ሙህራን ተወላጆችእና እኔም ለዚህ ፕሮጀክት ያገባኛል የሚል ሁሉ የከተማዋን የውሃ የማገኘት እጣፈንታ ከችግር እንድወጣ ሁሉም በአንድ ለይ በመረባረብ የከተማይቱ የውሃችግር እንድቀረፍ ፋታ የማይሰጠው ጉዳይ ነው ።
ሌላው መካነ ሰላም ከተማ ከየካቲት 23;1965በኋላ ከተማዋ የአውሮፕላን ማረፊያ የነበራት ቢሆንም እስከ 1997ግንቦት8 ድረስ በረራ ሲደረግ ቆይቶ በውል ባልጣወቀ ምክኒያትም ተዘግቶአል፡፡ ከተማዋ ደግሞ የቱሪስት መሰብ ያለትና የቦረና ሳይንት ወረሂመኖ ብሄራዊ ፓርክ /የቦሳወብፓ/ ጽ/ቤት መገኛ በመሆኗ የመቅደላ አምባ ዩኒቭረስቲ በዚቹከተማ ያለ ሲሆን አውሮፕላን ማረፊያው ቢከፈት ለከተማይቱ ከፍተኛ መነቃቃትን ይፈጥራል ተብሎ ይታሰባል፡፡
ሌላው ከተማዋ ለኢንድስትሪ ቦታ አመች ብትሆንም የመብራት ችግር ያለባት ወረዳነች የራሷ የሆነ ሰብ እስቴሽን ሰለሌላት መንግስት ይህንችግር በውል በማጤን አሜጃ ዶሮ ሰደቃላይ ከተማይቱ የረሷ የሆነ የመብራት ሰብ እስቴሽን ይገነባልተብሎ ከፌደራል ቃል ቢገባም እስካሁንድረስ ወደትግበራ ባለመገባቱ የከተማዋ ልክ እንደሰሟ መካነ ሰላም ከሰላም ወጭ ምንም ኩሽ የማይለባት ከተማ መሆን እንዳለባት በማመንና የሚያጋጥሙ ችግሮችንም ህዝብ ከመንግስት ጎን በመቆምና መንግስት ጋር በመነጋገር መፍታት አሌ የማይባል ሃቅ ነው።