Siz-Diart

Siz-Diart ሼም ባርት: የሼይ ወጣቶች : የአገር ሽማግሌዎች እና መወያያ ቦ?

19/01/2025

ለአቶ ጌታሁን ተክሌ (የቤንች ምሁራን ማህበር ፕሬዚዳንት)፣ ቤንች ሚዲያ ኔትወርክ እና ለገጹ ተከታዮች።

“በ፫፫ኛው ንጉስ_ዎተራሻ_ፍቃዱ_ፀጋዬ_የንግስና_ስርዓት ፕሮግራም ላይ ተገኝተው የእንኳን ደስ አሎዎት መልአክ አስተላልፎዋል።” ተብሎ የተለጠፈው ፤ ከእውነት የራቀ , ከታሪክ የተጣላ :ተቀባይነት የሌለው እና ታሪክንና የአከባቢውን ፖለቲካን ጠንቅቆ ካለማወቅ የመነጨ በመሆኑ እርምት እንዲወሰድ እጠይቃለሁ። በኢትዮጵያ ምድር እንኳን ፫፫ኛ ንጉስ_ዎተራሻ; ፩ኛ ወታራሻ የሚባል ንጉስ የለም፤ ምናልባት አቶ ጌታሁን ተክሌ ከቤተስባቸው እና ከሚመሩት ማህበር ጋር ሆነው አዲስ ስርዓ ካልፈጠሩ በስተቀር።

ለመሆኑ ወታራሻ(Wotarasho) የሚለው ስያሜ ምን ማለት ነው? ከየት መጣ?

ወታራሻ የሚለው ስያሜ የተፈጠረው ዎታ እና ራሻ (wota+Rasho) ከሚባሉ ሁለት ቃሎች ነው። ባጭሩ ዎታ ከሚባል የቦታ ስም እና ራሾ ከሚባል የማረግ ስም ነው። ራሾ ከሚባል የማረግ ስም ፤ በከፋ ንጉስ ስርዓተ መንግስት ውስጥ በተለያዩ የስልጣን ደረጃ ለሰሩ ግለሰቦች የሚሰጥ የማረግ ስያሜ ነው። ስያሜው ሲሰጥ ከራሾ ቀድሞ የመጡበት ጎሳ ወይም አከባቢ ስም በአብዛኛን ጊዜ ይገባል። ለምሳሌ እዚህ ላይ ንጉስ ተብለው የቀቡትን ማረግ ስም ስናይ ወታራሻ ማለት ዎታ አከባቢ አስተዳዳሪ ማለት ነው። አሁን የክልል-የዞን-ወረዳ-ቀበሌ- አስተዳደር እንደምንለው ማለት ነው። በከፋ ንጉስ ስርዓተ መንግስት ውስጥ ከፍተኛ ስልን ያላቸው እንደ ከተሜ ራሾ :- የንጉሡ ዋና እና የጦር መሪ, አዴራሾ፣ በዴራሾ፣ አዌራሾ.... እያለ ወደ ሰባት የሚሆኑ ናቸው። የዝቅተኛ ደረጃ ላይ ያሉት ለምሳሌ እንደ ጋዋታራሻ፡ጫታራሻ፡ ጌሻራሻ ፣ እና የመሳሰሉት አሉ። ለምሳሌ ለከፉ ንጉሱ በዘማ ሙዚቃ የሚመራ ሻታራሻ ነው።

(ወታ)ራሻ የሚባል ስያሜ ያላቸው ግለስቦች እንዴት ወደ ሼይ ቤንች እና አከባቢ ለማስተዳደር እንዴት መጡ?

የሲዝ ከተማ በጥንት ዘመን ከሚታውቁ እና እስትራቴክ ከሚባሉ ጥቂት ከተሞች አንዷ በምሆኗ የአፄ ምንሊክ ሰራዊት የከፋን ንጉስ ካስገበረ በኃላ ፤ የምንሊክ ንጉሳዊ ስርዓት በብዛት ይጠቅማቸው የነበረውን ቀኝ/ግራ አዝማች የሚለውን መጠሪያ በማስቅድም፣ የአከባቢን ስያሜ በመጨመር ሾመው እንደላኳቸው ይታወቅል። "ከአፄ ምንሊክ ሰራዊት ጋር" በሚል በአማርኛ በተተረጎመው Aleksandar Bulatovic መጽሐፍ ገፅ 95 ላይ ከፋ ንጉስ ያስገራቸ ጎሳዎች መሬት ዎታ የሚባል ሲሆ የሚስተዳድረውም ወታራሻ ይባላል።

በአጠቃላይ በየትኛውም የታሪክ መዛግብት የምንረዳው ራሾ የሚል ስያሜ ለመንግስት አስተዳደር የሚሰጥ ስያሜ እንጂ የንግስና ስም የለም። ኢትዮጵያ ውስጥ ያለው እና የምናውቀው አንድ መንግስት ነው። እሱም የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ መንግስት ብቻ ነው። በመሆኑም ሚዲያው እና ማህበሩ እርምት እዲያድርጉ እጠይቃለሁ።

ለበለጠ መረጃዎች ማጣቀሻች፣

Aleksandar Bulatovic ; “ከአፄ ምንሊክ ሰራዊት ጋር" በሚል በአማርኛ በተተረጎመው

Temesgen G Baye The Evolution and Development of Kingship and Traditional Governance in Ethiopia:
A Case of the Kefa Kingdom, Bahir Dar University, Ethiopia

Legesse G (1971) Conquest of the Kingdom of Kefa. Haile Selassie: Haile Selassie I University.

Linel Bender M (1976) The Non-Semitic languages of Ethiopia. Africa Studies Center, East Lancing, Michigan: Michigan State University.

Lange W (1979) Domination and Resistance: Narrative Songs of the Kefa Highlands. East Lansing: African Studies Center, Michigan State University.

በፍቅሩ ገብሬ የቀረበ

20/04/2024
ሼቴት! አንድ ለእናቱ! አንድ እሱን ለማውረድ ድናቁራት ዞናዊ ሹም ሽር አደረጉ!
19/01/2024

ሼቴት! አንድ ለእናቱ! አንድ እሱን ለማውረድ ድናቁራት ዞናዊ ሹም ሽር አደረጉ!

Address


Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Siz-Diart posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

  • Address
  • Alerts
  • Claim ownership or report listing
  • Want your business to be the top-listed Media Company?

Share