የኢትዮጵያውያን መረጃ ገፅ/Ethiopian's Info.page

የኢትዮጵያውያን መረጃ ገፅ/Ethiopian's Info.page ✅ የወቅታዊ ፣የጤና ፣ የጉዞ እና የማህበራዊ ጉዳይ መረጃ ምንጭ/ source of current & social affaire working For Peace
(1)

"ሕወሓት ጄኖሳይድ ጄኖሳይድ የሚለው የፈረንጆቹን ልብ ለማማለል ነው" ጀ/ል ባጫ ደበሌ ዝክረ ሰሜን ዕዝን በተመለከተ ከሰጡት አስተያየት የተቀነጨበ
03/11/2025

"ሕወሓት ጄኖሳይድ ጄኖሳይድ የሚለው የፈረንጆቹን ልብ ለማማለል ነው" ጀ/ል ባጫ ደበሌ ዝክረ ሰሜን ዕዝን በተመለከተ ከሰጡት አስተያየት የተቀነጨበ

ታማኝነት‼ዛሬ ሰኞ አይደል ‎የባቲ ገበያ ድምቅ ውሎ የዋለበት ቀን ነው።በዚህ መሐል አንድ እህታች የቤት አስቤዛ ገዝታ በቀን ሰራተኛ በማሸከም ወደ ቤት ከገበያ እየወጣች እያለ ተጠፋፉ።ታማኙ ...
03/11/2025

ታማኝነት‼

ዛሬ ሰኞ አይደል ‎የባቲ ገበያ ድምቅ ውሎ የዋለበት ቀን ነው።በዚህ መሐል አንድ እህታች የቤት አስቤዛ ገዝታ በቀን ሰራተኛ በማሸከም ወደ ቤት ከገበያ እየወጣች እያለ ተጠፋፉ።

ታማኙ የቀን ሰራተኛ እቃውን ይዞ ለፖሊስ አስረክቧል።የባቲ ከተማ አስተዳደር ፖሊስም ወጣቱን አመስግኖ እቃውን ተረክቧል።ባለቤት ነኝ የሚል ይውሰድ ብሏል።

ወዳጄ እንደዚህ አይነቱን ታማኝ ካላመሰገንክ አደራ ጠባቂ ትውልድ ማፍራት አይቻልም።ተባረክልኝ።
Wasu Mohammed

03/11/2025

"ሕወሓት ለሌላ እልቂት እየተዘጋጀ ነው፤ ሰራዊቱ ማንኛውንም ጥቃት ለመመከት ተዘጋጅቷል"
ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ

03/11/2025

‹‹ኢትዮጵያዊነቱን የሚያምን ሁሉ ግብፅ የምትሠራቸውን ሴራዎች ከመደገፍ ሊቆጠብ ይገባል››
ዶክተር ኢንጂነር ስለሺ በቀለ

የሱልጣኔቶች መናገሻ የሱልጣን ሀንፈሬ አሊሚራህ ሀገር አሳኢታ ከተማ በፎቶ ይህን ትመስላለች‼
03/11/2025

የሱልጣኔቶች መናገሻ የሱልጣን ሀንፈሬ አሊሚራህ ሀገር አሳኢታ ከተማ በፎቶ ይህን ትመስላለች‼

02/11/2025

እህታችን አስቸኳይ ድጋፋችሁን ትሻለች‼️በፎቶዉ ላይ የምትመለከቷት እህታችን አምበሪያ ናስር ትባላለች፤ የአራት ህፃናት ልጆች እናት ናት። በሳኡዲ አረቢያ ሪያድ ከተማ ነዋሪ ስትሆን አሁን ላይ...
01/11/2025

እህታችን አስቸኳይ ድጋፋችሁን ትሻለች‼️

በፎቶዉ ላይ የምትመለከቷት እህታችን አምበሪያ ናስር ትባላለች፤ የአራት ህፃናት ልጆች እናት ናት። በሳኡዲ አረቢያ ሪያድ ከተማ ነዋሪ ስትሆን አሁን ላይ በወሊድ ምክንያት ባጋጠማት ድንገተኛ የደም ካንሰር ምክንያት እየተሰቃየች ትገኛለች።

እህታችን ሪያድ ከተማ በሚገኘው መሊክ ሱዑድ ሜዲካል ሲቲ ሆስፒታል ለሁለት ወራት ያክል የኬሞ ቴራፒ ህክምና በመዉሰድ ቆይታለች። ነገር ግን በሽታው ሐገር ውስጥ እንደማይድን እና ህንድ መሄድ እንዳለባት ተነገሯታል። እህታችን በህንድ ቆይታዋም ምርመራ እና ሌሎች ህክምናዎች ከአዲስ በመጀመሯ ምክንያት እስካሁን ድረስ ከ10ሽህ ዶላር (ከአንድ ሚሊዮን አምስት መቶ ሽህ ብር) በላይ ጨርሳለች።

ይህን ያደረገችው ወደ ህዝብ ፊት ላለመምጣት በራሷና በቤተሰቧ አቅም እዛው ከጨረሰ ለመሞከር ነበር። ግን የአላህ ውሳኔ ሆነና አልቻለችም። አሁን ላይ ዶክተሮቹ በሰጧት ተስፋ መሠረት ካንሰሩ በአሏህ ፈቃድ ከ90% በላይ የመዳን እድል አለው። ነገር ግን በመሃል ገንዘቡን ስታጥ የተወሰነ ሕክምናው ተስተጓጉሎ ስለነበር አሁን ላይ ፈጥና አዲሱን ሕክምና ማግኘት አለባት።

እህታችን አሁን ላይ አዲሱን የመቅኒ ንቅለ ተከላ እንደሚያስፈልጋት የተነገራት ሲሆን፤ ንቅለ ተከላውን ለማከናወንም ለህክምና ወጪ ብቻ እስከ 40,000(አርባ ሽህ) ዶላር ወይም ስድስት ሚሊዮን ብር (6000000) ብር እንደሚያስፈልጋት ተነግሯታል። ሁላችንንም ተረባርበን እናሳክማት። እህታችን ወደ እኛ ከመምጣቷ በፊት ሁሉን ነገር አድርጋ ነበር። ግን ዛሬ ላይ እገዛችሁን ትሻለች። በአሏህ ፍቃድ እናንተም አታሳፍሯትም።

የእህታችን አምበሪያ ናስር አራት ህፃናት ልጀቿና ባልተቤቷ የእናታቸዉንና የባለቤቱን መዳን አሏህ እናንተን ሰበብ እንዲያደርግላቸው በገንዘባችሁና በዱዓችሁ እንድታግዟቸዉ ጠይቀዋል።

ይህንን እርዳታ ለማሰባሰብ በተከፈተ የባንክ የጋራ አካዉንት አሏህ ከሰጣችሁ ላይ የቻላችሁትን በመለገስ እህታችን ከአላህ በታች እናግዛት። 50 ሎሚ ለአንድ ሰው ሸክም ለ50 ሰው ደሞ ጌጥ ነው።

የአካውንት ስም:- ሙሐመድ፣ ማህመድ፣ ኦሳማ
ንግድ ባንክ:- 1000726689737
አቢሲንያ:- 241331121
አዋሽ:- 014251676310600
ዘምዘም:- 0069012920101

አነሰ በዛ ሳትሉ እህታችንን ተረባርበን እናሳክማት፤ የቻለ በገንዘቡ፣ ይህን ያልቻለ መልዕክቱን በማሰራጨትና በመልካም ዱዓችሁ አትርሷት።

ዛሬ ዓለም አቀፍ የከተሞች ቀን ነው። ከኢትዮጵያ የእርሶ ምርጥ ከተማ የቱ ነው?
31/10/2025

ዛሬ ዓለም አቀፍ የከተሞች ቀን ነው።

ከኢትዮጵያ የእርሶ ምርጥ ከተማ የቱ ነው?

የዚህች ሱዳናዊት  ሴት ታሪክ  ልብ  ይሰብራል‼የ (RSF)  ወታደሮች ሊገድሏት ወደ እሷ ቀረቡ፣ ልጆቿንም ለመጠበቅ ሞከረች።እርዳታ እንዲደረግላቸው ለመነችወታደሮቹ ግን ይባስ ብለው በልጆቿ ...
31/10/2025

የዚህች ሱዳናዊት ሴት ታሪክ ልብ ይሰብራል‼

የ (RSF) ወታደሮች ሊገድሏት ወደ እሷ ቀረቡ፣ ልጆቿንም ለመጠበቅ ሞከረች።

እርዳታ እንዲደረግላቸው ለመነች
ወታደሮቹ ግን ይባስ ብለው በልጆቿ ፊት እንደደፈሯት ተሰማ። ከዛም የደማ ልቧን ይበልጥ ለማሳመም ቀድመው ልጆቿን ፊቷ ገደአሏቸው በመጨረሻም እሷንም እዛው ጨረሷት ይላል ዘገባው
አለምን እያነጋገረ ያለ ክስተት ነው።

ከአዲስ አበባ ከተማ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ም/ቤት የተሰጠ መግለጫ።የአባታችን የክቡር ዶ/ር ተቀዳሚ ሙፍቲ ሐጂ ዑመር እድሪስ ሞት በሁላችንም ዘንድ ከፍተኛ የሐዘን ድባብ ፈጥሮብን መቆየቱ ...
30/10/2025

ከአዲስ አበባ ከተማ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ም/ቤት የተሰጠ መግለጫ።

የአባታችን የክቡር ዶ/ር ተቀዳሚ ሙፍቲ ሐጂ ዑመር እድሪስ ሞት በሁላችንም ዘንድ ከፍተኛ የሐዘን ድባብ ፈጥሮብን መቆየቱ ይታወቃል። ተቀዳሚ ሙፍቲ እስከ ሕልፈተ ሕይወታቸው ድረስ በብዙ መልኩ ኢስላምንና ሙስሊሞችን ሲያገለግሉ የኖሩ አባት ነበሩ። በተለይ ለአዲስ አበባ ከተማ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ደግሞ ተቋሙን በመሪነት ከአስር ዓመታት በላይ የመሩና አሻራቸውን ያስቀመጡ መሪያችን እንደመሆናቸው ኃዘናችን ጥልቅ መሆኑን ከዚህ በፊት ባወጠናቸው ተከታታይ መግለጫዎች መግለጻችን ይታወሳል።

አሁን በድጋሚ አላህ (ሱ.ወ) ምህረቱን እንዲለግሳቸዉና ጀነተል ፊርደዉስን ማረፊያቸዉ ያደርግላቸዉ ዘንድ አላህን እንማጸነዋለን። በማስከተልም ከሰሞኑ ከታዩ ሁነቶች ጋር በተያያዘ በቀጣይ ነጥቦች ላይ የምክር ቤቱን አቋም እንደሚከተለው ለመግለጽ እንወዳለን።

1. ለሕዝበ ሙስሊሙ አንድነት የመስራት ታሪክ ያላቸው ሙፍቲ ሞት ሕዝባችን በሀዘን ዉስጥ በነበረበት ሁኔታ ከቀብር ስፍራቸው ጋር ተያይዞ አላስፈላጊ የሆኑ ንትርኮች መነሳታቸው አሳዝኖናል። መሰል ዉዝግቦች ስሜትና ቡድንተኝነት ሲታከልባቸው ሙፍቲ ሲለፉለት የነበረውን አንድነትን ከማስጠበቅ በተቃራኒ ሕዝባችንን ወዳልሆነ ንትርክ፣ ጭቅጭቅ እና ክፍፍል የሚያመራ አደገኛ ነገር ነው።

2. ተቀዳሚ ሙፍቲ የተቀበሩበት ቦታ ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፕላንና ልማት ኮሚሽን በደብዳቤ ቁጥር አ/አ/ፕ/ል/ኮ02/910/2013 በቀን 05/10/13 በተፃፈ ደብዳቤ ከቅይጥ መኖሪያነት ወደ መካነ መቃብርነት የተቀየረ መሆኑን ለማረጋገጥ ችለናል፡፡ ስለሆነም ስፍራውን በአዲስ አበባ ውስጥ እንደሚገኙት የሕዝበ ሙስሊሙ መካነ መቃብሮች በመቁጠር በአስራ ሁለተኛ መካነ መቃብርነት እውቅና ሰጥተነዋል።

በመሆኑም የመቃብር ስፍራውም ተጨማሪ የማስፋሪያ ጥያቄ ለመንግስት ከማቃረባችን በተጨማሪ እንደሌሎቹ መካነ መቃብሮች ማንኛውም ሙስሊም ሲሞት የሚቀበርበት በመሆኑ ለመካነ መቃብሩ አስፈላጊውን ጥበቃ፣ ድጋፍ እና ክትትል በመጅሊሱ በኩል እንደሚደረግለት ማሳወቅ እንወዳለን። ስለሆነም ከአሁን በኋላ ከመካነ መቃብሩ ጋር በተያያዘ የሚደረጉ ማንኛውም ዓይነት አጀንዳዎች ሊቆሙ እንደሚገባ አናሳስባለን።

3. ከዚህ በኋላ የተለያዩ አጅንዳዎችን ምክንያት በማድረግ በሕዝባችን መካካል ክፍፍልን የሚፈጥሩና የሚያባብሱ እንዲሁም ሰላምን የሚያደፈርሱ ንትርኮች፣ ጭቅጭቆች እና ውግዘቶች እንዲቆሙ እናሳስባለን። ዉይይትን፥ መማማርንና መተሳሰብን ዓላማ ያላደረጉ መልዕክቶች በማህበራዊ ሚዲያም ሆነ በማንኛውም መድረክ እንዳይተላለፉ ጥሪ እናደርጋለን።

4. ለየትኛውም ሃይማኖታዊ አለመግባባቶች መፍትሄ ፍለጋው መንገዱ አላህ እንደነገረን መመለሻችን ቁርኣንና የነብያችን (ሰ.ዐ.ወ.) ፈለግ(ሱና) ዋቢ በማደረግ ሊሆን ይገባል። በዚህ ረገድ አርዓያዎቻችን መልዕክተኛው (ሰ.ዐ.ወ.) እና ሰሀቦቻቸው(ረ.ዐ.) ናቸው። ዑለሞችና ዱዓቶች የሕዝባችንን የዲን ግንዛቤና እውቀትን ለማስፋት የምታደርጓቸው አስተምህሮቶች፥ ዳዕዋዎች፥ በመልካም የማዘዝና ከመጥፎ የመከልከል ጥረቶች ከስሜት በራቀ፤ በእውቀት፣ በጥበብና በለዘብታ ቃል የተላበሰ መሆኑን ባረጋገጠ መልኩ ሊቀጥል እንደሚገባ እናሳስባለን።

5. አንዳንድ አካላት የተፈጠረውን ሁኔታ ሲጠብቁት እንደነበረ መልካም አጋጣሚ በማየት የራሳቸውን ድብቅ ፍላጎትና ዓላማን ለማሳካት ሕዝቡን የሚያሳዝኑ ድርጊቶችንና ንግግሮችን በማድረግ የሕዝባችንን ሐዘን አባብሰዋል። ምክር ቤቱ በምርጫ የተጣለበትን ታላቅ አደራ ለመወጣት በቁርጠኝነት የሚንቀሳቀስ ሲሆን በዚህ ረገድ ማንኛውንም የሕዝባችንን አንድነትና ጥቅሞችን የሚጎዱ አካላትንና አካሄዶችን ፈጽሞ እንደማይታገስ በጥብቅ ለማሳሰብ አንወዳለን።

6. በመጨረሻ በተከበሩ አባታችን ህልፈት ከፍተኛ ሀዘን ላይ ከሚገኙት ቤተሰቦቻቸው ጋር በመነጋገር ተቀዳሚ ሙፍቲ ሀጂ ዑመር እድሪስ የሚዘከሩበትና መልካም ሥራዎቻቸው ቀጣይነት እንዲኖራቸው የምናደርግበት ተቋም ጉዳይ ጥናት እየተደረገበት መሆኑን እየገለፅን ሙፍቲ ሐጂ ዑመርን ጨምሮ ሕዝበ ሙስሊሙን በማስተማርና አንድነቱ የተጠበቀ እንዲሆን ጥረት ሲያደርጉ የነበሩና በሞት የተለዩንን እንደነ ሐጅ ሙሐመድ ሳኒ ሐቢብ፥ ሐጅ ሙሐመድ ራፊዕ፥ ሐጅ ዘይኑ ሙቅና፥ ሐጅ ሙሳ ኪኪያና ሌሎችም ታላላቅ ዓሊሞቻችንንና ዱዓቶቻችን አላህ ጀነተል ፊርደውስን እንዲለግሳቸው አላህን እንማጸነዋለን።

ሕዝበ ሙስሊሙም የእነርሱን መልካም አርዓያነትን በመከተል ኢስላማዊ እውቀት እንዲሰራጭና የሕዝበ ሙስሊሙ አንድነት እንዲጠናከር የየበኩሉን ሚና እንዲወጣ ጥሪ እናደርጋለን።

አላህ ሃይማኖታችንን፥ሀገራችንና ሕዝባችንን ከክፉዎች ተልኮል ይጠብቀልን።

ጥቅምት 20 ቀን 2018
የአዲስ አበባ ከተማ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ
ም/ቤት

በአሜሪካ "ኬኬን በላብኝ" በማለት አንዲት ሴት 25 ዓመት በትዳር አብራ የኖረችውን ባል ፈታች   | ጥንዶቹ የጋብቻ በዓላቸውን ለማክበር የፍቅር እራት በልተው ነበር እና እያንዳንዳቸው አንድ...
30/10/2025

በአሜሪካ "ኬኬን በላብኝ" በማለት አንዲት ሴት 25 ዓመት በትዳር አብራ የኖረችውን ባል ፈታች

| ጥንዶቹ የጋብቻ በዓላቸውን ለማክበር የፍቅር እራት በልተው ነበር እና እያንዳንዳቸው አንድ የቺዝ ኬክ ወስደው ነበር። ባልየው ወዲያውኑ የራሱን በላ፣ ሚስት ግን ለጠዋት - ለቁርስ የሚሆን ትንሽ አስቀርታ ነበር።

በማግስቱ ጠዋት በቺዝ ኬክ አስደሳች ሀሳብ ከእንቅልፏ ስትነሳ... ግን በፍሪጅ ውስጥ ምንም አልነበረም - ባሏ እሷ ተኝታ ሳለ የሷን ኬክ በልቶት ነበር።

ሴትየዋ ክህደቱን መቋቋም ስላልቻለች ለፍቺ ጥያቄ አቀረበች ያለው ፊደል ፖስት ነው።

 🇪🇹❤
29/10/2025

🇪🇹❤

Address

Addis Ababa

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when የኢትዮጵያውያን መረጃ ገፅ/Ethiopian's Info.page posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to የኢትዮጵያውያን መረጃ ገፅ/Ethiopian's Info.page:

Share