Miidiyaa M/Lallaba Shaggar ሸገር ሀገረ ስብከት ሚዲያ

Miidiyaa M/Lallaba Shaggar  ሸገር  ሀገረ ስብከት ሚዲያ tiktok.com/
(1)

Biyya Lallaba Magaalaa Shaggar irraa kan darbu.
ከሸገር ከተማ ሀገረ ስብከት የሚተላለፍ።
This is the Official Shegercitydiocese page you can get all the latest news About EOTC in Afaan Oromoo and Amharic you can follow us.

Guyyaan Yaadannoo Ayyaanna  boqonnaa Qulqulluu  Pheexiroosii fi Phaawuloos Mana Kiristaanaa Tulluu Qermeloos Qulqulluu W...
12/07/2025

Guyyaan Yaadannoo Ayyaanna boqonnaa Qulqulluu Pheexiroosii fi Phaawuloos Mana Kiristaanaa Tulluu Qermeloos Qulqulluu Waaqa Abbaa,Wareegamaa qulqulluu giyoorgisi fi Qajeela Abbaa gabre Manfees Qidduus Alamganaatti haalaa Hoo'aa ta'en kabajameera.
+++++++++++++++++++++++++++++++++++++++
Adoolessa 5, 2017 B.A Miidiyaa M/Lallaba Shaggar

Mana Kiristaanaa Ortodoksii Tawaahidoo Itiyoophiyaatti guyyaan Ayyaana boqonnaa Qulqullootaa ifa Addunyaa Qulqulluu Pheexiroosii fi Phaawuloos biyyaa lallabaa Magaalaa Shaggar kutaa Mana Lubummaa Magaalaa Furii Mana Kiristaanaa Tulluu Qermeloos Qulqulluu Waaqa Abbaa,Wareegamaa qulqulluu giyoorgisi fi Qajeela Abbaa gabre Manfees Qidduus Alamganaatti haalaa Hoo'aa ta'en kabajameera.

Barumsa guyyicha ilaalatu Roome:- 8:37 Ka'umsa taasifachuun kan barsisaan Laike Wangel Lammeessaa Milkeesaa“Waan nu irra ga'e hundumaatti garuu, karaa isa nu jaallatee mo'icha guddaa arganna.” jedhu irratti hundaa'uun waa'ee kabaja guyyichaa barsiisaniiru.

Maddaa:- Laike Wangel Lammeessaa Milkeesaa“

በዓለምገና ደብረ ቀርሜሎስ ቅዱስ እግዚአብሔር አብ፣ ቅዱስ ጊዮርጊስ ወጻድቁ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ቤተክርስቲያን የብርሃናተ ዓለም ቅዱስ ጴጥሮስ ወጳውሎስ ዓመታዊ የዕረፍት  መታሰቢያ በዓ...
12/07/2025

በዓለምገና ደብረ ቀርሜሎስ ቅዱስ እግዚአብሔር አብ፣ ቅዱስ ጊዮርጊስ ወጻድቁ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ቤተክርስቲያን የብርሃናተ ዓለም ቅዱስ ጴጥሮስ ወጳውሎስ ዓመታዊ የዕረፍት መታሰቢያ በዓል በድምቀት ተከበረ።
+++++++++++++++++++++++++++
ሐምሌ 5 ቀን 2017 ዓ.ም||ሸገር ሀገረ ስብከት ሚዲያ ||

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን በሸገር ከተማ ሀገረ ስብከት በፉሪ ክፍለከተማ በዓለምገና ደብረ ቀርሜሎስ ቅዱስ እግዚአብሔር አብ፣ ቅዱስ ጊዮርጊስ ወጻድቁ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ቤተክርስቲያን የብርሃናተ ዓለም ቅዱስ ጴጥሮስ ወጳውሎስ ዓመታዊ የዕረፍት መታሰቢያ በዓል በድምቀት ተከብሯል።

በዕለቱም በላእከ ወንጌል ለሜሳ ሚልኬሳ
""በዚህ ሁሉ ግን በወደደን በእርሱ ከአሸናፊዎች እንበልጣለን።" ሮሜ 8፥37 በሚል ኃይለ ቃል መነሻነት የዕለቱን በዓል በተመለከተ አስተምረዋል።

ምንጭ፦ ላእከ ወንጌል ለሜሳ ሚልኬሳ

Guyyaan Yaadannoo Ayyaanna  boqonnaa Qulqulluu  Pheexiroosii fi Phaawuloos Mana Kiristaanaa Mekaane Hiwoot Abuna Gebre M...
12/07/2025

Guyyaan Yaadannoo Ayyaanna boqonnaa Qulqulluu Pheexiroosii fi Phaawuloos Mana Kiristaanaa Mekaane Hiwoot Abuna Gebre Menfes Qidduus Koyyeetti haalaa Hoo'aa ta'en kabajameera.
+++++++++++++++++++++++++++++++++++++++
Adoolessa 5, 2017 Miidiyaa M/Lallaba Shaggar ሸገር ሀገረ ስብከት ሚዲያ

Mana Kiristaanaa Ortodoksii Tawaahidoo Itiyoophiyaatti guyyaan Ayyaana boqonnaa Qulqullootaa ifa Addunyaa Qulqulluu Pheexiroosii fi Phaawuloos biyyaa lallabaa Magaalaa Shaggar kutaa Mana Lubummaa Magaalaa Kooyye Mana Kiristaanaa Mekaane Hiwoot Abune Gebre Menfes Qidduus kooyyetti Sirna hoo'aan kabajameera.

Barumsa guyyicha ilaalatu Kutaa Wangeelaa Qulqulluu, Mul'ata Yoohannis 2:10 Ka'umsa taasifachuun kan barsisaan Sooraa Wangeelaa Heenook Taayyeen "Hanga du'aatti amanamaa ta'i, anis gonfoo jireenyaa siif nan kenna" jedhu irratti hundaa'uun waa'ee kabaja guyyichaa barsiisaniiru.

Maddaa:- Sooraa Wangeelaa Heenook Taayyee.

በኮዬ መካነ ሕይወት  አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ቤተክርስቲያን የብርሃናተ ዓለም ቅዱስ ጴጥሮስ ወጳውሎስ የዕረፍታቸው መታሰቢያ በዓል በድምቀት ተከበረ። ++++++++++++++++++++++++...
12/07/2025

በኮዬ መካነ ሕይወት አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ቤተክርስቲያን የብርሃናተ ዓለም ቅዱስ ጴጥሮስ ወጳውሎስ የዕረፍታቸው መታሰቢያ በዓል በድምቀት ተከበረ።
+++++++++++++++++++++++++++++++
ሐምሌ 5 ቀን 2017 ዓ.ም||ሸገር ሀገረ ስብከት ሚዲያ||

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን በሸገር ከተማ ሀገረ ስብከት በኮዬ መካነ ሕይወት አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ቤተክርስቲያን የብርሃናተ ዓለም ቅዱስ ጴጥሮስ ወጳውሎስ የዕረፍታቸው መታሰቢያ በዓል በድምቀት ተከብሯል።

የዕለቱ ትምህርተ ወንጌል በመጋቤ ወንጌል ሄኖክ ታዬ
"እስከ ሞት ድረስ የታመንህ ሁን የሕይወትንም አክሊል እሰጥሃለሁ ራዕ 2፥10 በሚል ኃይለ ቃል መነሻነት የዕለቱን በዓል በተመለከተ አስተምረዋል።

ምንጭ፦ መጋቤ ወንጌል ሄኖክ ታዬ

Guyyaan Yaadannoo Ayyaanna  boqonnaa Qulqulluu  Pheexiroosii fi Phaawuloos Mana Kiristaanaa Bufataa Qulqullootaa  Tulluu...
12/07/2025

Guyyaan Yaadannoo Ayyaanna boqonnaa Qulqulluu Pheexiroosii fi Phaawuloos Mana Kiristaanaa Bufataa Qulqullootaa Tulluu Abbootti haalaa Hoo'aa ta'en kabajameera.
+++++++++++++++++++++++++++++++++++++++
Adoolessa 5, 2017 B.A Miidiyaa M/Lallaba Shaggar ሸገር ሀገረ ስብከት ሚዲያ ||

Mana Kiristaanaa Ortodoksii Tawaahidoo Itiyoophiyaatti guyyaan Ayyaana boqonnaa Qulqullootaa ifa Addunyaa Qulqulluu Pheexiroosii fi Phaawuloos biyyaa lallabaa Magaalaa Shaggar kutaa Mana Lubummaa Magaalaa Kooyye Faaccee fi Galaan Mana Kiristaanaa buufata Qulqullootaa Tulluu Abbootti Sirna hoo'aan kabajameera.

Sirna kana irratti Hayyuun Afaanii, luba Badhaasaa Tolaa hoji gaggeessaa Kutaa Mana lubummaa Koyyee faaccee fi galaan ,Sooraa Nagaa Abbabaa Zaawudu Itti gaafatamaan kutaa gurmaa’insaa Sabaaka Gubaa'e Biyya lallabaa Magaalaa Shaggar, Bulchitoonni mana Kiristaanaa fi Kawaaloota, Luboonni, farfaatoonii Mana Barumsaa Sanbataa, fi amantoota Argamaniruu.
Barumsii guyyicha ilaalatu Kutaa Wangeelaa Qulqulluu Mul'ata Yoohannis 2:10 Ka'umsa taasifachuun kan barsisaan Sooraa Nagaa Abbabaa Zaawudu "Hanga du'aatti amanamaa ta'i, anis gonfoo jireenyaa siif nan kenna" jedhu irratti hundaa'uun waa'ee kabaja guyyichaa barsiisaniiru.

Dhumarratti hoji geggeessan Waliigalaa kutaa mana lubummaa kooyyee faaccee fi galaan Hayyuun afaanii luba badhaasaa tolaa ergaa baga geessani dabarsuudhaan kadhannaafi Eebbaan xumuramaniiru.

በቱሉ አቦ ምዕራፈ ቅዱሳን አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ቤተክርስቲያን የብርሃናተ ዓለም ቅዱስ ጴጥሮስ ወጳውሎስ የዕረፍታቸው መታሰቢያ በዓል በድምቀት ተከበረ። +++++++++++++++++++++...
12/07/2025

በቱሉ አቦ ምዕራፈ ቅዱሳን አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ቤተክርስቲያን የብርሃናተ ዓለም ቅዱስ ጴጥሮስ ወጳውሎስ የዕረፍታቸው መታሰቢያ በዓል በድምቀት ተከበረ።
+++++++++++++++++++++++++++
ሐምሌ 5 ቀን 2017 ዓ.ም ||ሸገር ሀገረ ስብከት ሚዲያ||

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን በሸገር ከተማ ሀገረ ስብከት በኮዬ ፈጩና ገላን ክፍላተከተማ በቱሉ አቦ ምዕራፈ ቅዱሳን አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ቤተክርስቲያን የብርሃናተ ዓለም ቅዱስ ጴጥሮስ ወጳውሎስ የዕረፍታቸው መታሰቢያ በዓል በድምቀት ተከበረ።

በበዓሉም ላይ ሊቀ ልሳናት ቀሲስ በዳሳ ቶላ የኮዬፈጬና ገላን ክፍላተ ከተማ ዋና ሥራ አስኪያጅ ፣ መጋቤ ሰላም አበበ ዘዉዱ የሸገር ከተማ ሀገረ ስብከት ሰበካ ጉባኤ ማደራጃ መምሪያ ክፍል ኃላፊ የክፍላተ ከተማው የየመምርያ ክፍል ኃላፊዎች የገዳማትና አድባራት አስተዳዳሪዎች ጸሐፊያን ሊቃውንተ ቤተክርስቲያን መምህራን ካህናት የሰንበት ትምህርት ቤት ወጣቶችና በርካታ ምእመናን ተገኝተዋል።

በዕለቱም በመጋቤ ሰላም አበበ ዘዉዱ"ኩን መሃይምነ እስከ ለሞት ወእሁበከ አክሊለ ሕይወት" እስከሞት ድረስ የታመንህ ሁን የሕይወትም አክሊል እሰጥሃለሁ ራዕ 2፥10 በሚል ኃይለ ቃል መነሻነት የዕለቱን በዓል በተመለከተ አስተምረዋል።

በመጨረሻም የክፍላተ ከተማው ዋና ሥራ አስኪያጅ ሊቀ ልሳናት ቀሲስ በዳሳ ቶላ እንኳን አደረሳችሁ መልእክት አስተላልፈው የበዓሉ ፍጻሜ ሆኗል።

ሐምሌ ፭ ቀን ፳፻ ፲ወ፯ ዓ.ም ||ሸገር ሀገረ ስብከት ሚዲያየብርሃናተ ዓለም ቅዱስ ጴጥሮስና ጳውሎስ በዓለ ዕረፍት ክብረ በዓል በሸገር ከተማ ሀገረ ስብከት በሜታ ፈለገ ሕይወት አቡነ ገብረ ...
12/07/2025

ሐምሌ ፭ ቀን ፳፻ ፲ወ፯ ዓ.ም ||ሸገር ሀገረ ስብከት ሚዲያ

የብርሃናተ ዓለም ቅዱስ ጴጥሮስና ጳውሎስ በዓለ ዕረፍት ክብረ በዓል በሸገር ከተማ ሀገረ ስብከት በሜታ ፈለገ ሕይወት አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ቤተ ክርስቲያን በደማቅ ተከብሮ ዋለ።

ምንጭ፦ መጋቤ አእላፍ ተስፋዬ ቂጤሳ|| የሸገር ከተማ ሀገረ ስብከት የስብከተ ወንጌል ክፍል ኃላፊ

‎የሐዋሳ ታቦር ፍኖተ ጥበብ መንፈሳዊ ኮሌጅ ለሦስት ዓመታት ያስተማራቸውን ደቀ መዛሙርት ብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጁ እና የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊው በተገኙበት አስመረቀ።============...
12/07/2025

‎የሐዋሳ ታቦር ፍኖተ ጥበብ መንፈሳዊ ኮሌጅ ለሦስት ዓመታት ያስተማራቸውን ደቀ መዛሙርት ብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጁ እና የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊው በተገኙበት አስመረቀ።
================================
|| ሐዋሳ|| ሐምሌ ፭ ቀን ፳፻ ፲ወ፯ ዓ.ም

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የታቦር ፍኖተ ጥበብ መንፈሳዊ ኮሌጅ ፲፭ ደቀ መዛሙርትን ቅዳሜ ሐምሌ ፭ ቀን ፳፻ ፲ወ፯ዓ/ም ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ የጠቅላይ ቤተክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ፣የደቡብ ምዕራብ ሸዋና የሸገር አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ፣የምስካየ ኅዙናን መድኃኔዓለም ገዳም የበላይ ኃላፊ፣የቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ዩኒቨርሲቲ የቦርድ ሰብሳቢ፣ ብፁዕ አቡነ ዲዮስቆሮስ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ፣ የደቡብ ምዕራብ ትግራይና የራያ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ፣ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት፣የጠቅላይ ቤተ ክህነት የመምሪያ ኃላፊዎችና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት ለመጀመሪያ ጊዜበደማቅ ሥነ ሥርዓት አስመርቋል።

ብፁዕ አቡነ ዮሴፍ የሲዳማ ሀገረ ስብከትና የሀዋሳ ታቦር ፍኖተ ጥበብ መንፈሳዊ ኮሌጅ የበላይ ሊቀ ጳጳስ በዚሁ የምረቃ መርኃ ግብር ላይ ባስተላለፉት አባታዊ መልዕክት በዛሬው ዕለት የተመረቃችሁ ደቀ መዛሙርት በምትሰማሩበት ሁሉ ማስተዋልና ጥበብን በመከተል ወደ ዓለም ዳርቻ ሁሉ ሂዱ ወንጌልንም ስበኩ የሚለውን የወንጌሉን ቃል በመከተልና በመተግበር እንድታገለግሉ አደራ በማለት አገልግሎታችሁ ሁሉ ውጤታማና የተሳካ ይሆን ዘንድ አምላካችን እግዚአብሔርን እንለምናለን ብለዋል።

በማያያዝም ኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያናችን ይህንን የትምህርት እድል እንዲመቻች ያደረገችው ዶግማ፣ቀኖናዋና ትውፊቷ ተጠብቆ ለተተኪው ትውልድ ይተላለፍ ዘንድ ነው። ያሉት ብፁዕነታቸው ዛሬ ለምረቃ የበቃችሁ ደቀ መዛሙርትም ይህንን ታላቅ ኃላፊነት ለመወጣት መዘጋጀትና በየትኛውም ስፍራና ሁኔታ ውስጥ ሁሉ የሚጠበቅባችሁን ሁሉ ለመወጣት የተዘጋጃችሁ መሆን ይኖርባችኋል ብለዋል።

ወደ ኮሌጃችን ለመማር ስትመጡ የገባችሁትን ቃል እንዲሁም ዛሬም በዚህ የምረቃ መርኃ ግብር ቤተክርስቲያንን እና ሕዝብን በቅንነትና በታማኝነት ለማገልገል የገባችሁት ቃል ኪዳን ባገኛችሁት ዕውቀትና ክህሎት በትጋት እንደ ምትፈጽሙት እምነታችን ጽኑዕ ነው ያሉት ብፁዕ አቡነ ዮሴፍ የኮሌጃችን የመጀመሪያ ምሩቃን ደቀ መዛሙርት ልጆቻችን! በሥራችሁ ሁሉ የምታሳዩት ጥረትና ትጋት እንዲሁም ለሁሉ አርዓያና ምሳሌ በመሆን በምትሰጡት አገልግሎት ቤተ ክርስቲያንን እና የተማራችሁበትን ኮሌጅ የምታስመሰግኑ እንደ ምትሆኑ እምነታችን ነው። መጪው የሥራና የአገልግሎት ዘመናችሁ ሁሉ የተቃና እንዲሆን ዘወትር ጸሎታችን ነው በማለት መልዕክታቸውን አጠናቀዋል።

በምረቃ መርኃ ግብር ላይ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶችና የተመራቂ ደቀ መዛሙርት ቤተሰቦች ተገኝተዋል።

በኮሌጁ ትምህርታቸውን ሲከታተሉ የቆዩትና በዛሬው ዕለት ለምረቃ የበቁት ደቀ መዛሙርት በሲዳምኛ፣በኦሮምኛ፣በዳውሮኛ፣
በከምባትኛ፣በሃድይኛ፣በጋሞኛ፣በኮይሬኛ፣በጌዲኦኛ፣በከፋኛና በወላይትኛ ቋንቋዎች ማስተማር የሚችሉ በመሆናቸው በቤተክርስቲያን አገልግሎት ዙሪያ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንደሚያበረክቱ ይታመናል።

በመጨረሻም ብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ የምሥራቅ ሸዋ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ለተመራቂ ደቀ መዛሙርት የእንኳን ደስ አላችሁ አባታዊ መልዕክት አስተላልፈው መርሐ ግብሩ በጸሎት ተጠናቋል።

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርሰቲያን የታቦር ፍኖተ ጥበብ መንፈሳዊ ኮሌጅ ለሦስት ዓመታት ሲያስተምራቸው የነበሩ 15 ደቀ መዛሙርትን በማስመረቅ ላይ ይገኛል።||ሐዋሳ|| ሐምሌ 5/20...
12/07/2025

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርሰቲያን የታቦር ፍኖተ ጥበብ መንፈሳዊ ኮሌጅ ለሦስት ዓመታት ሲያስተምራቸው የነበሩ 15 ደቀ መዛሙርትን በማስመረቅ ላይ ይገኛል።

||ሐዋሳ|| ሐምሌ 5/2017 ዓ/ም ||ሸገር ሀገረ ስብከት ሚዲያ||

ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ የጠቅላይ ቤተክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ፣የደቡብ ምዕራብ ሸዋና የሸገር ከተማ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ፣ ብፁዕ አቡነ ዲዮስቆሮስ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊና የራያ ሀገረ ስብከት ሊቀጳጳስ፣ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳትየ፣የጠቅላይ ቤተ ክህነት የየመምሪያ ኃላፊዎችና ጥሪ የተደረገላቸው የክብር እንግዶች በተገኙበት ለመጀመሪያ ጊዜ በማስመረቅ ላይ ይገኛል።
የ/ኢ/ኦ/ተ/ቤተክርስቲያን ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ/Department of Public Relation,EOTC

ብርሃናተ ዓለም ጴጥሮስ ወጳውሎስ ሐምሌ 5 ቀን 2017 ዓ. ም+++++++++++++++++++++++++++++++++++++ሐምሌ ፭ ቀን በአንድ በኩል የጾመ ሐዋርያት ፋሲካ የሚከበርበት ዕለት ...
12/07/2025

ብርሃናተ ዓለም ጴጥሮስ ወጳውሎስ

ሐምሌ 5 ቀን 2017 ዓ. ም
+++++++++++++++++++++++++++++++++++++
ሐምሌ ፭ ቀን በአንድ በኩል የጾመ ሐዋርያት ፋሲካ የሚከበርበት ዕለት ሲኾን፣ በሌላ በኩል ደግሞ የብርሃናተ ዓለም ቅዱስ ጴጥሮስና ጳውሎስ በዓለ ዕረፍትም በዚሁ ዕለት ይዘከራል፡፡ በዚህ ዝግጅታችን የእነዚህን ቅዱሳን ታሪክ በቅደም ተከተል በአጭሩ ይዘንላችሁ ቀርበናል፡፡

ቅዱስ ጴጥሮስ

ቅዱስ ጴጥሮስ በአባቱ የሮቤል፣ በእናቱ የስምዖን ነገድ ሲኾን፣ የተወለደውም በገሊላ አውራጃ በቤተ ሳይዳ ነው፡፡ ወላጆቹ ያወጡለት ስም “ስምዖን” ነበር፡፡ ጌታችን አምላካችንና መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ “ጴጥሮስ” ብሎ ጠርቶታል፡፡ ትርጕሙም በግሪክ ቋንቋ ዓለት (መሠረት) ማለት ነው፡፡ ቅዱስ ጴጥሮስ የሚተዳደረው በዓሣ አጥማጅነት የነበረ ሲኾን፣ ሰዎችን በወንጌል መረብ እያጠመደ ወደ ክርስትና ሕይወት ይመልስ ዘንድ ጌታችን ለሐዋርያነት ጠርቶታል /ሉቃ. ፭፥፲፤ማር.፩፥፲፮/፡፡

ቅዱስ ጴጥሮስ በመንፈሳዊ ቅንዓቱና ለጌታችን በነበረው ፍቅር የሐዋርያት አለቃ ኾኖ ተሹሟል፡፡ ለአገልግሎት ከተጠራበት ጊዜ ጀምሮም በእስያ፣ በሮም፣ በሰማርያ፣ በልዳ፣ በኢዮጴ፣ በአንጾኪያ፣ በገላትያና በሌሎችም አገሮች እየተዘዋወረ ወንጌልን ሰብኳል፡፡ በስብከቱ ምክንያትም ልዩ ልዩ መከራን ተቀብሏል፡፡ በክርስቶስ ኀይል አጋዥነት ብዙ ድንቆችንና ተአምራትን አድርጓል፡፡ ከተሰጠው ጸጋ ብዛት የተነሣ በጥላው ሕሙማን ይፈወሱ ነበር /ሐዋ. ፭፥፲፭/፡፡ ሐዋርያው በቃል ካስተማረው ትምህርት በተጨማሪ በመጽሐፍ ቅዱስ በስሙ የተመዘገቡ ሁለት መልእክታትን ጽፏል /፩ኛ እና ፪ኛ ጴጥሮስ/፡፡

የቅዱስ ጴጥሮስ ምድራዊ የአገልግሎት ዘመኑ ሊፈጸም ሲቃረብም እንዲህ ኾነ፤ በዘመኑ የክርስቲያኖች ጠላት የነበረው የሮም ንጉሥ ወደ አካይያ ዘምቶ ድል አድርጎ በደስታ ወደ ሮሜ ሲመለስ መኳንንቱን ለማስደሰት፤ ጣዖታቱንም ለማክበር ሲል በቅዱስ ጴጥሮስና በሌሎችም ክርስቲያኖች ላይ የሞት ፍርድ ዐወጀ፡፡ ቅዱስ ጴጥሮስም በሮም ሲያስተምር ቆይቶ የሮም መኳንንት እንዳይገድሉት ትጥቁን ለውጦ ከሮም ሲወጣ ጌታችን መስቀል ተሸክሞ ተገለጸለት፡፡

በዚህ ጊዜ “አቤቱ ጌታ ሆይ ወዴት ትሔዳለህ?” ሲል ቢጠይቀው ጌታችንም “ልሰቀል ወደሮም እሔዳለሁ” አለው፡፡ “ዳግመኛ ትሰቀላለህን?” ባለው ጊዜም “አንተ ስትፈራ ጊዜ ነው እንጂ” ሲል መለሰለት፡፡ ያንጊዜም “ጐልማሳ ሳለህ ወገብህን ታጥቀህ ወደ ወደድኸው ትሔድ ነበር፡፡ ስትሸመግል ግን እጅህን ታነሣና ሌላ ሰው ያስታጥቅሃል፤ ወደ ማትወደውም ይወስድሃል” /ዮሐ. ፳፩፥፲፰/ በማለት ጌታችን የነገረው ቃል አሟሟቱን የሚያመለክት መኾኑን አስታውሶ ወደ ሮም ተመልሶ ስብከቱን ቀጠለ፡፡ በሮማውያን ሕግ ቅጣት የተፈረደበት ወንጀለኛ የሮም አገር ተወላጅ ከኾነ የወንጀሉ ክብደትና ቅለት እየታየ ግርፋት ወይም ሞት ይፈረድበታል እንጂ፤ በአንድ ወንጀል ሁለት ቅጣት አይቀጣም ነበር፡፡ ወንጀለኛው የውጪ አገር ዜጋ (ከሮም ውጪ) ከኾነ ግን ለምሳሌ ቅጣቱ ግርፋት ከኾነ ከተገረፈ በኋላ እስራት ይጨመርበታል፤ ቅጣቱ ሞት ከኾነም ከገረፉት በኋላ በመስቀል ወይም በሌላ መሣሪያ ይገድሉት ነበር፡፡ ቅዱስ ጴጥሮስ ዜግነቱ ሮማዊ አልነበረምና በግርፋትም፣ በእስራትም በሞትም እንዲቀጣ ተፈረደበት፡፡

እንደ ሥርዐታቸውም ቅዱስ ጴጥሮስን ከገረፉት በኋላ ሊሰቅሉት ሲሉ ወታደሮቹን “እንደ ክብር ንጉሥ እንደ ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስአቁማችሁ ሳይኾን፣ ዘቅዝቃችሁ ስቀሉኝ” አላቸው፡፡ እነርሱም እንዳላቸው አድርገው ሐምሌ ፭ ቀን ዘቅዝቀው ሰቅለውታል፡፡ በመስቀል ላይ ሳለም ተከታዮቹን በሃይማኖታቸው እንዲጸኑ ካዘዛቸው በኋላ ነፍሱን ለእግዚአብሔር ሰጠ፡፡ ሥጋውንም መርቄሎስ የሚባለው ደቀ መዝሙሩ ሽቱ ቀብቶ፣ በነጭ ሐር ገንዞ ዛሬ ቫቲካን በምትባለዋ ሥፍራ በክብር ቀብሮታል፡፡

ቅዱስ ጳውሎስ

ቅዱስ ጳውሎስ ለአገልግሎት ከመጠራቱ በፊት “ሳውል” ይባል ነበር፡፡ ከኦሪቱ ምሁር ከገማልያል ሕገ ኦሪትንና መጻሕፍተ ነቢያትን ተምሯል፡፡ ለሕገ ኦሪት ቀናኢ ከመኾኑ የተነሣም የክርስቶስ ተከታዮችን ዅሉ ያሳድድ ነበር፡፡ ቅዱስ እስጢፋኖስ በድንጋይ ተደብድቦ በሰማዕትነት በሞተ ጊዜ ቅዱስ ጳውሎስ የገዳዮቹ ልብስ ጠባቂ ነበር /ሐዋ.፯፥፶፰፤ ፳፪፥፳/፡፡ ክርስቲያኖችን ለማሳደድ ወደ ደማስቆ ሲሔድ ከመንገድ ላይ ለሐዋርያነት ተጠርቷል /ሐዋ. ፱፥፩-፴፩፤ ፳፪፥፩-፳፩/፡፡

ለሐዋርያነት ከተጠራበት ጊዜ ጀምሮም በመላው ዓለም እየተዘዋወረ ወንጌልን በመስበክ ብዙዎችን በኢየሱስ ክርስቶስ ስም አሳምኗል፡፡ ሲሰብክም ጣዖት አምላኪ፣ ሕመምተኛ፣ ችግረኛ፣ አረማዊና አይሁዳዊ እየመሰለ ብዙዎችን አስተምሮ ለእግዚአብሔር መንግሥት አዘጋጅቷል /፩ኛ ቆሮ. ፱፥፲፱-፳፫/፡፡ ዐረብ፣ አንጾኪያ፣ እልዋሪቆን፣ ሊቃኦንያ፣ ሦርያ፣ ግሪክና ልስጥራን ካስተማረባቸው አገሮች ጥቂቶቹ ናቸው፡፡ ወንጌልን በመስበኩ ምክንያትም ከአይሁድና ከአረማውያን ዘንድ ብዙ መከራና ስቃይ ደርሶበታል፡፡ ቅዱስ ጳውሎስ ከእግዚአብሔር በተሰጠው ጸጋ ብዙ ድንቆችንና ተአምራትን አድርጓል፡፡ በልብሱ ቅዳጅም ሕሙማን ይፈወሱ ነበር /ሐዋ. ፲፱፥፲፩/፡፡ ሐዋርያው በቃል ካስተማረው ሌላ በመጽሐፍ ቅዱስ በስሙ የተመዘገቡ ፲፬ መልእክታት አሉት፡፡

አገልግሎቱን ሊፈጽም ሲልም የሮም ንጉሥ ኔሮን ቄሣር የክርስቲያኖች ቍጥር እየጨመረ የመጣው በቅዱስ ጳውሎስ ትምህርት በመማረካቸው ምክንያት መኾኑን ተረድቶ፤ ይልቁንም የቤተ መንግሥቱ ሰዎች ሳይቀር በቅዱስ ጳውሎስ በመማረካቸው ተቈጥቶ ቅዱስ ጳውሎስን ወደ ፍርድ ሸንጎው አስቀረበው፡፡ ቅዱስ ጳውሎስም በቀኝ እጁ ከሰንሰለቱ ጋር መስቀሉን ይዞ ንጉሡንና ወታደሮችን ሳይፈራ የኢየሱስ ክርስቶስን የእግዚአብሔር ልጅነትና አምላካዊ ሥልጣን ይመሰክር ነበር፡፡ ንጉሡም በቍጣ ይሙት በቃ ፈረደበት፡፡ ከላይ እንደ ተገለጸው ሮማውያን የሞት ፍርድ ሲፈርዱ የሚቀጣው ሰው የሌላ አገር ዜጋ ከኾነ ከፍርዱ ውጪ ተጨማሪ ቅጣት ይቀጡትና ይገድሉት ነበር፡፡ ቅዱስ ጳውሎስ ግን የሮም ዜግነት ስለ ነበረው ሳይገርፉ በአንድ ቅጣት ብቻ በሰይፍ እንዲገደል ወስነውበታል፡፡ ወደሚገደልበት ስፍራ ሲወስዱትም በንግግሩና በአስተያየቱ ሁሉ ምንም ፍርኀት አይታይበትም ነበር፡፡ እንዳውም በጦርነት ድል አድርጎና ማርኮ እንደ ተመለሰ ወታደር ይደሰት ነበር እንጂ፡፡ ለሚገድሉትም ይቅርታን ይለምን ነበር፡፡

በገዳዮቹና በተከታዮቹ ፊትም የክርስትና ሽልማቱ የእግዚአብሔር መንግሥት መኾኑን የሚያስገነዝብ ቃል እያስተማረ እግዚአብሔር የሚሰጠውን የጽድቅ አክሊል ለመቀበል ይቻኮል ነበር /፪ኛ ቆሮ. ፬፥፮-፲፰/፡፡ ወታደሮች ሊገድሉት ሲወስዱትም ከንጉሥ ኔሮን ወገን የኾነችውን የአንዲት ብላቴና መጐናጸፊያ “ዛሬ እመልስልሻለሁ” ብሎ ከተቀበላት በኋላ “መልካሙን ገድል ተጋድያለሁ፤ ሩጫዬንጨርሻለሁ፡፡ ሃይማኖቴን ጠብቄአለሁ፤ ወደፊትም የጽድቅ አክሊል ተዘጋጅቶልኛል” በማለት ራሱ በመልእክቱ እንደ ተናገረው (፪ኛ ጢሞ. ፬፥፯-፰)፣ ፊቱን በብላቴናዋ መጐናጸፊያ ተሸፍኖ አንገቱን በሰይፍ ተቀልቶ አገልግሎቱን በሰማዕትነት ፈጽሟል፡፡
ደቀ መዛሙርቱም ራሱን ከአንገቱ ጋር ቢያደርጉት እንደ ቀድሞው ደኅና ኾኖላቸው በክብር ገንዘው ቀብረውታል፡፡ ሰያፊው ቅዱስ ጳውሎስን እንደ ገደለው ለመናገር ወደ ንጉሡ ሲመለስም ያቺ መጐናጸፊያዋን የሰጠችው ብላቴና “ጳውሎስ ወዴት አለ?” አለችው፡፡ እርሱም “ራሱን ተቈርጦ በመጐናጸፊያሽ ተሸፍኖ ወድቋል” ሲላት “ዋሽተሃል፤ እነሆ ጴጥሮስና ጳውሎስ በእኔ በኩል አልፈው ሔዱ፡፡ እነርሱም የመንግሥት ልብስ ለብሰዋል፡፡ በራሳቸውም በዕንቍ ያጌጡ አክሊላትን አድርገዋል፡፡ መጐናጸፊያዬንም ሰጡኝ፡፡ ይህችውምእነኋት፤ ተመልከታት” ብላ ሰጠቸው፡፡ ከእርሱ ጋር ለነበሩትም አሳየቻቸው፡፡ አይተውም አደነቁ፤ ስለዚህም በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ አመኑ፡፡

ቅዱሳን ጴጥሮስ እና ጳውሎስ በስብከተ ወንጌል አገልግሎታቸው ጨለማውን ዓለም በማድመቃቸው “ብርሃናተ ዓለም” ተብለው ይጠራሉ፡፡ የቅዱሳኑ አገልግሎት፣ ገድላቸው እና ተአምራቸው በመጽሐፈ ስንክሳር፣ በዜና ሐዋርያት እና በገድለ ሐዋርያት በሰፊው ተጽፎ ይገኛል፡፡ ቅዱሳን ሐዋርያት ያቆዩልንን የቤተ ክርስቲያን አስተምህሮ ጠብቀን፣ በክርስቲያናዊ ምግባር ጸንተን እንድንኖር፤ የእግዚአብሔርን መንግሥት ለመውረስ እንድንበቃ የቅዱሳኑ ጸሎት ይርዳን፡፡

ወስብሐት ለእግዚአብሔር

ዋቤ መጻሕፍት፡-
መጽሐፍ ቅዱስ
መጽሐፈ ስንክሳር
ዜና ሐዋርያት
ገድለ ሐዋርያት

BAGA AYYAANA QULQULLUU PHAAWULOOS FI PHEEXIROOS GESSAAN.Adoolessa 5: Boqonna Qulqulluu Phaawuloos fi Qulqulluu Pheexiroo...
12/07/2025

BAGA AYYAANA QULQULLUU PHAAWULOOS FI PHEEXIROOS GESSAAN.

Adoolessa 5: Boqonna Qulqulluu Phaawuloos fi Qulqulluu Pheexiroosiitu kabajama.
❶ Qulqulluu Phaawuloos

Phawuloos jechuun meeshaa qulqulluu jechudha. “Meeshaa qulqulluu koon si taasisa” akkuma jedhu (Duuk.9:15). Maqaan isaa kan jalqabaa Saawul jedhama ture. Saawul jechuunis, kennaa Waaqayyoo jechuudha. Qulqullu Phaawulos biyyi isaa Israa’eli, gosa Biniyaam irraa iddoo magaalaa Tarsees jedhamtutti dhalate. Lammummaa Roomaa, qaba ture. Kunis, Room dur bulchiinsa ishee jala jiraniif lammummaa kennaa waan turteefi. Qulqulluu Phaawulos waggaa 15 yemmuu guutu, Tarseesii gara biyyaatti deebi’ee Gamaaliyaal irraa seera Yihudootaa hanga waggaa 30tti barate. Innis jalqaba yemmuu Gooftaan barsiisu Iyyaruusaalem waan tureef, seera Yihudotaa fi Ooritiif hinaafaa waan tureef kiristaanota ari’aa, baqachiisaa, ajjeesas ture (Ho.Du.Bu 8:1).
➡ Kana boodaas hinaaffaa isaa kana cimsuun waraqaa eeyyamaa kan kiristaanota hunda akka ajjeesuuf kennameefis waggaa 32ffaa isaatti argatee Iyyaruusalemii gara Damaasqoo ldeemee uummata kiristaanaa ajjesuufis karoorfatee karaa eegale. Gara Damaasqoo deemee l magaalatti seenuuf dhiyaatutti garuu, Gooftaan sagalee isaa dhageessise. “Saawul Saawul maaf na ari’ataa?” jedheen (Ho.Du.Bu. 9:4).
Saawulis “Ati eenyu” jedhee yoo gaafatu, “Ani Iyyasuus Isa Naazireeti” jedheen. Yeroo kanas kufee maal godhu jedhee kadhate. Waan gochuu qabus ni hubate. Gara magaalattiis galee ijji isaas arguu waan dadhabdeef, lubni Hanaaniyaa jedhamu tokko kadhateefii cuuphamee kiristaana ta’e, ijji isaas ni banamteef. Sana booda, gochaa isa duraa sanatti hin deebine (Gal. 1:12). Erga cuuphamee booda, Qulqulluu Phaawulos gara biyyoota Arabaa deemeera. Biyyoota garaa garaatti barsiisee, hidhamee waa hedduu argee, ergaawwan kitaaba qulqulluu 14 barreessees jira.
➡ Ayihudoonni waanyituu waan turaniif, waanuma hundaan sababa itti barbadanii isa reebaa turan. Yeroo tokkos Siilaas waliin hidhame halkan qixxee yoo tahu sagalee isaa ol fuudhee yemmuu kadhatu ifti manicha guute karri hundi banamee ture. Waardiyyaan isaanis, namootni hidhaman hundi waan deemanii bahan itti fakkaatee goraadee isaa ofitti luqqisee of ajjeesuf ka’e. Phaawulos garuu, “hundi keenyaa jirra, namni tokko osoo hin badin ati ammoo, of ajjeestaa?” jedheen. Wardiyyichis osoo of hin ajjeesin dhiiseera (Duuk16:39).pl
➡ Qulqulluu Phaawuloos, fakkaatee barsiisuudhaan ogummaa addaa qaba. Warra waaq-harkeetti bulanis akka nama waaq-harkeetti buluu ta’uudhaan isaan barsiiseera. Warra seera hin qabneef akka nama seera hin qabneen ta’e” akkuma jedhe (1Qor 9:21). Yeroo tokko Qulqulluu Pheexirosiifi Yoohanisiin Anitsooqiyaa dhaqaa barsiisaa jedheen. Duumessaan achi gahan. Yeroo kana uummani biyyasii waaq-harkeetti bulu turan. Warri biyya sanaas, Yohaannisiin mataa irraa haadanii karrarrati gatan; Pheexiroosinis jabeessanii reeban. Yeroo kana uffata lubootni waaq-harkee uffatan uffatee qulqulluu Phaawuloos dhufe. Magaalattii keessa ol seenee bilbila rukutee, uummataanis “ani Qeesaar irraa ergameen dhufe; namootni Gooftaa Kiristoos fudhaa jedhanii lallaban akka jiran dhagaheen dhufe; amma dafaa warra akkasii walitti naaf qabaa” jedheen.
Isaaninis ‘gara kootti fidaa’ jedhee ofitti waamee, uummata fuulduratti ‘Mee maal jettanii barsiiftuu?” jedheen. Isaanis, “Goftaan dhalatee du’ee dhala namaa fayyise; isa malee Gooftaan biraa hin jriu” jennee barsiifna” jedhaniin. Yeroo kana, “sobdoota” jedhee Pheexiroosiin kaballaadhan dhahe; “akkamitti Gooftaan du’aa ka’a?” jedheen. Pheexiroos ammoo, wanta hojii duraa isaa sanatti deebi’e itti fakkaatee, “Phaawuloos gara hojii kee duraatti deebite” jedheenii ture. “Egaa mee erga du’aa kaastu ta’ee, kan du’e kaasaatii anatti agarsiisaa” jedhee, mucaa motichaa erga du’ee ji’a lama ta’e, “naaf kaasaa” isaaniin jedheen. Isaanis, mucaa du’e kana kadhannaadhaan ni kaasan. Innis yeroo isaan mucicha kaasuuf kadhatan, dhoksaadhaan keessa isaatti ni kadhata ture.
Yeroo sana mucichi “eenyutu du’aa si kaase?” jedhanii yemmuu gaafatanitti, bifa qulqulluu Phaawuloos barbaadee, “isa kanatu na kaase” jedhee dubbate. Phaawuloos gara hojii isa durii sanatti deebi’innaa laata jedhanii Pheexiroos fa’a shakkanii waan turaniif malee, kadhannaan kanuma hunda isaanii ture.Uummanni walitti qabame sunis ajaa’iba kana yemmuu argan, amananii cuuphamaniiru.
Boodas bara 65tti, yemmuu sababa gubachuu magaalaa Roomaatiin Neeroon Qeesaar kiristaanota ajjeesaa turetti, magaalaa Niqoophiliyoon jedhamtutti yemmuu barsiisu, qabamee mana hidhaa gale. Waggaa lamaa fi baatii jaha mana dukkanaa keessatti erga hidhamee booda wareegame. Ayyaanni yaadannoo qulqulluu Phaawuloos Adoolessa 5 yaadatama.

❷ Qulqulluu Pheexiroos

Qulqulluu Pheexiroos Beetasaayidaa Galiilaatti dhalate (Yoh 1:45). Gosti inni irraa dhalates gosa Roobeel jedhama. Yeroo ijoollummaa isaattis, seera Yihuudootaa baratee guddate. Boodas, mana ijaarratee, maatii horatee, qurxummii kiyyeessee jiraachaa ture. Gooftaan keenya Iyyasuus Kiristoos garuu, qurxummii kiyyeessuu gachisiisee duuka bu’aa isaa taasise (Mat.4:18). Erga guyyaa tajaajila kanaaf waamameeti booda, duuka bu’oota waliin Gooftaa irraa baratee hanga guyyaa Gooftaan fannifamuuttis biraa hin dhabamne ture.
➡ Qulqulluu Pheexiroos yemmuu Gooftaan “Namoonni ilma namaatiin eenyu jedhu” duuka bu’oota gaafatetti. isaanis “kuun Eeliyaas, kuun Yohaannis cuuphaa siin jedhu; Kuun ammoo, raajota keessaa isa tokko siin jedhu” jedhanii deebisaniif. Gooftanis deebisee, isin hoo eenyu anaan jettu?” jedhee yemmuu gaafatutti, Qulqulluu Pheexiroos “ati Masihicha Ilma Waaqayyoo Jiraataati” jedhee deebiseef. Gooftaanis deebisee, “Yaa Simoon ilma Yoonaa, kana kan siif ibse Abbaa koo isa samiiwwan irraati malee, yaada foonii fi dhiigaa miti; kanaaf ati kan eebbifamteedha. Anis sittan hima, ati Pheexiroosi, kattaa kana irratti mana kiristaanaa koo nan ijaara, balballoonni si’oolis sochoosuu hin danda’an” (Maat.16:13-19).
➡ Ol ba’uu Gooftaa keenyaa Iyyasuus Kiristoos durattis erga du’aa ka’ee booda, gara Galaana Xibriiyaanoos cinaatti itti muldhatee, “Pheexiroos ilma Yoona na jaalattaa?” jedhee yeroo sadi irra deddeebi’ee Pheexiroosiin Gooftaan gaafateera. Kanaanis, “Ilmoolee koo bobbaasi, gorommii/da’aa koo eegi, hoolota koo bobbaasi” jedhee akeekkachiisee imaanaa itti kennee jira (Yoh.21:16-18).
➡ Qulqulluu Pheexiroos guyyaa shantammaffaa booda, lallaba guyyaa tokkootiin qofa namoota kuma sadi cuuphuu danda’eera (Ho.Du.Bu.2:41). Qulqulluu Pheexiroos ergaawwan lamas barreesseera. Ergaa isa jalqabaa kan barreesses, warra Yihudoonni arai’atanii fi warra rakkinni itti hammaatee baqannaadhan addunyaa garaa garaatti kiristaanota baqataniif ture. Ergaa isaa isa lammaffaa kan barreesse ammoo, Neeroon Qeesar kiristaanota irratti ka’ee gadadoo hamaa irraan gahaa waan tureef, qulqulluu Pheexiroos Eeshiyaadhaa hanga Baabiloon deemee yemmuu barsiisutti, kiristiiyanotni Eeshiyaa jiranis labsii Neeroon Qeesaar kanaan garmalee dhiphamanii osoo jiran, barumsa shakkii namoota barsiisanif haalli waan mijateefiif, dubbii sobaa kanaan kiristaanotni akka hin gowwoomnee fi amantaa isaannitti akka jabaataniif barreessee ture.
➡ Qulqulluu Pheexiroos tajaajila lallaba wangeelaa baldhaa taasise. Roomaa deemuun duratti, Iyyaruusaaleemi fi Samaariyaatti, Lidaa fi Iyyoopheetti, Eeshiyaa Xiqqootti, Phaanxoosi fi Qephedooqiyaatti, Galaatiyaa fi Biitaniyaatti akkasumas, biyyoota biraa hedduu keessa deemuun wangeela Kiristoos lallabeera. Boodas, gara Roomaatti ce’eera. Roomaattis wangeela barsiise dhukkubsattoota fayyisee, sababa ibidda Roomaa keessatti ka’ee Roomaa balleesseen, bara Neeroon Qeesaar kiristaanotni hedduun dhumaa waan turaniif, innis qabamee hidhame. Duutis irratti murtaa’ee akka fannifamu ta’e. Yemmuu fannifamus, “Ana akka Gooftaa ol na hin garagalchinaa gadi na gombisaatii na finnisaa” jedhee gadi garagalee fannifameera.
Erga du’ee boodas, barataa isaa kan ta’e Marqeelos fannoo irraa buusee akka seera biyyattiitti waynii fi aannaniin dhiqee, urgooftuu dibee uffata adiidhaan kafanee, saanduqa damma dibame keessa kaa’ee, hardha iddoo Vaatikaan jennee waamnu keessatti awwaaleera. Ayyaanni yaadannoo isaas Adoollesa 5 dha. Guyyaan qulqulluu Phaawuloos itti wareegame, kan qulqulluu Pheexiroos waliin tokko waan ta’eef, ayyanichi kun biyya keenyatti ayyaana qulqulluu Phaawuloosi fi qulqulluu Pheexiroos jedhamee kabajama.
Galanni Waaqayyoof haa ta’u; nuunis kadhannaa qulqulloota kanaatiin Waaqayyo dhiifama isaa nuuf haa taasisu; sugni isaas nu waliin haa ta’u; hanga bara baraatti Ameen.
, Obsaan Birhaanuu

በጠቅላይ ቤተ ክህነት በተዘጋጀው የክረምት የመምህራን ሥልጠና ለሸገር ከተማ ሀገረ ስብከት በተሰጠው ኮታ መሠረት የሚላኩት አገልጋዮች ዛሬ በሀገረ ስብከቱ ጽ/ቤት ተገኝተው መመሪያ ተቀብለዋል።...
11/07/2025

በጠቅላይ ቤተ ክህነት በተዘጋጀው የክረምት የመምህራን ሥልጠና ለሸገር ከተማ ሀገረ ስብከት በተሰጠው ኮታ መሠረት የሚላኩት አገልጋዮች ዛሬ በሀገረ ስብከቱ ጽ/ቤት ተገኝተው መመሪያ ተቀብለዋል።

ሐምሌ 04 ቀን 2017 ዓ.ም ሸገር ሀገረ ስብከት ሚዲያ

በብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ የደቡብ ምዕራብ ሸዋ እና የሸገር ከተማ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ የምስካየ ኅዙናን መድኃኔዓለም ገዳም የበላፊ ኃላፊ፣ የቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ዩኒቨርሲቲ የቦርድ ሰብሳቢ፣ መመሪያ ሰጪነት እና ፈቃድ የነገዋ ቤተ ክርስቲያን ተረካቢ ትውልድ በሆነው የሰንበት ት/ቤት ላይ ትኩረት ተሰጥቶ
ያለመታከት እየሠሩ መሆኑ ይታወቃል።
በመሆኑም ከሐምሌ 6 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ የሸገር ከተማ ሀገረ ስብከት ከመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት በተሰጠው ኮታ መሠረት በሸገር ከተማ ዙርያ ማለትም
1.ከሰበታ ገላን ጉዳ እና ፉሪ፣
2. ከቡራዩ፣ገፈርሳ ጉጄ እና መልካ ኖኖ ፣
3.ከኮዬ ፈጬ እና ገላን ፣
4. ከለገጣፎ ለገዳዲ እያ ኩራ ጂዳ እና
5. ከሱሉልታ እና መና አቢቹ ከፍላተ ከተሞች ቤተ ክህነት የተውጣጡ 6 የሰንበት ት/ቤቶች መምህራን የክረምት የመምህራን ሥልጠና እንዲወስዱ በብፁዕነታቸው የተፈቀደላቸው ደቀ መዛሙርት ዛሬ በሸገር ከተማ ሀገረ ስብከት ጽ/ቤት ተገኝተው መመሪያ ተስጥቷቸው ጸሎት ተደርጎላቸው ወደ ቅድስት ሥላሴ ዩኒቨርስቲ ተላኩ።
አያይዞም የሸገር ከተማ ሀገረ ስብከት ዋና ሥራ አስኪያጅ መልአከ ሰላም ቀሲስ አለማየሁ ተፈራ አባታዊ መመሪያ ሲሰጡ ሰንበት ት/ቤቶች ከየትኛውም ጊዜ በላይ በትኩረት ሥራ ሊሠራባቸው፣ ሊጠናከሩ፣ሊደራጁ እና በሥልጣናም ራሳቸው ሊያጎለብቱ እንደሚገባ እንዲሁም ከሥልጣናው በተመለሱ ጊዜ በትጋት ማገልገል እንደሚገባ ሀገረ ስብከቱ ትኩረት ሰጥቶ እንደሚሰራ ገልጸዋል።
በመጨረሻም ጸሎት በማድረግ ደቀመዛሙርቶችን ወደ ቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ዩኒቨርስቲ ተሸኝተዋል።
#መጋቤ ወንጌል ሄኖክ ታዬ|| የሸገር ከተማ ሀገረ ስብከት የሰ/ት/ቤት ማደራጃና ክፍል ኃላፊ።

Address

Addis Ababa

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Miidiyaa M/Lallaba Shaggar ሸገር ሀገረ ስብከት ሚዲያ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share