31/08/2024
እንኳን ደስ አለን!!
🏆🏆🏆🏆🏆🏆
የጉለሌ ከፍለ ከተማ ወረዳ 8 የብልፅግና ፓርቲ ወጣቶች ሊግ በ2016 በጀት አመት ማጠቃለያ ምዘና በክፍለ ከተማዉ ከሚገኙ ከ10 ወረዳዎች 2ኛ በመሆን ላስመዘገበዉ የላቀ የአፈፃፀም ዉጤት በከተማ ደረጃ የዕዉቅና የምስክር ወረቀት ተሸለሚ ሆኗል።
የጉለሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 08 ብልጽግና ፓርቲ ወጣቶች ሊግ አስተባባሪ ወጣት ታዬ ላይኬ እንደተናገሩት በከተማ ደረጃ በተደረገው ምዘና በክፍለ ከተማችን ካሉ 10 ወረዳዎች 2ኛ በመውጣቱ የእውቅና ሰረተፍኬት ተሸላሚ እንዲሆን አስተዋጾ ላደረጉ ወጣቶች ሊግ አባላቱን እና ባለድርሻ አካላት ምስጋና አቅርቧል።