Sabbontu Oromo

  • Home
  • Sabbontu Oromo

Sabbontu Oromo Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Sabbontu Oromo, Digital creator, .

01/07/2025
01/07/2025
01/07/2025

በማዕከላቱ ከ 1 መቶ ሺህ በላይ ወጣቶችን ተጠቃሚ ማድረግ ተችሏል።

ሐረር ሰኔ 24/2017(ሐክመኮ):-በሐረሪ ክልል የወጣቶች ስብዕና ልማት ማዕከላት ከ1 መቶ ሺህ በላይ ወጣቶችን ተጠቃሚ ማድረግ መቻሉን ተጠቆመ።

የሐረሪ ክልል ወጣቶች ስብዕና ልማት ማዕከል ስራ አስኪያጅ ወጣት ኢምራን አብዱሰመድ ማዕከሉ በዘርፉ ያከናወናቸውን አበይት ተግባራት በሚመለከት መግለጫ ሰጥተዋል።

በመግለጫውም በ2017 በጀት አመት በክልሉ በገጠር እና ከተማ በሚገኙ ስድስት የወጣቶች ስብዕና ልማት ማዕከላት የወጣቶች ተጠቃሚነትን በማረጋገጥ አበረታች ውጤት ተመዝግበዋል።

በተለይ ማዕከሉ እየሰጠው የሚገኘው አገልግሎት ወጣቶችን በሥነ-ምግባር ከማነፅ ባሻገር ተሰጥኦቸውን አውጥተው እንዲያዳብሩ ዕድል የፈጠረ መሆኑን ገልፀዋል።

በማዕከላቱ ወጣቶች ግዜያቸውን በአለባሌ ቦታ ከማሳለፍ ይልቅ ዕውቀት የሚገበዩበትን ስርዓት ለመፍጠር ዘርፈ ብዙ እንቅስቃሴዎችን እያደረገ እንደሚገኝም አክለዋል።

በተለይ በአስተሳስብ፣በስነ-ልቦና እና በስፖርት የዳበረ ወጣት ለመፍጠር በትኩረት ሲሰራ መቆየቱን ጠቁመዋል።

ማዕከላቱ ወጣቶች ያላቸውን ዕምቅ አቅም በመጠቀም ለክልሉ ዘላቂ ሰላምና ልማት የበኩላቸውን ሚና እንዲወጡ ማስቻሉንም አንስተዋል።

በኪነጥበብ፣ በስነ-ተዋልዶ፣ በፈጠራ እና ሰርቶ ማሳያ፣ በኢንፎርሜሽን ኮሙንኬሽንና ቴክኖሎጂ እንዲሁም ለስፖርታዊ እንቅስቃሴዎች ትኩረት በመስጠት ከ1 መቶ ሺህ በላይ ወጣቶችን ተጠቃሚ ማድረግ መቻሉንም ገልጸዋል።

በቀጣዩ የ2018 አዲሱ አመትም የወጣቱን ማሕበራዊ፣ ፓለቲካዊ እና ኢኮኖሚያዊ ተሳትፎ እና ተጠቃሚነት ይበልጥ ለማረጋገጥ የተጀመሩ ሁሉን አቀፍ ስራዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ ገለፅፀዋል።

30/06/2025

Address


Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Sabbontu Oromo posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

  • Address
  • Alerts
  • Claim ownership or report listing
  • Want your business to be the top-listed Media Company?

Share