Ethiopian Engineering Corporation

Ethiopian Engineering Corporation Engineering Service

08/07/2025
04/07/2025

ወልመል መስኖ ፕሮጀክት ቪድዮ

💦 🚜

28/06/2025

ሰንዳፋ - ጨፌ ዶንሳ የመንገድ ኮንስትራክሽን ፕሮጀክት ቪድዮ

ኮርፖሬሽኑ (EEC) ለመጀመሪያ ጊዜ በተቋራጭነት የሰንዳፋ - ጨፌ ዶንሳ የመንገድ ሥራ ፕሮጀክትን ወስዶ እየገነባ ነውፕሮጀክቱ ለ350 ሰዎች የሥራ ዕድል ፈጥሯል(ሰኔ 13 ቀን 2017 ዓ.ም)...
20/06/2025

ኮርፖሬሽኑ (EEC) ለመጀመሪያ ጊዜ በተቋራጭነት የሰንዳፋ - ጨፌ ዶንሳ የመንገድ ሥራ ፕሮጀክትን ወስዶ እየገነባ ነው

ፕሮጀክቱ ለ350 ሰዎች የሥራ ዕድል ፈጥሯል

(ሰኔ 13 ቀን 2017 ዓ.ም)፣ አዲስ አበባ፤

የኢትዮጵያ ኢንጅነሪንግ ኮርፖሬሽን (EEC) ቀድሞ ይታወቅበት ከነበረው የመንገድ ዲዛይንና የማማከር ሥራው ባሻገር፣ ከኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር የመንገድ ግንባታ ሥራ ተረክቦ ፤በጥራትና በፍጥነት በመገንባት ላይ ነው፡፡

የፕሮጀክቱ ሥራ አስኪያጅ ንጉሴ ነጋሽ (ኢንጅነር)፣ ከኮሙዩኒኬሽን አገልግሎቱ ጋር አድርገውት በነበረው ቃል- ምልልስ እንደገለጹት፤ መንገዱ፣ ከቢሾፍቱ ተነስቶ ሰንዳፋ ድረስ 51 ኪ.ሜ የሚሸፍን ሊንክ ሮድ መሆኑንና በሁለት የተከፈለ ሩራል ሴክሽን ኖሮት በ7 ሜትር ስፋት እንዲሁም ቀበሌ ሴክሽን 12 ሜትር ስፋት ያለው መንገድ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

ከዚህ ውስጥም ኮርፖሬሽኑ፣ ከቢሾፍቱ 29 ኪ.ሜ ተጉዞ ያለውንና ሰንዳፋ ለመድረስ 7 ኪ.ሜ እስኪቀር ድረስ ያለውን 14.71 ኪ.ሜ የሚሸፍን የአስፋልት ሊንክ ሮድ ሥራ ተረክቦ በመገንባት ላይ እንደሚገኝና ከ80% በላይ አፈጻጸም ላይ መድረሱን ጨምረው አስረድተዋል፡፡

ፕሮጀክቱ በቀጣዩ ከአንድ ወር ባልበለጠ ጊዜ ውስጥ ሙሉ ለሙሉ እንደሚጠናቀቅ የገለጹት የፕሮጀክቱ ሥራ አስኪያጅ ንጉሴ ነጋሽ (ኢንጅነር)፣ እስከአሁን ቋሚና የኮንትራት ሠራተኞችን ጨምሮ፣ ለ350 ሰዎች የሥራ ዕድል መፍጠሩንም ተናግረዋል፡፡

አክለውም፤ ኮርፖሬሽኑ ከዚህ ቀደም በርካታ የመንገድ ዲዛይንና የማማከር ፕሮጀክቶችን በአማካሪነትና በተቆጣጣሪነት እንዲሁም ሪኢኖቬሽንን ጨምሮ ልዩ ልዩ የኮንስትራክሽን ግንባታዎችን በጥራትና በፍጥነት መሥራቱንና በመሥራት ላይ መሆኑን በማስታወስ፤ በተቋራጭነት በመንገድ ግንባታ ደረጃ የመጀመሪያው ፕሮጀክቱ መሆኑን ጠቁመው በዚህም ልምድ መቀሰሙንና ሥራውም በመገባደድ ላይ መሆኑን አመላክተዋል።

የመንገዱ ፕሮጀክቱ ከአማራ ክልል በደብረ ብርሃን አዲስ አበባ - አዳማ ይደረግ የነበረውን ጉዞ፣ አዲስ አበባ መግባት ሳይጠበቅባቸው በአቋራጭ መጓዝ የሚያስችል ሲሆን በተጨማሪም በኦሮሚያ ክልል ውስጥ የሚገኙትን ምስራቅና ሰሜን ሸዋ ዞኖችን የሚያገናኝ መንገድ በመሆኑ፤ የአካባቢው ማኅበረሰብ ምርቶቹን ወደገበያ ለማቅረብ ከፍተኛ ጠቀሜታ ይኖረዋል፡፡

13/06/2025
“እየተጠናቀቀ ባለው የበጀት ዓመት ኮርፖሬሽኑ (EEC) ትላልቅ አገራዊ ፋይዳ ያላቸው ፕሮጀክቶችን በማጠናቀቅ ያስረከበበት ዓመት ነው”    ሽመልስ እሸቱ (ኢንጅነር)  ዋና ሥራ አስፈጻሚ(ሰኔ...
11/06/2025

“እየተጠናቀቀ ባለው የበጀት ዓመት ኮርፖሬሽኑ (EEC) ትላልቅ አገራዊ ፋይዳ ያላቸው ፕሮጀክቶችን በማጠናቀቅ ያስረከበበት ዓመት ነው”

ሽመልስ እሸቱ (ኢንጅነር) ዋና ሥራ አስፈጻሚ

(ሰኔ 4 ቀን 2017 ዓ.ም)፣ አዲስ አበባ፤

ሊጠናቀቅ ቀናት በቀሩት የ2017 ዓ.ም የበጀት ዓመት፣ የኢትዮጵያ ኢንጅነሪንግ ኮርፖሬሽን (EEC)፣ ትላልቅ አገራዊ ፋይዳ ያላቸው ፕሮጀክቶችን በማጠናቀቅ ያስረከበበት ዓመት መሆኑን፤ የኮርፖሬሽኑ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ሽመልስ እሸቱ (ኢንጅነር) ገልጸዋል፡፡

ዋና ሥራ አስፈጻሚው ከኮርፖሬት ኮሙዩኒኬሽን አገልግሎቱ ጋር በነበራቸው ቆይታ ወቅት እንደገለጹት፤ ከፕሮጀክቶች አፈጻጸም አኳያ 76 ገደማ ፕሮጀክቶች መጠናቀቃቸውን አስረድተዋል፡፡

የ2017 ዓ.ም ዕቅድን አስመልክቶም ያነሱት ዋና ሥራ አስፈጻሚው፣ በፋይናንሻልም ሆነ ኢ- ፋይናንሻል (Financial / Non Financial KPI’S) ረገድ ጥሩ አፈጻጸም የተመዘገበበት ዓመት መሆኑን አመልክተዋል፡፡

በዚህም ከባለፈው በጀት ዓመት ጋር ሲነጻጸር በፋይናንሱ 60% አመታዊ ጭማሪ (Year on year growth )የታየበት መሆኑንና ይህም ለኢንዱስትሪው ትልቅ ማሳያ በመሆኑ፤ በየአመቱ እየተመዘገበ ያለውን ውጤታማ አፈጻጸም በመጪው በጀት ዓመትም ማስቀጠል መቻል እንደሚገባ በማኔጅመንት ደረጃ መግባባት ላይ እንደተደረሰበት በአጽንኦት አንስተዋል፡፡

በመጨረሻም ኮርፖሬሽኑ (EEC) በበጀት ዓመቱ ከሀገር ውስጥ በተጨማሪ በሌሎች የአፍሪካ አገራት የመንገድና የውኃ የማማከር ፕሮጀክቶችን እያከናወነ መሆኑን ያወሱ ሲሆን ከፋይናንስ ጤናማነት አኳያ የ2016 በጀት ዓመት የፋይናንስ ኦዲት ሪፖርት ከነቀፌታ የፀዳ (Clean on unqualified) ሆኖ የተጠናቀቀ መሆኑንም ኃላፊው ጨምረው ገልጸዋል፡፡

09/06/2025

የወይጦ (RV3-HPP) የጂኦቴክኒካል እና ጂኦፊዚካል ጥናት ቪድዮ

እንኳን ለ1446ኛው የኢድ አል-አድሃ (አረፋ) በዓል በሰላም አደረሳችሁበዓሉ የሠላም፣ የፍቅርና የደሰታ እንዲሆንላችሁ እንመኛለን።ኢድ ሙባረክ!የኢትዮጵያ ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን
05/06/2025

እንኳን ለ1446ኛው የኢድ አል-አድሃ (አረፋ) በዓል በሰላም አደረሳችሁ

በዓሉ የሠላም፣ የፍቅርና የደሰታ እንዲሆንላችሁ እንመኛለን።
ኢድ ሙባረክ!

የኢትዮጵያ ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን

ኮርፖሬሽኑ (EEC) የመንገድ ሥራ ፕሮጀክቱን እስከ በጀት አመቱ መጨረሻ ድረስ ለማጠናቀቅ ተግቶ እየሰራ መሆኑን አስታውቋልግንቦት 20 ቀን 2017 ዓ.ም፣ (ኢተያ-ሮቤ)፤ኮርፖሬሽናችን (EEC...
28/05/2025

ኮርፖሬሽኑ (EEC) የመንገድ ሥራ ፕሮጀክቱን እስከ በጀት አመቱ መጨረሻ ድረስ ለማጠናቀቅ ተግቶ እየሰራ መሆኑን አስታውቋል

ግንቦት 20 ቀን 2017 ዓ.ም፣ (ኢተያ-ሮቤ)፤

ኮርፖሬሽናችን (EEC)፣ ያለፉትን ሁለት አመታት በአማካሪነት እየተሳተፈበት የሚገኘውንና ከተጀመረ ስምንት አመታት ያስቆጠረውን የኢተያ - ሮቤ - ሴሩ የመንገድ ግንባታ ፕሮጀክት፣ እየተገባደደ ባለው እስከ በጀት ዓመቱ መጨረሻ ድረስ ለማጠናቀቅ ርብርብ እየተደረገ መሆኑን አስታውቋል፡፡

ይህ ከአዲስ አበባ 150 ኪ.ሜ ከምትርቀው ኢተያ ተነስቶ፤ አርሲ- ሮቤ ከተማ ላይ የሚያልቀው ምዕራፍ አንድ የመንገድ ሥራ ፕሮጀክት በአጠቃላይ 75.6 ኪሎ ሜትር ርዝመት ያለው የአስፋልት ኮንክሪት የመንገድ ግንባታ ፕሮጀክት ሲሆን ከዚሁ ውስጥ 68.5 ኪ.ሜ የአስፋልት ንጣፍ ሥራው መከናወኑን በኢትዮጵያ ኢንጅነሪግ ኮርፖሬሽን (EEC) የፕሮጀክቱ ተጠሪ መሃንዲስ ጌታቸው ዳንኤል (ኢንጅነር) ገልጸዋል፡፡

በዋንኛነት የሚቀሩ ሥራዎችን አስመልክቶም ከኮርፖሬት ኮሙዩኒኬሽን አገልግሎቱ ለቀረበላቸው ጥያቄ ሲመልሱ፡- ቀሪ ሥራው በሮቤ ከተማ መሆኑን በመጠቆም፤ ይኸውም በመንገዱ ከሚገኙ አራት የወረዳ ማዕከላት፣ ሮቤ በፕሮጀክቱ መጨረሻ የሚገኝ ሲሆን ርዝመቱ 5.6 ኪ.ሜ ገደማ መሆኑንና የአፈር ቆረጣና ሙሌት እንዲሁም የተፋሰስ (Derange) ሥራን ጨምሮ የ ድልድይ ግንባታ ሥራ እየተከናወነ መሆኑን ሥፍራው ድረስ በመውሰድ አስመልክተዋል፡፡

ለፕሮጀክቱ እስካሁን መዘግየትም የተቋራጩን በሙሉ አቅም ወደሥራ ሳይገባ መቆየትና መንገዱ በአብዛኛው የሚያልፍበት ወደ 23 ኪ.ሜ ገደማ፣ የወረዳ ማዕከላትና ቀበሌዎች እንደመሆናቸው፣ ከወሰን ማስከበርና ከከሳ ክፍያ ጋር ተያይዞ መሆኑን ተጠሪ መሃንዲሱ አስገንዝበዋል፡፡

ይሁን እንጂ ኮርፖሬሽናችን (EEC) የማማከሩን ኮንትራት ወስዶ ወደሥራ ከገባበት ያለፉትን ሁለት ዓመታት አንስቶ፤ ለኮንትራክተሩ አስፈላጊውን ድጋፍ በማድረግ የተሻለ የሥራ ፍጥነትና ጥራት ለማምጣት መቻሉን የጠቀሱት ተጠሪ መሃንዲሱ፤ ጠቅላላ የፕሮጀክቱን ሥራ እስከ ሰኔ መጨረሻ ድረስ ለማጠናቀቅ ርብርብ በመደረግ ላይ መሆኑን በመግለጽ፤ በዚህም በፕሮጀክቱ መዘግየት ሳቢያ ከአካባቢው ኅብረተሰብ ይነሱ የነበሩ ጥያቄዎች ምላሽ የሚያገኙበት ጊዜ ሩቅ እንደማይሆን ጌታቸው ዳንኤል (ኢንጅነር) ጨምረው አስረድተዋል፡፡

ይህ የአግረኛ እና የውሃ ማፈሰሻን ጨምሮ በወረዳና በከተማ ከ19 – 21 ሜትር በተመሳሳይ በቀበሌ 15 ሜትር የመንገድ ስፋት፣ በገጠር ደግሞ የመንገድ ትከሻን ጨምሮ 10 ሜትር ስፋት ያለው የመንገድ ፕሮጀክት፣ ከዚህ ቀደም በጠጠር ደረጃ የነበረ ሲሆን ካለው ከፍተኛ ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ጥቅም አኳያ ደረጃውን በጠበቀ መልኩ በአስፋልት ኮንክሪት እየተገነባ ይገኛል፡፡

ይህን ተከትሎም በአርሲ ዞን ውስጥ የሚገኙትን የሄጦሣ፣ የሎዴ ሄጦሳ፣ የዲክሲስ እና ሮቤ ወረዳዎችን እንዲሁም ቦሩ ሌንጫ፣ የጎበያ፣ የአርብ ገበያ፣ የእድገት ፋና እና የቡላላ ቀበሌዎችን በማስተሳሰር ምቹ የትራንስፖርት እንቅስቃሴ እንዲኖር ከማስቻሉ በተጓዳኝ በአካባቢው የሚመረቱ የግብርና ምርቶችን በቀላሉ ወደ መሃል አገር ተደራሽ በማድረግ፤ የአካባቢውን አምራችና ሸማቹን ኅብረተሰብ ተጠቃሚ እንደሚያደርግ ታምኖበታል፡፡

“የሀዋሳ ከተማ ኮሪደር ልማት ፕሮጀክት በከፍተኛ ትኩረትና ክትትል እየተሰራ ነው ” ዮሴፍ መኮንን (ኢንጅነር)ግንቦት 17 ቀን 2017 ዓ.ም፣ (ሀዋሳ) ፤የኢትዮጵያ ኢንጅነሪንግ ኮርፖሬሽን (...
25/05/2025

“የሀዋሳ ከተማ ኮሪደር ልማት ፕሮጀክት በከፍተኛ ትኩረትና ክትትል እየተሰራ ነው ” ዮሴፍ መኮንን (ኢንጅነር)

ግንቦት 17 ቀን 2017 ዓ.ም፣ (ሀዋሳ) ፤

የኢትዮጵያ ኢንጅነሪንግ ኮርፖሬሽን (EEC) በሀዋሳ ከተማ በግንባታ ላይ ያለው የመንገድ ሥራ ግንባታ ፕሮጀክት ጥራቱን ጠብቆ በማጠናቀቅ የከተማውን የትራፊክ ፍሰት እንዲያሳልጥ ትኩረት ተደርጎ እየተሰራ መሆኑን አስታውቋል፡፡

በኮርፖሬሽኑ (EEC) የፕሮጀክቱ ተጠሪ መሃንዲስ ዮሴፍ መኮንን (ኢንጅነር) በተለይ ለዝግጅት ክፍላችን እንደገለጹት፤ፕሮጀክቱ የሀዋሳ ሐይቅ ዳርቻ ላይ እንደመገኘቱ፣ ወደከተማዋ የሚመጡ ጎብኚዎችን ጨምሮ የእግረኛና የብስክሌት መንገድ፣ እና የአረንጓዴ ስፍራዎችን ጭምር ማካተቱን በመግለጽ፤ ይህ ፕሮጀክት እንደተጠናቀቀ በሁለተኛው ፌዝ የህፃናት መጫወቻን አካቶ የመዝናኛና የፓርኪንግ አገልግሎቶች ያሉበት ግንባታ እንደሚኖር አስታውቀዋል፡፡

ይህ በአምስት ሎቶች ተከፋፍሎ በግንባታ ላይ ያለው የመንገድ ሥራ ፕሮጀክት 5.43 ኪ.ሜ የሚሸፍን ሲሆን ለአብነትም በሎት 1 ላይ በጠቅላላው 26 ሜትር ስፋት ያለውና በአንድ ጊዜ ስምንት ተሽከርካሪዎችን ማሳለፍ እንዲችል ሆኖ ግንባታው እየተከናወነ ይገኛል፡፡

በኮርፖሬት ኮሙዩኒኬሽን አገልግሎቱ የመስክ ምልከታም፣ ከሳውዝ ስፕሪንግ እስከ ሐይሌ ሪዞርት መጋጠሚያ ድረስ ያለው መንገድ የእግረኛ መንገዱን ጨምሮ ሙሉ ለሙሉ የአፈር ቆረጣው ሥራ ተጠናቆ፤ የመጨረሻ ንጣፍ (Base Course) ሥራዎች በመከናወን ላይ መሆኑን ተመልክቷል፡፡

ከዚሁ ጋር በተያያዘ የአስፋልት ንጣፍ ሥራውንም በቅርብ ቀናት ውስጥ ለመጀመር በዕቅድ ተይዞ እየተሰራ መሆኑም ታውቋል፡፡

ኮርፖሬሽናችን (EEC) በሀዋሳ ከተማ የኮሪደር ልማት ግንባታ ፕሮጀክት ላይ በዲዛይንና ሱፐርቪዥን ሥራዎች ተሳትፎ እያደረገ ሲሆን ከከተማው ወደ አውሮፕላን ማረፊያ የሚወስደውን መንገዱን ጨምሮ ላለፉት ሁለት አስርተ ዓመታት በከተማዋ የውስጥ ለውስጥ መንገዶችም ላይ በዲዛይንና ሱፐርቪዥን ጉልህ አሻራውን ማሳረፉ ይታወሳል፡፡

ከዚህ ቀደም የአዲስ አበባ፣ ጅማ፣ አዳማና ቢሾፍቱ ከተሞች የኮሪደር ልማት ፕሮጀክቶች ላይ ኮርፖሬሽናችን (EEC) እንደሚሳተፍ መዘገባችን ይታወቃል።

Agreement signed Between EEC and Federal First Instance Court of the FDRE.May 23, 2025 (Lideta, Addis Ababa)The scope of...
23/05/2025

Agreement signed Between EEC and Federal First Instance Court of the FDRE.

May 23, 2025 (Lideta, Addis Ababa)

The scope of work encompasses study design, supervision, and contract administration for a 2B+G+9 Building project with a built-up area of 1600m² with the Contract Value of 25 million Birr.

We Got Our First Private Client for the Construction Sector!May 21,2025 (Addis Ababa)We are delighted to announce that w...
21/05/2025

We Got Our First Private Client for the Construction Sector!

May 21,2025 (Addis Ababa)

We are delighted to announce that we have signed a contract with Ethiopia Union Mission of the Seventh-Day Adventist Church

Client: Ethiopia Union Mission of the Seventh-Day Adventist Church

Consultant: Zeleke Belay Architect PLC

Scope: Construction works of the structure works of Eastern Ethiopia Union Mission of the Seventh-Day Adventist Church 2B+G+15 multipurpose building

Amount: 803,970,655.48 ETB

Duration: 540 calendar days

Location: Addis Ababa, Ethiopia

We thank our team for their dedicated work on securing this project. We wish good luck and success to the entire team to be involved.

Address

Addis Ababa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Ethiopian Engineering Corporation posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share