kassa Gelana

kassa Gelana Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from kassa Gelana, Media/News Company, .

07/06/2025

ኢትዮጵያ ትቅደም

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) ከናይጄሪያዊው ባለሃብት አሊኮ ዳንጎቴ ጋር ተወያዩአዲስ አበባ፣ ግንቦት 30፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከናይጄሪያዊው ...
07/06/2025

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) ከናይጄሪያዊው ባለሃብት አሊኮ ዳንጎቴ ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 30፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከናይጄሪያዊው ባለሃብት አሊኮ ዳንጎቴ ጋር ተወያይተዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሑፍ ÷ዛሬ ወንድሜን አሊኮ ዳንጎቴን ተቀብዬ አነጋግሬያለሁ ብለዋል።

በውይይታቸውም ለኢትዮጵያ ወሳኝ የሆኑ ፍላጎቶችን ለማሟላት የሚያስችሉ ስልታዊ የኢንቨስትመን መስኮች ላይ መክረዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) ከአሊኮ ዳንጎቴ ጋር ያለው ትብብር ተጠናክሮ እንደሚቀጥል እምነታቸው መሆኑን ገልጸዋል፡፡

ሩሲያ በዩክሬይን ላይ በ407 ድሮኖችና በ45 ሚሳኤሎች ጥቃት ሰነዘረች፡፡ በትላንትናው እለት ሩሲያ በፈፀመችው በዚህ ጥቃት ቢያንስ አምስት ሰዎች መገደላቸውንና ከ70 በላይ መቁሰላቸውን የዩክ...
07/06/2025

ሩሲያ በዩክሬይን ላይ በ407 ድሮኖችና በ45 ሚሳኤሎች ጥቃት ሰነዘረች፡፡ በትላንትናው እለት ሩሲያ በፈፀመችው በዚህ ጥቃት ቢያንስ አምስት ሰዎች መገደላቸውንና ከ70 በላይ መቁሰላቸውን የዩክሬይን ባለስልጣናት ገልፀዋል፡፡
የዩክሬይን አየር ሀይል ባወጣው መግለጫ ሩሲያ ከላከቻቸው 407 ድሮኖች መካከል 368ቱን ማክሸፉን ገልፆ ከ45ቱ ሚኤሎች ውስጥ 36ቱን መመከቱን አስረድቷል፡፡ ከእነዚህ መካከል ስድስቱ ኢስካንዳር የሚባሉት ሚሳኤሎች መሆናቸውንም ገልጿል፡፡
ሩሲያ ዛሬ አርብ ይህንን ጥቃት የፈፀመችው በመላው ዩክሬይን ሲሆን በተለይ ዋና ከተማዋ ኬይቭ ላይ ከፍተኛ የሚባለው ምት መድረሱ ተዘግቧል፡፡ በተለይም በበርካታ መሰረተ ልማቶች ላይ ጥቃቱ ያነጣጠረ መሆኑን የጠቀሱት ዘገባዎች በዩክሬይን የሚገኙ ቁጥራቸው ቀላል የማይባሉ የባቡር መስመሮች መቋረጣቸውንም አስረድተዋል፡፡ በተያያዘ የሩሲያ መከላከያ ሚኒስትር ባወጣው መግለጫ ዛሬ መጠነ ሰፊ ጥቃት ማከናወኑን አስታውቋል፡፡
በመግለጫው ‹‹የኬይቭ መንግስት ለፈፀመው የሽብር ጥቃት መልስ የሚሆን በምድር፣ በአየርና በባህር የሚወነጨፉ ሚሳኤሎችንና ድሮኖችን ተጠቅመን እርምጃ ወስደናል፡፡ ሁሉም ኢላማዎቻችን ወታደራዊ ናቸው›› ብሏል፡፡ ይህ በእንዲህ እንዳለ የአሜሪካው ፕሬዝደንት ትራምፕ ትላንት ባደረጉት ንግግር ዩክሬይንና ሩሲያን ወደሰላም ከማምጣት ይልቅ ትንሽ ጊዜ እንዲዋጉ መፍቀድ የተሻለ ሊሆን ይችላል ማለታቸው ይታወሳል፡፡

03/06/2025
03/06/2025
03/06/2025
03/06/2025
02/06/2025
30/05/2025
27/05/2025
23/05/2025

Address


Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when kassa Gelana posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

  • Address
  • Alerts
  • Claim ownership or report listing
  • Want your business to be the top-listed Media Company?

Share