Borkena

Borkena Borkena - Your online Ethiopian News portal. We believe that Truth Matters! Support - https://borkena.com/subscribe-borkena/ Truth Matters!

https://borkena.com/ is Ethiopian News and Informed opinion website.

የገዳዮቹ መለቀቅ ለእኛ ሁለተኛ ሞት ነው - ቤተሰቦቿከሁለት ዓመት በፊት በመቐለ በአሰቃቂ ሁኔታ ተገድላ በነበረችው ዘውዱ ሃፍቱ ግድያ ተጠርጥረው እድሜ ልክ እስራት የተፈረደባቸው ሁለት ፍርደ...
06/08/2026

የገዳዮቹ መለቀቅ ለእኛ ሁለተኛ ሞት ነው - ቤተሰቦቿ

ከሁለት ዓመት በፊት በመቐለ በአሰቃቂ ሁኔታ ተገድላ በነበረችው ዘውዱ ሃፍቱ ግድያ ተጠርጥረው እድሜ ልክ እስራት የተፈረደባቸው ሁለት ፍርደኞች በነጻ እንዲሰናበቱ መወሰኑ ተገልጿል።

የመቐለ መካከለኛ ደረጃ ፍርድ ቤት፣ ያሬድ ገብረስላሴ እና አንገሶም ኃይለማርያምን ነጻ ናቸው ብሏቸዋል።

ውሳኔው የተላለፈው ለታችኛው ፍርድ ቤት በማስረጃነት ቀርቦ የነበረ ዲጅታል ሰነድ ከፍርድ ቤቱ መዝገብ ቤት በመጥፋቱ መሆኑን የዘውዱ ቤተሰቦች ተናግረዋል።

ዘውዱ ነሃሴ 13/2015 የአሸንዳ በዓል ለመታደም ተዘጋጅታና የጓደኛዋን ልደት ለማክበር ከቤት በወጣችበት አዲሃውሲ በተባለ ቦታ ምሽት ላይ ተገድላ አስክሬኗ በመኪና ተጎትቶ መንገድ ላይ ተጥሎ ነው የተገኘው።

በዚህ ዘግናኝና አስደንጋጭ ግድያ ምክንያት መሪር ሃዘን ውስጥ የገቡት የሟች አባት ህይወታቸው አልፏል።

ነገርግን በትናንትናው እለት በዋለው ችሎት
ፍርደኞቹ ነጻ መባላቸውን የተናገረችው የሟች ታናሽ እህት ብርቱካን ሃፍቱ ተከሳሾች መጀመሪያ ወደ ክልል ፍርድ ቤት ነው ይግባኝ ያሉት ክልል ፍርድ ቤት መዝገቡን አይቶ የተፈረደው ፍርድ ትክክል ነው ብሏል፣
አሁን ፍርዱ ተቀልብሶ በነጻ እንዲፈቱ ተወስኗል ስትል በሀዘን ስሜት አስረድታለች።

ይህ ለቤተሰብ ከባድ ነው። ለእኛ ሁለተኛ ሞት ነው። አዲስ ሀዘን ነው የሆነብን። ለእኛ እዚህ ለምንቀረው እንጂ ለሷ ምንም ነገር አይደለም ማለቷን ቢቢሲ ዘግቧል።

ትንሽ በአእምሮ እረፍት አግኝተን ነበር። አሁን ተመስሎ ነጻ ነው ሲባሉ ቤተሰቡ ሁለተኛ ሀዘን ነው ቁጭ ያለው። እንደ አዲስ ሀዘን ነው ቁጭ ያልነው። ስናለቅስ ነው የዋልነው በማለት ተናግራለች።

የተከሳሽ ወገኖች ችሎት ውስጥ ረብሻና ግርግር መፍጠር፣ መበጥበጥ፣ ዳኞችን እንደመስሳችኋለን ቀናችሁን ጠብቁ እያሉ ሲያስፈራሩ ነበር።

ልክ ውሳኔ ሊሰጥ ሲልም በረብሻ ምክንያት ውሳኔዎች ቀናቸው ሲቀየር ነበር። በተጨማሪ ወንጀለኞቹ ፍርድ እንደማይቀርላቸው ሲያውቁ ፍርድ እንዲቀልላቸው የቆየ ህመም አለብን ቢሉም ምንም አይነት የቆየ ህመም እንደሌለባቸው በህክምና ማስረጃ ሁሉ ተረጋግጦ እድሜ ልክ እስራት ነው የተፈረደባቸው።
#ፍትህ #ትግራይ #መቀሌ #ዜና

የመንግሥት ባለስልጣናት ያልተገባ ተፅዕኖ እያሳደሩ ነው - ተመካካሪዎች ባለስልጣናት የሚመጡት ለተሳትፎ እንጂ ለጫና አይደለም - ፕሮፌሰር መስፍን የአገራዊ የምክክር ጉባዔ በአጀንዳ ጭብጦች ላ...
06/08/2026

የመንግሥት ባለስልጣናት ያልተገባ ተፅዕኖ እያሳደሩ ነው - ተመካካሪዎች

ባለስልጣናት የሚመጡት ለተሳትፎ እንጂ ለጫና አይደለም - ፕሮፌሰር መስፍን

የአገራዊ የምክክር ጉባዔ በአጀንዳ ጭብጦች ላይ ገለጻና ማብራሪያ እንዲሰጡ የተመደቡ አመካካሪዎች፣ምሁራንና ቃለ ጉባዔ ያዦች፣ ተመካካሪዎች የሚያነሱትን ሃሳብ ባለመቀበልና በተለይ የመጡበትን ተቋም መሠረት ያደረገ አቋም በመያዝ፣ ተመካካሪዎች ሐሳብ እንዲቀይሩና የምክክር ሒደቱ እንዲዘገይ ተፅዕኖ እያሳደሩ መሆኑን ስማቸው እንዲገለጽ ያልፈለጉ ተመካካሪዎች ተናግረዋል።

በተለይ መንግሥትን ወክለው የመጡ አመካካሪዎች እንደ የመንግሥት አደረጃጀትና አገር ግንባታ ያሉ አጀንዳዎችን በተመለከተ ከምክክሩ ሒደት ባፈነገጠ መልኩ የራሳቸውን ሐሳብ ማንፀባረቃቸውን ምንጮች ተናግረዋል።

የመንግሥት አደረጃደት አጀንዳን በተመለከተ እንዲያወያዩ በኮሚሽኑ የተመደቡ አመካካሪዎች በዚህ የተነሳ ለቀናቶች ውይይት እንዳይመሩና ማይክ ብቻ እንዲያቀብሉ በማድረግ፣ በእነርሱ ምትክ ደግሞ ከቡድን መሪዎች ተመርጠው ውይይት እንዲመሩ መደረጉን ገልጸዋል።

ከዚህ አልፎ የኮሚሽኑ አመካካሪዎች ውይይት እንዲመሩ የተደረገበት ሁኔታ መኖሩን ጨምረው ተናግረዋል። በዚህ የአጀንዳ ሐሳብ በተለይ የተለያዩ የፓርቲዎችን ወክለው የተገኙ ተመካካሪዎች የአመካካሪዎች አካሄድ በተመለከተ ቅሬታ አቅርበው ሁኔታው ከላይ በተገለጸው መንገድ እንዲመራ መደረጉን ተመካካሪዎቹ ተናግረዋል።

አመካካሪዎች በሙስናና መልካም አስተዳደር አጀንዳ ሥር፣ ንዑስ አጀንዳ በሆነው የሙስና ጉዳዮች፣ በአንዳንድ ቡድኖች ከስምምነት እንዳይደረስና ለውይይት በተያዘለት ጊዜ እንዳይጠናቀቅ ማድረጋቸውንም ጠቁመዋል። በዚህ ምክንያት ሐሳብ ተንዛዝቶ ከመግባባት ለመድረስ እስከ ረቡዕ ሐምሌ 29 ቀን ድረስ ውይይት እንዲቀጥል ማስገደዱን አስረድተዋል።

የፌዴራል ከተሞች አዲስ አበባና ድሬዳዋ ከተማን በተመለከተ የፅንሰ ሐሳብ ገለጻና ማብራሪያ እንዲሰጡ በኮሚሽኑ የተመደቡ ምሁራን (Panel of Experts)፣ በተለይ አዲስ አበባ የኦሮሚያ ክልል አካል ትሁን
በሚለው የአጀንዳ ሐሳብ ፅንፍ በያዘ ሁኔታ መከራከራቸውን ጨምረው ገልጸዋል።

ሆኖም ይህን አካሄድ የተከተሉ ምሁራን ሰፊ ክርክር ከተደረገ በኋላ ይቅርታ መጠየቀታቸውን ተመካካሪዎቹ ጨምረው ተናግረዋል። በቃለ ጉባዔ ያዥነት የተመደቡ አንዳንድ ባለሙያዎችም የቀረቡ ሐሳቦችን በሙሉ ያለማጠናከርና በፈለጉት መንገድ ብቻ የመሰነድ ችግር እንደተስተዋለባቸው ተናግረዋል። እነዚህ ቃለ ጉባዔ ያዦች የአንዱን ሐሳብ ይዘው የሌላውን የመተው አካሄድ መከተላቸው ተነግሯል።

በመሆኑም እንዲህ ያሉ ድርጊቶች አስፈላጊ እንዳልሆኑ፣ የምክክሩም ዓላማ ይህ እንዳልሆነ የገለጹት የመረጃ ምንጮቹ አሁን ያሉ ተቋማት ብቁ፣ ነፃና ገለልተኛ ሆነው የማይሰሩና የሚቀርቡ ጥያቄዎችን የመፍታት ከፍተኛ ችግሮች ስላሉባቸው፣ ውሃው እንዳይደርቅና አሳውም እንዳይሞት መታረምና መስተካከል እንዳለባቸው በአፅንኦት አሳስበዋል።

ፕሮፌሰር መስፍን አርአያ በሰጡት መግለጫ የመንግስት ባለስልጣናት እንደሚመጡ አረጋግጠው፣ ለተሳትፎ እንጂ የተለየ ጫና እንደማያሳድሩ አብራርተዋል።

#ምክክር #ብልፅግና #ዜና

ባለስልጣናት በምክክሩ አጀንዳ አስቀየሩ  የሞት ፍርደኞቹ ተፈቱ፡፡ https://youtu.be/2g3yRoA3Eqc
06/08/2026

ባለስልጣናት በምክክሩ አጀንዳ አስቀየሩ የሞት ፍርደኞቹ ተፈቱ፡፡

https://youtu.be/2g3yRoA3Eqc

ቻናላችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ፡፡ ...

06/08/2026

ባለስልጣናት በምክክሩ አጀንዳ አስቀየሩ የሞት ፍርደኞቹ ተፈቱ፡፡

ዝርዝር ዜናውን ቻናላችን ላይ ያገኛሉ፡፡ #ቦርከና #ሰበር #ቦርከናዜና

91 የመንግስት ባለስልጣናት በቁጥጥር ስር ዋሉ።የመንግሥትን ገቢ ባሳጡ እና የሙስና አሰራር በዘረጉ የገቢዎች እና ጉምሩክ አካላት ላይ በተካሄደ የተቀናጀ ኦፕሬሽን ከፍተኛ የህግ ማስከበር እር...
06/08/2026

91 የመንግስት ባለስልጣናት በቁጥጥር ስር ዋሉ።

የመንግሥትን ገቢ ባሳጡ እና የሙስና አሰራር በዘረጉ የገቢዎች እና ጉምሩክ አካላት ላይ በተካሄደ የተቀናጀ ኦፕሬሽን ከፍተኛ የህግ ማስከበር እርምጃ ተወስዷል ሲሉ የመንግስት ኮሚኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር እናታለም መለስ ተናግረዋል።

ተጠርጣሪዎቹ ተቋማዊ ኃላፊነታቸውን በመጠቀም የሚከተሉትን ከባድ የሙስና እና የታክስ ማታለል ወንጀሎች ሲፈጽሙ ተይዘዋል ብለዋል።

ሚኒስትሯ የተፈፀሙትን ወንጀሎች ሲዘረዝሩ
ለግል ጥቅም ሲሉ የታክስ ውሳኔዎችን አዛብተው በመወሰን የመንግሥት ገቢ እንዲቀንስ አድርገዋል ብለዋል።

ህጋዊ መሰረት የሌላቸውን እና ህገ-ወጥ ሐሰተኛ ደረሰኞችን በስርዓቱ ውስጥ በማካተት የታክስ ማሸሽ ወንጀል መፈፀማቸው አብራርተዋል።

የተፈጸሙ የታክስ እና የፋይናንስ መረጃዎች ከዲጂታል ስርዓቱ (System) እንዲጠፉ በማድረግ የቁጥጥርና የኦዲት ሂደቱን ለማወናበድ ሞክረዋል በማለት ገልፀዋል።

በተጨማሪም የተገኘውን ህገ-ወጥ ገንዘብ ለመሸሸግ እና የባንክ ዝውውሩን ለመደለዝ የራሳቸውን፣ የዘመዶቻቸውን እንዲሁም የሹፌሮቻቸውን የባንክ አካውንቶች እንደ ማዛወሪያ በመጠቀም የተደራጀ የወንጀል መረብ ዘርግተዋል ነው ያሉት።

በአጠቃላይ መንግስት የጀመረውን የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ የኑሮ ውድነት እንድንር በማድረግና ህዝብ ላይ ጫና በመፍጠር አተገባበሩን አደናቅፈዋል ሲሉ እናታለም ገልፀዋል።

#ሌብነት #ሙስና #ዜና

ጦርነት እንዲቆም እንጸልይ — አቡነ ማትያስ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ነገ የሚጀምረውን ጾመ ፍልሰታ አስመልክቶ አባታዊ መልእክት አስተላልፈዋል።ቅዱስነታቸው ምእመናን የእግዚአብሔርን ትእዛዝ...
06/08/2026

ጦርነት እንዲቆም እንጸልይ — አቡነ ማትያስ

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ነገ የሚጀምረውን ጾመ ፍልሰታ አስመልክቶ አባታዊ መልእክት አስተላልፈዋል።

ቅዱስነታቸው ምእመናን የእግዚአብሔርን ትእዛዝ በመጠበቅና ፍቅርን በመተግበር ሱባዔውን እንዲያሳልፉ አሳስበዋል።

​ እግዚአብሔርን መውደድ በሚታይ መልኩ ትእዛዙን በመጠበቅና ባልንጀራን እንደ ራስ አድርጎ በመውደድ የሚገለጽ በመሆኑ ምእመናን በፍቅርና በመከባበር ሊኖሩ ይገባልም ብለዋል።

​በ16ቱ የጾም ቀናት የተራቡትን በመመገብ፣ የታረዙትን በማልበስ፣ የተጣሉትን በማስታረቅና የታሰሩትን በመጠየቅ ሱባዔውን እንዲያሳልፉ አደራ ብለዋል።

​በፍጥረታት ላይ ሥጋት የሆነውን አውዳሚ ጦርነት አምላክ በመለኮታዊ ሥልጣኑ እንዲያስቆም በትሕትናና በቅን ልቦና መጸለይ እንደሚገባ አሳስበዋል።

#ጦርነት #ቤተክርስቲያን #ፆም #ዜና

Address


Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Borkena posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Borkena:

Shortcuts

  • Want your business to be the top-listed Media Company?

Share