01/09/2026
አልሀጂ ሀሊፋ የቀበሌው መሪ፣
የወጣቶች ፌዴሬሽን ምክትል አስተዳዳሪ፤
ትላንት በ10+3 ዲፕሎማ ያወጣው፣
ዛሬ ማስተርሱን ይዞ ሚዲያ ላይ ብቅ አለልን ያው!
ቀበሌውን እየመራ ፌዴሬሽኑን ሲያንቀሳቅስ፣
የት አገኘው ጊዜው ጥናትና ምርምር የሚያደርግስ?
ስብሰባው ሳይበቃው የህዝቡ አደረጃጀት፣
በአንድ አመት ውስጥ ተጠናቀቀ የማስተርሱ ትምህርት!
ወይ የአልሀጂ ስልጣን ወይ የትምህርቱ አስማት፣
ከዲፕሎማ ወደ ማስተርስ በብርሃን ፍጥነት፤
ወጣቱን ሊያስተምር ይሆን በምሳሌነቱ?
ወይንስ ሊቀመንበር ስለሆነ አጠረው መንገዱ?
ነገ ደግሞ አልሀጂ ዶክተር ነኝ ሲለን፣
አስቂኙ ድራማ ይቀጥላል ወይ ብለን፤
ስልጣንና ማዕረግ በአንድ ላይ ተጋብተው፣
የሳቅ ምንጭ ሆኑልን የቀበሌው መሪው!