
18/09/2025
የጥንታውያኑ የካፈቾ ነገሥታት ዕውነተኛው ዘውድና ዙፋን ወደ ካፋ ዞን ገባ፡፡
የካፋ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ እንዳሻው ከበደ ከ121 ዓመታት ቆይታ በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ሙዚየም የተረከቡትን የጥንታውያኑ የካፈቾ ነገሥታት ዕውነተኛው ዘውድና ዙፋን በመያዝ ዛሬ ወደ ካፋ ዞን ገብቷል ፡፡
አስተዳዳሪው ይህንን ታላቅ ቅርስ ይዞ ወደ ዞኑ ጎጀብ ከተማ ሲደርሱ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል መንግስት ምክትል ርዕሰ መስተዳደርና የግብርና ቢሮ ሀላፊ አቶ ማስረሻ በላቸው ፣ የካፋ ዞን የመንግስት ዋና ተጠሪ አቶ አጥናፉ ኃይሌን ጨምሮ የካፋ ዞን ከፍተኛ አመራሮች፣ የጎጀብ ፣ ኡፋ እንዲሁም የቦንጋ ከተማ ነዋሪዎች ደማቅ አቀባበል አድርጎላቸዋል ።
ከ700 ዓመት በላይ ዕድሜ ጠገብ የሆነው ይህ ታላቅ ቅርስ ከረጅም ዘመናት በፊት የነበረዉን የካፋን ህዝብ የስልጣኔ ከፍታ ያሰየ መሆኑን የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አቶ እንዳሻው ከበደ ገልፀዋል::
ቅርሱ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ሙዝዬም ዉስጥ ከ 62 ዓመት በላይ የቆየ መሆኑንም ዋና አስተዳዳሪው ጠቁመዋል ::
የካፈቾ ነገሥታት ዘዉድና ዙፋን ከ121 ዓመታት ቆይታ በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ የብሄረሰቡ ዘመን መለወጫ የሆነውን ማሽቃሮን ከባለቤት ከሆነው ሕዙቡ ጋር ለማሳለፍ በክብር ታጅቦ ዛሬ ወደ ዞኑ መግባቱን ዋና አስተዳዳሪው ተናግረዋል።
ዋና አስተዳዳሪው በመጨረሻም ለዘመናት ስትቆጩና ስትናፍቁ የነበራችሁ ሕዝቦች እንኳን ደስ አላችሁ በማለት መልካም ምኞታቸዉን ገልፀዋል።
ዛሬ ወደ መነሻውና መናገሻው የተመለሰው ይህ ታላቁ የነገሥታት ቅርስ የ13ኛዉ መቶ ክ/ዘመን የካፈቾዎች የጥበብ ዉጤት መሆኑ ይታወቃል::
Kaffa Tube.com-ካፋ ቲዩብ.ኮም
Kafa Zone Gov't Com. Affairs Department
Southwest Communications
South Radio and Television Agency
Southwest Ethiopian Peoples Unity for Ethiopia Prosperity
Kaffa Green Party
Bonga FM 97.4
Bonga University
Bonga University
Bench Sheko Zone Prosperity Party Branch Office
Bonga University
ውቢቷ ሸካ
ካፋ ዞን አስተዳደር ጽ/ቤት/kaffa zone Administration office