Boloso sore woreda media network

  • Home
  • Boloso sore woreda media network

Boloso sore woreda media network የአረካ ከተማ መኖሪያ ሠፈር ውጤቶች መረዳጃ ዕድር

ሂዝቦላህ ወደ ሃይፋ ከተማ ከ100 በላይ ሮኬቶችን አስወነጨፈአዲስ አበባ፣ መስከረም 28፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) ሂዝቦላህ በሰሜናዊ እስራኤል ወደምትገኘው ሃይፋ ከተማ ከ100 በላይ ሮኬቶችን ...
08/10/2024

ሂዝቦላህ ወደ ሃይፋ ከተማ ከ100 በላይ ሮኬቶችን አስወነጨፈ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 28፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) ሂዝቦላህ በሰሜናዊ እስራኤል ወደምትገኘው ሃይፋ ከተማ ከ100 በላይ ሮኬቶችን አስወነጨፈ።

ከተማዋ እንዲህ አይነት ጥቃት ሲያጋጥማት ከ18 ዓመታት በኋላ እንደሆነ ተገልጿል።

እስራኤል በሊባኖስ ውስጥ በአየርና በእግረኛ ጦር አማካኝነት ለምትፈጽመው ጥቃት አጸፋ እየመለሰ ያለው ሂዝቦላህ ሮኬቶችን ወደ እስራኤል እያስወነጨፈ ስለመሆኑ ቢቢሲ ዘግቧል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ የሊባኖስ መዲና የሆነችው ቤይሩት ባለስልጣናት በከተማዋ ከስጋት ነጻ የሆነ ስፍራ የለም ሲሉ ተናግረዋል።

እስራኤል በበኩሏ የሂዝቦላህ ይዞታዎችን ዒላማ ያደረገ ጥቃት እየፈጸመች እንደሆነ ገልጻ፤ በጥቃቷ የተገደሉትን የሂዝቦላህ መሪ ሀሰን ነስላህን በመተካት የቡድኑ ሃላፊ ሊሆን ይችላል የተባለው ግለሰብ ባለፈው ሳምንት ሳይገደል እንዳልቀረ አስታውቃለች።

የእግረኛ ጦሯ በደቡብ ምዕራብ ሊባኖስ በተሰጠው ስምሪት በድንበር አካባቢ ተልዕኮውን እየተወጣ ስለመሆኑም አመልክታለች።

ከመስከረም 28/2017 ዓ.ም ከምሽቱ 12፡00 ሰዓት ጀምሮ በሥራ ላይ የሚውለውን የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋን አስመልክቶ የተሰጠ መግለጫ የአገር በቀሉ ኢኮኖሚ ማሻሻያ አካል የሆነው...
08/10/2024

ከመስከረም 28/2017 ዓ.ም ከምሽቱ 12፡00 ሰዓት ጀምሮ በሥራ ላይ የሚውለውን የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋን አስመልክቶ የተሰጠ መግለጫ

የአገር በቀሉ ኢኮኖሚ ማሻሻያ አካል የሆነውና ከሐምሌ ወር 2017 የመጨረሻ ሳምንት ጀምሮ ተግባራዊ የተደረገው የውጭ ምንዛሪ አስተዳደር ማሻሻያ በዓይነቱ ፤በንግድ ዘርፉ ውጤታማነት ላይ በሚያሳድረው በጎ ተፅእኖ እና በታሪካዊነቱ የተለየና ሥር ነቀል ማሻሻያ ነው፡፡

በውጭ ምንዛሬ አስተዳደር ላይ የተደረገው ይህ የፖሊሲ ማሻሻያ ከሦስት አስርት አመታት በላይ ለሀገር ውስጥ ባለሀብቶች ብቻ ተከልሎ የቆየውና የውጭ ባለሀብቶች በገቢ፤ በወጪና በጅምላ የንግድ የሥራ መስኮች እንዲሣተፉ ለማድረግ ከተወሰደው የፖሊሲ ለውጥ ጋር ተቀናጅቶ ሲተገበር በዘርፉ ለበርካታ ዓመታት ማነቆ ሆነው የቆዩትን የግልፅነት፤የኢ-ፍትሃዊነትና የነፃ ውድድር ችግሮችን ከመሠረቱ ይቀርፋል ተብሎ ይታመናል፡፡

የንግድና ቀጣናዊ ትሥሥር ሚኒስቴር በመንግሥት የተደረገውን የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ ተከትሎ በገበያ ውስጥ የአቅርቦት መስተጓጓል እንዳይከሰትና ምክንያታዊ ያልሆነ የዋጋ ጭማሪ እንዳይኖር ባለፉት ወራት ከክልሎችና ከንግዱ ማህበረሰብ ጋር በመቀናጀት በተሠሩት የክትትልና የቁጥጥር ሥራዎች የተረጋጋ ግብይትና ዋጋ እንዲኖር አስችሏል፡፡

በገበያ ማረጋጋቱ ሂደት ጊዜያዊ ጥቅም ሳያማልላቸው ከመንግሥት ጎን በመቆም ለገበያ መረጋጋትና ለፖሊሲው ተፈፃሚነት የበኩላቸውን አስተዋፅኦ ላበረከቱት የንግዱ ማህበረሰብና የክልል አካላት ያለን አድናቆትና ምስጋና ከፍ ያለ ነው።

ምንም እንኳን የማክሮ ኢኮኖሚ ፖሊሲ ማሻሻያው በነዳጅ ዋጋ ላይ ከፍ ያለ ጭማሪ ያስከተለ ቢሆንም የህብረተሰቡን የኑሮ ሁኔታ ግምት ውስጥ በማስገባትና በመስከረም ወር የሚከበሩ ታላላቅ በዓላት በተረጋጋ ሁኔታ እንዲከናወኑ ለማድረግ ሲባል የነዳጅ ውጤቶች ዋጋ ከፖሊሲ ለውጡ በፊት በነበረበት መጠን እንዲቀጥልና የታየው ጭማሪ ሙሉ በሙሉ በመንግሥት ድጎማ እንዲሸፈን በመደረጉ ባለፉት ሁለት ወራት ብቻ መንግሥት ከብር 35 ነጥብ 8 ቢሊየን በላይ ወጪ አድርጓል።

በሌላ በኩል የውጭ ምንዛሪ አስተዳደር ማሻሻያውን መነሻ በማድረግ የነዳጅ የችርቻሮ ዋጋባለመስተካከሉ በአገራችን በሥራ ላይ ያለው የነዳጅ ዋጋ ከሁሉም ጎረቤት አገሮች በግማሽ ዝቅ ባለ መጠን የሚሽጥበት ሁኔታ በመጠፈሩ ነዳጅ በኮንትሮባንድና ለህገ ወጥ ንግድ እንዲጋለጥ አድርጓል፡፡

በእነዚህ መሠረታዊ ምክንያቶች ያለንበትን ሀገራዊ ሁኔታዎችን ባገናዘበ አግባብ መጠነኛ የነዳጅ ዋጋ ማስተካከያ ማድረግ አስፈልጓል፡፡ በዚህም መሠረት የኢኮኖሚውን ወቅታዊ ሁኔታና የህብረተሰቡን የመክፈል አቅም እንዲሁም የነዳጅ ዋጋ ጭማሪ ገበያ ላይ ሊያስከትል የሚችለውን ተፅዕኖ ያገናዘበ የዋጋ ማስተካከያ ስትራቴጂ ተነድፎ ሥራ ላይ እንዲውል በመንግሥት ተውስኗል፡፡

በስትራቴጂው መሠረት በነዳጅ ዋጋ ላይ ከታየው ጭማሪ ተጠቃሚው ህብረተሰብ እጅግ አነስተኛ የሆነ ዋጋ በየሶስት ወሩ እየከፈለ፣ መንግሥት ደግሞ ከፍ ያለውን መጠን እደጎመ በአንድ አመት ጊዜ ውስጥ የተሟላ የዋጋ ማስተካከያ የሚደረግ ይሆናል፡፡

ይህ አሰራር በመንግስት ላይ ከፍተኛ ወጪ የሚያስከትል ቢሆንም የተረጋጋ ሽግግር በማድረግ በገበያ ላይ በገበያ ላይ ሊፈጠር የሚችለውን የዋጋ ንረት ለማረጋጋት የሚኖረውን ፋይዳ ግምት ውስጥ በማስገባት የሚፈፀም ይሆናል፡፡

በዚሁ መሠረት የአለም የነዳጅ ዋጋ መነሻ በማድረግ የነዳጅ የችርቻሮ ዋጋ ማስተካከያ በየሦስት ወሩ የሚደረግ ሲሆን መንግሥት ለአንድ ዓመት የሚቆይ ጥቅል ድጎማ ያደርጋል፡፡ የድጎማው መጠን በነዳጅ ዓይነት የሚለያይ

አይረን ዶም ምንድን ነው? ... የዳዊት ወንጭፍስ? 🇮🇱  እሥራኤል ራሷን ከሚሳዔሎች የምትከላከልባቸው ጋሻዎች   | ከቅርብ ወራት ወዲህ እስራኤል ሐማስ ከጋዛ፣ ሄዝቦላህ ከሊባኖስ እንዲሁም ...
02/10/2024

አይረን ዶም ምንድን ነው? ... የዳዊት ወንጭፍስ?
🇮🇱 እሥራኤል ራሷን ከሚሳዔሎች የምትከላከልባቸው ጋሻዎች

| ከቅርብ ወራት ወዲህ እስራኤል ሐማስ ከጋዛ፣ ሄዝቦላህ ከሊባኖስ እንዲሁም ሁቲዎች ከየመን በኩል የሚሳዔል ጥቃት ሲፈጽምባት ቆይታለች።እነዚህን ጥቃቶች ለመመከት ሁሉንም የሚሳዔል መከላከያ ዘዴዎችን ተጠቅማለች።

እነዚህ የሚሳዔል መከላከያ ዘዴዎች የአጭር ርቀት ሮኬቶችን ከሚመክተው አይረን ዶም እስከ ባለስቲክ ሚሳዔል ድረስ የሚከላከለውን አሮው የተሰኘ ፀረ ሚሳዔል መሣሪያዎችን ያካትታሉ።

በእስራኤል የሚሳኤል መከላከያ ሥርዓት ውስጥ ያሉት የተለያዩ ፀረ ሚሳዔል መሳሪያዎች የትኞቹ ናቸው?

እስራኤል በርካታ የአየር መከላከያ ዘዴዎች አሏት። እንደየአቅማቸው በተለያየ ከፍታ እና ርቀት ላይ የሚመጡ ሚሳዔል ጥቃቶችን ለማክሸፍ የሚውሉ ናቸው።

ከእስራኤል የሚሳኤል ጋሻዎች መካከል በጣም የሚታወቀው “አይረን ዶም” ሲሆን፣ የአጭር ርቀት ሮኬቶችን ለመከላከል የሚያስችል ነው። ይህ መሳሪያ ሞርታሮችን እና ከሚሳዔል ማስወንጨፊያ የሚተኮሱ ከአራት እስከ 70 ኪሎ ሜትር ርቀት የሚጓዙትን ያከሽፋል።

የ“ዳዊት ወንጭፍ” (ዴቪድስ ስሊንግ) የተሰኘው ደግሞ እስከ 300 ኪ.ሜ ርቀት ርቀት የሚጓዙትን የረዥም ርቀት ሮኬቶችን፣ ክሩዝ ሚሳዔሎችን እና የመካከለኛ ወይም የረዥም ርቀት ባለስቲክ ሚሳዔሎችን ለመከላከል ያስችላል።

“አሮው 2” እና “አሮው 3” የሚባሉት ደግሞ እስከ 2400 ኪ.ሜ ርቀት የሚጓዙ መካከለኛ እና ረዥም ርቀት ሚሳዔሎችን ይከላከላሉ።

አይረን ዶም ፀረ ሚሳዔል

አይረን ዶም በጦርነት ውስጥ ተደጋግሞ የተሞከረ የዓለማችን የአየር መከላከያ ሥርዓት መሆኑ ይነገርለታል። ከቅርብ ዓመታት ወዲህ ሐማስ እና ሌሎች የጋዛ ታጣቂ ቡድኖች እንዲሁም ደግሞ ሄዝቦላህ ከሊባኖስ ሆኖ ወደ እስራኤል በተኮሷቸው የሚሳዔሎች ብዛት ነው መሳሪያው ተደጋግሞ የመሞከር ዕድል ያገኘው።

በመላው እስራኤል የሚገኙ የአይረን ዶም ማስወንጨፊያዎች (ባትሪዎች) አሉ። እያንዳንዱ ባትሪ ሦስት ወይም አራት ማስወንጨፊያዎችን ይዘዋል። እያንዳንዳቸው 20 ሚሳኤሎች የማክሸፍ ብቃት አላቸው።

አይረን ዶም ለጥቃት የሚመጡ ሮኬቶችን በራዳር ፈልጎ ይከታተላል። የትኞቹ ሮኬቶች ሕዝብ በሚበዛባቸው ቦታዎች ላይ ሊወድቁ እንደሚችሉ ያሰላል። ባዶ ቦታ ላይ የሚወድቁትን በመተው አይረን ዶሙ ሚሳዔሎቹን ወደ እነዚህ ሮኬቶች በመተኮስ ያጨናግፋቸዋል።

የእስራኤል መከላከያ ሠራዊት (አይዲኤፍ) እንደሚለው ከሆነ አይረን ዶም ካነጣጠረባቸው ሮኬቶች 90 በመቶ ያህሉን ያመክናቸዋል። “ታሚር” የሚሰኙት እያንዳንዳንዳቸው ሚሳዔሎቹ 50 ሺህ ዶላር ገደማ ያስወጣሉ።

እአአ በ2006 በእስራኤል እና በሄዝቦላህ መካከል ከነበረው ጦርነት በኋላ የተሠራ መሣሪያ ነው። በወቅቱ ሄዝቦላህ ወደ እስራኤል 4 ሺህ የሚጠጉ ሮኬቶችን በመተኮስ ከፍተኛ ጉዳት ከማድረስ ባለፈ በደርዘን የሚቆጠሩ ዜጎቿን ገድሏል።

ፀረ ሚሳዔል መሳሪያው የእስራኤል ኩባንያ በሆኑት ራፋኤል አድቫንስድ ዲፌንስ ሲስተም እና የእስራኤል ኤሮስፔስ ኢንዱስትሪስ የተነደፈ ሲሆን፣ የአሜሪካን መጠነኛ ድጋፍ በመጠቀም በ2011 ነበር የተመረተው።

አይረን ዶም ለመጀመሪያ ጊዜ በዘመቻዎች ላይ ጥቅም የዋለው በዚያው ዓመት ሲሆን፣ ከጋዛ የተተኮሱ ሮኬቶችን ማክሸፍ ችሏል።

የአይረን ዶም ሚሳኤሎች ከጥቅምት 2023 ወዲህ ብቻ ሐማስ እና ሌሎች ታጣቂ ቡድኖች ከጋዛ እንዲሁም ደግሞ ሄዝቦላህ ከደቡብ ሊባኖስ የተኮሷቸውን በአስር ሺህዎች የሚቆጠሩ ሮኬቶችን አክሽፏል።

የዳዊት ወንጭፍ (ዴቪድስ ስሊንግ) ፀረ ሚሳዔል

በዕብራይስጥ “

14/09/2024
ባህር ዛፍን ከማሳ በማንሳት የተለያዩ ሰብሎችን በማልማት ተጠቃሚ መሆናቸውን የቦሎሶ ሶሬ ወረዳ አርሶ አደሮች ተናገሩቦሎሶ ሶሬ፤ ጥር 2፤2016 ዓ.ም የወላይታ ዞን ከፍተኛ አመራሮች በቦሎሶ ...
11/01/2024

ባህር ዛፍን ከማሳ በማንሳት የተለያዩ ሰብሎችን በማልማት ተጠቃሚ መሆናቸውን የቦሎሶ ሶሬ ወረዳ አርሶ አደሮች ተናገሩ

ቦሎሶ ሶሬ፤ ጥር 2፤2016 ዓ.ም የወላይታ ዞን ከፍተኛ አመራሮች በቦሎሶ ሶሬ ወረዳ ከ113 ሄክታር በላይ ማሣ ላይ የነበረውን ባህር ዛፍን በማንሳት ተለያዩ ሰብሎችን እየለማ ያለውን ጎብኝተዋል።

የዞኑ ከፍተኛ አመራሮች ባህር ዛፍን በማንሳት ጎመን ጨምሮ በሌሎች በእህል ሰብሎች የለማ ማሣ ተዘዋውረው ተመልክተዋል።

አርሶአደሩ የባህር ዛፍን አሉታዊ ተጽዕኖ በሚገባ ተገንዝበው በዓመት 3 እና 4 ጊዜ ምርት የሚሰጡ ሰብሎችን ለመተካት ያደረጉት ጥረት የሚደነቅ ነው ብለዋል።

አመራሩ ባህር ዛፍን ከማሳ ለማነሳት ያደረገው አብዮት በተጨባጭ ውጤት እያመጣ እንደሚገኝና አርሶአደሩንም ጨምር ተጠቃሚ እያደረገ በመሆኑ ትልቅ እምርታ ነው ብለዋል።

በእርሻ ማሣ የተሸፈኑ ባህር ዛፎችን የመንቀል ተግባር ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበትና ዘርፈብዙ ጠቀሜታ ያላቸውን የግብርና ስራዎች ማዘመን እንደሚገባም አመላክተዋል።

በዞኑ በተለያዩ መዋቅሮች ባህር ዛፍን ከእርሻ ማሣ በማንሳት በሌሎች ሰብል ምርቶች የመተካት ተግባር በንቅናቄ መልክ እየተሠራ እንደሚገኝም ገልጸዋል።

ባህር ዛፍ የአፈር ለምነትን በመቀነስ ምርትና ምርታማነት ላይ የሚያሳድረው ተጽኖ እጅግ ከፍተኛ መሆኑን አስገንዝበዋል።

በአገራችን ጎልቶ የታየውን የምግብ ዋስትና ችግር ለማረጋጋት የሰብል ምርቶችን ማስፋፋት ሁነኛ መፍትሔ እንደሚሆንም ጠቅሰዋል።

የዞኑ መንግሥት የህብረተሰቡን የምግብ ዋስትና ችግር ለማቃለል ጥቅል ጎመን፣ እንሰት፣ ቲማቲም እና ሌሎች የሰብል ምርቶችን ለማስፋፋት በትኩረት እየሠራ ይገኛል ብለዋል።

በህብረተሰቡ ዘንድ የነበረው የግንዛቤ እጥረት በመቀረፉ ባህር ዛፍን ከእርሻ ማሣ የማንሳት ሥራ በንቅናቄ መልክ እየተከናወነ እንደሚገኝም ገልጸዋል።

እጅግ አስቸጋሪ ሆኖ የመጣውን የኑሮ ውድነትን የመቅረፍ ዓላማ ያነገበው ይህ ተግባር በሁሉም አከባቢዎች ተጠናክሮ የሚቀጥል እንደሆነም ጠቅሰዋል።

ከህብረተሰቡ ጋር በተፈጠረው መግባባት እያንዳንዱ አርሶአደር በገዛ ፍቃዱ ባህር ዛፉን ከእርሻ ማሣ በማንሳት በሌሎች ግብርና ሰብሎች በመተካት አመርቂ ውጤት እያስመዘገቡ እንደሆነም ተመልክተናል ብለዋል።

በእርሻ ማሣ የነበረው ዛፍ ከፍተኛ የምግብ እጥረት እያስከተለ መቆየቱንና በምትኩ የተተከሉ ሰብሎች ከፍተኛ ምርት እየሰጡ እንደሆነ አምራች አርሶአደሮች አቶ አሸናፊ ኡርቃቶ እና አቶ መንግሥቱ ማርዴ ተናግረዋል።

በዓመት ሶስትና አራት ጊዜ ምርት የሚሰጡ ሰብሎችን በማምረት የኢኮኖሚ ደረጃውን ጭምር በእጅጉ እያሻሻሉ እንደሚገኙም አንስተዋል።

በቦሎሶ ሶሬ ወረዳ የ2016 ዓ.ም የበጋ መስኖ ስንዴ የዘር ማስጀመሪያ ላውንች ተደርጓል።ህዳር 14፤2016 ዓ.ም ቦሎሶ ሶሬ ማጣላ ሄምቤቾ እና ጉሩሞ ኮይሻ ቀበሌ የበጋ መስኖ ስንዴ የዘር ማ...
24/11/2023

በቦሎሶ ሶሬ ወረዳ የ2016 ዓ.ም የበጋ መስኖ ስንዴ የዘር ማስጀመሪያ ላውንች ተደርጓል።

ህዳር 14፤2016 ዓ.ም ቦሎሶ ሶሬ ማጣላ ሄምቤቾ እና ጉሩሞ ኮይሻ ቀበሌ የበጋ መስኖ ስንዴ የዘር ማስጀመሪያ መርሃግብር ተካሂዷል።

በመርሃግብሩ የወረዳው ዋና አስተዳዳሪ ጨምሮ አጠቃላይ የወረዳ አስተባባሪዎች ፣ የግብርና ባለሙያዎች ፣ የቀበሌ አመራሮች እና አርሶአደሮች ተገኝተዋል።

የበጋ መስኖ ስንዴ በወረዳችን በቅርብ ጊዜ የተጀመረ ቢሆንም አመርቂ ውጤት እየተመዘገበ እንደሚገኝ የወረዳው ዋና አስተዳዳሪ አቶ አያኑ ቢረጋ ተናግረዋል።

አምና በተገኘው ውጤት ሞራል ሰንቄን የዘንድሮ የበጋ መስኖ ስንዴ በይፋ መጀመራቸውን ዋና አስተዳዳሪው ተናግረዋል።

የበጋ መስኖ ስንዴ የአርሶአደሩን የምግብ ዋስትና ችግር ለመቅረፍና እንደሀገር ስንዴውን ለውጭ ገበያ ለማቅረብ የተያዘውን ዕቅድ ከግብ ለማድረስ የሚያስችል ነው ብለዋል አቶ አያኑ።

አርሶአደሩ በቂ ቅድመ ዝግጅት በማድረግ የበጋ መስኖ ስንዴ ማሳቸውን እየሸፈነ እንደሚገኙ በማረጋገጥ ማሣ ሽፋኑ በተያዘለት ጊዜ እንዲጠናቀቅ አቅጣጫ አስቀምጠዋል።

የዘንድሮ የበጋ መስኖ ስንዴ ከመቼውም ጊዜ በልዩ ትኩረት ለመስራት አቅጣጫ ተቀምጦ ወደ ተግባር መገባቱን የወረዳው ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ኃይለገብርኤል ካሣዬ ተናግረዋል።

የበጋ መስኖ ስንዴ እንደሀገር የተሻለ ውጤት እያስገኘ እንደሚገኝ የገለፁት አቶ ኃይለገብርኤል ምርቱን ከማሣ እስከ ምንሰበሰብበት ጊዜ ልዩ ክትትል ድጋፍ ይደረጋል ብለዋል።

የግብርና ባለሙያዎች እና አመራሩ ለአርሶአደሩ በቅርበት ድጋፍና እንዲሰጡ አሳስበዋል።

በዘንድሮ በጋ መስኖ ስንዴ 158 ሄክታር ማሣ በማልማት 6636 ኩንታል ምርት ለመሰብሰብ መታቀዱን የወረዳው ም/አስተዳዳሪና ግብርና ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ዳዊት በሣ ተናግረዋል።

የበጋ መስኖ ስንዴ ከሌሎች ሰብሎች የተሻለ ምርት የሚሰጥና እጅግ አስቸገሪ ሆኖ የመጣውን የኑሮ ውድነትን ለማቃለል ወሳኝ ሚና እንዳውም አቶ ዳዊት ተናግረዋል።

በቦሎሶ ሶሬ  ወረዳ  እጅግ ተወዳጅ እና የትልቅ ዕውቀት ባለቤት የሆነው ጓደኛችን አቶ አክልሉ አንጁሎ ወደ ቤተሰብ ጥየቃ ከአረካ ወደ በዴሳ ስሄድ በድንገት በመኪና አደጋ ህይወቱ አልፏል ይህ...
15/10/2023

በቦሎሶ ሶሬ ወረዳ እጅግ ተወዳጅ እና የትልቅ ዕውቀት ባለቤት የሆነው ጓደኛችን አቶ አክልሉ አንጁሎ ወደ ቤተሰብ ጥየቃ ከአረካ ወደ በዴሳ ስሄድ በድንገት በመኪና አደጋ ህይወቱ አልፏል ይህ እጅግ በጣም የምያሳዝን ክስተት ስለሆ ለቤቴሰቦቹና ለወዳጅ ዘመዶቹ እግዚአብሄር መጽናናትን እንድሰጥ እንመኛለን። ዓለም ይህች ናት ።

Address


Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Boloso sore woreda media network posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

  • Address
  • Alerts
  • Claim ownership or report listing
  • Want your business to be the top-listed Media Company?

Share