Ethio election 2012

  • Home
  • Ethio election 2012

Ethio election 2012 The battle of election 2012 begins hear!

29/04/2019

የመጀመሪያ ጥያቄ ምርጫ(election) ምንድን ነው? አላማውስ?
ምርጫ ሰዎች ወይም ቡድኖች ስልጣን ለመያዝ የሚያደርጉት ውድድር ሲሆን የተሻለ እቅድና እቅዳቸውን የሚያስፈፅሙበት ሰትራተጂ ያላቸው በመራጮች የሚመረጡበት ፥ ባለው ህግም መሰረት በአብላጫ የተመረጡ ግለሰቦች የሚያሸንፉበትና መንግስት የሚመሰርቱበት ስርአት ነው።
አላማውስ?
የምርጫ አላማ አንድ ሲሆን እሱም የመወሰን አቅሙንና ትልቁን ስልጣን ለህዝብ መስጠትና ማሳደግ ነው። በሌላ አገላለፅ ዲሞክራሲን ለማሳደግ የህዝብ አገዛዝን ለማሳደግ ነው።
ዲሞክራሲን ለመፍጠርና ለማሳደግ ምርጫ(election) የተሻለው መንገድ ነው። ዲሞክራሲን ለማሳደግ በምርጫ ውስጥ መወዳደር የግድ ነው። ውድድርና ፉክክር መልመድ አሸናፊነትን መልመድ ተሸናፊነትን መቀበል መልመድ ያስተምራል ምርጫ። እራሱን በእውቀትና በልምድ ሁሌ የሚያሳድግ ተወዳዳሪ ሁሌ አሸናፊ ይሆናል። በፉክክር ውስጥ ነው ሳይታሰብ በፍጥነት ሚታደገው ጌታዬ።
ሰዎች በምርጫ ሂደት ውስጥ በምንድን ነው ሚወዳደሩት?
ሰዎች ሚወዳደሩት ብዙ ባወቀ ነው ከልምድ ጋር የተገናኘ እውቀት አለበለዚያ information ብቻ ነው የሚሆነው። እስከዛሬ የምናየው ግን ምንም ያላወቀ ሌጣ ሰው ያሸንፋል የተባለ ነው ሚመስለው። ጭንቅላታቸው ከውሀ የጠራ ሰዎችን ነው በብዛት ስናይ የነበረው። ይሄ ግን ይሻሻላል ተብሎ ይጠበቃል። በ2012 ምርጫ ተወዳዳሪዎች በእውቀት ላይ የተመሰረተ እቅድ ይኖራቸዋል፤ እቅድም ብቻ ሳይሆን እቅዱን የሚያስፈፅሙበት ትክክለኛ strategy ወይም መንገድ ያቀርባሉ ተብሎ ይጠበቃል። ዝም ብለው ከመፅሀፍ ያነበቡት ሳይሆን እነሱ ልምድ ባላቸው መንገድ እና ሌላ አገር የሰራ እቅድና strategy ያቀርባሉ ተብሎ ይጠበቃል።

እንቀጥላለን!!

25/04/2019

ለምርጫ 2012 እየተደረገ ያለ ዝግጅት ብዙም አይታይሞ የምርጫ ቦርድ አንዳንድ ዝግጅት እያረገ እናያለን። ነገር ግን ምርጫ 2012 interesting ይሆናል ተብሎ ይጠበቃል።ለዚህ ደግሞ ዋናው ምክንያት ወሳኝ ወሳኝ የጨዋታ ህጎቹ መቀየራቸው ነው።
ከነዚ ህጎች ዋነኛው ደግሞ እውቀት ጠሎች ማለትም ስለ ኢኮኖሚ(ግብርና፥ኢንደስትሪ፥ስራእድል ፈጠራ፥ግብር፥ፕራይቬታይዜሽንና የመንግስት ሚና የግል ሴክተር ሚና) ስለ ውጭ ጉዳይ ፓሊሲ ፥ ስለ ፓለቲካ ስርአት ፥ ስለ ስራ እድል ፈጠራ መፍትሄዎች ፥ ስለ መሬት ስሪትና ፌደራሊዝም፥ ስለ ትምህርት ፖሊሲ ባጠቃላይ ስለ ችግሮችና pragmatic( ሊተገበር የሚችልና ተደርጎ የሚያውቅ ውጤቱና ውጤታማነቱ የሚታወቅ) መፍትሄዎች የማያቅ ሰው ይዋጣል ተብሎ ይጠበቃል። ከእውቀት የራቀና strategy የሌለው ተወዳዳሪ እራሱን ከውድድሩ ያባርራል ተብሎ ይጠበቃል።
እውቀት እና የሚጠቅም ልምድ የሌለሽ ተበላሽ በነገራችን ላይ።

እና ምን ለማለት ነው የምርጫ ሩጫውን በግል ተነሳሽነት አስጀምሬዋለው ለማለት ነው። 🏇🏇🏇🏇🏇🏇🏇🏇🏇🏇🏇🏇🏇🏇🏇🏇🏇🏇🏇

Address


Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Ethio election 2012 posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

  • Want your business to be the top-listed Media Company?

Share