
08/05/2025
Sutta Karetta Amado Wolayttay Oychchiyooganne Baaxiya agoppa. Kawoy qanxxo kushe duxappe attin aleeqo gidenna.
"ችግራችሁ በእርግጥ የእርቅ ከሆነ በሁለት ወር ውስጥ በግለሰብ እብርተኛ ትዕዛዝ ከቦታው በህገወጥ መንገድ የተነሳ የጠቅላይ /ፍ/ቤት ሶዶ ምድብ ችሎት ማስመለስ ጨምሮ የሚቆጠሩ ተጨባጭ አፋጣኝ ምልክቶች እናያለን። ይህ ካልሆነ ግን የተለመደ የድግስ ግርግር ከመሆን አያልፍም።
የደኢህዴን/ኢህአዴግ መዳከም ተከትሎ የደቡብ ብ/ብ/ህ/ክ ብሄሮች ሹመኞቻቸው ለወትሮው የሚታወቁበት ሙልጭ ያለ የገዥው ፓርቲ ታማኝነት በማላላት አንዳንዶቹ የወጡበት ማህበረሰብ መሰረታዊ ጥያቄዎች ደግፈው ማራመድ ጀመሩ። ይህ ግን ሹመት ሰጥቶና ቀለብ ሰፍሮ ባሰማራው ድርጅታቸው ስላልተወደደ ፓርቲያቸው ጥርስ ነከሰባቸው። "የህዝብ ጥያቄ ሰምቶ ክልልነት የሚፈቅድ መንግሥት ከሌለ፣ ክልል መሆን የሚከለክልም መንግሥት የለም" በማለት የደቡብ ክልል ር/መስተዳድር የነበረው ሰው የሲዳማ ዞን በአዋሳ አደባባይ ባዘጋጃው ህዝባዊ ሰልፍ ላይ በድፍረት በመገኘት ንግግር ያሰማውን የሲዳማ ተወላጅ ከፍተኛ የድኢህዴን ባለድልጣ ሳያስቀስፈው የዞን አስተዳዳሪ ሆኖ በራሱ ዞን ግን ባልደረቦቹን አዳራሽ ውስጥ ሰብስቦ ስለ ክልል ጥያቄ የመከረው የወላይታ ዞን ፕሬዚዳንት ከነካቢኔው ታንቆ እስር ቤት እንዲጣል ሆነ።ምክንያቱም የሲዳማ ክልል ጥያቄ ከጀርባው የወቅቱ ኦህዴድና የጃዋር መሀመድ የተናበበ ድጋፍ ነበረውና።
በወቅቱ እንግዲህ በደቡብ ብሄሮች ተሹዋሚ ካድሬዎች መካከል ሁለት አንጃ ብቅ አለ። በእነዚህ አንጃዎች መካከል የተፈጠረው የሀሳብ መስመር ልዩነት መሰረቱ ግልፅ ነበር። ይኼውም የብሄራቸውን አጀንዳ በሚደግፉትና የብሄራቸውን ፍላጎት ደፍቀው የድርጅታቸውን አጀንዳ ለማስፈፀም ምንዳ አደላድለው የተሰማሩት መካከል የተፈጠረ መሻኮት ነው የነበረው። በዚህም የተነሳ የብሄር ክልል ጥያቄ ጎልቶ የተፋፋመባቸው በወላይታና ሁዋላም በጉራጌ አከባቢዎች የገዥው ፓርቲ (ደኢህዴን/ብልፅግና) ፍላጎት አስፈፃሚ ጥቅመኛ ካድሬዎች የገዥው ፓርቲ መሳሪያ በመሆን የየብሄራቸውን ጥቅም አቅፈውና አንግበው የተነሱት ካድሬዎችን፣ የንቅናቄው ደጋፊ ወጣቶች፣ ነጋዴዎች፣ ምሁራን ወዘተ አሳድደው በማስወገድ ምንዳቸውን አደላደሉት። ስለዚህ ወላይታ ውስጥ ዛሬ ድረስ የቀጠለው የካድሬ ሽኩቻ መሰሩቱ ለህዝብ ጥያቄ ታምኖ መቆም እና የህዝብ ጥያቄ ለስልጣንና ጥቅማጥቅም በመሸጥ የድርጅታቸው ፍላጎት ታማኝ አስፈፃሚ ሆኖ በገዥው ፓርቲ ጉያው ሥር የመወሸቅ ጉዳይ ነው።
ዛሬ የወላይታ ፖለቲከኞች "ታረቀን!" ብለዋል። እርቅ በቃላት ደረጃ ጥሩ ነው። አብራችሁ ከአንድ ማዕድ ላይ ቆርሳችሁ ብሉ፣ አንድ ቡሊኮም በጋራ ደርባችሁ ተጎናፀፉት፣ ችግር የለውም። ግን የህዝብ ጥያቄ ተስማምታችሁ በመሸጥ አንድ ላይ ለድርጅቻችሁ ጥቅምና ግላችሁ ስልጣን ከለላ ሽጣችሁ ለወንበራችሁና ድርጅቻችሁ ያላችው ታማኝነት ብቻ ለማስከበር ከሚል ስሜት ራሳችሁን ለማረጋጋት የሚደረግ ግርግር ከሆነ የተለመደው ህዝብ የመሸጥ ድብቅ ዓላማ ያዘለ ትዕይንት ከመሆን የዘለለ ለህዝብ ጠብ የሚል ነገር አይኖረውም።
ከአሁን በፊትም ታርቀናል ካላችችሁ በሁዋላ ወዲያው የእምቦይ ካብ ሆናችሁ ስታበቁ አንደኛው አንጃ ጠቅልሎ ሄዶ የክልል ብልፅግናና ለአቶ ጥላሁን ከበደ ካዳሚ ሆኖ በመቅረቱ የወላይታ ህዝብ መብትና ሀብቱን በጠራራ እየተመዘበረ አንገቱን ለማቀርቀር ተገድዱዋል። አሁንም የብቃት ክፍተት በእርቅ ስም ለመሸፈን አስባችሁ እንዳይሆን ይጠረጠራል።
በኔ እምነት የእናንተ መሰረታዊ ችግር ለህዝብ ጥቅም ዴንታ ማጣትና የብቃት እንጂ የእርቅ አይመስለኝም። ችራችሁ እውነት የእርቅ ከሆነ በ60 ቀናት ውስጥ በእናንተ መዝረክረክ ምክንያት የህዝብ መከራ የበዛበት ጠቅላይ ፍ/ቤት ሶዶ ምድብ ችሎት ቦታው መመለስ፣ የወልማ አባያ መሬትና በስታድየም ስም ህግ ባልተከተለ ሁኔታ የተዘረፈ የክልል ህዝብ በጀት ጉዳይ ይፋ ምላሽ እንጠብቃለን።"
By Dr Medhin Marcho