Alex Abreham- በነገራችን ላይ

  • Home
  • Alex Abreham- በነገራችን ላይ

Alex Abreham- በነገራችን ላይ Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Alex Abreham- በነገራችን ላይ, Publisher, .

የሆነ ዘመን የሆነ ጊዜ ወደድንም ጠላንም የትውልዱ ምልክት የሚሆኑ ሰዎች አሉ! ስንደሰት የምናመሰግናቸው፣ ስንበሳጭ መድረኩ ላይ ናቸውና እጃችን የገባውን የምንወረውርባቸው ! እና እንዲህ አይ...
14/01/2024

የሆነ ዘመን የሆነ ጊዜ ወደድንም ጠላንም የትውልዱ ምልክት የሚሆኑ ሰዎች አሉ! ስንደሰት የምናመሰግናቸው፣ ስንበሳጭ መድረኩ ላይ ናቸውና እጃችን የገባውን የምንወረውርባቸው ! እና እንዲህ አይነት ሰዎች "ሞቱ" ሲባል ከእይታችን ላይከዘመናችን አየር ላይ የሆነ ነገር ይሸረፋል! ሞት የሙላታችን መሸረፍ ነው! ነፍስህ በሰላም ትረፍ አስፋው መሸሻ፤ ለቤተሰቡና ለወዳጆቹ ሁሉ መፅናናትን🙏

‹‹አልሞትኩም ብየ አልዋሽም ››    (አሌክስ አብርሃም) መጥቻለሁ!!  በቃ መመለሴን ለመግለፅ ይሄው አንድ ቃል ይበቃ ነበር፡፡ ግን ማንም እየተነሳ እንደቤንዚን ሰልፍ የረዘመ መግለጫ በሚሰ...
11/05/2022

‹‹አልሞትኩም ብየ አልዋሽም ››
(አሌክስ አብርሃም)

መጥቻለሁ!!
በቃ መመለሴን ለመግለፅ ይሄው አንድ ቃል ይበቃ ነበር፡፡ ግን ማንም እየተነሳ እንደቤንዚን ሰልፍ የረዘመ መግለጫ በሚሰጥባት አገር የስድስት ትንንሽ ወረዳዎች ህዝብ የሚያክል ተከታይ ህዝብ ያለኝ እኔ እንዴት ከድፍን አንድ አመት መጥፋት በኋላ ‹‹ መጥቻለሁ›› ብቻ ብየ ዝም ልበል?…. በላይክ በሸርና ፎሎው (((የመረጠኝን))) ህዝብ መናቅ አይመስልም? 😃 የለም የለም እንዲያውም ይሄን ፅሁፍ እስክጨርስ አልመጣሁም!! ‹‹እጅግ የተከበርከው የፌስቡክ ህዝብ ሆይ ›› ብየ እጀምራለሁ…

እጅግ የተከበርከው የፌስቡክ ህዝብ ሆይ ..... ደህንነቴ አሳስቧችሁ በኢንቦክስ ለጠየቃችሁኝ ...በሰው በሰው አፈላልጋችሁ ሰላምታ ለላካችሁልኝ ...ይሄ ልጅ የት ጠፋ ያላችሁኝ (ሰውየ ወደመሆን ብሸጋገርም) እንዲሁም በዓመቱ ውስጥ በተከበሩት በዓላት ሁሉ ሳታዛንፉ የእንኳን አደረሰህ ምኞት ለላካችሁልኝ ሁሉ ከልቤ አመሰግናለሁ፡፡ በህይዎት ባልኖር እንኳን ነፍሴን እንደማታሳርፏት በማወቄ ደስ ብሎኛል!

ያልፈለጋችሁኝ ... ከነመፈጠሬ የረሳችሁኝም ብትሆኑ ‹‹ውይ ሳልጠይቀው መጣ›› ብላችሁ እንዳትሳቀቁ አደራ እላለሁ😎 በዚህ ሰዓት ኢትዮጵያ ውስጥ አእምሮን የጠፋ ወዳጅ ለመፈለግ ከማዋል ይልቅ የጠፋ ዘይት ፣ ነዳጅ ፣ ዳቦ ፣ ስራ ፣ ሰላም ፣ የሚከራይ ቤት ፣ ራስን ፣ እንዲሁም የጠፋ መኪናና የጠፋ ዶክሜንት በጌጡ ተመስገን በኩል ማስፈለግ ቅድሚያ የሚሰጠው ተግባር እንደሆነ አውቃለሁ😊 ስለዚህ አትጨነቁ ዋናው ነገር በ((ሰላም)) መገናኘታችን ነው፡፡

ትዝ ይለኛል ልጠፋ ሰሞን በዓል አካባቢ ስለነበር ስለክትፎ ስለዶሮ ስለበሬ ቅርጫ በጣም እየተወራ ነበር… ያኔ በስጋ ብልቶች መሃል አልፌ ነው ሎግ አውት አድርጌ የወጣሁት! አሁን ስመለስ ወዙ እየተፍለቀለቀ የዶሮ ቅልጥም ይዞ የተሰናበትኩት ልጅ ሙዝ በዳቦ እየገመጠ አመዱ ቡን ብሎ በለጠፈው ፎቶ ተቀበለኝ! በዚህም የኑሮ ውድነቱ የት እንደደረሰ ታዝቢያለሁ😊 እንደውም ፌስቡክ በሙዝ ከመጥለቅለቁ ብዛት በደቡብ ክልል በሙዝ ምርቷ የምትታወቀው እንግጭላ ወረዳ ላይ የተከሰትኩ እስኪመስለኝ ተገርሚያለሁ! ይሄ የሙዝ ነገር ((ብልህ መካሪ)) እንዳለን እንዳውቅ እረድቶኛል፡፡ ለምን በሉኝ? ...አገሪቱ በቂ የመፀዳጃ ቤቶች የሏትም ፣ ሙዝ ደግሞ የሆድ ድርቀት በማስከተል ይታወቃል … በልቶ ከማደር ባለፈ የአካባቢ ብክለትን መቀነስ ቀላል ነገር ነው ወገኖቸ ?😊

የአገሪቱን ሰላም በተመለከተ ….አስጊ ሁኔታዎች መጨመራቸውን ያወኩት ገና ከመግባቴ ነው፡፡ አሁንም የጦርነት ነፋስ ፣ አሁንም እዛና እዚህ ግጭቶች ግድያዎችና መፈናቀሎች ይወራሉ ! ድሮ ‹‹እርስዎ ቢሆኑ ምን ያደርጋሉ ›› በሚል የሬዲዮ ፕሮግራም ላይ የሚቀርቡ እንግዶች ‹‹ ባለቤቴ ቡታጅራ ለስራ ሂዶ በዛው ቀረ… በኋላ ስሰማ አንዲት ቡታጅሪት ጋር ትዳር መመስረቱን ሰማሁ ›› የሚሉ ብሶቶች ይሰሙ ነበር …አሁን ‹‹ሄሎ …መቶ ሃያ ሽ ብር አውጥቸ የገዛሁት ሰላሳ ጎራሽ ክላሽንኮቭ ጥይት እየነከሰ እምቢ አለኝ…እንዳወጣ ሸጨ ትንሽ ጨምሬ ድሽቃ ልግዛ ይሆን ወይስ ምን ትመክሩኛላችሁ ?… ለዛ ነው የደወልኩት ›› የሚሉ አድማጭ አጋጠሙኝ (የቀልዱ ቀልድ ነው) ግን ከአመት በኋላ ሌላ የጦርነት ነፋስ በአገሪቱ ላይ እያንዣበበ ሌሎች መቶ ሽዎችን ሊቀጥፍ ዳር ዳር እያለ ነው! ምናልባትም ሚሊየኖችን ለመፈናቀል አገሪቱንም በቀላሉ ለማትወጣው የተራዘመ ችግር የሚዳርግ! በእንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ !

መቸም የተደሰቱት ጋር ሳንደሰት ያዘኑትን ሳናፅናና ፣ የሚፅፉልንን ሳናነብ ለሚያነቡን ሳንፅፍ አመት ሙሉ በራስ ጉዳይ ተሰቅዞ ከምንወደውና ካቀናነው ሜዳ መጥፋት ከሞት አይተናነስምና አንተ ልጅ በህይዎት አለህ ላላችሁ ሁሉ ‹‹አልሞትኩም ብየ አልዋሽም›› ቢሆንም ሕይዎት ለእድለኞች ብዙ እንደገና አላትና እንደገና የሆድ የሆዳችንን ልንጨዋወት ከወዳጆቻችን ልንማር እድል ተሰጥቶናል! እንግዲህ ፖለቲካው አኗኗራችንን ሊያቀና አለሁ ቢለንም፣ ኑሮን እንኖራት ዘንዳ ብንፈጠርም ፣ ኑሮው ከፖለቲካ ትላንታችን ከዛሬ … የተገመደ የእሳት ጅራፍ ሰርቶ የግርፋት ኑሮ የምንመራ እኛ ምን ይበጃል ብለን በተሰጠን ልክ ያየነውን ሲመር በምሬት ዝቅ ሲልም እያዋዛን እናሳይ ዘንድ ዳግም ወደመንበራችን ተመልሰን ከሰፊው ህዝብ ጋር ሐሳብ ልንጋራ ተመልሰናልና እንኳን ሰላም ቆያችሁን ለማለት ያክል ነው!!

አሸባሪው ጋዜጠኛአብዛኛው ጋዜጠኞች በዚህ ስራ ላይ አንሳተፍም  በማለት ከደሙ ነፃ  ሲሆኑ  ይህ ብስራት መለሰ የተባለ  ቱሪ ናፋ ቦርባሬ ጋጠወጥ  ትርካውን ለኔ ተውት በማለት   በሙሉ ፍላጎ...
04/05/2022

አሸባሪው ጋዜጠኛ

አብዛኛው ጋዜጠኞች በዚህ ስራ ላይ አንሳተፍም በማለት ከደሙ ነፃ ሲሆኑ ይህ ብስራት መለሰ የተባለ ቱሪ ናፋ ቦርባሬ ጋጠወጥ ትርካውን ለኔ ተውት በማለት በሙሉ ፍላጎቱ እንደተሳተፈ አንድ ቀድሞ ፋና ውስጥ ሲሰራ የነበረ አሁን ሌላ ቲቪ ላይ የሚሰራ ጋዜጠኛ ሚስጥር አውጥቷል አብዛሀኛው ጋዜጠኞች በድርጊቱ መበሳጨታቸውንም አጋልጧል ዶክመንተሪው ሲቀናበርም ንትርክ እንደነበረም አክሎ ገልፇል
ጋዜጠኞቹም በቦታው ላይ ሳይኬድ የተለያዩ የህብረተሰብ አካላትን ቃለ_ መጠይቅ ሳይካተትበት እንደት ከሶሻል ሚዲያ ላይ ድምፆችንና ምስሎችን ሰብስቦ ዶክመንተሪ ሊሆን ይችላል? በዚህ ሰዓትስ ከጥቅሙ ጉዳቱ አያመዝንም ወይ? በህወሓት ጊዜስ እንደዚህ አይነት ዶክመንተሪዎች ምን ለውጥ አስገኝተው ነበር? መስጂድ የተቃጠለው ጎንደርና ደባርቅ ሰው የሞተውም እዛው የወራቤው ብቻስ አልገዘፈም ወይ?
የሚሉና ተያዥነት ያለው ጥያቄዎች ቢሰነዝሩም ኢትዮጲያ ፕሬስ ድርጂት ውስጥ በተሰገሰጉ ፅንፈኞች ገፋፊነት ፊልሙ አየር ላይ እንድውል ተደርጓል
✔ውስጥ አዋቂያችን እናመሰግናለን

ምንጭ
Islam Dinu Selam

27/04/2022

ከሞጣው የከፋ!

#የጎንደርጭፍጨፋ

በጎንደር በአክራሪዎችና በፋኖ ታጣቂዎች የተገደሉ ሙስሊሞች ቁጥር 24
መድረሱን ሰምተናል። በጣም አስደንጋጭ ነው። በርካታ የጎንደር ሙስሊም የንግድ ሱቆችና መስጂዶች መቃጠላቸውንና መዘረፋቸውን የሚያሳዩ ፎቶግራፎችና ቪዲዮዎች በስፋት እየተሰራጩ ነው። የደረሰው ጥፋት ከሞጣው ጥቃት የከፋ መሆኑን ከወዲህ ማወቅ ተችሏል።

የክልሉ መንግሥት ይህ ነው የሚባል ጥበቃ ለሙስሊሙ ማኅበረሰብ ለመስጠት ካለመፍቀዱም በላይ፣ የበርካታ ሙስሊሞች ሕይወት የተቀጠፈበትን ክስተት የክልሉ ሚዲያ ''መጠነኛ የጸጥታ ችግር'' በሚል አቅልሎ ዘግቦታል። የሀገሪቱ አማርኛ ሚዲያ በሙሉ የተያዘው በእነማን እንደሆነ ይታወቃል።

አንዱ አጥቂ ሌላው ተጠቂ፣ አንዱ ታጣቂ ሌላው ጾመኛ፣ አንዱ ገፊ ሌላው ተገፊ የሆነበትን ክስተት የእርስ በእርስ ግጭት፣ አንድአንዶቹም ለቀብር የወጣውን ሙስሊም የግጭት ጠንሳሽ አድረገው እየወነጀሉ ነው።

በደልህን የሚነግርልህም ሆነ የሚደርስልህ የክልልም ሆነ የፌዴራል መንግስት ስለሌለ ራስህ ከታች ያለውን ሀሽታግ እየተጠቀመክ እየተገደለ ላለው የጎንደር ሙስሊም ድምጽህን አሰማለት።

#የጎንደርጭፍጨፋ

Address


Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Alex Abreham- በነገራችን ላይ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

  • Address
  • Alerts
  • Claim ownership or report listing
  • Want your business to be the top-listed Media Company?

Share