
19/09/2024
አሳዛኝ ዜና! THE GREATEST SAD NEWS!
እጅግ መልካም፣ ለጋስ፣ አሩህሩህ፣ ቅን፣ አገር ወዳድ፣ ለፍቶ አዳሪውና ሰርቶ የማይደክመው የወጣቶች አርዓያ የነበረው የስነ-ምግባር ሰው ወጣት አበበ ጌጤ አረፈ!
ወንድማችንና መመኪያችን አቤ በፋርማሲ እና በነርሲንግ ትምህርት ተመርቆ ለረጅም አመት ለህብረተሰቡ በተለይም ለድሆች በተቆርቋሪነትና በለጋስነት ሲያገለግልና ሰወችን ሲረዳ የነበረ ሲሆን ድንገት በማይጠበቅ ሁኔታ በህክምና ላይ እያለ ህይወቱ አልፏል!
አቤ በእውነት ሞትህ ከምንም በላይ ሁሉንም ሰው በእጅጉ ያሳዘነ ሆኖ አልፏል! ክርስቶስ ነፍስህን በአፀደ-ገነት ያሳርፋት፡፡
እኛ አንተ ሞተህም ከጎንህ ነን፤ መቸም አንረሳህም፤ ከዛ ድግስ ከሆነ የአብረሃም ምግብ ቤትህ የተመገበ ሁሉ፣ ርህራሄና ስነ-ምግባር ከተሞላበት የህክምና ፋርማሲ ቤትህ የተጠቀመ ሰው በሙሉ አንተን ያውቅሃልና አንተን ያስታውሳል፣ አንተን ያመሰግናል - አንተን መርሳት አይቻልም!!
አፈሩ ይቅለልህ ውድ ወንድማችንና ጓደኛችን ውድ አቤ!
የዚህ ልጅ ሞት መላውን የባህር ዳር እና አካባቢዋን ወጣት በእጅጉ ያሳዘነ ሆኖ አልፏል፡፡