17/10/2024
✍️ካንቺ ጋራ ስሆን...❤️
የኔ አለም አዳምጪኝ ካንቺ ጋራ ስሆን..... ፍቅርሽን ሳጣጥም ፣ አይኖቼ በፍቅር ፡ ከአይኖችሽ ሲገጥም ፤ ካንቺ ጋራ ስሆን ንፋሳት ሁልጊዜ ፡ በፍቅር ያዜማሉ ፣ አይገርምም የኔ ዉድ ፡ እኔና አንቺ ሊያዩ ፣ ዥረቶች ለአፍታ ፡ ጉዞ ያቆማሉ ፣ ክዋክብት, ጨረቃ ፡ በኛ ይቀናሉ ፡፡ 'ካንቺ ጋራ ስሆን'
ምሽቱ ይደምቃል ፣ ሀሳቤ ይሰምራል፣ አስቀያሚው ያምራል ፣ ጨለማው ያበራል ። ሰማሽኝ የኔ አለም ፡ ካንቺ ጋራ ስሆን ፣ ህይወቴ በሀሴት ፡ ፅዋ ትሞላለች ካንቺ ጋራ ስሆን :: ❤️
አለም ለኔ እንዲህ ነች