20/09/2025
የ90 ዎቹ ትዝታ የቀድሞ የኢቲቪ ጋዜጠኛ ሙዲ አሊ
***************
በ1980 ዓ.ም የጋዜጠኝነት ሙያን ሀ ብሎ የጀመረው ሙዲ አሊ፤ በአስመራ ራዲዮ ከመምህርነት ህይወት ወደ ጋዜጠኝነቱ እንደተሸጋገረ ይናገራል፡፡
በ1985 ለመጀመሪያ ጊዜ በቴሌቪዥን መስኮት ብቅ ያለው ሙዲ አሊ በኢቲቪ የትግረኛ ዜናን በማንበብም ነበር የጀመረው፡፡
በወቅቱ የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ሲገባ ክፍያው 40 ብር እንደነበረም ከኢቲቪ ጋር በነበረው ቆይታው ተናግሯል፡፡
"ትልቁ ሀብቴ ህዝብ ነው" የሚለው ሙዲ፤ ከህዝቡ ያገኘው ፍቅር የሚደንቅ እንደነበር ይናገራል፡፡
ማንበብ ዝንባሌው እንደሆነ የሚናረው ሙዲ አሊ፤ ካነበብነው የተሰኘው ፕሮግራሙን እጅግ አብልጦ ይወደው እንደነበር ያነሳል፡፡
አርቲስት ኪሮስ ዓለምአየሁ የሙዲ የቅርብ ቤተሰብ ነበርና ህልፈተ ዜናውን ያነበበው እራሱ ሙዲ አሊ በመሆኑ ፈታኝ ጊዜ እንደነበርም ያስታውሳል፡፡
ታህሳስ 9 2008 ዓ.ም የመጨረሻው የጋዜጠኝነት ህይወቱ እንደነበርም ያስታውሳል፡፡
በሜሮን ንብረት