
22/09/2025
በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ቅዱስ ሚካኤል ለማንም ያልተሰጠ እጅግ ታላቅ የሆነ ክብር እንደተሰጠው ተጽፎ እናገኛለን፡፡
ይኸውም በዕለተ ምጽአት ጌታችን ቅዱሳን መላእክትን አስከትሎ በክበበ ትስብአት በግርማ መለኮት በሚመጣበት ጊዜ ከእግዚአብሔር ዘንድ በሙታን ላይ ሥልጣን የተሰጠው ለዚሁ ለኃያሉ መልአክ ለቅዱስ ሚካኤል ነው፡፡ ይህንንም ቅዱስ ጳውሎስ በሚገባ ገልጾታል፡፡ ‹‹እነሆ አንድ ምሥጢር እነግራችኋለሁ ሁላችን አናንቀላፋም፡፡ ነገር ግን የኋለኛው መለከት ሲነፋ ሁላችን በድንገት በቅጽበተ ዓይን እንለወጣለን፤ መለከት ይነፋል፤ ሙታንም የማይበሰብሱ ሆነው ይነሣሉ፤ እኛም እንለወጣለን ይላል›› (1ቆሮ.15÷51-52) ከዚሁ ጋር በተጨማሪ ‹‹በጌታ ቃል የምንላችሁ ይህ ነውና እኛ ሕያዋን ሆነን ጌታ እስኪመጣ ድረስ የምንቀር ያንቀላፉትን አንቀድምም ጌታ ራሱ በትእዛዝ በመላእክትም አለቃ ድምፅ በእግዚአብሔርም መለከት ከሰማይ ይወርዳልና በክርስቶስ የሞቱ አስቀድመው ይነሣሉ…›› (1ተሰ..4÷15-16) በማለት በዕለተ ምጽአት ምን ያህል ክብርና ጌትነት እንደሚሰጠው ይገልጽልናል፡፡