Ethio Lead

Ethio Lead ስለ ኢትዮጵያና በአለም ዙሪያ ስለሚሆኑ ወሳኝ መረጃዎች አጋራችኋለሁ. Bring you best and trending stories around the world.

Permanently closed.
01/09/2026

ቲክቶክ ከፍተህ ድምፁን እስከ አፍንጫው የጨመርከው ታክሲ ውስጥ ነው። የግል መኪናህ ውስጥ ያለህ መስሎህ እንዳይሆን ብዬ ነው 🤝

አንድ ግለሰብ መኖሪያ ቤቱን ሰርቶ ከጨረሰ በኋላ ውድ የሆነ የጥበቃ ሰራተኛ (ዘበኛ) ከማቀጠር ይልቅ ያልተጠበቀና ስልታዊ አማራጭ በመጠቀም በግቢው ዙሪያ የነፃ ዋይፋይ (Wi-Fi) ኢንተርኔት...
30/08/2026

አንድ ግለሰብ መኖሪያ ቤቱን ሰርቶ ከጨረሰ በኋላ ውድ የሆነ የጥበቃ ሰራተኛ (ዘበኛ) ከማቀጠር ይልቅ ያልተጠበቀና ስልታዊ አማራጭ በመጠቀም በግቢው ዙሪያ የነፃ ዋይፋይ (Wi-Fi) ኢንተርኔት ገጠመ።

በየምሽቱ የአካባቢው ነዋሪዎችና ወጣቶች አገልግሎቱን ለመጠቀም በግቢው አጥር ዙሪያ በብዛት የሚሰበሰቡ ሲሆን፣ ነዋሪዎቹ ግለሰቡን እንደ ደግና ለህዝብ የሚያስብ ሰው አድርገው ቢቆጥሩትም፣ እርሱ ግን ሳይታወቃቸው አጥር ግቢውን ሌሊቱን ሙሉ የሚጠብቁ የነፃ ደህንነት አካላት አድርጎ የመቀየሪያ ብልሃት ተቀምጦበታል።

ይህ አነስተኛ ወጪን በመጠቀም የአካባቢውን ማህበረሰብ የደህንነቱ አካል ያደረገበት የተለየና ፈጠራ የታከለበት መንገድ በማህበራዊ ሚዲያ ላይ ከፍተኛ ትኩረትና አድናቆትን ስቧል።

በአዲስ አበባ፤ መሪ ሎቄ ሰፈር በሚገኘው የኅብረት ባንክ ቅርንጫፍ የጥበቃ ሥራቸውን በታማኝነት የሚያከናውኑት እኚህ አባት፣ ከሥራቸው ጎን ለጎን በተቀመጡበት ወንበር ላይ ሆነው በጽናትና በጥበ...
29/08/2026

በአዲስ አበባ፤ መሪ ሎቄ ሰፈር በሚገኘው የኅብረት ባንክ ቅርንጫፍ የጥበቃ ሥራቸውን በታማኝነት የሚያከናውኑት እኚህ አባት፣ ከሥራቸው ጎን ለጎን በተቀመጡበት ወንበር ላይ ሆነው በጽናትና በጥበብ ዳንቴል ሲሰፉ የሚያሳየው ምስል የማህበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎችንና የመንገደኞችን ቀልብ ስቧል።

በተለይም በዚህ የዕድሜ ክልል ውስጥ ሆነው የዳንቴል ሥራን «የሴት ሥራ ነው» ወይም «ነውር» ብለው ብዙዎች ከሚንቁበትና ከሚያገሉበት ባህላዊ አስተሳሰብ በመውጣት፣ እኚህ አባት የፈጠራ ጥበባቸውንና የድካማቸውን ፍሬ በመንገድ ዳር ባስቀመጧት ወንበር ላይ አድርገው ለአላፊ አግዳሚው በመሸጥ ህይወታቸውን በክብር ለመደገፍ ይጥራሉ።

በአሁኑ የከበደ የኑሮ ውድነትና አስቸጋሪ ጊዜ፣ ለሰው እጅ ሳይዘረጉና ተስፋ ሳይቆርጡ በራሳቸው ጥረትና ላብ ህይወታቸውን ለመቀየር የሚያደርጉት ጥረት ለብዙዎቻችን ትልቅ የሞራልና የተስፋ ትምህርት አስተላልፏል። እውነተኛው ጀግንነትና ታላቅነት የሚገኘው በንጹህ ላብ በሚገኝ ቅን ሥራ ውስጥ መሆኑን በተግባር ያሳዩት እኚህ አባት፣ የብዙዎችን ልብ ከመንካታቸውም በላይ «ሥራ ክብር ነው» የሚለውን የቆየ የሀገራችንን ድንቅ እሴት ዳግም ያነቁ ታላቅ አባት ናቸው።

በደቡብ ትግራይ ስለዋ ወረዳ በአንበሳ ኢንተርናሽናል ባንክ ዴላ ቅርንጫፍ በጥበቃ ሥራ ላይ የሚገኙት አቶ ሰይፉ ተስፋይ፣ እድሜና የሥራ ሁኔታ ሳይገድባቸው ባደረጉት ከፍተኛ ጥረት በ2018 ዓ....
28/08/2026

በደቡብ ትግራይ ስለዋ ወረዳ በአንበሳ ኢንተርናሽናል ባንክ ዴላ ቅርንጫፍ በጥበቃ ሥራ ላይ የሚገኙት አቶ ሰይፉ ተስፋይ፣ እድሜና የሥራ ሁኔታ ሳይገድባቸው ባደረጉት ከፍተኛ ጥረት በ2018 ዓ.ም በተሰጠው የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና 320 ውጤት በማምጣት ወደ ዩኒቨርሲቲ ከሚያልፉ ተማሪዎች አንዱ ለመሆን በቅተዋል።

አቶ ሰይፉ ላሳዩት አስደናቂ ጽናትና ላስመዘገቡት ውጤት የባንኩ ቅርንጫፍ ሥራ አስኪያጅ አቶ ሓጎስ መዝገበ እና የሥራ ባልደረቦቻቸው በሙሉ የተሰማቸውን ታላቅ ኩራት የገለጹ ሲሆን፣ ለመጪው የትምህርት ጉዟቸውም መልካም ተመኞታቸውን አስተላልፈዋል።

በትግራይ ክልል ሰሐርቲ ወረዳ በሚገኝ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ላይ በተፈጸመ የድሮን ጥቃት በዓለም ባንክ «3R» ፕሮግራም አማካይነት 35 ኮምፒውተሮች ተገጥመውለት የነበረው የኢንፎርሜሽን...
28/08/2026

በትግራይ ክልል ሰሐርቲ ወረዳ በሚገኝ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ላይ በተፈጸመ የድሮን ጥቃት በዓለም ባንክ «3R» ፕሮግራም አማካይነት 35 ኮምፒውተሮች ተገጥመውለት የነበረው የኢንፎርሜሽን ኮሙኒኬሽን ቴክኖሎጂ (ICT) ማዕከል ሙሉ በሙሉ መውደሙን የትግራይ ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ኪሮስ ጉዕሽ አስታወቁ።
ኃላፊው ባወጡት መግለጫ፣ ትምህርት ቤቱ ከ1999 ዓ.ም. ጀምሮ ከ500 በላይ ተማሪዎችን ሲያገለግል የቆየና ለአካባቢው ማህበረሰብ ወሳኝ የትምህርት ማዕከል እንደነበር ገልጸው፣ ጥቃቱ በተፈጸመበት ወቅት በአካባቢው ምንም ዓይነት የወታደራዊ ዒላማ፣ ውጊያ ወይም የታጠቀ ኃይል እንቅስቃሴ እንዳልነበረ አብራርተዋል።

አክለውም የፌዴራል መንግሥት በትምህርት መሠረተ ልማቶች ላይ ሆን ብሎ ጥቃት እያደረሰ ነው ሲሉ ከሰዋል።

በአዲስ አበባ አድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚየም በተካሄደው የኢትዮጵያ ታፕ ፋይት ቻምፒዮና (ETFC 002፤ Adwa Fight Night) ዋና ፍልሚያ ጆኒ ጁጁትሱ ሰዶን ማሸነፉን ተከተሎ፣ ታዋቂው ...
28/08/2026

በአዲስ አበባ አድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚየም በተካሄደው የኢትዮጵያ ታፕ ፋይት ቻምፒዮና (ETFC 002፤ Adwa Fight Night) ዋና ፍልሚያ ጆኒ ጁጁትሱ ሰዶን ማሸነፉን ተከተሎ፣ ታዋቂው ድምፃዊ ታሪቁ ጋንክሲ በማህበራዊ ሚዲያው ያስተላለፈው የትችት መልእክት ከፍተኛ መነጋገሪያ ሆኗል።

በሺዎች የሚቆጠሩ ተመልካቾችን በሳበው በዚህ ውድድር ዙሪያ ድምፃዊው «ማደሪያ የሌለው ህዝብ - ሲገፋ የኖረ፣ እርግጫ ለማየት - ጎዳና አደረ» የሚል ግጥማዊ ቅሬታ ያቀረበ ሲሆን፣ ይኸውም በአሁኑ ወቅት በሀገሪቱ ውስጥ እየተስፋፋ ያለውን የፍትህ ማጣት፣ የጦርነት ስቃይ፣ ተቋማዊ የሌብነትና የዘረፋ ወንጀል እንዲሁም የከፋ የኢኮኖሚ ውደቀት ችላ በማለት ህዝቡ ጥልቅ ማህበራዊና ፖለቲካዊ ችግሮች ውስጥ እያለ በእንደዚህ አይነት የትግል ትዕይንቶች ላይ ትኩረት ማድረጉን ለመኮነን እንደሆነ ተገልጿል።

ድምፃዊው ይህን ማህበራዊ ተቃርኖ በማንሳት የሰጠው አስተያየት በበርካቶች ዘንድ ድጋፍና የተለያየ ትችት በማስተናገድ በማህበራዊ ሚዲያ መድረኮች ላይ ሰፊ አከራካሪ አጀንዳ ሆኖ ቀጥሏል።

የቀድሞው የአማራ ክልል ፕሬዝደንትና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶክተር ገዱ አንዳርጋቸው በአሜሪካ የሥራ ላይ እያሉ የተቀረጸውን ቪዲዮ በተመለከተ ምላሽ ሰጡ።ዶክተር ገዱ ባስተላለፉት መልእክት፣ በ...
26/08/2026

የቀድሞው የአማራ ክልል ፕሬዝደንትና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶክተር ገዱ አንዳርጋቸው በአሜሪካ የሥራ ላይ እያሉ የተቀረጸውን ቪዲዮ በተመለከተ ምላሽ ሰጡ።

ዶክተር ገዱ ባስተላለፉት መልእክት፣ በስደት ሀገር ለመኖር በራሳቸው ጥረትና በነፃነት አግኝተው የሚሰሩትን ሥራ በመስራት ህይወታቸውን እየመሩ መሆናቸውን በመግለጽ፣ ቪዲዮውን ቀርጸው ያሰራጩ አካላት ያሰቡት ነገር ምን እንደሆነ እንደማያውቁ ተናግረዋል።

አክለውም እርሳቸው በነፃነት ሰርተው እየኖሩ በመሆኑ በግል ሁኔታቸው ላይ ትኩረት ማድረግ እንደማያስፈልግ የገለጹ ሲሆን፣ ይልቁንም ህዝቡና አክቲቪስቶች ትኩረትና አጀንዳ ማድረግ ያለባቸው በሀገር ቤት በችግርና በስቃይ ላይ ባለው፣ ለተፈናቀለውና ህይወቱ ለሚያልፈው የአማራ ህዝብና የኢትዮጵያ ህዝብ መሆን እንዳለበት አሳስበዋል።

25/08/2026

የህዝብ ትራንስፖርት ላይ አፍንጫ ነካክቶ ወንበር ላይ ወይንም ብረት ላይ መጥረግ "ነውር" በመባል ይታወቃል

ሃገረ ዌልስ ለህዝብ ሆን ብለው የሐሰት መረጃ የሚያቀርቡ ወይም ውሸት የሚናገሩ ፖለቲከኞችንና የምርጫ ዕጩዎችን በሕግ የሚያስጠይቅ እና ከኃላፊነታቸው የሚያስወግድ ሕግ በማፅደቅ በዓለም የመጀመ...
25/08/2026

ሃገረ ዌልስ ለህዝብ ሆን ብለው የሐሰት መረጃ የሚያቀርቡ ወይም ውሸት የሚናገሩ ፖለቲከኞችንና የምርጫ ዕጩዎችን በሕግ የሚያስጠይቅ እና ከኃላፊነታቸው የሚያስወግድ ሕግ በማፅደቅ በዓለም የመጀመሪያዋ ሀገር ልትሆን መሆኗ ተገለፀ።

የሀገሪቱ ፓርላማ፤ ትኩረት ሰጥቶ በመወያየት ላይ የሚገኘው ይህ ሕግ፣ ፖለቲከኞች በምርጫ ቅስቀሳ ወቅት ወይም በሥልጣን ላይ ሳሉ ህዝብን ለማደናገር የሚያስተላልፏቸውን የሐሰት ንግግሮች በመግታት በሕዝብና በፖለቲካ ተቋማት መካከል ያለውን የመተማመን ደረጃ ለመመለስ ያለመ እንደሆነ ተመላክቷል።

ሕጉ በይፋ ከጸደቀ ፖለቲከኞች የሰጡትን የሐሰት ቃል እንዲያስተካክሉ የሚገደዱ ሲሆን፣ ጥፋቱ የጎላ ከሆነም ከሥልጣናቸው እንዲነሱ የሚያስችል አሰራር የሚፈጥር ቢሆንም፣ በሌላ በኩል «እውነትን የመወሰኑ ድንበር» የሐሳብ ነፃነትን ሊገታ ይችላል በሚል ስጋት ያቀረቡ ወገኖች አከራካሪ ነጥብ አድርገው አንስተውታል።

አለምዓቀፉ የሕንድ የዜና አውታር የሆነው "ፈርስትፖስት" (Firstpost) ባወጣው ዘገባ፣ በኢትዮጵያ ውስጥ የሚንቀሳቀሱ ሰባት ወታደራዊና አማፂ ኃይሎች ጥምረት በመፍጠር የጠቅላይ ሚኒስትር ...
25/08/2026

አለምዓቀፉ የሕንድ የዜና አውታር የሆነው "ፈርስትፖስት" (Firstpost) ባወጣው ዘገባ፣ በኢትዮጵያ ውስጥ የሚንቀሳቀሱ ሰባት ወታደራዊና አማፂ ኃይሎች ጥምረት በመፍጠር የጠቅላይ ሚኒስትር አቢይ አህመድን አስተዳደር ከስልጣን ለማስወገድ እንቅስቃሴ በማድረግ ላይ መሆናቸውን ገለፀ።

በዘገባው መሠረት፣ እነዚህ ስብስብ የፈጠሩት ኃይሎች ከአማራ ፋኖ፤ ከትግራዩ መከላከያ ሰራዊት፤ ከኦሮሚያው የነፃነት ሰራዊት እንዲሁም በሀገሪቱ ልዩ ልዩ አካባቢዎች የሚንቀሳቀሱና ከተለያዩ ብሔሮች የተወከሉ ሲሆኑ፣ ዓላማቸውም አሁን ያለውን የፌዴራል መንግሥት ስርዓት በመቃወም የተቀናጀ ወታደራዊና ፖለቲካዊ ጫና በመፍጠር አስተዳደሩን ለመገልበጥ እንደሆነ ተመላክቷል።

አጋጣሚው በኢትዮጵያ ያለውን የፖለቲካና የደህንነት ውጥረት ይበልጥ እንደሚያባብሰውና በምስራቅ አፍሪካ ቀጣናዊ ረጋ ላይ ተጨማሪ ስጋት እንደሚደቅን የዘገባው መረጃ ያመላክታል።

Address

Dub
Dubai

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Ethio Lead posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share