Yotor Media ዮቶር ሚዲያ

Yotor Media ዮቶር ሚዲያ Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Yotor Media ዮቶር ሚዲያ, Media/News Company, Dubai.

   የልቤ ከተማ ከነ እንከኗ ሙ ቸ የምወዳት ጎንደር ሰሞኑን በማህበራዊ ሚድያ ሲዘዋወሩ በማያቸዉ ፎቶዎች ናፍቆቷ አገረሸብኝና በትዝታ እየተወዘወዝኩ ለሙሽርነቷ የምታደርገዉን ዝግጅት ቆሜ ለማ...
08/11/2024



የልቤ ከተማ ከነ እንከኗ ሙ ቸ የምወዳት ጎንደር ሰሞኑን በማህበራዊ ሚድያ ሲዘዋወሩ በማያቸዉ ፎቶዎች ናፍቆቷ አገረሸብኝና በትዝታ እየተወዘወዝኩ ለሙሽርነቷ የምታደርገዉን ዝግጅት ቆሜ ለማድነቅ ተነሳሁ።
ጎንደር
በሸራ ተወጥራ የስደተኞች ካንፕ የሚያስመስላትን የመንገድ ዳር ንግድ ከላዯ ከልታለች::
የሲራራ ንግድ እመቤት የምስራቃዉያን እና ምዕራባዊያን የንግድ መገበያያ ደሴታቸዉ የለም የኮንቲነር ንግድ በቃኝ ዘመኑን በዋጀ ሁናቴ ንግዴን አስቀጥላለሁ ብላ ኮንቲነር አልባሷን አዉልቃለች።

24 ሰዓት ሳይታክቱ በሚሰሩ ልጇቿ የጎንደር ንጋት ሊገልጡ አሁን አሁን እያሉ ይመስላል::

10 ዓመታት የፈጀዉ ህዝብ ያማረረዉ የአዘዞ ፒያሳ የመንገድ ፕሮጀክት ከሰሞኑ ስራዉን አሟሙቆ አፋፍሞ ይዞታል።ይበል የሚያሰኝ ነዉ🫶🏻

የጀኔሬተሩ የእስካቫተሩ የጉልበት ሰራተኛዉ የመሃንዲሱ የዲዛይንና ቁጥጥር ሰራተኛዉ የሬንጅ አንጣፊዉ የቡናና ሻሂ አቅራቢዉ ጥምረትና በባለቤትነት ስሜት የሚያደርጉት ሩጫ ልብን ያሞቃል
ምን አለፋቸሁ ሥራና ሰራተኛ ጣትና ጥፍር ሆነዉ እየሰሩ እንደሆነ እያየን ነዉ።
ያልተሰራን ስንነቅፍ የሰራን እያመሰገን ነዉ🙏🏿

የታላቁ የጎንደር አብያተ መንግስታት እድሳት በጥራትና በፍጥነትእየተሰራ ይገኛል።
የመስቀል አደባባይ ደረጃዉን በጠበቀ መልኩ በመሰራት ላይ ነዉ አጄብ🙏🏿

በአጠቃለይ የኮሪደር ልማቱ እንቅስቃሴ የጎንደር ጎህ እየቀደደ መሆኑን ያበስራል

በዚህ ሂደት ዉስጥ ታድያ በርካቶች መመስገን አለባቸዉና የምስጋና መንሾ ማንሳት የግድ ይላል።
👉🏼ምስጋና
🫶🏻ለጎንደር ከተማ አስተዳደር
🫶🏻 ለመምሪያ
🫶🏻ለክፍለ ከተማና ለቀበሌ አመራሮች
🫶🏻 ለኮሪደር ልማት መሳካት ቦታችሁን ለለቀቃችሁ
🫶🏻 ለዚህ ስራ መሳካት ያለ ረፍት ለምትደክሙ
🫶🏻🫶🏻 አጠቃላይ ለጎንደር ከተማ ህዝብ🫶🏻🫶🏻_

 ‼️ትርፍ አምራች በሆነው ምድር የተከበበችው ወረታ ከተማ በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በደቡብ ጎንደር ዞን አስተዳደር ከባህር ዳር ጎንደር በሚወስደው ጎዳና ላይ የምትገኝ ከተማ ናት፡፡ወ...
15/03/2024

‼️

ትርፍ አምራች በሆነው ምድር የተከበበችው ወረታ ከተማ በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በደቡብ ጎንደር ዞን አስተዳደር ከባህር ዳር ጎንደር በሚወስደው ጎዳና ላይ የምትገኝ ከተማ ናት፡፡

ወረታ ከአዲስ አበባ 620 ኪሎ ሜትር ከክልሉ ርዕሰ ከተማ ከባህር ዳር በ55 ኪሎ ሜትር፣ ከጎንደር ከተማ 120 ኪሎ ሜትር፣ ከደብረ ታቦር ከተማ ደግሞ 45 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ትገኛለች፡፡ 14,097 ወንድ እና 14,379 ሴት በድምሩ 28,475 ህዝብ የሚኖርባት ወረታ በ1942 ዓ.ም ገደማ ነበር የተቆረቆረችው፡፡ ይሁን እንጂ ፈጣን ልማቷን ተከትሎ በሚሊኒየሙ ማለትም በ2000 ዓ.ም በከተማ አስተዳደርነት ተደራጀች፡፡

ትርፍ አምራቹ የፎገራ ምድር የከበባት ወረታ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በተለየ መልኩ እያደጉና ፈጣን እድገት እያስመዘገቡ ከመጡ የሰሜኑ የሀገራችን ክፍል ከተሞች አንዷ ለመሆን በቅታለች፡፡

ከጣና ሐይቅ ምስራቃዊ አቅጣጫ ከአዲስ ዘመን ከተማ በስተ ደቡብ ከባህር ወለል በላይ በ1828 ሜትር ከፍታ ላይ ያረፈችው ወረታ በ18ኛው ክፍለ ዘመን የበቀለች መንደር እንደነበረች ታሪኳ ያስረዳል፡፡ የዛሬዋ ወረታ ለቀጠናዋ የኩራት ተምሳሌት ለመሆን የበቃች ከተማ ሆናለች፡፡ በዋናው የሀገራችን ታሪካዊ የቱሪዝም መስመር ላይ የምትገኘው ወረታ ደረጃቸውን የጠበቁ ሆቴሎች ተገንብተውባታል፡፡

በጣና ሐይቅ አቅራቢያ ከታሪካዊዎቹ ጎንደርና ደብረ ታቦር ከተሞች አማካይ ስፍራ ላይ የምትገኝ ከተማ ስትሆን በአጼ ዘርዓያቆብ ዘመን የተመሰረተው የወረታ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያና በ1942 ዓ.ም የተቋቋመው የወረታ ኑር አምባ መስጂድ የከተማዋ የጎብኚ መዳረሻ የሆኑ ቅርሶች ናቸው፡፡
፡በተለይም በ28 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የሚገኘውና በየዓመቱ 55,000 ጎብኚዎች የሚጎበኙት የክርስቶስ ሳምራ ገዳም፣ የጉራምባ የተፈጥሮ ፍል ውሐ፣ የአሞራ ገደል የተፈጥሮ አምቦ ውሃ፣ በ22 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የሚገኘው የአጼ ሱሲንዮስ ካብና 12 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የሚገኘውና ከፍተኛ ትኩረትን እየሳበ የመጣው የአውራምባ ማህበረሰብ ወረታን መዳረሻ ካደረጉ የጎብኚ መዳረሻዎች መካከል ይጠቀሳሉ።

Naky hotel - ናኪ ሆቴል

የእቴጌ ጣይቱ ብጡል ሀውልት ተመረቀብርሃን ዘኢትዮጵያ እየተባሉ ለሚጠሩት ስመ ጥር የሀገር ባለውለታ እቴጌ ጣይቱ ብጡል በትውልድ ቦታቸውና ለቁምነገር በበቁበት በደብረታቦር ከተማ የመታሰቢያ ሀ...
03/02/2024

የእቴጌ ጣይቱ ብጡል ሀውልት ተመረቀ

ብርሃን ዘኢትዮጵያ እየተባሉ ለሚጠሩት ስመ ጥር የሀገር ባለውለታ እቴጌ ጣይቱ ብጡል በትውልድ ቦታቸውና ለቁምነገር በበቁበት በደብረታቦር ከተማ የመታሰቢያ ሀውልት ቆመላቸው።

ሀውልቱ በህብረተሰቡ ተሳትፎ ተገንብቶ በዛሬው እለት እየተመረቀ ይገኛል።

እለቱ በዓለ መርቆሪዎስ የሚከብርበት ጥንት የበጌምድር አርበኞችን የሚዘክረው የፈረስ ጉግስ በአጅባር የሚደምቅበት ጭምር ነው።

"አጅባር:- ምስጢር የተገለጠበት፤ ንጉሥ የሠረገበት''''በታርቆ ክንዴ''ሊቃውንቱ  ጉባኤያትን አደረጉበት፣ ስለ ሃይማኖት መከሩበት፣ ምስጢር ገለጡበት፣ የረቀቀውን ጥበብ በፈጣሪ እየተመሩ ነገ...
02/02/2024

"አጅባር:- ምስጢር የተገለጠበት፤ ንጉሥ የሠረገበት''
''በታርቆ ክንዴ''

ሊቃውንቱ ጉባኤያትን አደረጉበት፣ ስለ ሃይማኖት መከሩበት፣ ምስጢር ገለጡበት፣ የረቀቀውን ጥበብ በፈጣሪ እየተመሩ ነገሩበት፣ የከበደውን አቀለሉበት፣ ያልተፈታውን ፈቱበት፣ የደነደነውን ልብ በጥበባቸው አለዘቡበት።

ንጉሠ ነገሥቱ ሠርግ ሠረጉበት፤ የጠፋች ደስታቸውን መለሱበት። መኳንንቱን፣ መሳፍንቱን፣ ሊቃውንቱን፣ የጦር አበጋዞቻቸውን፣ የእልፍኝ አስከልካዮቻቸውን፣ በፊታቸው፣ በኋላቸው፣ በግራ እና በቀኛቸው እጅ እየነሱ የሚከቧቸውን ባለሟሎቻቸውን ጠርተው ዓለም አዩበት፣ የንጉሥ ሙሽራ ታየበት፣ ዘውድ እና ሠርግ ተገናኘበት።

ዘውድ የጫኑ ንጉሥ ከንግሥና ሙሽራ በላይ ሌላ ሙሽርነት ጨመሩበት፣ በሚያስፈራው ግርማቸው ተገማሸሩበት፣ በሚያስደነግጠው ክብራቸው ታዩበት። በዚያ ሥፍራ እጥፍ ድርብ ግርማ ተደራረበበት፣ እልልታና ምስጋና በዛበት፣ ፉከራና ሽለላ በረከተበት። ንጉሡ ሠርግ ሠርገዋል፣ ተሞሽረዋልና ያ ሥፍራ ደስታ መላበት። ሆታው አየለበት።

አንዳንድ ሥፍራዎች አሉ ከሁሉ የሚመረጡ፣ በከበረ ታሪክ ላይ የሚቀመጡ፣ ታሪካቸውን ትውልድ ሲሰማቸው ለነብስ የሚጣፍጡ፣ ትውልድ የሚኮራባቸው፣ እውነት የሚገለጥባቸው፣ ጥበብ የሚፈስስባቸው፣ ከዘመን ዘመን የማይቋረጥ ታሪክ የሚሠራባቸው፣ ታሪክም የሚነገርባቸው።

ዘመናት አልፈው ዘመናት ሲተኩ የትናንት ታሪክ እየተነገረበት፣ የዛሬ ታሪክ እየተሠራበት፣ ለነገ ታሪክ እየተመከረበት፣ እየተዘከረበት፣ ሥርዓት እየጸናበት፣ ሃይማኖት እየተሰበከበት፣ እሴት እየተገለጠበት፣ ጀግንነት እየታየበት፣ የአባት እና የእናት ቃል ኪዳን እየተጠበቀበት፣ ልጅ የአባቱን አደራ እየተቀበለበት፣ ቃሉን ላይሽር ቃሉን እየሠጠበት ዛሬ ላይ ደርሷል። ስሙ በግርማ ይነሳል፣ በኩራት ይወሳል አጅባር።

አጅባር ሜዳ ብቻ አይደለም ፈረሶች የሚግጡበት፣ በቅሎዎች የሚውሉበት፣ ልጆች የሚጫወቱበት፣ እንቦሶች የሚፈረጥጡበት፣ ላም እና በሬዎች ፣ ወይፈን እና ጊደሮች የሚሠማሩበት፣ እረኞች ዋሽንት የሚነፉበት።

እጅባር ብራና ነው ታሪክ የሚነበብበት፣ ቀለም ነው ታሪክ የሚፃፍበት፣ መንበር ነው ታቦታት የሚቀመጡበት፣ ቤተመቅደስ ነው ኪዳን የሚደረስበት፣ ቅዳሴ የሚቀደስበት፣ ስጋና ደሙ የሚፈተትበት፣ ሕዝብ ሁሉ የሚሠባሠብበት፣ በረከትና ረድኤት የሚቀበልበት፣ አጅባር ዙፋን ነው ነገሥታት የሚቀመጡበት፣ እልፍኝ ነው ግብር የሚበላበት፣ አዳራሽ ነው ስለ ሀገር አንድነት የሚመከርበት፣ ስለ ሀገር ፍቅር የሚዘከርበት። ቃል ኪዳን ነው የሀገር ፍቅር የሚጸናበት። ከሜዳ በላይ እልፍ ነገር የተሠራበት ነው።

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የደብረ ልዑላን ደብረ ታቦር መድኃኔዓለም ቤተ ክርስቲያን የአራቱ ጉባዔያት መምህር መምህረ መምህራን የኔታ በጽሐ ዓለሙ ነገረ ሃይማኖት፣ ነገረ ቤተ ክርስቲያን እና ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን በጉባኤያት ይወሰናሉ ይላሉ። ሊቃውንቱ በተለያዩ ጊዜያት ጉባኤያትን አድርገዋል። ጉባኤ ኒቅያ አርዮስ የተረታበት፣ አፈ ጉባኤው ለእለስክንድሮስ የነበረበት፣ በቁስጥንጥንያ የተደረገው መቅዶንዮስ የተረታበት፣ ሊቁ ጢሞቲዎስ ድል የነሳበት፣ በኤፌሶን የተካሄደው ንስጥሮስ የተወገዘበት፣ አፈጉባኤው ቅዱስ ቄርሎስ የነበረበት ጉባኤያት በታሪክ ከፍ ብለው ይነሳሉ ይሏቸዋል።

አባ ጎርጎርዮስ የቤተክርስቲያን ታሪክ በዓለም መድረክ በሚለው መጽሐፋቸው ከጉባኤ ኒቅያ፣ ከጉባኤ ቁስጥንጥንያ እና ከጉባኤ ኦፌሶን በተጨማሪ ጉባኤ ኬልቄዶን መካሄዱን ጽፈዋል። አባ ጎርጎርዮስ በመጽሐፋቸው እንደ እህቶቿ የምሥራቅ አብያተ ክርስቲያናት ሁሉ የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን የኬልቄዶንን ጉባኤ ውሳኔ እና ቀኖና አልተቀበለችውም። አትቀበለውም ብለው አስፍረዋል።

ሊቃውንቱ ይሰባሰባሉ፣ ጉባኤያትንም ያደርጋሉ፣ በአንድ ሃይማኖት በተመሳሳይ አስተምህሮ ይጸናሉ። ከአስተምህሮው የወጣውንም በትክክለኛው አስተምህሮ ያሳምናሉ። ድልም ይነሳሉ። ሥርዓት አፈርሳለሁ፣ ሕግም እጥሳለሁ ያለውን አውግዘው ይለያሉ። በዓለም ታሪክ በሃይማኖት ላይ የተለየ አስተምህሮ የያዙ፣ አስመስለው የመጡ ሰዎች በተነሱ ጊዜ ጉባኤያት ይደረጋሉ። በጉባኤያትም ትክክለኛው አስተምህሮ ይነገራል። ይገለጣል ነው የሚሉት።

ሊቁ እንደሚሉት በኢትዮጵያ የተለያዩ ዘመናት ጉባኤያት ተካሂደዋል። በ9ኛው መቶ ክፍለ ዘመን በአክሱም ጽዮን ታላቅ ጉባኤ ተካሂዶ ነበር። ጉባኤውም እንደ ንቅያ ሁሉ 318 ሊቃውንት ተሠብሥበው ነበር። በታሠበው ልክ በነገረ ሠሪ ጉባኤው ባይሰምርም፡፡

በዘርዓያቆም ዘመንም ሊቃውንቱ ጉባኤያትን አካሂደው ነበር። ይሄ ብቻ ጉባኤ አልነበረም ሌሎች ጉባኤያትም በየዘመናቱ ተደርገዋል። በመናገሻዋ በጎንደር በርከት ያሉ ጉባኤያት ተካሂደዋል። በነገሥታቱ ዘመን በተለይም በአጼ ፋሲል ዘመነ መንግሥት በካቶሊካውያን እና በተዋሕዶ ሃይማኖት ሜንዲዝ እና በትረ ጊዮርጊስ ያደረጉት ጉባኤ ይጠቀሳል። ይህም ጉባኤ በታሪክ ተመዝግቦ ያለ ከፍ ያለ ጉባኤ ነበር። በአጼ ዮሐንስ (በፃዲቁ ዮሐንስ) ዘመንም በቅባት፣ በተዋሕዶ እና በጸጋ ሃይማኖት መካከል በተፈጠረው ችግርም ጉባኤ ተካሂዶ ነበር ይላሉ ሊቁ። ፃዲቁ እየተባሉ የሚጠሩት አጼ ዮሐንስም በጉባዔው ላይ ተቀምጠው ነበር። በዚህም ጉባኤ የተዋሕዶ ሊቃውንት ድል አድርገው በንጉሡ አዛዥነት አዋጅ ተነገረ። በአጼ ዳዊትም በጎንደር አዘዙ ተክለሃይማኖት ጉባኤ ተደርጎ እንደነበር ሊቁ ያነሳሉ። የተዋሕዶ ሃይማኖት ሊቃውንትም ድል አደረጉ። በደስታም ከአዘዞ እስከ አጣጣሚ ሚካኤል ድረስ በደስታ ሄዱ።

በአጼ በካፋ ዘመንም ከግብፃውያን ሊቃውንት ጋር ጉባኤ ተደርጎ ነበር ይላሉ ሊቁ። በዚያን ዘመን የነበሩ አቃቢ እሳት ከብቴ የተባሉ ሰው አፈጉባኤ ኾነው ጉባኤው ተካሄደ። አቃቢ እሳት ከብቴም ድል አደረጉ። በኋለኛው ዘመንም አጼ ቴዎድሮስ በእናታቸው እንጂ በአባታቸው ከቤተ መንግሥት የሚመዘዝ ሀረግ የላቸውምና ንግሥና አይገባቸውም የሚል ጉዳይ በተነሳ ጊዜ ጉባኤ ተደርጎ ነበር። በዚህም ጉባኤ የቴዎድሮስን ንግሥና የሚያጸና መልስ ተገኘ። ሊቃውንቱ በንግሥናቸው ተስማሙ።

ጉባኤያት እየቀጠሉ የደብረ ታቦር አጅባር ሜዳ ጉባኤ ዘመን ደረሰ። ይህም ጉባኤ በዘመነ ቴዎድሮስ የተካሄደ ነበር። ጉባኤውን የጠሩት አጼ ቴዎድሮስ ነበሩ። በኢትዮጵያ በሁሉም አካባቢዎች የሚገኙ ሊቃውንትም ተሠባሠቡ። ሊቁ ሲናገሩ አጼ ቴዎድሮስ ጉባኤውን የጠሩበት ምክንያት የመጀመሪያው የሀገር ፍቅር ነው ይላሉ። ሁለተኛውም የሃይማኖት ፍቅር ነው። አጼ ቴዎድሮስ ስለ ምን ይሄን ጉባኤያት አስጠሩት የተባሉ እንደሆነ ከእርሳቸው በፊት በነበረው በዘመነ መሳፍንት የሃይማኖት ሽኩቻ ነበር። እርሳቸውም ይሄን የሃይማኖት ሽኩቻ ይዘጉ ዘንድ ጉባዔውን አስጠሩ።

አጼ ቴዎድሮስም በጉባኤው ሀገሬን እመራ ዘንድ አምላክ ቀብቶኛል። ሀገሬ አንድ ኾና እንድትቀጥል የሊቃውንቱ ምክር ያስፈልገኛል። የሊቃውንቱን ምክር በውል ለማግኘት ደግሞ አንድነታችሁ ያስፈልገኛል። ስለዚህም ተነጋግራችሁ አንዲት እውነተኛ ሃይማኖት እንድትይዙና እኔንም ልጃችሁን እንድትመክሩኝ እፈልጋለሁ። በመካከላችሁ ጠብ እና ጭቅጭ ሳይኖር ተመካክራችሁ አንዲት እውነት አውጥታችሁ በእናንተ እየተመከርኩ ሀገሬን መምራት እፈልጋለሁ ሲሉ በትሕትና ጠየቋቸው ይላሉ ሊቁ።

በዚህም ጊዜ አንድ ሊቅ "አጼ ቴዎድሮስ ቸርነታቸውን ቆራጥነታቸው፣ ቆራጥነታቸውን ቸርነታቸው ሳይጣሉባቸው የሚኖሩ ንጉሥ ናቸው" አሉ ይባላል። መፃሕፍት ተመረመሩ። ሊቃውንቱ ምስጢሩን አመሰጤሩ። ሊቃውንቱም ተስማሙ። መምህረ መምህራን የኔታ በጽሐ የአጅባር ሜዳ ጉባኤ የታሪክ ሰዎች ያልተረባረቡበት ጉባኤ ነው ይሉታል። በአጅባር የተካሄደው ጉባኤ የራሱ ጠባይ የነበረው ነው ይላሉ። በሌሎች ጉባኤያት አንዱ ረቶ ሌላኛው ተረትቶ የሚሄድበት ነበር። በዚህ ጉባኤ ግን ሁሉም ተስማምተው በአንድ ሃይማኖት አምነው የተለያዩበት ነበር ይላሉ። በዚህም ጉባኤ ሊቃውንቱ በደስታ ቅኔ ሲቀኙ ዋሉ ይላሉ ሊቁ።

አራት ዓይና ጉሹ የተባሉ ሊቅም ከሁሉ የላቀ ቅኔ ተቀኙ አሉ " ሁለቱ ወንድማማቾች አጼ ቴዎድሮስ እና አቡነ ሰላማ ባሉበት ተደርጎ የማያውቅ ነገር ተደረገ። ለነፍሱ ሥራ ጥበበኛ የኾነ ቴዎድሮስ ጽዮንን ማደሪያው አድርጓታልና የማይደረግ ነገር ተደረገ። በታቦር ጉባኤውን ባደረገ ጊዜ የማይደረግ ነገር ተደረገ። ይሄ ጉባኤ ከተደረገማ ከዚህ በኋላ ቁስጥንጥንያ ምንድን ናት፣ ከዚህ በኋላ ቁስጥንጥንያ ማለት ኢትዮጵያ ናት። ንቂያም ደብረ ታቦር ናት" አሉ ይላሉ ሊቁ። ንቅያን፣ ኤፌሶንን እና ቁስጥንጥንያን ከመተረክ ይልቅ ደብረ ታቦርን እና አጅባርን እንዲተርኩ ያስተላለፉት ቅኔ ነበር ይባላል።

አጅባርም ጉባኤ እንዲኾን የተደረገበት ምክንያት የንጉሠ ነገሥት ቴዎድሮስ መናገሻ በደብረ ታቦር መኾኑ፣ የጳጳሱም መቀመጫ በዚያው ስለነበር፣ ጉባኤውን የጠሩ ንጉሡ ስለኾኑ እና የሜዳው ሥፋትም ታላቅ በመኾኑ ነው ይላሉ ሊቁ። አጅባር ከዚያ አስቀድሞም የታቦታት ማደሪያ እንደነበር ይናገራሉ። አጅባር ጉባኤ ተደርጎበታል። ሃይማኖት ጸንቶበታል ነው የሚሉት።

ሊቁ ለመኾኑ አጅባር ማለት ምን ማለት ይኾን? ሲባሉ ሀጅ ባሕር ማለት ነው። በስፍራው ባሕር ነበር። ደብረ ታቦር ኢየሱስ ቤተ ክርስቲያን ተተክሎ ታቦተ ሕጉ ወጥቶ የጥምቀት በዓልን ለማክበር ባሕሩ ያስቸግር ነበር። በዚያም ጊዜ ሊቃውንቱ በሐሩን ብናስተነፍሰው እኮ ይሄዳል። ጥምቀቱንም በዚህ እናክብር አሉ ይባላል። ስያሜውንም ከዚያው አገኘ የሚሄድ ባሕር እንደማለት ነው ይላሉ።

ሊቁ የአጅባርን ጉባኤ የሀገር ፍቅር የወለደው ጉባኤ ይሉታል። የሀገርን አንድነት የሚወዱ ነገሥታት የሊቃውንቱን አንድነት፣ የሊቃውንቱን ኅብረት ይፈልጋሉ። አጼ ቴዎድሮስም የሀገር ፍቅር ነበራቸውና ሊቃውንቱ አንድ ይኾኑ ዘንድ ወደዱ። የወደዱትንም አደረጉ።

እነሆ ዛሬም አጅባር ታላላቅ ሃይማኖታዊ ሥርዓቶች እየተፈጸሙበት ቀጥሏል። ይህ ታሪካዊ ሜዳ አጼ ሠይፈአርድ ደብረ ታቦር ኢየሱስን አስተክለው ጥምቀተ ባሕሩን አጅባር ሜዳ እንዲኾን ካደረጉ ጊዜ ጀምሮ በታሪካዊቷ ከተማ የተተከሉ አብያተ ክርስቲያናት ሁሉ ጥምቀተ ባሕራቸውን በአጅባር አድርገዋል ይላሉ ሊቁ። ስለ ምን ቢሉ ታሪካዊ ነውና። በአጅባር ከሌሎቹ ሁሉ በተለየ መልኩ ረዘም ላሉ ቀናት ታቦታት እየወረዱ ጥምቀት ይከበራል። ሕዝቡና ምድሩም ይባረካል። ሊቁ ሲናገሩ አጅባር የታቦታት ሁለተኛ መንበራቸው ነው። ቀደም ባለው ጊዜ ሕዝብ እንዳሁኑ ሳይሰፋ በጥምቀት ጊዜ የአጼ ቴዎድሮስ ድንኳን ይዘረጋ ነበር።

አጅባር የንጉሥ ዳስ የተጣለበት፣ የንጉሥ ሰርግ የተሰረገበት ነውም ይላሉ ሊቁ። አጼ ቴዎድሮስ በታወሱ ጊዜ አብሮ የሚወሳ ታላቅ ሜዳም ነው። አጅባር ነገሥታቱ፣ መሳፍንቱ እና መኳንንቱ የፈረስ ጉግስ የሚጋልቡበት፣ ልዑላኑ የፈረስ ጉግስ የሚማሩበት፣ የቤተ መንግሥቱን ትምህርት እና የጦሩን ስልት የሚያውቁበት ነው። የትናንት ታሪክ ሀገርን ከፍ ያደርጋል፣ የታላቋን የኢትዮጵያን ታሪክ ማውጣት ይገባል፣ የአባቶች ታሪክ ድንቅና ረቂቅ ነውና። ሊቁ እንደሚሉት ኢትዮጵያ በተጠራች ጊዜ የዓለም ልብ የሚደነግጠው አባቶች በሠሩት ታሪክ ነው። ይህን የከበረ ታሪክ ለዓለም ማስተዋወቅ ግድ ይላል፣ አጼ ቴዎድሮስን የሚወድ እና እሳቸውን የሚያነሳ ሁሉ አጅባርን ያንሳው ነው የሚሉት።

አጅባር ላይ የተካሄደው ጉባኤ በታሪክ እየተዘከረ እና እየተነገረ ይኖር ዘንድ ከሊቃውንቱ ጉባኤያትን ማሳደግ ይጠበቃል ይላሉ። የከበረው ታሪክ ይወጣ እና ይገለጥ ዘንድ ግድ ይላልና። አጅባር የታላቅ ታሪክ ባለቤት ታላቅ ምድር። ሂዱ ታሪክ በበዛበት፣ ሃይማኖት በጸናበት፣ ሊቃውንቱ በማይነጥፉበት፣ ሕዝብ በሚሠባሠብበት፣ ታቦታት በሚያድሩበት፣ ጀግኖች በሚመላለሱበት፣ ነገሥታት በተመላለሱበት በአጅባር ሰማይ ሥር ተጠለሉ። ያን ጊዜ በአንድ ሜዳ እልፍ ነገር ታገኛላችሁ።

ከአጅባር ሜዳ እስከ አምቦ ሜዳ(ከታቦር ተራራ እስከ ዴንሳ ተራራ)❗------------------------------------------ጥር 25 ከማማው ደብረታቦር እስከ መካነ እየሱስ፣ ከታቦር...
31/01/2024

ከአጅባር ሜዳ እስከ አምቦ ሜዳ
(ከታቦር ተራራ እስከ ዴንሳ ተራራ)❗
------------------------------------------
ጥር 25 ከማማው ደብረታቦር እስከ መካነ እየሱስ፣ ከታቦር ተራራ እስከ ዴንሳ ተራራ፣ ከአጅባር ሜዳ እስከ አምቦ ሜዳ በአንድ በኩል ሰማዕቱ ቅዱስ መርቆሪዎስ ይነግሳል በሌላ በኩል ደግሞ የጎንደሩ አማራ የአባቶቹን የጦር ስልትና ጥበብ የሚያሳይበት ታላቅ የፈረስ ጉግስ ውድድር ይካሔዳል።

በእለቱ በጥንታዊቷ ደብረታቦር አጅባር ሜዳ እና መካነዕየሱስ አምቦ ሜዳ ላይ ሲገኙ አገርን ለዘመናት አፅንቶና ጠብቆ ያኖረው የእነ ንጉስ አምደ ፅዮን...... የእነ ንጉስ ሰርፀ ድንግል......የእነ ንጉስ ፋሲለደስ.......የእነ ንጉስ ቴዎድሮስ (መይሳው)......... የጦርነት የጥበብ ውርስን በቀጥታ ከእጅባር ሜዳ እና ከአምቦ ሜዳ ይከታተላሉ።

ጥር 25 የሰማዕቱን ንግስ በዓል ከማክበር ባሻገር ዘመናት በተሻገረው የኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ የኢትዮጵያን ፈረሰኛ ጦር ሀገር በማቅናት ተልዕኮው የነበረውን ሚና የሚያሳይ ትዕይንት በፈረስ ጉግስ ተዎዳዳሪዎች አማካኝነት ይታያል። የፈረስ ጉግስ ውድድሩ ከታሪካዊ ዳራው ጋር ተንሳናስኖ ለታዳሚ በሚያስገርም ጥበብ ይቀርባል።

ሆኖም የሰማቱን የንግስ በዓል እያከበሩ በዕለቱ ጎንደሬው ከደብረታቦር እስከ መካነእየሱስ፤ ከታቦር ተራራ እስከ ዴንሳ ተራራ፣ ከአጅባር ሜዳ እስከ አምቦ ሜዳ ድረስ በሚደረገው የፈረስ ጉግስ ጥበብ ውድድር በመታደም ከትናንት የተሻገረውን የአባት ውርስ የጦርነት ስልት ህያው ሁኖ ይመልከቱታል።

የጦርነት ፊልሚያ በባህል፣ በወግና በታሪክ ለዛ ተሰናስኖ እና ሥጋ ለብሶ አካል ነሥቶ የሚታይበትን የፈረስ ጉግስ ትይንት እና ውድድር በጥር 25 ከጃን አድባር (አጅባር) ሜዳ እስከ ዴንሳ ተራራ(አምቦ ሜዳ) የፈረስ ጉግስ ውድድር ሜዳ ተገኝተው የትይንቱ ተሣታፊ ይሆኑ ዘንድ ተጋብዘዋል።

አስደናቂው  #የኮሶዬ መልክዓምድራዊ አቀማመጥ!ከሰባት ያላነሱ ነገሥታት ተመላልሰው ጎብኝተውታል፡፡ ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ በቦታው ከመማረካቸው የተነሳ ጎንደር በሄዱ ቁጥር ሳይዩት አይመለሱም ነበ...
26/01/2024

አስደናቂው #የኮሶዬ መልክዓምድራዊ አቀማመጥ!

ከሰባት ያላነሱ ነገሥታት ተመላልሰው ጎብኝተውታል፡፡ ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ በቦታው ከመማረካቸው የተነሳ ጎንደር በሄዱ ቁጥር ሳይዩት አይመለሱም ነበር፡፡ ንጉሠ ነገሥቱ የእንግሊዟ ንግሥት ዳግማዊት ኤልሳቤት በ1957 ዓ.ም ኢትዮጵያ በመጡ ጊዜም ካስጎበኞቸው ዋና ዋና የቱሪስት መስህቦች አንዱ ይህ የኮሶዬ ድንቅ ምድር ነው፡፡

ኮሶዬ - ውናንያ - ወገራ የምድር ሁሉንም ዓይነት ገጽታዎች በማራኪ ሁኔታ የተሳሉበት ምድር ነው፡፡ እንደ ሰንሰለት የተያያዙና ከሰማይ ጋር የገጠሙ የሚመስሉ ተራሮች፣ ጫፋቸውን ወደ ሰማይ የቀሠሩ አንድ ወጥና ረጃጅም አለቶች፣ ሸለቆዎችን ተከትለው ጥቅጥቅ ብለው የበቀሉ የተፈጥሮ ደኖች እና አለፍ አለፍ ብለው የሚገኙ ረባዳ ቦታዎችን ሁሉም በዚህ አሉ፡፡

ይሄን የተፈጥሮ ውበት ብዙዎች ከሰሜን ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ አንዳንዶች ደግሞ በኤስያ እና በምዕራቡ ዓለም ከሚገኙ ተራሮች ጋር ያመሳስሉታል፡፡

ይህ ድንቅ ምድር ከጎንደር ከተማ ወደ ደባርቅ በሚወስደው ዋና መንገድ 3ዐ ኪ.ሜ ርቀት ላይ ከምትገኘው የኮሶዬ ከተማ ምዕራብ አቅጣጫ ይገኛል፡፡ መዳረሻው ከጎንደር በመነሳት ለውሎ ገብ ጉብኝት የተመቸ ነው፡፡ ወሎ አዳሩን በዚያው አድርጎ ከኮሶዬ እስከ ውናንያ ያለውን ውበት መጎብኘት ለሚፈልግ ደግሞ የበፍቅር ኮሶዬ ሎጅ ደረጃውን የጠበቀ አገልግሎት ለመስጠት ሁሌም እንግዶችን በክብር ይቀበላል፡፡

ጎራ ብለው ይጎብኙ! በምድር የተፈጥሮ ውበት ይደነቁ!

Central Gondar Communications

የሰማዕቱ ቅዱስ  #ገላውዲዬስ ቤተክርስቲያን መግቢያ  #ደራ  #ጎንደር  - 1952 ዓ.ምቤተክርስትያኑ በአጼ ገላውዲዮስ ዘመነ መንግሥት (1540-1559 G.C) እንደተመሰረተ ይታመናልPeop...
25/01/2024

የሰማዕቱ ቅዱስ #ገላውዲዬስ ቤተክርስቲያን መግቢያ #ደራ #ጎንደር - 1952 ዓ.ም

ቤተክርስትያኑ በአጼ ገላውዲዮስ ዘመነ መንግሥት (1540-1559 G.C) እንደተመሰረተ ይታመናል

People at the gate of the Church of in South back in 1960

Key search term 'Galadios'

Oxford University/Pitt Rivers Museum/Wilfred Thesiger Photographs:
https://www.prm.ox.ac.uk

https://mahideretsibeb.art.blog/2022/07/22/kidus-gelawdiyos/

via ዝክረ ጎንደር

12ቱ የአጼ ፋሲል ግቢ መግቢያ በሮች  የአጼ ፋሲል ግቢ በመባል የሚታወቀው ቦታ ስፋት 70 ሺህ ካሬ ሜትር ይሸፍናል፡፡ ስፍራው በ17ኛው እና በ18ኛው መቶ ክፍለ ዘመን የኢትዮጵያ መሪዎች ከ...
03/01/2024

12ቱ የአጼ ፋሲል ግቢ መግቢያ በሮች

የአጼ ፋሲል ግቢ በመባል የሚታወቀው ቦታ ስፋት 70 ሺህ ካሬ ሜትር ይሸፍናል፡፡ ስፍራው በ17ኛው እና በ18ኛው መቶ ክፍለ ዘመን የኢትዮጵያ መሪዎች ከነበሩት መካከል የስድስቱን አብያተ መንግሥታት እና ሌሎች የሕንፃ ፍርስራሾችን የያዘ ነው፡፡

የአፄ ፋሲል ግቢ ቀደም ብሎ አገልግሎት የሚሰጡ 12 በሮች ነበሩት፡፡ እነዚህ በሮች አገልግሎት የሚሰጡት የኅብረተሰብ ክፍል እንደነበራቸው በግቢው ውስጥ አስጎብኝ የኾኑት ኪዳነማርያም ኃይሉ ይገልጻሉ፡፡

አስጎብኝው አቶ ኪዳነማርያም ስለበሮቹ እና ስለሚሰጡት አገልግሎት የሚከተለውን ብለዋል፡፡

👉 ፊት በር ወይም ጃን ተከል በር ንጉሰ ነገስቱ የሚገቡበት በር ነው፡፡
👉 ወንበር በር ዳኞች የሚገቡበት በር ነው፡፡
👉 ራስ በር መሳፍንት እና መኳንንት የሚገቡበት በር ነው፡፡
👉 አዛዥ ጠቋሬ በር የግቢው አዛዦች የሚገቡበት በር ነው፡።
👉 አደናግር በር ጥጥ ፈታዮች የሚገቡበት በር ነው፡፡
👉 ኳሊ በር የነገሥታት አጃቢዎች የሚገቡበት በር ነው፡፡
👉 እምቢልታ በር የሙዚቃ መሳሪያ የሚጫወቱ ሰዎች የሚገቡበት በር ነው፡፡
👉 ባልደራስ በር የቤተመንግሥት ፈረሶች አለቃ የሚገቡበት በር ነው፡፡
👉 እርግብ በር ስጦታዎች የሚገቡበት በር ነው፡፡
👉 ተስካር በር ለሙታን መታሰቢያ የሚመጡ ሰዎች የሚገቡበት በር ነው፡፡
👉 እንኮይ በር እትጌ ምንትዋብ እና ልዕልት እንኮየ የሚገቡበት በር ነው፡፡
👉 እቃ ግምጃ ቤት በር ወደ ግምጃ ቤት ማርያም የሚያስኬድ በር ነው፡፡

አስጎብኝው ብዙ ምስጢር የያዘውን ይህን ቦታ ጥምቀት እየተቃረበ በመኾኑ ለሀገር ውስጥም ለውጭ እንግዳም ለማስጎብኘት ዝግጅት እያደረጉ እንደኾነ ገልጸዋል፡፡ ሰዎች የእረፍት ጊዜያቸውን በዚሁ ስፍራ በመገኘት ታሪካቸውን እንዲያውቁ እና ራሳቸውንም እንዲያዝናኑ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

 አሞራ ገደል በአማራ ክልል በደቡብ ጎንደር ዞን በፎገራ ወረዳ በአለምበር ቀበሌ ዙሪያ የሚገኝ ታሪካዊ ና የመንፈሳዊ የትንቢት ቦታ ነው ።👉ታሪካዊ አመጣጡም ይህን ይመስላል ።=====* አቡነ...
01/01/2024



አሞራ ገደል በአማራ ክልል በደቡብ ጎንደር ዞን በፎገራ ወረዳ በአለምበር ቀበሌ ዙሪያ የሚገኝ ታሪካዊ ና የመንፈሳዊ የትንቢት ቦታ ነው ።

👉ታሪካዊ አመጣጡም ይህን ይመስላል ።=====

* አቡነ አቢብ ወአባ ቡላ የተባሉ ፃዲቅ ከሮም ሀገር ሉፌ ከሚባል አውራጃ ተወለዱ ::
* የአባታቸው ስም አብርሃም እና የእናታቸው ስም ደግሞ ሐሪክ ይባላሉ፡፡

እርሳቸው በተወለዱ ጊዜም አንድ ታላቅ ዛፍ በቀለ በቅጠሉም ላይ በሮማይስጥ ቋንቋ የእግዚአብሔር አገልጋይ በፅዮንም አድሮ የሚኖር የያዕቆብ
ፈጣሪ ያከበረው የሚል ፅሁፍ ነበር ፡፡

*በዚህ ዘመንም በከሀዲው ንጉስ'' መክስምያኖስ '' ዘመን ከሮም ወደ ኢትዮጵያ ተሰደዱ፡፡
ኢትዮጵያንም እየተዘዋወሩ ሲባርኩ እና ሲጸለዩ
:- ከሰው ተለይቼ
:- ከሀገር ወጥቼ የምጸልይበት ቦታ ስጠኝ ብለው ፈጣሪያቸውን ይጠይቁ ነበር፡፡

የለመኑትን የማይነሳ እግዚአብሔር በፈቃዱ ከደረቀ ተራራ ላይ ዉጣ የሚል መላክ ተላከ፡፡ ከተራራውም አወጣው ያለማቋረጥ እየታገለ ኖረ 42 ዓመት እህል ሳይበላ ውሃ ሳይጠጣ ፀለየ ዳግመኛም ቅንጭላቱ/ ፈስሶ እስኪያልቅ ድረስ 12 ወር በራሱ ተተክሎ ኖረ፡፡

👉የእረፍት ጊዜው ሲደርስደ ተራራው የወጣው የእግዚአብሔር መላክ ከተራራው ስር አወረዳቸው ከተራራው ስር ቁመው ሲፀልዩ እግዚአብሔር መላዕክቶችን አስከትሎ መጣ ፡፡

አቢብ :- [ `` ብሒል አበ ብዙሐን ``] ማለት የብዙዎች አባት ማለት ነው፡፡ አቡነ አቢብ ወአባቡላ የብዙዎች አባት እና አማላጅ ስለሆነ እግዚአብሔርም
ለአቡነ አቢብ ቃል ኪዳን ሰጣቸው መታሰቢያውን ለሚያደርግልህ እኔ ሀጢያቱን አስተስርይለት ዘንድ በራሴ ማልኩልህ ወይም ለተራቆተ የሚያለብሰውን ለተራበም የሚያጠግበውን ለተጠማ የሚያጠጣውን እስከ 1ዐ ትውልድ እምርልህ አለው ብሎ እግዚአብሔር መላይዕክቶችን ይዞ ከፊቱ ተሰወረ ፡፡

በዘመነ ተሳቱ ቅዱሳን ዘመን ጥቅምት 25 ነፍሳቸውን በእግዚአብሔር እጅ ሰጡ ፡፡

በመንፈስ ቅዱስ ሀይል ቅዱሳን ወደ አቡነ አቢብ መጥተው ሲደርሱ አሞራው ከአስከሬናቸው ላይ አርፎ ሞቶ አገኙት በዚያን ጊዜ ከእግዚአብሔር የመጡት ቅዱሳኖች የሞተውን አሞራ አይተው ይህስ አሞራ ገደል /ጠብቆ ሲነበብ/ ጻዲቅ ነው ብለው ሰየሙት ተብሎ በታሪኩ ላይ ሰፍሯል ።

ከዚያን ዘመን ጀምሮ አሞራ ገደል እየተባለ /ተብሎ/ሲጠራ ይኖራል፡፡
--------አሁን ላይ አቡነ አቢብ ወአባ ቡላ ያረፋበት ቦታ----
➢ፀበል ፈልቆ እውር እየበራበት
➢መካን እየወልደበት
➢የሆድ በሽታ ያለባቸው እየዳኑበት
➢ህሙማን እየተፈወስበት ይገኛል፡፡

የዚህ ታላቅ በዓል ጥር 25 የሚከበር ብቸኛ ንግስ ሲሆን ታቦቱ ወጥቶ በህዝቡ ታጅቦ ህዝቡን ቀድሶ ወደ መንበሩ ይመለሳል ። የፃድቁ በረከት አይለየን ።
======ይምጡና ይጎብኙት =====

መገኛ ቦታ:- ከወረታ ወደ ደብረታቦር ሲሔዱ ከአለምበር ቀበሌ በሲራባ ማርያም ቤተክርስቲያን ውስጥ እየተቀደሰ ይገኛል።

==========አሞራ ገደል ================


Esubalew Mesfin-እሱባለው መስፍን

Address

Dubai

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Yotor Media ዮቶር ሚዲያ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Yotor Media ዮቶር ሚዲያ:

Share