Zemelak Media Network

Zemelak Media Network Breaking news,technology updates, world events, and the future generation insights with Zemelak Media

12/08/2026

አዲስ ወሳኔ #ክልል

ሰበር ዜና መንግስት ያቀረበውን የይቅርታ ሰነድ አንፈርምም ያሉ ተከሳሾች እነማን እንደሆኑ የሚያመላክት ስም ዝርዝር የወጣ ሲሆን በዋናነት የቀድሞው የአማራ ክልል ምክር ቤት አባል ዮሐንስ ቧያ...
12/08/2026

ሰበር ዜና መንግስት ያቀረበውን የይቅርታ ሰነድ አንፈርምም ያሉ ተከሳሾች እነማን እንደሆኑ የሚያመላክት ስም ዝርዝር የወጣ ሲሆን በዋናነት የቀድሞው የአማራ ክልል ምክር ቤት አባል ዮሐንስ ቧያለው፣ ዶ/ር ወንደወሰን አሰፋ፣ ዶ/ር ሲሳይ አውግቸው፣ መምህርት መስከረም አበራ፣ ጋዜጠኛ ዳዊት በጋሻው፣ ጎበዜ ሲሳይ፣ ገነት አስማማው ይገኙበታል፡፡

ሙሉ ዝርዝራቸው ተከታዩ ነው፡-

1. አቶ ዮሐንስ ቧያለው
2. ዶ/ር ቴዎድሮስ ኃ/ማርያም
3. ዶ/ር ሲሳይ አውግቸው
4. ዶ/ር ወንድወሰን አሰፋ
5. ዶ/ር መሠረት ቀለመወርቅ
6. ዶ/ር ዘሪሁን ባህሪው
7. ጋዜጠኛ መስከረም አበራ
8. ጋዜጠኛ ገነት አስማማው
9. ጋዜጠኛ ዳዊት በጋሻው
10. ጋዜጠኛ ዓባይ ዘውዱ
11. ጋዜጠኛ ጎበዜ ሲሳይ
12. አቶ አለልኝ ምህረት
13. አቶ መንበር አለሙ
14. አቶ ማይክ መላክ
15. አቶ አሳምነው ታደሠ
16. አቶ ደሳለኝ እጅጉ
17. አቶ እሱባለው በለጠ
18. አቶ እስክንድር ሽፈራው
19. አቶ መሰለ ቸሩ
20. ኢ/ር ፍርዱ ተፈራ
21. አቶ ጫኔ ዘየደ
22. ወ/ት ሃሊማ አህመድ
23. ወ/ት ህይወት አለማየሁ
24. አቶ ሲሳይ መልካሙ
25. አቶ ታደሰ ወዳይነው
26. አቶ በላይ ሲሳይ
27. አቶ ያሬድ ግርማ
28. አቶ ማረው ስለሺ
29. አቶ ሠለሞን ተፈሪ
30. አቶ ሙሉቀን ተስፋዬ

ደብዳቤው እንደሚያመላክተው የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን(ኢሰመኮ) ከመንግስት ጋር በጀመረው ውይይት በመጨረሻ ፈርሙ የተባሉት ተከታዮቹን ጉዳዮች ያካትታል፡-

“በአማራ ክልል ለተፈጠረው ቀውስ ኃላፊነት ውሰዱ፤ በአማራ ክልል በተፈጠረው ቀውስ ለሞቱ ሰዎች፣ ለቆሰሉ ሰዎች (በየመዝገብ ቁጥሩ ይለያያል) ፈጽመናል ብላችሁ እመኑ፤ ለወደመው በበሊዮን የሚገመት ንብረት
ፈጽመናል ብላችሁ እመኑ፤ ሀገሪቱ በአማራ ትውፊቶችና እና እሳቤ ካልተመራች ማለታችሁን ወንጀል ነው በሉ፤ ያለ አግባብ የተወሰዱ የአማራ ርስቶች መመለስ አለባቸው ስለማለታቸው እና ይህም ወንጀል መሆኑን እንዲያምኑ” በቅድመ ሁኔታ እንደቀረበላቸው አዲስ ማለዳ የተመለከተችው ያመላክታል፡፡

ይህንን ተከትሎ ተከሳሾቹ በሰጡት ምላሽ “እኛ ወንጀለኛ ነን ብለን አንፈርምም፤ በህግም፣ በሞራልም፣ በታሪክም ተቀባይነት የለውም ብለን አንፈርምም” ብለዋል፡፡

አክለውም፤ “የአማራ ህዝብ ጥያቄዎችም ህጋዊ ናቸው ብለው እንደሚያምኑ በመግለጽ የ60 ሚሊዮን ህዝብን መልካም እሴት ወንጀል ነው ብለን አውቀን አንሰጥም ወንጀልም አይደለም፤ በህገመንግስት እና በዓለምአቀፍ ህጎች ነፃ ሆኖ የመኖር መብታችንን ፈቅደን አንተውም፤ በህግ የተከለከለውን ራስን መከላከል እና ራሳችንን ወንጀለኛ አናደርግም” ሲሉ ምላሽ መስጠታቸውን መመልከት ተችሏል፡፡

12/08/2026

ፋኖን አዉግዙ ና ልፍታቹ መንግስት ለነ ክርስቲያን ታደለ ጥሪ ቀረበላቸው #አማራ #ፅምዶ

11/08/2026

#አማራ

11/08/2026

አቶ ወልደጊዮርጊስ ምላሽ ሰጡ

11/08/2026

የህውሀት ዋና መስራች ስብሀት ነጋ ፅምዶን ተቃወሙ #ትግራይ #ፅምዶ

10/08/2026

"ፋኖ ናችሁ" ተብለው ከመኪና እንዲወርዱ ከተደረጉ በኋላ በአሰቃቂ ሁኔታ የተገደሉት ሦስት ወጣቶች አስከሬን ለሦስት ቀናት ውጭ ተጥሎ እንዲቆይ ተደረገ

​በማዕከላዊ ኢትዮጵያ በጉራጌ ዞን አበሽጌ ወረዳ አገና አካባቢ ከተሳፈሩበት የሕዝብ ማጓጓዣ መኪና ላይ ተመስገን ጌታቸው፣ ይታገሱ አሰግደው እና ግዛው ግርማዬ የተባሉ ሦስት ወጣቶች “ፋኖ ናችሁ” በሚል ውንጀላ ተገደው እንዲወርዱ ተደርገዋል።

​ኃይሎች ከአካባቢው ፖሊስ እና ሚሊሻ አባላት ጋር በመተባበር ዜጎቹን እጃቸውን በገመድ ካሰሩ በኋላ ጭንቅላታቸውን በጥይት በመምታት በግፍ እንደረሸኗቸው ተገልጿል። በተጨማሪም የሟቾቹን አስከሬን ወደ ትውልድ ቀያቸው ናቻ ቀሊት ቀበሌ በመውሰድ ማንም እንዳያነሳና እንዳይቀብር ጥብቅ ክልከላ በመደረጉ፣ አስከሬኖቹ እጃቸው ሳይፈታ ለሦስት ሙሉ ቀናት ክፍት ቦታ ላይ ተጥለው በእንስሳ እንዲበሉ መደረጉ ታውቋል።

​ሀሳብ አስተያየታችሁን በኮሜንት አጋሩን!
#አማራ

10/08/2026

ሰበር ዜና ሳልሳዊ ወያኔ መግለጫ አወጣ የትግራይ ወጣቶች እያለቁ ነው #ትግራይ #ፅምዶ

10/08/2026

በህውሀት ታጣቂዎች ላይ የድሮን ጥቃት ደረሰ #ትግራይ #ፅምዶ

09/08/2026

ሰበር ዜና በመቀሌ የኤርትራ ና የሱዳን የጦር መኪኖች ታዩ

#ትግራይ #ፅምዶ

Address

In
Dubai
1000

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Zemelak Media Network posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share