
26/06/2025
Ethiopia Real Estate Expo
በዱባይ የኢትዮጵያ ሪል እስቴት ኤክስፖ 2025 ሊዘጋጅ ነው
| በዱብይ ሪል እስቴት ላይ ስመጥር በሆኑ ኢትዮጵያውያን ኤክስፐርቶች ስብስብ የሚመራ የኢትዮጵያ ሪል እስቴት ኤክስፖ 2025 በነሃሴ ወር 2025 በዱባይ ሊዘጋጅ ነው።
የኤክፖው አላማ የአገራችንን ሪል እስቴት ማርኬት በዘመናዊ መልኩ ከዳያስፖራው ጋር ለማግናኝት ያለመ አለማቀፍ ኤክፖ ነው።
የአገራችን የሪል እስቴት አልሚዎች ከሰፊው የዳያስፖራ ማርኬት ጋር ለመገናኘት በዱባይ የኢትዮጵያ ሪል እስቴት ኤክስፖ 2025 ተሳታፊ እንደሚሆኑ የሚጠበቅ ሲሆን ፥ ሀገር ቤት የቤት ባለቤት የመሆን ህልም ያላቸው በዱባይና ሌሎች የUAE ከተሞች የሚኖሩ ኢትዮዕያውያን በኤክፖ በመገኘት ከሪል እስቴት አልሚዎችና ከኤክፖ የሪል እስቴት ኤክስፐርቶች ጋር በቅርበት ያለ ሶስተኛ ወገን ጣልቃ ገብነት በመገናኘት ስለ ፕሮጀችቶቹ ፥ የዋጋ ና አከፋፈል ሂደቱ ሙሉ መረጃ በመውሰድ የቤት ባለቤት የመሆን ህለማቸውን የሚያሳኩበት ኤክፖ ነው።
ይህ በነሃሴ ወር 2025 በዱባይ የሚዘጋጀው የኢትዮጵያ ሪል እስቴት ኤክስፖ 2025 ፥ ዱባይና ኤሎች በሪል እስቴት ኢንዳስትሪ ስመጥር ከተሞች የደረሱበትን የሚስተካከል አለማቀፍ ጥራቱን የጠበቀ ሆኖ ፥ የአገራችን የሪል እስቴት ዘርፍ የተሰማሩ ባለ ሀብቶችና ባለሞያዎችም እጅጉን ተጠቃሚ እንደሚሆኑበት ከኤክስፖ አዘጋጁ አፍሮክስ ኤቭንትስ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።