EthioCyber Group

  • Home
  • EthioCyber Group

EthioCyber Group Let's stand Up for Ethiopia!

25/07/2025

~~~~~~~~√√√√√
ለመምህር ፈንታሁን ዋቄ
wakie
//
እየውለዎት ትግሉን መደገፍ ይቻላል፤ በትግሉ ውስጥ ግን ገብቶ ብይን ለመስጠት መንቀሳቀስ ግልፅ ጣልቃ ገብነት ነው። የአማራ ብሄርተኝነት እርሰዎ እንደሚሉት ወይም እንደሌሎቹ የአውሬ ብሄርተኝነት አይደለም። የአባቶቻችንን ስነ-ልቦና እናስቀጥላለን እንጅ ከስሪታችን የምናፈገፍገው አይኖርም። ፓለቲካ የጋራ ጉዳይ ነው። የጋራ ካልሆነ ፓለቲካ ሊሆን አይችልም። ይሄ ማለት አይደለም አማራ ህዝብ ውስጥ ያለ ሃይማኖት እና ሌሎች መገለጫወች ቀርቶ የሌላውንም ክብር በሚሰጥ መልኩ የሚኬድበት ነው። ብዙ ጉዳዮች እንደ ትናንት አይደሉም። ዛሬ በአንድ በሚወጣ ቃል ብቻ የቀጣይ ፍላጎት እና እቅድ በቀላሉ በማሽን( AI) የሚታወቅበት ደረጃ ላይ ነው ያለነው። አንድ የተለመደ ሁላችንም የምናውቀው ጉዳይ ላይ ችክ ብሎ የግድ እንዲህ ካልሆነ የሚባል አካሄድ የለምም አይሰራምም!
ይሄ ትግል ሰፊ መስዕዋትነት እየተከፈለበት ያለ ነው። በዚህ ወቅት ጠላት ላይ በመረባረብ ሌሎች ጉዳዮችን በሌላ መልክ መሄድ ይቻል ነበር።
አላስፈላጊ ጣልቃ ገብነትን የተቃወምነው ወደ ፊትም እስከ ጥግ የምንታገለው ትናንት በብዓዴን ውስጥ ጉዳይ እንኳን ህውሃት ገብታ እያዘዘች እያንዳንዳችንን እንደ ህዝብ ከባድ መስዕዋትነት ከፍለናል። በዚያም አላበቃም አብይ አህመድ ብዓዴንን ራሴ እያዘዝኩ ካልመራሁ የአማራ ኢሊት ገብቶ ከስልጣኔ ያስወግደኛል ብሎ ስለፈራ ራሱ መሪወችን እነ ዶ/ር አምባቸውን በጀነራሉ በኩል ጀነራሉን ደግሞ ራሱ በቀጥታ ገድሎ ይሄው ትናንት ከህውሃት ጋር ዛሬ ደግሞ ከእኛ ጋር ይሄን ከባድ መስዕዋትነት እያሰከፈለን ያለው ለዚህ ነው ይሄ ጦርነትም የሃገርን ህልውና የሚፈታተን እንደሆነም ማሰብ ተገቢ ነው። በፓለቲካው ረገድ ትግሉን የጀመሩ መሪወች #ስለትናንት በቂ እውቀት፣ #ስለ ዛሬንሰፊ መረዳት #ስለ ነገም የመተምበይ ብቻ ሳይሆን ነገን የመበየን አቅም ያላቸው መሪወች ስላለን ምንም ጣልቃ ገብቶ እንዲህ አስቡ ተብሎ ምሪት አያሻቸውም።
ለዚህም ነው ውስጣዊ ጣልቃ ገብነትን አምርን የምንፀየፍ እስከ መጨረሻው የምንታገለው!
አሁን በተረዳሁዎት መሠረት ሰፊ የአካሄድ ችግር እንዳለብወት እና ለቀና ነገር እየታገሉ የሚሄዱበት ግን ታጋዮችን የማጠልሸት ፣መጠራጠርን የመዝራት ለጠላት የበለጠ አመቺ ሁኔታን የሚፈጠር እጅግ ያልተሰላ አካሄድ ነው! እርሰዎ የእኛ የህይወት እና የመንፈስ አስተማሪያችን፣ በቤተክርስቲያናችንም ውስጥ በምርምር ከፍተኛ ደረጃ የደረሱ ምሁር ነዎት እኔ በግሌ አከብረወታለሁ። የፓለተካ አካሄደዎ ግን Idealism የበዛበት ይባስም ብሎ ጠላት የሚፈልገውን ምንም የሃሳብ ዝምድና ሳይኖርወት እየፈፀሙለት መስሎ እየተሰማኝ ነው።
ደግሞም እንዲህ ዓይነት ያልተገባ በመረጃ ያልተረጋገጠ speculation እርስወን በማይመጥን መልኩ በተለይ ከሁሉም አቅጣጫ እሳት በሚወርድባቸው በአማራ ፋኖ በጎጃም መሪወች ላይ አጀንዳ የሚያስቀይራቸው አካል/ግለሰብ አለ" ብሎ ጥርጣሬን መፍጠር ተገቢ አይደለም።
በሌሎች በኀልዮት ጉዳዮች ላይ ሃሳብወትን ለመሸጥ የሚያቀርቧቸው ትንተናወችን እኛም የምናዳምጣቸው ናቸው። ጣልቃ ገብነት ሆነ ያለ ሚናችን ግን በውስጥ ጉዳያችን ገብቶ መፈትፈትን ግን ፈፅሞ አንታገስም!
እደግመዋለሁ እስከመጨረሻ እንታገላለን!
ከአክብሮት ጋር!
Bezabih Belachew

19/07/2025
02/07/2025

📢ክረምቱን ለሀገር በቀል ትምህርት🔊
🎤የጥንቱን ትምህርት ወደ አሁኑ ትውልድ፣የአሁኑን ትውልድ ወደ ጥንት አባቶች ለማድረስ መገናኛ መንገዱ አብነትና ቁራን ነው።
🎤ሁለገብ ትውልድ ማውጣት እየተቻለ ማንም ወላጅ በክረምት የልጆቹን ጊዜ በከንቱ ማሰለፍ የለበትም።"ከንጹሕ ባሕር የማይቀዳ ከእውነተኛ መምህር ጠይቆ የማይረዳ።"ቢኖር አግባብ ነው?አይደለም።
🎤ልጆች ከነጻው ባሕር ሊቀዱ ከበቀል መምህሩ ሊረዱ ይገባቸዋል።"ካልተማሩ አያውቁ፤ካላወቁ አይጠይቁ፤ ካልጠየቁ አይጸድቁ" አይደል ብሂሉስ?
🎤ልጆቻችንን በአግባቡ አብነታቸውን ካላስተማርናቸው መሠረታቸውን ማረዳት የተሳናቸው ይሆኑና የነገ ፈተናችን ከዛሬው የባሰ ይሆናል።
🎤በችግር ወራት ጠንክረን ከመሠረቱ ጀምረን ካላስተማርን ክፉው መንፈስ የመከራ ድኃ አይደለም።"ከዚህ የሚብስ እንዳይደርስብህ ወደ ፊት አትበድል።" እንዲል።ዮሐ.፭፥፲፬
🎤ከጥንቱ ከመሠረቱ ጀምረን ካስተማርናቸው ግን የነገው ዘመን በልጆቻችን ይቀደሳል።እውነተኛው ትምህርት የማይጠፋ ፀሐይ ሁኖ በልጆች እና በልጅ ልጆች አእሞሮ ሰማይ ላይ ተቀርጾ ሲያበራ ይኖራል።
🎤እናት እና አባቶች ሆይ! አለመማርን አለማወቅን ያህል ዕዳ ለትውልድ ማትረፍ ትልቅ በደል አይደለም ወይ?
ነገ የምትቅሙ የምትለቅሙ ዛሬ በልጆቻችሁ ላይ የዘራችሁትን የተስፋ ዘር ነው።
የነገዋ ሀገር፣የነገዋ ቤተ ክርስቲያን ዛሬ በዘራነው የትውልድ ዘር ልክ ትወሰናለች።
🎤የችግራችን መፍትሄው በቀል አባቶችን ለልጆች ማስተዋወቅ ተተኪ ልጆችን ወደ አባቶች መመለስ ነው።
🎤ለዛሬ መሠረት የሆነው ርቱዓን ትጉኃን አባቶቻችን በበበቀል ዕውቀት በሐዋርያዊ ጽንዓት የዘሩት የትናንቱ የተግባር ዘር ነው።
ለነገው ትውልድም የነገ ዘር የነገ መርህ የሚሆነው የዛሬው የዓላማ አብነታዊ ሥራችን ነው።
🎤ከአቀባይ መምህር ተቀድቶ በትውልድ አእምሮ ላይ የተቀመጠ እውነት መጥፋት አይችልም።
🎤የአብነት ትምህርት ጠንክረው ከተማሩት ተኖ የሚጠፋ፦"የድምጫ ትምህርት የገቦ አዝርዕት"አይደለም።ልጆቻችንን ጠንክረን ብናስተምራቸው ቢያንስ ቢያንስ ለመካሪ አያስቸግሩም።
🎤ሴት ልጆቻችሁንም ወደ አብነት ትምህርት ላኳቸው።
"አርፈሽ ተቀመጭ አንቺ አትቀድሺ"?የምትሉ ወላጆች ትክክል አይደላችሁም።
የቅዳሴም የማኅሌቱም ዋነኛዋ ሴት አይደለችም እንዴ?
ሴቶች በዕውቀት በእምነት ሲጸኑ ያን ጊዜ ቤተ ክርስቲያን በብዙ የአገልጋይ ፍሬ ትሞላለች።
እግዚአብሔርም በነቢዩ አድሮ "ሴቶች ልጆቼ ቍርባኔን ያመጡልኛል።"ሶፎ.፫፥፲እንዳለ።
🎤ሴቶችም ወንዶችም ልጆቻችን፦ፊደል ቆጥረው፣ውዳሴ ማርያም አጥንተው፣ ዳዊት ደግመው፣የቤተ ክርስቲያንን ታሪክ አውቀው፣ትምህርተ ሃይማኖት ተምረው፣ሥነ ምግባርን ተላብሰው፣ከመቅደሱ ሥር ዕጣን አሽተው፣ጸበል ጠጥተው፣እምነት ተቀቦተው..ቢያድጉ ጉዳቱ ምንድን ላይ ነው?
🎤እንኳን ከእግዚአብሔር ለተቀበልነው ለአብነት ለሌላውስ ተምህርትስ ቢሆን ይጠቅማል ብለን ገንዘብ ውጥተን ጊዜ በጅተን ደክመን የለም ወይ?
🎤መርጌቶች፣ካህናት፣ዲያቆናት፣ሰባክያን፣የከፍተኛ የአብነት ደቀ መዛሙርት የክረምት ሥራችን በአብነት ትምህርት በኩል ትውልድ መተካት ላይ መሆን አለበት።
አጥቢያዎች፣መንደሮች ሁሉ በየአቅራቢያው ትምህርት ሊሰጥባቸው ይገባል።
ወላጆች፣ሰበካ ጉባኤያት፣ወጣቶች፣ማኅበራት፣ሰንበት ትምህርት ቤቶች፣ማኅበረ ካህናት፣ሰንበቴዎች..ዐይናችሁን ወደ አብነት መልሱ።
እየተደራጃችሁ መምህር መቅጠር ካለባችሁ ቅጠሩ፣መደጎም ካለባችሁ ደጉሙ።
በተለይም ሰበካ ጉባኤው የትምህርት ኬላዎን አበጅቶ በበቂ ሁኔታ መምህራንን መመደብ እና መከታተል አለበት።
🎤መምህር የማይመድብ ሰበካ ጉባኤ ካለ ምእመናን አጥብቃችሁ ጠይቁት።
የሰበካ ጉባኤ ዋነኛ ሥራው ይሄ ነው።ሕንጻ ግንባታዎ፣ልማቶች ከዚህ ባሻገር ናቸው።በምድር ላይ ሁሉም ከሰው በታች ነው። ሰው ግን ከሁሉም አመክንዮ በላይ ነው።
🎤ዘመኑን መዋጀት፣ቀድሞ መገኘት ማለት ትውልድ ላይ መሥራት ነው።
ኋለቀር ማለት የነገውን ትውልድ መርሳት ነው።
ስለዚህ በተተኪ ትውልድ ላይ እንሥራ ማለት መጻኢ ዘመኑን እንዋጅ ማለት ነው።
🎤የሰንበት ተማሪዎችም ከነጠላ ዘፈናዊ ዝማሬ ወጥተን ወደ መሠረታዊ የአብነት ትምህርት እና ትምህርተ ሃይማኖት ብናተኩር ጥሩ ነው።ሀምሳ ዝማሬ ከመላስ አንድ ውዳሴ ማርያም አጥንቶ መቅመስ ይሻላል።
🎤በተለይም በጦርነት ቀጠና ያሉ ሕጻናት ሦስት ዓመት ሙሉ ያለ ትምህርት በመባጀታቸው በነገው ማኅበረ ሰብእ መካከል ትልቅ ክፍተት ነው።
ስለዚህ የማያነብ፣የማይጽፍ፣የማይረዳ፣የማይጸልይ ትውልድ እንዳይኖር ጥልቅ እሳቤ ቅን ህሊና፣ትጋት ያለው ተግባር ይጠይቃል።
🎤የማያነብ፣የማይጽፍ፣የማያሰላ ትውልድ ያለበትን ክፍተት አስበችሁታል?
በዲጅታል ዓለም፣በ5G ትውልድ፣በAI ዘመን፣በበርችዋል ሥርዓት መካከል ፊደል ሳይቆጥሩ ሂሳብ ሳያሰሉ ተቀምጠው እንዴት ነው ራሳቸውን መምራት እና ዘመኑን መዋጀት የሚችሉት?
🎤ቢያንስ በየገጠሩ ሁሉ ሰላም መጥቶ የትምህርት ዕድሉ እስኪገኝ ድረስ በአብነት ትምህርት ቤት ከየኔታዎቻች ተምረው ማንበብ፣ መጻፍን፣ቁጥር ማስላት መለማመድ አለባቸው።
🎤በሥሁት ትርክት የተጠለፉት ግን ከትናንት እስከ ዛሬ የሀገር እና የቤተ ክርስቲያን መልካም እና ርቱዕ የሆኑ ሀብተ-ትምህርቶችን አይፈልጓቸውም።
አለዚያም በጣሊያን ወለድ ድረታ የደብተራ ዕውቀት እያሉ ያጣጥሏቸዋል።ደብተራ የትምህርት ሚንስተር ሁኖ የሠራት፣ የጠበቃት፣ ያቆያትን ሀገር መሆኗን ስለዘነጉት "ድንቡልቡል መሀይምነታቸው"ሊገልጹብን ይሞክራሉ።
🎤በዚህ መንገድ "ዘመናዊ ፊት ኋላ ቀር ልቦች"በማያባራ ትርክትና ትችት እየነዘነዙ ሀገር በቀል ዕውቀቶችን ያናንቋቸዋል ያጠፏቸዋል።
🎤እውነተኛውን መንገድ ከሚያመክኑባቸው ነገሮች አንዱ ትውልዱን ያለ ዕረፍት በሰላም እጦች፣በድረታ ትርክት፣በሥሁት ሥርዓት፣ በመነዝነዝ ማሰላቸት ማፍዘዝ እና ራስ ጠል አድርጎ ከርቱዕ ሀገር በቀል እሳቤው ጋራ ማጣላት ነው።
🎤ከመሠረቱ፣ከጥንቱ፣ከአብነቱ እየለዩ የትውልዱን ህሊናቸውን ብኩን ተግባሩን ትኑን ብኑን ማድረግ ተገቢ አይደለም አልነበረም።በጭፍን ግልበጣ የተዋስነው ያደረሰብንን የማያውቅ የለም ማለት ይቻላል። "ጥንቱን የተውሶ ያውም ጠፋ ተጨርሶ"እንዲሉ።
🎤የባከነ ህሊና እና የተነነ ተግባር ሀገር የለውም፣ሃይማኖት የለውም፣ሥርዓት የለውም፣ሞራል የለውም፣ሰብአዊነት የለውም፣ኪዳን የለውም፣ባህል የለውም፣ ወግ መዕረግ የለውም፣መረጋጋት የለውም፣ዕውቀት የለውም፣ተተኪ ትውልድ የለውም..።
🎤በድርት ስሁት ሀሳባቸው እና ዕቅዳቸው ወደ ጥንተ መሠረታችን እንዳናይ፣ከትምህርት ከመሠረት እንድንፋታ የሚፈልጉ በለ ጊዜዎች በሚያመጡት የመከራ ዜና ጧት መነዝነዝ፣ማታም መነዝነዝ፣ነገም መነዝነዝ፣በቃ ነገር እየፈለጉ መነዝነዝ ዕረፍት ማሳጣት ማባከን ማዋከብ ከተጀመረ ዓመታት ተቆጥረዋል።
🎤ስለሆነም በችግር ዘመን ያልሠራነውን ትውልድ በሰላም ዘመን ትክክለኛ ሰው ሁኖ አናገኘውም።
🎤መፍትሄው ከጥፋት በላይ የሆነ፣መሠረተ-ዕውቀት ያለው፣ ራስ በቅ የሆነ፣ሁሉን መመዘን የሚችል፣ በራሱ የማያፍር፣አዲስ ተቸኪ ትውልድ በአብነት ትምህርት በሀገር በቀል ዕውቀት መቅረጽ ነው።
🎤ከመሠረቱ የተፋታ ትውልድ ግን ጽኑዕ ሃይማኖት፣ የተረጋጋ ሀሳብ፣ሀገር በቀል ዕቀት፣መልካም ሰብእና፣ትሁት እና ጠቢብ ሰውነት..አይኖረውም።
🎤ሀገር በቀል ዕውቀት የሌለው ሰው ልቡን የተበላ ሰው ነው።ማሰቢያ ልቡን የተበላ ትውልድ ደግሞ መዳረሻው ጉጻጉጽ ነው።መስተሀልይ ህሊናውን ከአብነት አፋትቶ አንተ እለቅ እኔ ላጥልቅ፣አንተ ጥፋ እኔ ላናፋ የሚል ሰው መዳረሻው ወና ነው።
🎤ተተኪውን ትውልድ ከመሠረቱ እያነጹ መተካት እና ማውጣት ካልተቻለ፦ዛሬ በትቂቱም ቢሆን ጽኑዕ ሃይማኖት፣ መልካም ሰብእና፣ቋሚ ጠቃሚ ሀሳብ፣ቅን ህሊና ያላቸው ሰዎችም ከንዝነዛው ብዛት የተነሣ መሰላቸት መፋዘዝ መደንዘዝ ያገኛቸዋልና መንገድ የሚያሳይ ጠፍቶ ጨርሶ መናድ መውደም ሊመጣ ይችላል።
🎤በሥሁት እሳቤ ከሚፈልቀው ንዝናዜ ብዛት የተነሳ አብነት የሚሆነውን አባት እና የህሊና ዕረፍት ያጣ ምእመን ደግሞ ከአስጨኛቂ ጫጫታዎች ሁሉ ለመራቅ ሲል የሚያደርገው የስደት ሽሽት፣የማስመሰል ኑሮ፣የህሊና መታወክ፣ሀገርንም ቤተ ክርስቲያንንም ይጎዳታል።
🎤የአንዱ ዳፋ ሌላውንም ያዳፋልና የአንዱ ንዝነዛ ወደ ሁሉም ምእመናን ይጋባና አዚም በሚመስል መልኩ ብዙዎቻች ንዝነዛው ሰልችቶን ከርቱዓዊ መንገዱ እንዳንወጣ ወሳኙ ጠጋኙ አብነት ትምህርት ነው።
🎤ሚልዮን ብራናዎች፣የተራቀቁ ቅኔዎች፣የለዘቡ ዜማዎች፣የተቀደሱ ባህሎች፣ተሻገሪ ቀመሮች፣ምሥክር የሚሆኑን ውቅሮች፣የርቱዓዊነት መገለጫዎች፣ትናንታዊ ታሪኮች፣ሀገር በቀል ፍልስፍናዎች፣ጣዕም ያላቸው የአባቶች ጫወታዎች፣...የአብነት ፍሬዎች ናቸው።
🎤አብነት ትምህርታችን የትናንት ማያ፣
የነገ ማስያ፣ የዛሬም መዋያ ነው።በራሳችን ዐይን ወደ ኋላ ማየት እና ለነገም መተንበይ የሚቻለው
በአብነት መረዳት ውስጥ ተሁኖ ነው።
🎤ስለሆነም ሁሉም ሕጻናት እና ጊዜ ያለን ወጣቶች በሙሉ ክረምቱን በአብነት ማሳለፍ መቻል አለብን።
ያልሰማ እንዳይኖር በየአካባቢያችን እንቀስቅስ።
🎤(ክረምቱን በአብነት)🎤

02/07/2025

ልክ አይደለም!
ወንድሜ ቢከፋህም ስማኝማ!
1. የመቶ ዓመት ፕሮጀክት ቀርጾ ሊያጠፋህ የቆመ እልፍ የዐምሓራ ጠላት ተሰልፎ እነርሱን ትተህ ቀኑን ሙሉ አንዱን ታጋይ ከሌላው ታጋይ ስታበላልጥ፣ ስታንጓጥጥ፣ ስታጎጥጥ(ጎጥ ስትመድብ) ከዋልህ አንተ ትግልና ተጋድሏችን ምንም አልገባህም
2. በሚሊዮን የሚቆጠር የተፈናቀለ እየተራበ ያለ ዐምሓራ እያለ የሚድያ ላይ አሸሸ ገዳሜ ገብተህ በቲክቶክ ሙዚቃ ከፍተህ እየጨፈርህ እታገላለሁ የምትል ከሆነ አንተ ለትግሉ ጉልበት ሳትሆን እንቅፋት ነህ።
3. የሚገድሉህ የሚያንቋሽሹህ እልፍ የሳይቨር ሚድያ በብልጽግናና በአጋሮቹ ተቀጥረውና ተቀጣጥረው ድምጥማጥህን ሊያጠፉት ሌት ተቀን ሲሠሩ አንተ የዐምሓራ ወንድሞችህን ጎንደርና ጎጃም ወሎና ሽዋ እያልህ ውኃ በወንፊት ስትዘግን የምትውል ድኩም ከሆንህ አንተ የትግሉ በሽታ ደዌ ነህ።
4. ስለ ኦሮሙማ፣ ስለ ሕወሓት ስለ ወሃብያ ስለ ውጭ ሰርጎገብነት ስለ ሃይማኖታዊና ተቋማዊ የዐምሓራ መጠቃት ምንም ብለህ የማታውቅ፣ ወይም ምንም ደግሞ የማታውቅ፣ ጠላቶችህ እነማን እንደሆኑ እንኳ ለይተህ የማትረዳ፣ ራስህን ለራስህ ጠላት ያደረግህ፣ የራስህን አካል በራስህ ጥፍር እየፎከትህ የምታደማ አንተ ከጠላት በላይ የዐምሓራ ሕዝብ ጠላት ነህ።
5. አንድነት ሊመጣ ነው ሠራዊቱ ሊዋሃድ ነው፤ አመራር ሊመረጥ ነው ሲባል እገሌን አትመኑት የዚህ አካባቢ ልጆች ስልጣኑን በሙሉ ሊወስዱት ነው እያልህ የጥርጣሬን እሾህ የምትተክልና የህልውና ትግሉን የስልጣን አባዜ አድርገህ የምትመለከት አንተ ደማችንን የማታፈስ የጠላት ሰይፍ ነህ።
6. ሁለት ገጽ እንኳ አንብቦ መዝለቅ የማትችል የፖለቲካ ሴራንና ኪሳራን በትክክል ያልተገነዘብህ ዲፕሎማሲና ዲሞክራሲ ድርድርና ንግግር ምን እንደሆነ በቅጡ ያልተገነዘብህ ሆነህ ሳለህ የፖለቲካ ተንታኝና አሳማኝ ሆነህ የቆምህ አንተ የኦነግ እኩያ የህወሓት አምሳያ ነህ።
7. የሚሠሩትን የምታሰንፍ፣ የተሠራውን የምትነቅፍ ሰማይ ቅርቡ አያ ቁጭ እንበል አንተ የመኖርን ህልም የትግልን ድካም የምታመክን የዐምሓራ ሕዝብና ትግል ቁራኛ ነህ
8. የሁሉም ዐምሓራ መጎዳት መጠቃት መመታት መሞት እንቅልፍ የማይነሳህ አንድ ሰዓት ቲክቶክ ላይ አቅራርተህ ፎክረህ ተሰዳድበህ ሌሊቱን ሙሉ ዲስኮ ገብተህ ውስኪ እየተራጨህ አካለ ዘማ እየዳበስህ የምታደር አንተ ታላቅ ሐሳዊ መሲህና የሕዝብ ባላንጣ ነህ።
9. ሚድያ ላይ አውራ ስለተባልህ ሁሉንም የማደርግ የሚመስልህ አማራጭ ይዘህ የማትቆም ለአነጋገርህ ለከት፣ ለሐሳብህ ብስለት፣ ለአቋምህ ጽናት የሌለህ ያገኘኸውን ተናግረኽ የምትጮኸውን ጩኸህ አካባቢውን የምትረብሽ በጥባጭ ከአርባ ጉጉ አራጄ ከወለጋ ጨፋጫፊየ ለይቼ የማላይህ ባላንጣየ ነህ።
10. ሸፍጠኛና ሸረኛ፣ አማሳኝና አስመሳይ ታጋይ መሳይ ቀበሮዎች በበግ ለምድ ተጠቅልለው ሲመጡ ቆዳቸው ተገፎ ተኩላነታቸው በግልጽ ተሸክፎ ተኩላ ናቸው ሲባል ዐይኔን ግንባር ያድርገው ተኩላዎች አይደሉም በግ ናቸውና አብረውን ይሰማሩ ብለህ ለሚበሉህና ለሚያስበሉህ ጥብቅና ቁመህ ተከላካይ እረኛህን የምትወጋ አንተ ሆይ አንተ ገና በግና ተኩላ ያልለየህ ራስህም አዳኝ እረኛ እሚያስፈልግህ በግ ነህና እባክህ በግ ሆነህ እንደ እረኛ ላስብ ልምራ አትበል።
አባክህ አትቀየመኝ ግን ስማኝ። የያዝነው የህልውና ትግል እንጂ የልጆች እቃቃ ጨዋታ አይደለም! እሯ!!!
Banteamlak Ayalew Abate

27/06/2025

እውነተኛ አማራ ጠይቅ! ምን አየሆነ ነው?
# ፋኖ ወደ ማጥቃት በሚሸጋገርበት ወሳኝ የክረምት ወቅት ለምን በአፋብኃ ስም አንዱን ጥሎ ሌለውን አንጠልጥሎ የሚመስል አወዛጋቢ መግለጫ በFB አወጡ?
👉 ይህ አወዛጋቢና ከፋፋይ መግለጫ ለፋኖና ህዝባችን ነው ወይስ ለጠለት ነው ግብዓት እየሆነ ያለው?
👉እስከ ቋራ ድረስ የተኬደው ለእውነተኛ ድርጅት ምስረታና የጋራ አለማ ከሆነ አሁን ምን የተለየ ነገር ተፈጥሮ ነው በተናጠል ለመግለጫ የጣደፉት?
👉 አንድ የፋኖን ትግል እመራለሁ የሚል አካል በFB ገፅ ላይ አወዛጋቢ ነገር በመለጠፍ ህዝብን ማደናገር ለምን ተፈለገ?
👉ይህን አወዛጋቢ መግለጫ በFB የለጠፈ አካላት ካመኑበት ለምን በሚድያ ቀርበው ጉዳዩን ማስረዳት ከበዳቸው? ነው ወይስ ይህ መግለጫ የወጣው በጠምዛዥ አካለት ግፊት ነው?
👉እነዚህ አካለት እንዲህ አይነት መግለጫ ሲያወጡ እንደ አማራ በማሰብና እንደ አማራ ለመታገል ነው ወይስ እንደቀጠና አስበው ነው?
👉ይህን አወዛጋቢ መግለጫ የተወሰኑ ሚድያዎች ተሽቀዳድመው አራገቡት?
...ወዘተ...

ይደረስ ለአርበኛ ዋርካው ምሬ ወዳጆ!"ከዚህ በላይ ምን እንሁን"እንዴት ዘነጋሀው የነገርከን ያ ቃል ኪዳን የገባሀልን መሀላ የገደብን ደም ልትመልስ የንፁሀንን ጭፍጨፋ፣ከምኔውስ ተረሳህ ትልቁ ...
26/06/2025

ይደረስ ለአርበኛ ዋርካው ምሬ ወዳጆ!
"ከዚህ በላይ ምን እንሁን"

እንዴት ዘነጋሀው የነገርከን ያ ቃል ኪዳን የገባሀልን መሀላ የገደብን ደም ልትመልስ የንፁሀንን ጭፍጨፋ፣ከምኔውስ ተረሳህ ትልቁ ሰው በሸለቆ አሸዋ ለብሶ ድንጋ አንጥፎ ህመሙም ህመም አድርጎ ወራትን ሳይሰለች ሌትና ቀን የጠበቀህ ታግሶ፣ይዘነጋል እንዴ ወዳጀ ያንጠፈጠፍነው ነጭ ላብ የተነከረው ልብሳችን ፣በሀሩር ተጠብሶ የነደደው ገላችን።

ወገንህን ዘነጋህ፣ በሞቴ ብሎ ያጎረሰህ ፣ሰራዊቱንም ዘነጋህ ጌታየ ብሎ የጠበቀህ ፣እውነት ጎጃም ንፉግ ነው? እውነት ጎጃም ከሀዲ፣ቃላችንን በጠበቅን ከፊት ቁመን ለተዋደቅን መልሱ ይህነው ልጠይቅህ የዚያ ሁሉ መንከራተት?

ዙሪያው ገባው ሞሽሮ አሳምሮ እንዳልያዘህ፣መረገጫህን ጠብቆ ሸሽጎ አቅፎ እንዳልያዘህ ፣እውነቱን አስታውስ አለቃ ጎጃምን ነው የዘነጋህ፣ከህመማችን ሳናገግም ስብራቱ ሳይለቀን ፣ቂያችን ሳንመለስ ከደጃጅን ሳንደረስ ምነው እረሳህን ወንድማለም ማስታዋሻው ታወረህ ፣ዋርካ ነህ ብለን ከቀትሩ እሳት ተጠልለን ፣ስናርፍብህ ደረቁ ቅጠሎችህ አሳልፈህ ሰጠህን ፣ፈጀን ቋያው ልባችንን ፣መካድ እዳ ነው ወንድም ሰው፣ ደርሶብህ እንዳትቀምሰው።

የቧጠጥነው ተራራ የወረድነው ቁልቁለት ያንሸራተተን ሸለቆ የወረወረን አርቆ ፣ያስ መከራ ተረሳህ በሶማ ያሳለፍነው፣የበላይ እመነት ጀግንነት ወኔው ያልጠፋበት ምድር ነው።

ሶም በረሀ ከመሀል ላይ ያሰርነው ውድም ቃል ነው፣ ይብላኝ ለአንተ ግዴለም ጎጀምስ ሁሌም የበላይ ነው።

ከማንስ ጋር መከርክ ከማንስጋር ተነጋገርክ ዝናቡ ሳይወርድ ከሰማይ ዘመኑ ሳይቀየር፣ ከምኔውስ አስረሳህ፣ ወንድሞችህን አስተዋሽ እንዴት አንድ ሰው አጣህ ፣ጣራ የሌለው ግርግዳ ፣ምሰሶ የሌለው ቤት ናፍቆህ ጎጃምን ያክል ሀገር ጎጃምን ያክል ብርቱ ህዝብ ከአይነ ህሊናህ ጠፋብህ?

በዛ በረሀ ከኋላህ ሳይሆን ከፊትህ በእጅ ስልኩ አነጣጥሮ ምስልህን ያስቀረልህ ድካምህን በቀይ ቀለም አድምቆ ተዳፍኖ እንዳይቀር ታሪክህ በአደባይ የዘከረህ ከህመሙ ሳያገግም ጠየቀህ። መልሱን ለህዝቤ አደራ ይህም አይዘንጋህ።

ወዳጅህ ፋኖ ባየ ደስታ።

ታላቅ የማህበራዊ ሚዲያ ዘመቻ Social media Campaign on X (Twitter)ቅዳሜ እና እሁድ በኢትዮጲያ ሰዓት አቆጣጠር ከምሽት 2:00-5:00 Saturday June 14th and...
13/06/2025

ታላቅ የማህበራዊ ሚዲያ ዘመቻ
Social media Campaign on X (Twitter)
ቅዳሜ እና እሁድ በኢትዮጲያ ሰዓት አቆጣጠር ከምሽት 2:00-5:00
Saturday June 14th and 15th 1:00 PM - 4:00 PM EST

አዘጋጅ፦ የአማራ ሚዲያ ካውንስል

ዶ/ር Arega Abate  እዚህ ሰፈር ብዙ ጊዜ በቤተክርስቲያን ጉዳይ የሚጽፉ ሰው ናቸው።አሁን ከ1 ሰዓት በፊት ግን ይኼንን ከትበዋል 👇👇👇*******************************...
08/06/2025

ዶ/ር Arega Abate እዚህ ሰፈር ብዙ ጊዜ
በቤተክርስቲያን ጉዳይ የሚጽፉ ሰው ናቸው።
አሁን ከ1 ሰዓት በፊት ግን ይኼንን ከትበዋል 👇👇👇
**********************************

አሁን ደግሞ የብልጽግና አጭበርባሪዎችን ሐሰትና ዳብል ስታንዳርድነት እናጋልጣለን፡፡

ከጧት ጀምረው 'ለአማራ እታገላለሁ የሚለው ዘመነ እንዴት የአማራ ችግር ጠንሳሽ የሆነው ስብሐት ነጋ በተገኘበት መድረክ ተገኝቶ ዐሳብ ይሰጣል? ስለሆነም ወያኔ ነው፣ የአማራ ጠላት ነው፡' የሚል የዘንዘሪጡን የአይጥና ድመት ተረት የመሰለ ነገር እየደረቱ መሆኑን እያየን ነው፡፡

ቀጣፊዎች በሏቸው፡፡ ይኸንን የሚሉት እኮ በተደጋጋሚ በድሮን ለመግደል ሲያሳድደው ከነበረ፣ ከ15 በላይ ጠባቂዎችን በአንድ ቀን በድሮን ከጨፈጨፈበት ከጌታቸው ረዳ ጋር ተስማምቶ መሥራቱን እንደ ከፍተኛ ጽድቅ የሚቆጥሩለትን ድንኩን ዐቢይ አህመድን የሚደግፉ ናቸው፡፡ ዐቢይ አህመድን ከመቀሌ እስከ ደብረ ብርሃን ሲያሯሩጡት ከነበሩት፣ ከጌታቸው ረዳ ጋር፣ ከታደሰ ወረደ ጋር ተስማምቶ እየሠራ ያለን ግለሰብና ፓርቲ ደግፈህ የአይጥና ድመት ተረት ብትተርት ቱሪናፋ መሆንህን ከማሳየት ያለፈ ሚና የለህም፡፡

በሌላ በኩል ካየነው፣ ላለፉት ሰባት ዐመታት የአማራን ሕዝብ ሲጨፈጭፍ ከነበረው እና ዘመነን ለመግደል በየቀኑ ድሮን ከሚልከው ዐቢይ ጋር ተስማምቶ ይሠራ ዘንድ የሚማጸኑ ሰዎች ናቸው ዘመነ ከጃዋርና ከአቦይ ጋር ቀርቦ ተናገረ ብለው የሚያጭበረብሩት፡፡

ሲጀምር ዘመነ የአቦይን በመርሐ ግብሩ ላይ መቅረብ አለመቅረብ ላያውቅ ይችላል፡፡ ሁለቱም በተለያየ ቦታና ጊዜ የተቀረጹቱ የድምጽ ወምስል ነው በዝግጅቱ ላይ የቀረበው፡፡ ሲቀጥል ዘመነ ሊመዘን የሚገባው ባስተላለፈው ጉዳይ እንጂ የተገኘውን አጋጣሚ ለሚመራው ትግል በመጠቀሙ አይደለም፡፡ የዘመነን መልእክት ጠላቱ የሚዘውረው ኢቲቪና ፋናም ቢያስተላልፉለት አልጠቀምም ካለ የፖለቲካ ሞኝ ነው ማለት ነው፡፡

ቁም ነገሩ በዚያ ንግግር ያስተላለፈው ነው፡፡ ተቃውሟቸው በዚያ ንግግር ዐቢይንና ስብስቡን ድንኮች መሆናቸውን አበጥሮ ስለነገራቸው በብስጭት ለማጣጣል የፈጠሩት ማምለጫ ነው፡፡

ስለሆነም ይኸን መሰሉን ዳብል ስታንዳርድ ድስኩር ለሚደሰኩርላችሁ ሰው 'አስቀድመህ የራስህን ተቃርኖና አለቃህን ተመልከት' በሉት፡፡

ወያኔን ሰይጣን አድርገው ለመሳል የሚሞክሩ ብልጽግናዎች ወያኔ ለ27 ዓመት ደክማ፣ አሠልጥና፣ አስተምራ ከራሷም የከፉ አረመኔዎች አድርጋ በፈጠራቻቸው በአረመኔነት ላይ አረመኔነትን እየጨመሩ በሚሄዱት በድንኩ ዐቢይ ዙሪያ በተኮለኮሉ ጨካኞች እየተመሩ መሆናቸው ነው፡፡

ሐቅ በተዛነፈበት ሁሉ እውነትን እንገልጣለን፡፡

ይኸው፡፡

01/05/2025
03/04/2025

Check out MF-ሽፎን’s video.

ማንም አምሓራ ነኝ የሚል ቢኖር https://www.youtube.com/watch?v=JTrrPVHBDt8 ትንታኔና በዚህ ሚዲያ የሚቀርቡ ትንታኔዎችን ማስታዎሻ እየያዘ ይከታተል።
26/02/2025

ማንም አምሓራ ነኝ የሚል ቢኖር
https://www.youtube.com/watch?v=JTrrPVHBDt8
ትንታኔና በዚህ ሚዲያ የሚቀርቡ ትንታኔዎችን ማስታዎሻ እየያዘ ይከታተል።

ለኤቢሲ ቴሌቪዥን የጥቆማ መረጃዎችን ለማድረስ በኤቢሲ የTelegram እና WhatsApp ስልክ ቁጥር +17203093725 ያድርሱን። የኤቢሲ ቴቪ መረጃዎችን በአማራጭ ይከታተሉ:-1) You tube - ➻ የኤቢሲ እለታዊ የዜና ዘ....

Address


Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when EthioCyber Group posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

  • Address
  • Alerts
  • Claim ownership or report listing
  • Want your business to be the top-listed Media Company?

Share