On-Time

On-Time On-Time is a website based news platform and it is intended to deliver its news in Amharic.

ኩሌ (Khuullee) በርካቶችን እያከራከር የሚገኘው አዲሱ የአፋን ኦሮሞ ፊደላትለረጅም አመታት በአገልግሎት ላይ ያለውን የአፋን ኦሮሞ የላቲን ፊደላትን ለመተካት “ኩሌ” በሚል ስያሜ የተዘጋ...
03/02/2024

ኩሌ (Khuullee) በርካቶችን እያከራከር የሚገኘው አዲሱ የአፋን ኦሮሞ ፊደላት

ለረጅም አመታት በአገልግሎት ላይ ያለውን የአፋን ኦሮሞ የላቲን ፊደላትን ለመተካት “ኩሌ” በሚል ስያሜ የተዘጋጀው አዲሱ ፊደላት ሰሞኑን መነጋገሪያ ሆኖ ቆይቷል።

ይህ “ኩሌ” የተባለው የአፋን ኦሮሞ ፊደላት የተዘጋጀው ከ19 አመታት በፊት ሲሆን እስከ አሁን ከአስር በላይ መጽሓፍት በፊደላቱ ተጽፈው ታትመዋል። የዚህ ፊደላት ቀራጺ የሆኑት ማስተር ሃሰን አብዱልቃዴ አዪሞ ከ5000 በላይ ተማሪዎችም በዚህ አዲሱ ፊደላት መማራቸውን እና የላቲን ፊደላት ያሉትን እጥረቶች የሚፈታ መሆኑን ለአዲስ ስታንዳርድ ገልጸዋል። በአዲሱ ፊደላት በሀረርጌ፣ ባሌ፣ ቦረና እና አርሲ የማሰተማር ተግባር ሲከወንበት መቆየቱንም አክለው ገልጸዋል።

የፊደላቱ አዘጋጅ የሆኑት ማሰተር ሀሳን አልዱላቃድር “ ፊደላቱ የተቀረጹት ከአረብ ውይም ከቻይና ፊደላት ሳይሆን ከኦሮሞ ባህላዊ እና ፍልስፍና እሴቶች የተቀዳ ነው” ሲሉ ገልጸዋል።

ነባሩን የላቲን ፊደላትን ለመተካት ታስቦ የተዘጋጀው ይህ አዲስ ፊደላት (ኩሌ)፣ በአገልግሎት ላይ ያለው የአፋን ኦሮሞ ፊደላት ላይ የሚስተዋለውን ችግሮች ለማሻሻል ያለመ መሆኑን የገለጹት ማስተር ሀሰን “በአገልግሎት ላይ ያለው የላቲን ፊደላት ችግሮች አሉት፤ ኩሌን የቀረጽኩትም በዚሁ ምክንያት ነው” ብለዋል።

ይህ አዲስ ፊደላት ከሚቀረፉት ችግሮች ውስጥ አንዱ በአፋን ኦሮሞ ውስጥ ያለው ድርብ ፊደላት ሲጥብቁ እና ሲላሉ የሚሰጡትን የተለያየ ትርጉም መለየት የማያስችሉ በመሆኑ ኩሌ ይህን ችግር ይፈታል ሲሉ ገልጸዋል።

ከዚህ በተጨማሪም አዲስ ፊደላት ብስርዓተ ነጥብ አጠቃቀም ላይ የሚፈታችው ችግር መኖሩን እና የአፋን ኦሮሞን ቃላት ርዝማኔን ማሳጠር መቻሉን አክለው ተናግረዋል።

ቀራጺው በፊደላቱ ጋዜጣን ጨምሮ በርካታ ጽሁፎች መታተማቸውን እና አሁንም ይህ አዲስ ፊደላት በጥናት ላይ መሆኑን ነው ያሰረዱት።

“በዚህ ጉዳይ ላይ ምክክር ለማደረግ ከድሬ ደዋ እና ሀረመያ ዩኒቨርሲቶዎች ጋር ስምምነት አለን። በምምክር መድረኩ ከ 18 ዩኒቨርሲቲዎች መሁራንን አንድ ላይ በማምጣት ለመምከር ታቀዷል። በተጨማሪም አራት ሰዎች በጉዳዩ ላይ ጥናት እንዲያደርጉ ተመርጠዋል” ብለዋል።

ጥናት እንዲያቀርቡ ከተመረጡት ሰዎች መካከል አንዱ በወለጋ ዩኒቨርሲቲ የአፋን ኦሮሞ ረዳት ፕሮፌሰር የሆኑት ፌደሳ ታደሰ ሲሆኑ በዩኒቨርሲቲው ጥናታዊ ጽሁፍም አቀረበዋል።

በአዲሱ ፊደላት ላይ ጥናታዊ ጽሑፋቸውን ያቀረቡት ረዳት ፕሮፌሰር ፌደሳ ታደሰ፤ ኩሌ ፊደላት ዝግጅት በጣም በሳል ሆኖ ስላገኘሁት ፊደላቱን መርጬ ጥናት አድርጊያለው ሲሉ ገልጸዋል። ጥናቱን መጨረሳቸውን የገለጹት ረዳት ፕሮፌሰሩ ምሁራን ሊወያዩበት ይችላሉም ብለዋል።

ይሁን እንጂ ይህን አዲሱን ፊደላት የተቹ ምሁራንም ቀላል አይደሉም። የአፍሪካ ቋንቋዎች ድርጅት የቦርድ ሰብሳቢ የሆኑት ፕሮፌሰር ቶሎሳ ሶሬሳ “ “ለአፋን ኦሮሞ አዲስ ፊደላት መቅረጽ አስፈላጊ አይደለም። አፋን ኦሮሞ ከድርብ ፊደላት ጋር ተያይዞ ችግር የለውም። ኢንግለዝኛን ጨምሮ በርካታ ቋንቋዎች የራሳቸው ችግሮች አሏቸው። አፋን ኦሮሞ ውስጥ እጥረት ካለ የሚሻለው ለችግሮቹ መፍትሄ እየፈለጉ መሄድ እንጂ አዲስ ፊደላት መቅረጽ ምላሽ አይሆንም” ብለዋል።

በተጨማሪም የአይቲ በለሙያ የሆነው አብዲስ ባንቻ አዲሱን ፊደላት ከተቹ ሰዎች መካከል ሌላኛው ግለሰብ ነው። አብዲሳ ኩሌ በቋንቋው እድገት ላይ ተጽዕኖ እንዳለው አስታየቱን ገልጿል።

ነገር ግን የኩሌ ቀራጺ ማስተር ሀሰን በተነሳው ነቀፌታ ላይ “ የሚነቅፉ ሰዎች ለአፋን ኦሮሞ ካላቸው ተቆርቋሪነ

ብሄራዊ ባይቶ ዓባይ ትግራይ ባይቶና የሀገር አቀፍ ፖለቲካ ፓርቲ ሁኖ በምርጫ ቦርድ ተመዘገበብሔራዊ ባይቶ ዓባይ ትግራይ ባይቶና ሀገር አቀፍ የፖለቲካ ፓርቲ ሁኖ መመዝገቡ ያስታወቀው የኢትዮጵ...
31/01/2024

ብሄራዊ ባይቶ ዓባይ ትግራይ ባይቶና የሀገር አቀፍ ፖለቲካ ፓርቲ ሁኖ በምርጫ ቦርድ ተመዘገበ

ብሔራዊ ባይቶ ዓባይ ትግራይ ባይቶና ሀገር አቀፍ የፖለቲካ ፓርቲ ሁኖ መመዝገቡ ያስታወቀው የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ ነው።

ብሔራዊ ባይቶ ዓባይ ትግራይ ባይቶና በትግራይ ካሉ ፖለቲካ ፓርቲዎች ሕጋዊ ሆጋዊ ሆኖ የተመዘገበ የመጀመረያ ፓርቲ ነው።

የዓለም ምግብ ድርጅት WFP በትግራይ ከ13 ወራት ቦኋላ ለተፈናቃዮች እርዳታ መስጠት ቢጀምርም በሁለተኛው ቀኑ ሙሉበሙሉ እርዳታ መስጠት ኣቆመ።ይህ የሆነው የነቀዘ ፣ የተበላሸና መጥፎ ጠረን ...
31/01/2024

የዓለም ምግብ ድርጅት WFP በትግራይ ከ13 ወራት ቦኋላ ለተፈናቃዮች እርዳታ መስጠት ቢጀምርም በሁለተኛው ቀኑ ሙሉበሙሉ እርዳታ መስጠት ኣቆመ።
ይህ የሆነው የነቀዘ ፣ የተበላሸና መጥፎ ጠረን ያለው የአርዳታ ዱቄት መስጠት በመጀመሩ መንግስት ደብዳቤና ማስጥነቀቅያ በመፃፉ ምክንያት ነው።

ላለፉት 13 ወራት ሰብአዊ እርዳታ ባለማግኘታቸው በከባድ ችግር ውስጥ የሚገኙ ተፈናቃዮቹ ከረጅም ጊዚያት በኃላ ትናንት የተጀመረው ዱቄት ጥራት የሌለው ፣ የተበላሽ ፣ የነቀዘና መጥፎ ጥረን ያለው በመሆኑ ተቋርጧል መባሉ እንደሳዘናቸው ተናግረዋል።

ጌታ በህልሜ ነግሮኛል በሚል ሚሊዮን ዶላሮችን ያጭበረበረው ሰባኪ ታሰረበአሜሪካ ኮሎራዶ ግዛት በሚገኝ የእምነት ተቋም የሚያገለግለው ኤሊ ሪጋላዶ፥ ጌታ የምናባዊ ገንዘብ ወይም ክሪፕቶ ከረንሲ ...
31/01/2024

ጌታ በህልሜ ነግሮኛል በሚል ሚሊዮን ዶላሮችን ያጭበረበረው ሰባኪ ታሰረ

በአሜሪካ ኮሎራዶ ግዛት በሚገኝ የእምነት ተቋም የሚያገለግለው ኤሊ ሪጋላዶ፥ ጌታ የምናባዊ ገንዘብ ወይም ክሪፕቶ ከረንሲ ድርጅት እንድናቋቁም ነግሮኛል በሚል አማኞችን ለማሳመን ሞክሯል።

የሰባኪያቸውን ህልም ያመኑት ተከታዮቹም በየጊዜው ገንዘባቸውን ሰባኪው ወደከፈተው ድርጅት ሂሳብ ቁጥር ሲያስገቡ መቆየታቸውን የአሜሪካ የደህንነት ተቋም ደርሶበታል።

ሪጋላዶ “ለምን ከተከታዮችህ አጭበርብረህ ገንዘብ ተቀበልክ?” በሚል ለቀረበለት ጥያቄ፥ “ምናልባት የጌታን መልዕክት በህልም መልክ ስረዳ አሳስቼ ተርጉሜው ሊሆን ይችላል” ሲል ምላሽ ሰጥቷል፡፡

የአገሪቱ ገዢ ፓርቲ ብልጽግና ምክትል ፕሬዝዳንት የሆኑት፤ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንንን ከፓርቲ ኃላፊነታቸው መሰናበታቸው ተገለጸ።የፓርቲው ማዕከላዊ ኮሚ...
26/01/2024

የአገሪቱ ገዢ ፓርቲ ብልጽግና ምክትል ፕሬዝዳንት የሆኑት፤ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንንን ከፓርቲ ኃላፊነታቸው መሰናበታቸው ተገለጸ።

የፓርቲው ማዕከላዊ ኮሚቴ እንዳለው “የአመራር የመተካካት መርኅን እና የአሠራር ሥርዓት በመከተል” አቶ ደመቀን በክብር መሸኘታቸውን ገልጿል።

አቶ ደመቀን በመተካትም የብሔራዊ መረጃ እና ደኅንነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር እና የፓርቲው ሥራ አስፈጻሚ አባል አቶ ተመስገን ጥሩነህ የብልጽግና ምክትል ፕሬዝዳንት ሆነው ተመርጠዋል።

አቶ ደመቀ ከፓርቲ አመራርነታቸው መሰናበት በአገሪቱን መንግሥት ውስጥ ይዘው ከሚገኙት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቦታን ሊለቁ እንደሚችሉ አመላካች ነው።

አቶ ደመቀ መኮንን ለረጅም ዓመታት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው ሲሰሩ ከቆዩ በኋላ ነበር አቶ ገዱ አንዳርጋቸውን በመተካት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትርነት ቦታን የያዙት።

በቀድሞው ኢህአዴግ እና በአሁኑ ብልጽግና ፓርቲው ውስጥ ቁልፍ ሥልጣንን ይዘው የቆዩት አቶ ደመቀ፤ ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በመቀጠል በፓርቲው ካሉት ሁለት ምክትል ፕሬዝዳንቶች መካከል አንዱ ነበሩ።

የብልጽግና ፓርቲ የመጀመሪያውን ጠቅላላ ጉባኤውን መጋቢት ወር 2014 ዓ.ም. ባካሄደበት ጊዜ፣ አቶ ደመቀ መኮንን ከፓርቲው የአመራርነት ቦታ የመልቀቅ ጥያቄ አቅርበው እንደነበር በወቅቱ መገለጹ ይታወሳል።

መቐለ የሚገኙ የምዕራብ ትግራይ ተፈናቃዮች ሰላማዊ ሰልፍ ኣካሄዱበመላ ትግራይ የሚገኙ ተፈናቃዮች ብሽረ፣ዓድዋ፣እክሱም፣ ዓብዪዓዲ እና ሸራሮ ላይ ከትናንት ወዲያ በ ጥር 13 2016 ትልቅ ሰል...
24/01/2024

መቐለ የሚገኙ የምዕራብ ትግራይ ተፈናቃዮች ሰላማዊ ሰልፍ ኣካሄዱ

በመላ ትግራይ የሚገኙ ተፈናቃዮች ብሽረ፣ዓድዋ፣እክሱም፣ ዓብዪዓዲ እና ሸራሮ ላይ ከትናንት ወዲያ በ ጥር 13 2016 ትልቅ ሰልፍ ያካሄዱ ሲሆን ዛሬ ደግሞ በመቐለ በሚገኙ የተፈናቃይ መጠልያዎች ተጠልለው የሚገኙ በመቶ ሽዊች የሚቆጠሩ ተፈናቃዮች ሰልፍ ኣካሂደዋል።

"ስቃያችን'ና ጭሆታችን ይሰማ፣ወደ ቤታችን መልሱን፣የምግባረ ሰናይ ተቋምዎች ግዴታችሁን ተወጡ፣ብርሃብ እያለቅን ነው እርዳታ ስጡን" በሰልፉ ላይ ከተሰሙ የተፈናቃይ ድምፆች ዋናዎቹ ናቸው።

አርብ ሊግ  በ  #ኢትዮጵያ እና  #ሶማሊያ ውጥረት ላይ ለመምከር አስቸኳይ ስብሰባ ሊያካሄድ ነውአርብ ሊግ በኢትዮጵያ እና በሶማሊያ መካከል በተፈጠረው ውጥረት ለመምከር ረቡ ጥር 8 2016 ...
15/01/2024

አርብ ሊግ በ #ኢትዮጵያ እና #ሶማሊያ ውጥረት ላይ ለመምከር አስቸኳይ ስብሰባ ሊያካሄድ ነው

አርብ ሊግ በኢትዮጵያ እና በሶማሊያ መካከል በተፈጠረው ውጥረት ለመምከር ረቡ ጥር 8 2016 በበይነመረብ የሚከናውን አስቸኳይ ስብሰባ ጠርቷል። የአረብ ሊግ ምክትል ዋና ጸሃፊ ሆሳም ዛኪ ስብሰባው በኢትዮጵያ እና ሶማሊ ላንድ መካከል "ህጋዊ ባልሆነ መንገድ" የተፈራረሙትን ስምምነት ዙሪያ እንደሚሆን ገልጸዋል።

ሁለቱ ሀገራት በአዲስ አበባ የተፈራረሙት የመግባቢያ ስምምነት ኢትዮጵያ በሰሜን ምዕራብ ሶማሊያ ቀይ ባህር አካባቢ ላይ እንድትቀሳቀስ የሚያስችል ስምምምነት ነው በለዋል።

ስብሰባውን አፍሪካዊቷ አገር ሞሮኮ ትመራዋለች የተባለ ሲሆን አስቸኳይ ስብሰባው በሶማሊያ ጥያቄ እና ከ22ቱ አባል አገራት በ12ቱ ድጋፍ የተጠራ ነው። ዛኪ የሶማሊያን አቋም ሙሉ በሙሉ እንደሚደግፉም ገልጸዋል። የሶማሊያ ጠቅላይ ሚኒስትር ሃምዛ አብዲ ባሬ የመግባቢያ ስምምነቱ “ትክክል” አለመሆኑን በመግለጽ ኢትዮጵያ በሶማሊያ ግዛት ጣልቃ አንዳትገባ አሳስበዋል።

ሁለቱ አገራት የተፈራረሙትን ስምምነት ግብጽን ጨመሮ በርካታ የአረብ ሊግ አባል አገራት በመቃወም የሶማሊያን ሊአላዊነት እንደሚደግፉ ገልጸዋል።

11/01/2024

በሶማሊያ የሚገኝ የቻይና ኢምባሲ፣ የሶማልያ ልአላዊነት እንደሚደግፍ ገለፀ።

የ  #ኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር የ  #ትግራይ ክልል ማእከላዊ ዞን የአምቡላንስ ሹፌር ማንነታቸው ባልቃወቁ ሰዎች በተተኮሰ ጥይት ህይወቱ ማለፉን ማህበሩ አስታወቀየኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማ...
11/01/2024

የ #ኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር የ #ትግራይ ክልል ማእከላዊ ዞን የአምቡላንስ ሹፌር ማንነታቸው ባልቃወቁ ሰዎች በተተኮሰ ጥይት ህይወቱ ማለፉን ማህበሩ አስታወቀ

የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር የትግራይ ክልል ማእከላዊ ዞን ‘የእምባስነይቲ ቅርንጫፍ’ የአምቡላንስ ሹፌር የሆኑ አቶ ወልዱ አረጋዊ በርሀ የወላድ እናትን ህይዎት ለማዳን እያሽከረከረ ባለበት ወቅት ማንነታቸው ባልቃወቁ ሰዎች በተተኮሰ ጥይት ህይወቱ ማለፉን ማህበሩ አስታወቀ።

ባለትዳርና የስድስት ልጆች አባት የነበሩት አቶ ወልዱ ተገደሉት ትላንት ጥር 1/ 2016 ዓ/ም ከሌሊቱ 5፡20 አከባቢ ምጥ ላይ የነበረችን እናት ሊያመጣ ወደ ‘ዓዲ ሄደም’ የተባለ ቀበሌ የሕክምና ባለሙያ ይዞ በመጓዝ ላይ እያለ ቀበሌው አከባቢ ሲደርስ ማንነታቸው ባልታወቁ ሰዎች በተተኮስ ጥይት መሆኑ ተገልጿል። የቀይ መስቀል መርህ እና ህግን ተከትለው በታማኝነት በማገልገል ላይ ሳሉ በአሰቃቂ ሁኔታ ህይወታቸው ሊያልፍ ችሏል ሲል ማሀበሩ የተሰማውን ሀዘን ገልጿል።

በኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር ሰራተኞችና አምቡላንሶች እንዲሁም ንብረቶች ላይ በተደጋጋሚ እየደረሰ ያለዉ ጥቃት ተቀባይነት የሌለዉ ብቻ ሳይሆን የኢትዮጵያ መንግስት የፈረመዉን ዓለም አቀፍ የጄኔቫ ስምምነት ህግ የሚጥስ በመሆኑ ማንኛዉም አካል የማህበሩን ሰራተኞችና ንብረቶች የጥቃት ኢላማ ከማድረግ እንዲቆጠቡ አሳስቧል።

ፕሬዝዳንት ሀሰን ሼክ መሃመድ “ኤርትራ ሁሌም ከሶማሊያ ጋር ናት” አሉበኤርትራ ይፋ የስራ ጉብኝት ያደረጉትን ፕሬዝዳንት ሀሰን ሼክ መሃመድ “ኤርትራ የሶማሊያን ሉዓላዊነትና የግዛት አንድነት ...
10/01/2024

ፕሬዝዳንት ሀሰን ሼክ መሃመድ “ኤርትራ ሁሌም ከሶማሊያ ጋር ናት” አሉ

በኤርትራ ይፋ የስራ ጉብኝት ያደረጉትን ፕሬዝዳንት ሀሰን ሼክ መሃመድ “ኤርትራ የሶማሊያን ሉዓላዊነትና የግዛት አንድነት ለማስጠበቅ ስትደግፍ መቆየቷን እና ይህም የኤርትራ አለም አቀፍ አቋም” መሆኑን ገልጸለዋል።

“ፕሬዝዳነት ኢሳያስ ዛሬም ይህንን አረጋግጠውልኛል” ያሉ ሲሆን፤ “ለዚህም እናመሰግናላን” ብለዋል።

የኤርትራ መንግስት ከሰፐማሊያ ጋር በሁለትዮሽ እና ቀጣናዊ ጉዳዮች ላይ በቅርቡ ሰፊ መግለጫ እንደሚያወጣም አስታውቋል።

ስራ ሳይኖረው ሶስት ሚስቶች እና ልጆች ያሉት አባወራሩታ ዋታናቢ የተሰኘው ጃፓናዊ የ35 ዓመት ጎልማሳ ሲሆን ሳፖሮ በተሰኘችው የጃፓን ከተማ ነዋሪ ነው፡፡ይህ ግለሰብ ሶስት ሚስቶች እና ሁለት...
08/01/2024

ስራ ሳይኖረው ሶስት ሚስቶች እና ልጆች ያሉት አባወራ

ሩታ ዋታናቢ የተሰኘው ጃፓናዊ የ35 ዓመት ጎልማሳ ሲሆን ሳፖሮ በተሰኘችው የጃፓን ከተማ ነዋሪ ነው፡፡

ይህ ግለሰብ ሶስት ሚስቶች እና ሁለት ፍቅረኞች አሉኝ ማለቱን ተከትሎ ከጃፓን ባለፈ በመላው እስያ ዋነኛ መነጋገሪያ ሆኗል፡፡

ከሶስት ሚስቶቹ ጋር በጋራ እየኖረ መሆኑን የሚናገረው ይህ ግለሰብ ከመጀመሪያ ሚስቱ ሁለት ልጆች ከሁለተኛዋ ሚስቱ ደግሞ አንድ ልጅ በድምሩ ሶስት ልጆች ያሉት ሲሆን ተጨማሪ ልጆችን የመውለድ ፍላጎት እንዳለውም ተናግሯል፡፡

08/01/2024

ሶማሊላንድ ከኢትዮጵያ ጋር ያደረገችው ውል አልተዋጠልኝም ህጋዊ አሰራር አልተከተለም ያለው የሶማሊላንድ የመከላከያ ምኒስትር ዓብዲቀኒ መሐመድ ሥልጣኑን ለቀቀ!

Adres

Brussels

Meldingen

Wees de eerste die het weet en laat ons u een e-mail sturen wanneer On-Time nieuws en promoties plaatst. Uw e-mailadres wordt niet voor andere doeleinden gebruikt en u kunt zich op elk gewenst moment afmelden.

Delen