
15/10/2023
በካፋ ዞን ጊምቦ ወረዳ በደረሰ የትራፊክ አደጋ በ14 ሰዎች ላይ ጉዳት ማድረሱን የጊምቦ ወረዳ ፖሊስ አስታወቀ።
በካፋ ዞን ጊምቦ ወረዳ ፖሊስ የትራፊክ ሞተረኛ ሳጅን ወንድሙ ገ/ሚካኤል እንደገለፁት ከጊምቦ ወደዲሪ ይጓዝ የነበረ የህዝብ ማመላለሻ ዶልፊን ከጎጀብ ጊምቦ ይጓዝ ከነበረ ሌላ ዶልፊን መኪና ጋር ተጋጭተዉ በ14 ተሳፋሪዎች ላይ ቀላልና ከባድ የአካል ጉዳት መድረሱን ተናግረዋል።
እንደሳጅን ወንድሙ ገለፃ በ10 ሰዎች ላይ ቀላል ጉዳት የደረሰባቸዉ ሲሆን 4 ተሳፋሪዎች ከባድ የአካል ጉዳት ደርሶባቸዉ ጅማ ሆስፒታል ሪፈር መደረጋቸዉን ገልፀዋል።
አክለዉም መንገድ ላይ የነበረዉን አህያን ሁለቱም አሽከርካሪዎች ለማዳን ሲሞክሩ አደጋዉ መድረሱን ጠቅሰዉ መንገድ ላይ ከብቶች የሚገኙ በመሆናቸዉን ጥንቃቄ ማድረግ እንዳለባቸዉ አሳስበዋል።
👉ዘገባዉ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ፖሊስ ኮሚሽን የህዝብ ግንኙነትና ኮሚንኬሽን ነዉ