Tadiasaddis

Tadiasaddis Official account for TadiasTube. the best radio show in town, bringing live # entertainment # sport # current-affairs.......stay tuned.

tadiastube
https://youtu.be/EnUhY0IpsYQ Official account for tadiasaddis radio show. The best radio show in town, bringing live -affairs ......stay tuned

የሰርፀ ፍሬስብሃት መልዕክት   | ስለ ዳዊት ጽጌ የተዋጣለት ድምፃዊነት ዛሬ ምን ዐዲስ ነገር መናገር ይቻላል? ኹሉ የመሠከረለት ዜማ የሚኩል እና ሸምኖ የሚቋጭ አዚያሚ ነው። በሙያም በግብረ...
03/02/2024

የሰርፀ ፍሬስብሃት መልዕክት

| ስለ ዳዊት ጽጌ የተዋጣለት ድምፃዊነት ዛሬ ምን ዐዲስ ነገር መናገር ይቻላል? ኹሉ የመሠከረለት ዜማ የሚኩል እና ሸምኖ የሚቋጭ አዚያሚ ነው። በሙያም በግብረ ገብም ማንነቱን ያስመሠከረ የዘመን አርአያ ነው።

ወደ ኋለኛው የኢትዮጵያ ሙዚቃ ዘመን መለስ ብሎ፥ "ወትረ ኅልው" (classic) የምንላቸውን ዜማዎች ተጫውቶ አዳመጥኳቸው። እጅግ በሚገርም ብቃት እና ዘመን አሻጋሪ በኾነ መንፈስ ውብ አድርጎ ነው ያዜማቸው። የተመረጡት ሙዚቃዎችም በተሠጡት ጋዜጣዊ መግለጫዎች ላይ እንደተወሳው፣ ከዘወትር ድምጫችን የራቁ እና በቀላሉ የማናገኛቸው ሥራዎች ናቸው።

አበጋዙ ክብረወርቅ ሺዎታ፥ በተለመደ የሙያ አክብሮት እና ጥንቃቄው፣ የቀደሙ አቀናባሪዎችን አሻራ እንዳይለቅ አድርጎ በዘመን Expression የተጌጠ Adaptation እና Re-Arrangement የተዋሐዱበት ፕሮዳክሽን አስደምጦናል። የጥላሁን ገሠሠን፣ የማሕሙድ አሕመድን፣ የዓለማየሁ እሸቴን፣ የምኒልክ ወስናቸውን፣ የአስቴር ዐወቀን፣ የተፈራ ካሣን (በግርማ ተፈራ) ሥራዎች፤ በልዩ ጥራት እና ከፍታ (ራሳቸውን ድምፃውያኑን ባሳመነ ብቃት) ፕሮዲውስ ማድረጉ ይታወቃልና፣ እንዲህ ያለውን ፕሮዳክሽን እንዴት re-arrange ሊያደርገው እንደሚችል መገመት አይሳነንም ።

የሙዚቃ መሣሪያዎቹ formation እና የሙዚቀኞቹ የየግል ብቃት ብዙ የሚያስጽፍ፣ ምሁራን ሙዚቀኞችን ያገናኘ አስደናቂ መሰባሰብ ነው። እንደ አንድ ኦርኬስትራ ወይም ባንድ አብረው ብናያቸው ኹሌም የምመኛቸውን ሙዚቀኞች ይህ ፕሮዳክሽን ማገናኘት ችሏልና በጣም ደስ ይላል።

እያንዳንዱ ሥራ የራሱ ፈተና ስላለው፥ ይሄኛውም ለሙዚቀኞቹ ፈተና ይኖረዋል። ግን የተሳካለት ስሜት ሰጪ ፕሮዳክሽን መሠራቱን መመስከር ይቻላል።

የማ (የማን) ...?!በብርቱካን ሚደቅሳ   | ለራሴ በሚገባኝ መልኩ ፈጣሪን የጠየኩት (ያልጎመጎምኩለት ) አንድ ነገር ነበር፤ ያልተሠሙትን ቃላት፣ ያልተቀመሩትን ዜማዎች ያልተሳሉትን ሥእሎች...
31/01/2024

የማ (የማን) ...?!

በብርቱካን ሚደቅሳ

| ለራሴ በሚገባኝ መልኩ ፈጣሪን የጠየኩት (ያልጎመጎምኩለት ) አንድ ነገር ነበር፤ ያልተሠሙትን ቃላት፣ ያልተቀመሩትን ዜማዎች ያልተሳሉትን ሥእሎች ያልተባሉትን ነገሮች ለጦብያ ልጆች አሳይላት ብዬ፡፡ አረገላት መሰለኝ ሰሞኑን……..

የጋሞ ዞኗ ቦንኬ ወረዳ የጋሽ አሰፋ ሠፈር እንደ ሆነችው ጬንቻ ተራራማ ነች አሉ፡፡ ይህን የሰማሁት ባለፈው ቅዳሜ የደጋ ሰው አልበም ድምጻዊ የማ እና ፕሮዲውሰሩ ኢዩኤልን ለማክበር በኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ በተዘጋጀው ውይይት ላይ በተገኘሁበት ወቅት ነው፡፡

ቦንኬ እና ማህበረሰቧ ለሙዚቃው ንሸጣ የተገኘበት ስፍራ ነው፡፡ጋሞን ሙሉ በሙሉ አውቃለሁ ብዬ ስለምኩራራ ቦንኬን ለመጀመሪያ ጊዜ የዛን ዕለት በመስማቴ ተቁነጠነጥኩ፡፡ እዛው ሆኜ አንዳንድ ማጣራቶች አረኩ፡፡ ለካ በምርጫ ቃላት ቦንኬ የምትጠራው በጎረቤቷ ወረዳ ገረሴ ነው፡፡ ሁለቱ ተዋህደው አንድ የፓርላማ መቀመጫ፡፡

ታዲያ እነ የማ ደጋነትን ለሙዚቃቸው መጠሪያ ከቦንኬ ብቻ ወስደው የጣፉት ነገር አይደለም፡ ፡የሙዚቃው እና የግጥሙ መንፈስ ከድምጻዊዋ ጋር ይዋሀድ ዘንድ ባሌ ተራራ ወጥተዋል፡፡ለእኔ ለማይሟ ለማብራራት ከባድ የሆነ የሙዚቃ ጥበባ (ግስ ነው) ተጠቅመው የደጋን ጉም እና ውርጭ የሚዘውረውን የንፋስ ድምፅ በሙዚቃው ውስጥ በስሱ እንዲሰማ አድርገዋል (የኢዩኤል ስራ ነው)፡፡ አይገርምም? ነገሩ የገባኝ የደጋ ሠውን እንደገና ቅዳሜ ማታ ስሰማው ነው፡፡

የራያ ራዩማን ነገር ካነሳሁ አውርቼ አላበቃም፤ በፍቅር ዘፈን አዘቦም ቆቦም የማ (የማን) እንደሆነ ጠይቆ ሁሉም የኛ ብሎ መመለስ እንዴት መታደል ነው?! ትርጉም የእኔ! የጎበዙን ገጣሚ ሀሳብ ወደፊት የምንሰመው ይሆናል፡፡

የሆነው ሆነና እነዚህ ሙዚቀኞች በነጻ ለሰጡን ለዚህ ውበት እንዲሁም የሙዚቃውን ሀሳብ አፍታቶ ለነገረን ሰርፀ ፍሬ ስብሀት እግዜር ይስጥልን ብዬ ተናግሬ ሳበቃ ስልኬን ነካ ነካ አርጌ በየማ ስም ያለውን የዩቲዩብ አካውንት https://www.youtube.com/ ሳይ ለካ ሰብስክራይብ አላደረኩትም፡፡(you don’t need to say it. I know it is old age)
ለማንኛውም እንደ እኔ ቴክኖሎጂ ላይ ዘገም የሚል አይጠፋም ብዬ ይቺን ጣፍኩ፡፡

ለጥበብ ከባድ በሆነበት በዚህ ዘመን (ከባድ ይመስለኛል) እንደተደራሲ ልናደርገው የምንችለው ትንሹ ይሔ ነው ብዬ አስባለሁ፡፡

Please subscribe https://www.youtube.com/
ወይም በድሮ ቋንቋዬ ሰብስክራይብ እንድታደርጉ እና የደጋ ሰውን ከነውርጭ እና ነፋሱ ጭምር እንድትሰሙ ጥሪ አቀርባለሁ😀
https://www.youtube.com/
https://www.youtube.com/watch?v=U75MwwWLxiA

ልጅነቴ፣ ከተማዬ ድሬዳዋ:-  ሊብሮ እና ኢንተር ጋዜጣን አለ ማንበብ እንደ ወንጀል ይቆጠር ነበር።በሁለት ሳምንት አንዴ ትወጣ የነበረችው ሊብሮ ጋዜጣ በተለይ ለሀገር ውስጥ ዘገባ ማንበብ የም...
23/01/2024

ልጅነቴ፣ ከተማዬ ድሬዳዋ:- ሊብሮ እና ኢንተር ጋዜጣን አለ ማንበብ እንደ ወንጀል ይቆጠር ነበር።

በሁለት ሳምንት አንዴ ትወጣ የነበረችው ሊብሮ ጋዜጣ በተለይ ለሀገር ውስጥ ዘገባ ማንበብ የምጀምረው ከጥርቅምቃሞ ነበር። ፈገገ ያደርገኛል፣ በዚህ ላይ ተገልብጠው በሚፃፉ ቃላት ድሬዳዋ ከነበረው የ"ጋሪንቻ" ጋዜጣ አዘጋጅ ፈክሪ ጋር በኮድ የሚያወሩበት ይገርመኝ ነበር።

ሊብሮ ጋዜጣ ላይ ክስተት ዘግቤአለሁ፣ ክስተት ሆኜ ተዘገቤአለሁ።

ገነነ፣ ስለ ጥልቅ የማስታወስ ብቃቱ ተንቀሳቃሽ የሀገር ውስጥ የእግርኳስ ታሪካችን መዝገብ ብለን እንጠራው ነበር።

ማንም ባይቀበላችሁም ባመናችሁበት ነገር የመፅናህትን ብቃት ተምሬበታለሁ።

የራሱ የአስተሳሰብ ፍልስፍና ያለው፣ ወጣቶችን ለመምከርና ሀሳብን ለማጋራት የማይሰለች፣ የስፖርት ጋዜጠኛ ብቻ ሳይሆን የታሪክ ፀሐፊ የነበረው ገነነ ማረፉን መስማት አሳዛኝ ብቻ ሳይሆን አስደንጋጭ ሆኖብኛል።

መታመመህን ሳንሰማ ማረፍህ ሰማን።

ሲያወራ ጥርስ የማያስከድነው ... እና ብዙ ብዙ የነበረው ጉምቱ ጋዜጠኛና 'ታሪክ መዝጋቢ' ገነነ መኩሪያ መታመሙን ሳንሰማ ማረፉን ሰማን። በጣም ያሳዝናል። 😭😭😭
ለወዳጅ ዘመዶቹ፣ ለአድናቂዎቹና ለስፖርት ቤተሰቦች መጽናናት ይሁን!

ነፍስህ በሰላም ትረፍ

ታደለ አሰፋ

እያዩ ፈንገስ ... "ቧለቲካ" ቴአትር ታገደ‼ደራሲ ... በረከት በላይነህተዋናይ ... ግሩም ዘነበየመንግስት የፀጥታ አካላት ለዓለም ሲኒማ የስራ ኃላፊዎች ባስተላለፉት ትእዛዝ ከነገ ሐሙስ ...
10/01/2024

እያዩ ፈንገስ ... "ቧለቲካ" ቴአትር ታገደ‼
ደራሲ ... በረከት በላይነህ
ተዋናይ ... ግሩም ዘነበ

የመንግስት የፀጥታ አካላት ለዓለም ሲኒማ የስራ ኃላፊዎች ባስተላለፉት ትእዛዝ ከነገ ሐሙስ ጥር 2 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ እያዩ ፈንገስ "ቧለቲካ" ቴአትር ለህዝብ እንዳይታይ መከልከሉን ከአዘጋጆቹ አረጋግጫለሁ።

ቴአትር ቤቱም ይህንኑ የመንግስት የፀጥታ ኃላፊዎች ትዕዛዝ ለቴአትሩ አዘጋጆች በማሳወቅ ውሉን ማቋረጡም ታውቋል።

ማስታወሻ፦
* በኢትዮጵያ ታሪክ የመጀመሪያው የአንድ ሰው የሙሉ ጊዜ ቴአትር
* የመጀመሪያው እያዩ ፈንገስ በመጋቢት ቀን 2006 ዓ.ም መታየት ጀመረ
* እያዩ ፈንገስ ዘንድሮ ( 2016 ) 10 ዓመት ሞልቶታል
* በራስ ሆቴል ይዘጋጅ በነበረው ጦቢያ ፖይቲክ ጃዝና በተለያዩ መድረኮች ከ25 በላይ ( ከ20 - 30 ደቂቃ ) የሚፈጁ ክፍሎች የተሰራ
የሙሉ ጊዜ ቴአትር
1. እያዩ ፈንገስ ቁጥር 1 ..... "ፌስታሌን"
2. እያዩ ፈንገስ ቁጥር 2 ..... "አጀንዳዬን"
3. እያዩ ፈንገስ ቁጥር 3 ..... "ቧለቲካ" ተሰርተዋል።

* "ቧለቲካ" መታየት የጀመረው ጥቅምት 15/2016
* ዘወትር ሐሙስና እሁድ ሲታይ መቆየቱ ይታወሳል
* "ቧለቲካ" ከጥቅምት 15/2016 ጀምሮ 20 መድረኮች ተሰርቷል።
ከያሬድ ሹመቴ ገፅ

የአእላፋት ዝማሬን አለማቀፍ ሚዲያዎች በገፆቻቸው ተቀባብለው ዘግበውታል ❤Al Jazeera    USA TodayCGTNThe CitizenThe Boston GlobeNOS (Nederlandse Omr...
08/01/2024

የአእላፋት ዝማሬን አለማቀፍ ሚዲያዎች በገፆቻቸው ተቀባብለው ዘግበውታል ❤

Al Jazeera
USA Today
CGTN
The Citizen
The Boston Globe
NOS (Nederlandse Omroep Stichting)
Archive Africa
The Gurdian

በገጾቻቸው ላይ በፎቶና በቪድዮ ዘግበውታል::

የኢትዮጵያዊው ጃንደረባ ትውልድ በጸሎት በገንዘብ በሃሳብ እንደግፍ።የኢትዮጵያዊው ጃንደረባ ትውልድን ለመደገፍhttps://donate.janderebaw.org/በቴሌ ብርMerchant ID 7775...
08/01/2024

የኢትዮጵያዊው ጃንደረባ ትውልድ በጸሎት በገንዘብ በሃሳብ እንደግፍ።

የኢትዮጵያዊው ጃንደረባ ትውልድን ለመደገፍ

https://donate.janderebaw.org/

በቴሌ ብር
Merchant ID 777582
The Ethiopian Jandereba Generation

8261
Commercial Bank of Ethiopia

8261
Abyssina Bank

Henok Haile መምህር ዲያቆን ሄኖክ ሀይሌ እንዲህ ብሎናል።

የበሬን ምስጋና ወሰደው ፈረሱ (ርእስ)

የአእላፋት ዝማሬን ዕውን ለማድረግ ላለፉት ሦስት ወራት እንቅልፍ ያጡ ፣ የታመሙ ፣ ልባቸው በስድብና በሽሙጥ ንግግር የቆሰለ ፣ በረዣዥም ስብሰባዎችና የጉልበት ሥራዎች የዛሉ ፣ ዝግጅቱን በዚህ ደረጃ ከፍ እንዲል ሰዎችን አሳምኖ ገንዘብ በማሰባሰብ የተንከራተቱ ፣ በአንድ ትንፋሽ ሠላሳ መዝሙር ሲያጠኑ የከረሙ ፣ መዝሙር ለማስቀረጽ ሥራ ትተው በስቱድዮ የዋሉ ፣ ሦስት ጊዜ revise የተደረገውን Stage design የሠሩ ፣ በመሐረነ አብ ጸሎት በየአድባራቱ ደጅ የጠኑ ፣ የዘማርያን ልብስና ልብሰ ተክህኖ ዲዛይን ሲያደርጉ ፣ ተነግሮ የማያልቅ ድካም የደከሙ ትሑታንና ታዛዦች የሆኑ የኢትዮጵያዊው ጃንደረባ ትውልድ የቦርድና የሥራ አስፈጻሚ አባላት ፣ የጃን ያሬድ ኅብረ ዝማሬ መዘምራን ፣ የጃን አጋፋሪ event organizing ቡድንና በሥሩ የተቋቋሙ 15 ቡድኖች ፣ የጃን አግናጥዮስ የሕፃናትና አዳጊዎች project አባላት ፣ የጃን እስጢፋኖስ ዲያቆናት ፣ የጃንደረባው ሚድያ እሳት የላሱ የካሜራና ኤዲቲንግ የግራፊክስ ባለሙያዎችና የማኅበራዊ ሚድያ ዘመቻ ወጣቶች የአእላፋት ዝማሬን እውን ለማድረግ የከፈሉት መሥዋዕትነት እጅግ ብዙ ነው::

ለዚህ አገልግሎት ምስጋና የሚገባው ዕንባና ተማጽኖአችንን ያልናቀ ልዑል እግዚአብሔር ነው::

ዓለም ዘመኑ ጥሩ አይደለም ብላ ስካሩን ጭፈራውን ፈንጠዝያውን ግድያውን አላቆመችም:: እኛም ስብሐተ እግዚአብሔር የወቅቱን ሁኔታ እያየች የማታስታጉል ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ልጆች እንደመሆናችን ሲከፋን የምንተወው ደስ ሲለን የምንቀጥለው መዝሙር የለም ብለው ለጸሎተ ምሕላና ለአእላፋት ዝማሬ የተሠጡ ወጣቶች ብዙ ናቸው:: "አርምሞ ጽርዓት በሌለበት ምስጋና ሳናቋርጥ ዘወትር እናመሰግንሃለን:: ይኸውም ሊቃነ መላእክት የሚያመሰግኑህ ምስጋና ነው" (ጸሎተ ኪዳን)

ምግብ ቤት ገብተን ጥሩ ስንበላ አስተናጋጁን እናመሰግናለን:: ቲፕ እንሠጠዋለን:: ማዕድ ቤት ውስጥ እሳት የበላቸውን ሼፎችና ተባባሪ ሠራተኞች ግን አናያቸውም:: የአእላፋት ዝማሬንም በተመለከተ ሊመሰገን የሚገባው እንቅልፉን የሠዋ ብዙ ወጣት ከጀርባ አለና አስተናጋጁን ለቀቅ አድርጋችሁ ሼፎቹ ላይ አተኩሩ::
ከዚያ ውጪ ግን ከታመነበት ተአምር መሥራት የሚችለውን ቅን 1/21ኛውን ጃን ያሬድ ብቻ ሳይሆን መላውን የኢትዮጵያዊው ጃንደረባ ትውልድ በጸሎት በገንዘብ በሃሳብ ደግፉ::

የኢትዮጵያዊው ጃንደረባ ትውልድን ለመደገፍ

https://donate.janderebaw.org/

በቴሌ ብር
Merchant ID 777582
The Ethiopian Jandereba Generation

8261
Commercial Bank of Ethiopia

8261
Abyssina Bank

Janderebaw Media
የኢትዮጵያዊው ጃንደረባ ትውልድ The Ethiopian Jandereba Generation

" ሁሉም ኢትዮጵያዊ ስለ ሰላም መፀለይ አለበት በፀሎት ሁሉ ነገር ይገኛልና። ሰላም ከሌለ ሁሉ ነገር የለም። ሰላም ካለ ግን ሁሉ ነገር ነገር አለ። ለሰላም የሚሆን ዋጋ የለም፣ ወርቅም ብርም...
06/01/2024

" ሁሉም ኢትዮጵያዊ ስለ ሰላም መፀለይ አለበት በፀሎት ሁሉ ነገር ይገኛልና። ሰላም ከሌለ ሁሉ ነገር የለም። ሰላም ካለ ግን ሁሉ ነገር ነገር አለ። ለሰላም የሚሆን ዋጋ የለም፣ ወርቅም ብርም ቢሆን አይገዛትም ። ሰላም ካለ ሁሉ ነገር አለ፣ ደሀ በጉልበቱ ሀብታምም በሀብቱ ለራሱ ኖሮ ሀገርን ያኮራል፣ ስለ ሰላም መፀለይ ግድ ይላል። ሰላም አለምን ይገዛል ምክንያቱም ሁሉ ነገር የሚስተካከለው በሰላም ስለ ሆነ። "

ብፁእ ወቅዱስ ፖትሪያርክ ርዕሰ ሊቃነጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት
አቡነ ማትያስ

እንኳን ለጌታችን ለመድሀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በአል አደረሳችሁ።

ከሀይማኖት አባቶች በላይ ትህትና ገዝፋ የተገኘችበት ሰው፣ በዚህ ዘመን አይገባኝም ሳይሆን "(ሲሞናዊነት)" ሹመትን በገንዘብ የመግዛትና መሸጥ ሩጫ ባየንበት ለመሾም አንቀፅ ማስለወጥ የተደረሰ...
21/07/2023

ከሀይማኖት አባቶች በላይ ትህትና ገዝፋ የተገኘችበት ሰው፣ በዚህ ዘመን አይገባኝም ሳይሆን "(ሲሞናዊነት)" ሹመትን በገንዘብ የመግዛትና መሸጥ ሩጫ ባየንበት ለመሾም አንቀፅ ማስለወጥ የተደረሰበት ዘመን ድንቅ ሰው ተገኘ አይገባኝም ምን ሰርቼ የሚል።

ቢኒያም መቄዶኒያ ተግባሩ ያባቱን ስም ቀይሮት ቢኒ መቄዶኒያ ደውሎ ነበር በቢሮአችን የምንጠራው እንደዛ ነው፣ ትውውቃችን አመታትን ተሻግሮአል፣ በማእከሉ ውስጥ ለአንድ ቀን የሚሆን የምግብ ወጪ እንኳ አጥቶ ለህዝቡ ንገሩልኝ በሚል ነበር ወደ ቢሮአችን መጥቶ በልበ ቀናው ወዳጄ ጋዜጠኛና መድረክ አጋፋሪ ታዬ ወርቁ በኩል ያወቅኩት።

አመታት ተቆጠሩ እርሱ ግን ዛሬም የመጀመሪያ ቀን ያየሁት ትህትናው አብሮት አለ፣ ይህ መሰጠት ነው፣ መመረጥ፣ ብሎም መታደል።

ግን ግን ቢኒ ሁሌም እንደምልህ እባክህን የአንተ መኖር ለብዙዎች ተስፋ ነውና የህክምናህን ነገር አደራ

የክብር ዶክትሬት በሚገባው ቦታ ሲውል

ይህን ክብር ማግኘት ይገባሀል።
10/06/2023

ይህን ክብር ማግኘት ይገባሀል።

Address


Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Tadiasaddis posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Tadiasaddis:

  • Want your business to be the top-listed Media Company?

Share