Peace ሰላም

Peace ሰላም ይህ ፔጅ ለተበደሉና ድምፅ ለሌላቸው ኢትዮጵያኖች ድምፅ በመሆ

08/30/2025

ሙዓዝ ሀቢብ 🤝 ቴዲ አፍሮ

ከአፄ ቴዲ የተሰረቀ ዜማ ነው አሉ ሙአዝ ሀቢብ ያወጣው ዘፈን‼

እውነተኞች ነን
የድሉ ቀን ቅርብ ነው 😂

ግእዝ ብንማር ምን ችግር አለው? ለምትሉ ደዩሶች በሰፈራችሁ ያሉ ቄሶች ጋር ሄዳችሁ መማር መብታችሁ ነው። የቆሎ ተማሪም ብትሆኑ ከተመቻችሁ መብታችሁ ነው። ይሄን ያህል ሞራል ካላችሁ ኪትቡሲታ...
08/30/2025

ግእዝ ብንማር ምን ችግር አለው? ለምትሉ ደዩሶች በሰፈራችሁ ያሉ ቄሶች ጋር ሄዳችሁ መማር መብታችሁ ነው። የቆሎ ተማሪም ብትሆኑ ከተመቻችሁ መብታችሁ ነው። ይሄን ያህል ሞራል ካላችሁ ኪትቡሲታ በቀራችሁ ጥሩ ነበር። ይህም ቢሆን ተምራችሁ ለንጽጽርም ይሁን ለ ሳይንስ career ብትጠቀሙበት ምንም ተቃውሞ የለንም። 💥 👉 እያልን ያለነው ልጆቻችንን ለቄሶች፣ ቆሎ ተማሪና፣ መነኮሳት እንዲሁም ፔዳጎጂ ላልሰለጠነ ሰው ከ ቀጣይ ህይወታቸው አንጻር ቦታ ለሌለው ነገር አምነን አሳልፈን አንሰጥም ነው። ለጤናቸውም ስጋት አለኝ።

የአማራ ፖለቲካ መቆሚያውን ባላወቅነው ትርምስ ላይ ሆኖ ልጆቻችንን መነገጃ አይደሉም ነው።

© Kal Hassen

ፋኖ ተኩሶ ገ*ደ*ለ ህዝቡ ተከፋፈለ😭ትናንት በ 23/12/2017 በአማራ ክልል ከአዲስ ዘመን ጎንደር ባለው መንገድ  የግለሰቦችን እና የነጋዴዎችን  የገበያ ግብአቶች ጭነው ሲጓዙ በነበሩ መኪ...
08/30/2025

ፋኖ ተኩሶ ገ*ደ*ለ ህዝቡ ተከፋፈለ😭
ትናንት በ 23/12/2017 በአማራ ክልል ከአዲስ ዘመን ጎንደር ባለው መንገድ የግለሰቦችን እና የነጋዴዎችን የገበያ ግብአቶች ጭነው ሲጓዙ በነበሩ መኪኖች ላይ ፋኖ ተኩሶ ሹፌር በመግደል የአከባቢው ሰው ደግሞ ንብረቱን በመዝረፍ ሲረባረቡ ተስተውሏል።
የከሸፈ ትውልድ‼

ዛሬ በተመረቁት ሀገራዊ ወታደሮች ፋኖ እና ሞአ ተዋህዶ ለቅሶ ላይ ናቸው። ፋኖ በእነዚህ ሀገራዊ ጀግኖች ይገረፋል።
08/30/2025

ዛሬ በተመረቁት ሀገራዊ ወታደሮች ፋኖ እና ሞአ ተዋህዶ ለቅሶ ላይ ናቸው።
ፋኖ በእነዚህ ሀገራዊ ጀግኖች ይገረፋል።

እኛስ መቼ ጠፋን የአፄ ዩሀንስን ታሪክ ልትደግሙት እንደሆነ።
08/30/2025

እኛስ መቼ ጠፋን የአፄ ዩሀንስን ታሪክ ልትደግሙት እንደሆነ።

በጭራሽ ልጆቻችን እህት ወንድሞቻችን የቄስ ትምህርት ግእዝን አይማሩም።ፅንፈኛው አክራሪው ሀይል እናንተ እንደሆናችሁ ማወቅ አለባችሁ። በግድ ካላጠመቅናችሁ በመንግስት እናስረሽናችኋለን እያሉን ...
08/30/2025

በጭራሽ ልጆቻችን እህት ወንድሞቻችን የቄስ ትምህርት ግእዝን አይማሩም።
ፅንፈኛው አክራሪው ሀይል እናንተ እንደሆናችሁ ማወቅ አለባችሁ።
በግድ ካላጠመቅናችሁ በመንግስት እናስረሽናችኋለን እያሉን ነው እነ መንግስቱ ዘገየ።
እንግድህ እንተያያለና‼

© የድሉ ቀን ቅርብ ነው የዘገየ ልጅ እድል ቢያገኝ አፄ ዩሀንስን ነው የሚሆንብን።

08/29/2025

ወገኖቼ #ፋኖን ከአይሁድ ወታደር ለይታችሁ አትዩት። ሁለቱም ለሙስሊም ያላቸው ጥላቻ እና አመለካከት አንድ ነው።

የድሉ ቀን ቅርብ ነው

እውነተኞች ነን

08/28/2025

በፉከራ መንግስትን ገልባጩ ቄስ😂

እውነተኞች ነን
የድሉ ቀን ቅርብ ነው እነ ፋኖ ቄሴ ከዚህ የተሻለ ሀሳብ የላቸውም።

08/28/2025

"ከዚህ በኋላ የማንኛውም የፖለቲካ ንቅናቄ ውስጥ ኦርቶዶክስ የኦርቶዶክስን ፍላጎት እስካሁን የደረሰባትን መከራ ታሳቢ የማያደርግ ትግል ሊኖር አይችልም። የአማራ ክልል 80 ምናምን በመቶ ኦርቶዶክስ ነው። ከሃይማኖቱ ተነጥሎ ሊያስብ አይችልም።>>
( የሞዐ ተዋህዶ መስራች መምህር ፋንታሁን ዋቄ)
----------------------------------------------------------------

የአማራ ክልል ፖለቲካ እና ቤተክህነቷን ዋሻ ያደረጉ ሃይሎች የሚያደርጉት እንቅስቃሴ እንዲሁም ቤተክርስቲያኗን ከፖለቲካ ንቅናቄዎች ጋር ያላት ውስብስብ ግንኙነት የአንድን ማኅበረሰብ የጋራ ማንነት በመጠቀም ፖለቲካዊ ዓላማዎችን ለማሳካት የጥንታዊ እና የዘመናዊ ስልቶችን ውህደት የሚያሳይ ነው።

መምህር ፋንታሁን ዋቄ እንደገለጹት፣ የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ እምነት እና የአማራ ማንነት ተነጣጥለው ሊታዩ እንደማይችሉ መግለጽ፣ የፖለቲካ ስነ-ልቦና ዋና መርህ የሆነውን "የቡድን ማንነት መገንባት" የሚለውን ስልት ያሳያል።

በዚህ ፍልስፍና መሰረት፣ የአንድን ቡድን ታሪካዊ ስቃይና መከራ ለፖለቲካዊ ትግል መሰረት ማድረግ የቡድኑን አባላት ስሜታዊ በሆነ መንገድ በማነሳሳት የጋራ ጠላትና ዓላማ እንዲኖራቸው ያደርጋል።

ይህ ደግሞ በድንገት የተወሰነ የሚመስለውን የግእዝ ቋንቋ የትምህርት ፖሊሲ ውሳኔ ምክንያታዊ እና ስልታዊ ያደርገዋል። ይህ ውሳኔ ከትምህርት ጥራት ይልቅ በሕቡእ ቡድን የሚመራ ሃይማኖታዊ እና ፖለቲካዊ ስልጠና የመስጠት ዓላማ እንዳለው ይገመታል።

ምክንያቱም፣ በአማራ ክልል ላሉ 8,000 በላይ ለሚሆኑ የአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች በሳይንሳዊ መንገድ የሰለጠኑ የግእዝ መምህራንን በድንገት ማዘጋጀት የማይታሰብ ሲሆን፣ ይህ የፖሊሲ ለውጥ የተደረገው የትምህርት ስርዓቱን የፖለቲካ ንቅናቄ ማፍሪያ ሜዳ ለማድረግ መሆኑ ግልጽ ነው።

በመሆኑም የሃይማኖታዊ ማንነትን በዘላቂነት በህፃናት አእምሮ ውስጥ ለመቅረጽ እና ለወደፊት የፖለቲካ ትግሎች ጠንካራ መሠረት ለመጣል የተደረገ ጥረት መሆኑን ያመላክታል።

© ዐብዱልጀሊል ሸኽ ዐሊ ካሳ/ Abduljelil Ali

ግዕዝ መፀለያ እና ማምለኪያ  እንጂ መግባቢያ አይደለም ።
08/28/2025

ግዕዝ መፀለያ እና ማምለኪያ እንጂ መግባቢያ አይደለም ።

ነገረ-ግእዝ!!(በአብዱልጀሊል ሸኽ ዐሊ) 🔸️⚛️🔹️💥️🔸️⚛️🔹️ አንድ ቋንቋ በአገራዊ ወይም በክልላዊ የትምህርት ሥርዓት ውስጥ በግዴታ እንዲካተት የሚደረግ የፖሊሲ ውሳኔ፣ ስሜታዊ ወይም ጠባ...
08/28/2025

ነገረ-ግእዝ!!

(በአብዱልጀሊል ሸኽ ዐሊ)
🔸️⚛️🔹️💥️🔸️⚛️🔹️


አንድ ቋንቋ በአገራዊ ወይም በክልላዊ የትምህርት ሥርዓት ውስጥ በግዴታ እንዲካተት የሚደረግ የፖሊሲ ውሳኔ፣ ስሜታዊ ወይም ጠባብ የፖለቲካ ፍላጎት መሆን የለበትም። ይልቁንም፣ ውሳኔው በተጨባጭና በተጨባጭ ባልሆኑ (quantitative and qualitative) ሳይንሳዊ፣ ማኅበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ፍልስፍናዊ መሠረቶች ላይ በጥብቅ የተመሠረተ መሆን አለበት።

ይህን የመሰለ አቅጣጫ ከማስቀመጥ በፊት፣ የፖሊሲ አውጪዎች የሚከተሏቸው መመዘኛዎችና ሊነሱ የሚችሉ ጥያቄዎች በሰፊው ሊተነተኑ ይገባል።

1. የሶሺዮ-ቋንቋዊ እና ስነ-ሕዝባዊ ትንተና

የአንድ ቋንቋ ሕያውነት (viability) እና የመኖር ብቃት ሳይንሳዊ በሆኑ መለኪያዎች መገምገም ለግዳጅ ትምህርት መመዘኛ መሠረታዊ ነው። ይህ ትንታኔ የቋንቋውን አጠቃላይ ተናጋሪዎች ብዛት፣ የአፍ መፍቻ ቋንቋ (L1) እና የሁለተኛ ቋንቋ (L2) ተናጋሪዎች ጥምርታን ያጠቃልላል። የዓለም ቋንቋዎች በዩኔስኮ (UNESCO) በተቀመጠው መመዘኛ መሠረት፣ አንድ ቋንቋ ከትውልድ ወደ ትውልድ የማስተላለፍ ሂደቱ ሲቋረጥ፣ ለአደጋ የተጋለጠ እንደሆነ ይቆጠራል።

ግእዝ ቋንቋ ከዘመናዊው ማኅበረሰብ ጋር ያለው መስተጋብር ሲታይ፣ ከጥቂት የቤተክርስቲያን ምሁራንና ምእመናን ውጪ በሰፊው የአማራ ክልል ማኅበረሰብ ውስጥ ተግባራዊ ተናጋሪ የሌለው መሆኑ፣ ይህንን ቋንቋ በግዳጅ ትምህርት ሥርዓት ውስጥ የማካተት ፍልስፍናን ከሥር መሠረቱ ይሞግታል።

አንድ ቋንቋ በሕዝብ የዕለት ተዕለት ሕይወት ውስጥ ተግባራዊ ካልሆነ፣ በግዴታ ትምህርት ሥርዓት ውስጥ ማካተቱ የሀብትና የጊዜ ብክነትን ያስከትላል። የቋንቋ ትምህርት ዋነኛው ዓላማ ተግባቦትን ማጎልበት ነው። ግእዝ ከሃይማኖታዊ ሥርዓቶች ውጭ የሕዝብን የዕለት ተዕለት ሕይወት የማይመራ በመሆኑ፣ በፖሊሲ ደረጃ አስገዳጅ ትምህርት ከመሆኑ በፊት ለምን እና ለምን ዓላማ እንደሚያገለግል አሳማኝ ማስረጃ ያስፈልጋል። ያለበለዚያ፣ የትምህርት ሥርዓቱን ውጤታማነት ከመቀነስ ባለፈ፣ በሕዝቡ ላይ ጫና ሊፈጥር ይችላል።

2. ማኅበራዊ፣ ባህላዊ እና ኢኮኖሚያዊ ፋይዳ

የአንድ ቋንቋ ታሪካዊ ፋይዳ ብቻውን የትምህርት ሥርዓት አካል ለመሆን በቂ አይደለም። ቋንቋው ለሕዝቡ የጋራ ማንነት ግንባታ፣ ለዘመናዊ ኢኮኖሚያዊ ዕድገት እና ለማኅበራዊ ትስስር ያለውን አስተዋጽኦ በጥልቀት መመርመር አስፈላጊ ነው።

🔸️ የባህልና ማኅበራዊ ትስስር፡ ግእዝ ቋንቋ ከኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ጋር ጥብቅ ቁርኝት አለው። ሆኖም፣ አንድ ክልል በውስጡ በርካታ የባህልና የእምነት ማኅበረሰቦችን ሲያቅፍ፣ ከአንድ የተወሰነ ባህል ጋር ብቻ የተቆራኘን ቋንቋ በግዴታ ማስተማር የጋራ ማንነትን ከማጎልበት ይልቅ ማኅበራዊ ክፍፍልን ሊፈጥር ይችላል።

በኦርቶዶክሳዊ እምነት ውስጥ ከሆኑትም ውጭ፣ ሌሎች የክልሉ ማኅበረሰቦችና የእምነት ተከታዮች ከግእዝ ጋር የባህል ትስስር የላቸውም። ግእዝ ባለመኖሩ ምክንያት የሚታጣ አንገብጋቢ የሆነ የወል የሕዝብ ባህል የሌለ መሆኑ፣ ቋንቋውን የጋራ ባህል መገለጫ አድርጎ የመውሰድን አስተሳሰብ ያዳክማል።

🔸️የኢኮኖሚያዊ ፋይዳ (Economic Utility): የኢኮኖሚክስ ፍልስፍና እንደሚጠቁመው፣ የአንድ ሀብት ዋጋ የሚወሰነው ከሚያስገኘው የኢኮኖሚ ምላሽና ጠቀሜታ አንፃር ነው። አንድ ቋንቋ ለንግድ፣ ለሥራ ቅጥር ወይም ለሌሎች የልማት መስኮች እድሎችን የማይፈጥር ከሆነ፣ በግዴታ ማስተማር የትምህርት ሀብትን ማባከን ሊሆን ይችላል።

ግእዝ በክልሉ ውስጥ ለየትኛውም ኢኮኖሚያዊ ፋይዳ የሚያስገኝ መስክ ውስጥ እንደ ቅድመ ሁኔታ የሚፈለግበት ሁኔታ አለመኖሩ፣ ይህን ቋንቋ የግድ መማር ለምን ያስፈልጋል ለሚለው ጥያቄ ተጨባጭ ምላሽ አይሰጥም። በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ ውስጥ ያለው ባህላዊና ኢኮኖሚያዊ ጥቅም ቋንቋውን የሕዝብ ሊያደርገው የሚችልበት አመክንዮአዊ መሠረት የለውም።

3. የትግበራ ስትራቴጂ እና የሎጂስቲክስ ትንተና
አንድ ቋንቋ በግዴታ የትምህርት ሥርዓት ውስጥ ሲካተት፣ ተግባራዊነቱ የፖለቲካዊ ፍላጎትን ብቻ ሳይሆን፣ የትምህርት ፍልስፍናን ጭምር ማዕከል ማድረግ አለበት።

🔸️ሴኩላሪዝም እና የትምህርት ሥርዓት: ግእዝን ከኦርቶዶክሳዊ ተጽዕኖ ነፃ አውጥቶ በሴኩላር የትምህርት ሥርዓት ውስጥ ማስተማር ይቻል እንደሆነ ትልቅ ጥያቄ ነው። የትምህርት ሥርዓት የሁሉም ማኅበረሰብ መስተዋት መሆን አለበት። ቋንቋው ከሃይማኖት ጋር በቅርብ የተሳሰረ በመሆኑ፣ የመማሪያ ቁሳቁሶችና የመምህራን ሥልጠና ከሃይማኖታዊ ይዘት ነፃ መሆናቸውን ማረጋገጥ እጅግ ፈታኝ ነው።

ቋንቋው በግደታ ለህፃናት በመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤቶች እንዲሰጥ ያነሳሳው ድራይቪንግ ፋክተር ምንድን ነው? እያንዳንዱ ቋንቋ ከጀርባው ያዘለው ባህል እና የበቀለበት ባህል እንደመኖሩ ግእዝን ከኦርቶዶክስ ባህልና ተፅእኖ አላቅቆ ሴኪዩላር አድርጎ ማስተማር ይቻላል? የመርጃ ቁሳቁሶቹ ከሴኪዩላሪዝም መስፈርት አንፃር ፍፁም ከኦርቶዶክስ ተፅእኖ ነፃ ማድረግ ይቻላል? የአማራ ክልል ስቴት ካልቸር ካለው የኦርቶዶክስ መር ስነልቦና አንፃር ምን ያክል ቋንቋው ሴኪዩላር በሆነ መልኩ በት/ቤቶች እንዲሰጥ አፈፃፀሙን ይገመግማል? ከዚህ በፊት በኢትዮጵያ የኦርቶዶክስ ቤተክህነት የትምሀርት ዘርፉን በምትመራበትና በምታስተባብርበት ጊዜ ሙስሊሙ ራሱን ከትምህርት እንዲያርቅ የተፈፀመበትን ነውረኛ ታሪክ የመድገም እድል የለውም ወይ? የትምህርት ቁሳቁሶቹ እና መምህራኑ ሴኪዩላር በሆነ የትምህርት ስርዓት ቀድመው ባልተዘጋጁበት ሁኔታ ህፃናትን በቀሳውስት ከማስተማር አማራጭ የለም። በቂ ሴኪዩላር መምህራን አልተዘጋጁም።

ይህ ካልሆነ ግን፣ በታሪክ ውስጥ እንደታየው የኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን የትምህርት ዘርፉን ስትመራ የነበረውን የሙስሊም ማኅበረሰቦችን ከትምህርት የማራቅ ነውረኛ ታሪክ የመድገም ዕድል ይፈጠራል።

🔸️የሀብት ምደባ (Resource Allocation): የትምህርት ሀብት ውስን በመሆኑ፣ ለግእዝ ቋንቋ ትምህርት የሚያስፈልጉት ሀብቶች (የመምህራን ሥልጠና፣ የመማሪያ መጻሕፍትና ሌሎች ቁሳቁሶች) በሌሎች አንገብጋቢ ትምህርቶች (ለምሳሌ ሳይንስና ቴክኖሎጂ) ላይ የሚያሳድሩት ተጽእኖ በጥንቃቄ መታየት አለበት።

4. የፖለቲካዊ እና ማኅበራዊ ተጽእኖ ግምገማ
አንድ የትምህርት ፖሊሲ፣ በተለይም የቋንቋ ፖሊሲ፣ የብዙኃንንና የአናሳዎችን መብቶች ማክበር አለበት።

🔸️የአናሳዎች መብት: የአማራ ክልል የተለያዩ ብሔር ብሔረሰቦችን ያቀፈ ነው። ግእዝ ቋንቋን በግዴታ ማስተማር የአማራን ማንነት ከኦርቶዶክሳዊነት ጋር የማያያዝ አጀንዳ ካለው፣ የአናሳ ብሔረሰቦች የሆኑትን አገው፣ ቅማንት፣ ኦሮሞ እና አርጎባ ማኅበረሰቦችን ሊያገለል ይችላል። ይህ ደግሞ የፌደራል ሥርዓቱ መሠረት የሆነውን የብዝኃነት መርህ የሚጋፋ ሲሆን፣ የክልሉን ማኅበራዊና ፖለቲካዊ መረጋጋት ሊያናጋ ይችላል።

🔸️የክልል አንድነት እና የማንነት ፍልስፍና: አንድ ክልል ራሱን የሚተነትንበት ፍልስፍና ከአንድ ጠባብ ማንነት (ለምሳሌ አማራነት ወይም ኦርቶዶክሳዊነት) ሲመነጭ፣ የክልሉን ታሪካዊና ባህላዊ ብዝኃነትን የሚክድ ነው። የዚህ ዓይነቱ ፖሊሲ ትግበራ ክልሉ ራሱን የሚበይንበትን እይታ ወደ አንድ አቅጣጫ እንዲያመራ ያደርጋል። በዚህ ረገድ፣ የግእዝ ቋንቋን የትምህርት ሥርዓት አካል የማድረግ ውሳኔ፣ ክልሉን ከልሙጥ አማራነት እና ኦርቶዶክሳዊነት አሰራር ጋር ለማያያዝ በሚንቀሳቀሱ ኃይሎች መሻት ላይ የበቀል ፖሊሲ ያለመሆኑን ማረጋገጥ ፈታኝ ነው።

🔸️ይህ ግእዝ ቋንቋን በክልሉ የትምህርት ስርአት በአስገዳጅነት እንዲክተት የወዋጣው ፖሊሲ ከዚህ በፊት በርካታ ሃይሎች በአማራ ክልል የስቴት ማንነት፣ ስነልቦና፣ ክልሉ የቆመበትን ፍልስፍና፣ አማራ ክልል ራሱን የሚተንትንበትን የሚበይንበትን እይታና እሳቤ ከልሙጥ የአምሃራነት እና የኦርቶዶክስ አንፃር እንዲሆን ይወተውቱ የነበሩ ሃይሎች፣ የአማራ ክልል ስቴታዊ አሰራር ከልሙጥ አማራነት እና ኦርቶዶክሳዊነት gearing machine የሚመንጭ እንዲሆን በይፋም በህቡእም ሲንቀሳቀሱ የነበሩና ያሉ ኃይሎች ድፕ ስቴትስዊ መሻት ላይ የበቀል ፖሊሲ አለመሆኑን የአማራ ክልል ፕሩፍ ማድረግ የሚችል እይደለም

አንድ ቋንቋ በትምህርት ሥርዓት ውስጥ በግዴታ እንዲካተት የሚደረገው ውሳኔ በሰፊ ሳይንሳዊ እና ፍልስፍናዊ ትንታኔዎች ላይ የተመሰረተ መሆን አለበት። የግእዝ ቋንቋን በተመለከተ፣ የሕዝብ ተናጋሪዎች የሌሉት መሆኑ፣ ከኦርቶዶክስ ሃይማኖት ውጭ ያለው ኢኮኖሚያዊ እና ማኅበራዊ ፋይዳ አናሳ መሆኑ፣ እንዲሁም ሴኩላር በሆነ መንገድ ለማስተማር የሚያስችሉ የሎጂስቲክስ እና የትምህርት መሠረተ ልማቶች አለመኖራቸው፣ የግዴታ ትምህርት ፖሊሲው በቂ ጥናትና ማስረጃዎች ላይ የተመሠረተ እንዳልሆነ ያመላክታል። ስለዚህ፣ እንዲህ ያለው ውሳኔ የብዙኃኑን እና የአናሳዎችን መብት ከግምት ውስጥ ማስገባት አለበት።

08/26/2025

ዘመነ ካሴ የዙ 23 አምራች ሳይንቲስቶች ያመረቱትን መሳሪያ እንድተኩሱ ትእዛዝ መስጠቱ ታወቀ። ብልፅግናም ድንጋጤ ላይ መውደቁ ታውቋል።
የፋኖ ረጅም ርቀት ተምዘግዛጊ ሚሳኤሎች አለምን እያስደመሙ ነው። በቅርቡም 4 ኪሎ እንደሚገቡ መነኩሴ ዘመነ ካሴ አሳውቀዋል።

እውነተኞች ነን

የድሉ ቀን ቅርብ ነው

Address

Toronto, ON

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Peace ሰላም posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share