Fact Check Ethiopia

Fact Check Ethiopia Fact Check

የአሜሪካው ፕሬዚዳንት አማካሪ ፀረ-ኢትዮጵያ ኃይሎች ላይ አቋም ወስደዋል ተብሎ የተሰራጨው መረጃ ሐሰተኛ ነው የአሜሪካው ፕሬዚዳንት የመካከለኛው ምሥራቅ፣ የአረብ አገራት እና የአፍሪካ ጉዳዮች...
07/30/2026

የአሜሪካው ፕሬዚዳንት አማካሪ ፀረ-ኢትዮጵያ ኃይሎች ላይ አቋም ወስደዋል ተብሎ የተሰራጨው መረጃ ሐሰተኛ ነው

የአሜሪካው ፕሬዚዳንት የመካከለኛው ምሥራቅ፣ የአረብ አገራት እና የአፍሪካ ጉዳዮች ከፍተኛ አማካሪ የሆኑት ማሳድ ቡሎስ አገራቸው በፀረ-ኢትዮጵያ ኃይሎች ላይ የጠነከረ እርምጃ ትወስዳለች ብለው ተናግረዋል ተብሎ በማህበራዊ ሚዲያ የተሰራጨው መረጃ መሠረት የሌለውና ሐሰተኛ መሆኑን ኢትዮጵያ ቼክ ባደረገው ማጣራት ማረጋገጡን ይፋ አድርጓል፡፡

ከኢትዮ ቼክ ለመመልከት አንደተቻለው ከ193 ሺህ በላይ ተከተዮች ያሉት «ጌትነት አልማው ጥሩነህ» የተባለው የፌስቡክ ገፅ ይህ ከፍተኛ የአሜሪካ መንግሥት ኃላፊ «ፀረ-ኢትዮጵያ አደረጃጀቶች ላይ አሜሪካ እርምጃ እንደምትወስድ ተናግረዋል» በሚል የተሳሳተ መረጃ አጋርቷል።

ይህ የፌስቡክ ገፅ ያሰራጨው መረጃ አሳሳች መሆኑ ሳይታወቅ በበርካታ የማህበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎች መልሶ እንዲሰራጭ እና የህዝብን ትኩረት እንዲስብ ተደርጓል።

ኢትዮጵያ ቼክ ያደረገው ጥልቅ ማጣራት እንደሚያሳየው ማሳድ ቡሎስ በይፋዊ የኤክስ (X) ገፃቸው ላይ ባጋሩት መግለጫ አሜሪካ የተባለውን ዓይነት እርምጃ ትወስዳለች የሚል ንግግር አላደረጉም።

ማሳድ ቡሎስ በሰጡት ቀጥተኛ ማብራሪያ በአፍሪካ ቀንድ ላይ ያተኮረው የአሜሪካ ዲፕሎማሲ «ፀረ-ኢትዮጵያ ጥምረትን ለማጠናከር እየሞከረ ነው» ተብለው በየቦታው የቀረቡት ዘገባዎች ሙሉ በሙሉ ውሸት አሳሳችና ህዝብን የሚያሳስቱ መሆናቸውን በግልጽ አስረድተዋል።

በተጨማሪም አሜሪካ ከኢትዮጵያ እንዲሁም ከሌሎች የአፍሪካ ቀንድና የሰፊው ቀይ ባሕር ቀጣና አገሮች ጋር በጋራ የልማት፣ የሰላምና የደህንነት ጉዳዮች ላይ በቅርበትና በትብብር እየሰራች እንደምትገኝ ገልጸዋል።

የአሜሪካ ዲፕሎማሲ ዋነኛ አላማ ተፎካካሪ ጎራዎችን መፍጠር ወይም የቀጣናውን ቅራኔዎች ማጥበቅ ሳይሆን ግጭቶችን በማስቀረት ዘላቂ ሰላምና ደህንነትን ማረጋገጥ እንደሆነ አብራርተዋል።

በሌላ በኩል መቀመጫውን ፓሪስ ያደረገው «አፍሪካ ሪፖርት» (The Africa Report) የተባለው የዜና ምንጭ በቅርቡ ባወጣው የትንታኔ ዘገባ የአሜሪካ ዲፕሎማሲ በግብፅ-ሶማሊያ-ኤርትራ ምህዋር በኩል እና በኢትዮጵያ-ሶማሊላንድ-እስራኤል ምህዋር በኩል ባለው አህጉራዊ ፖለቲካዊ ውጥረት መካከል ሊወጠር እንደሚችል አመላክቷል።

ይህ የትንታኔ ዘገባ የቀጣናውን ፖለቲካዊ ሁኔታ የሚያስረዳ እንጂ ማሳድ ቡሎስ እርምጃ እወስዳለሁ ብለው የተናገሩትን የሚያረጋግጥ አይደለም።

በፖለቲከኞች፣ በዲፕሎማቶች እና በታዋቂ ሰዎች ስም ያልተናገሩትን ንግግር እንደተናገሩ አስመስሎ ማሰራጨት በማህበራዊ ሚዲያ ላይ ሰፊ ተቀባይነት ለማግኘት የሚደረግ የተለመደ የሐሰተኛ መረጃ (Disinformation) ስልት ነው።

ስለሆነም የማህበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎች እንደዚህ ያሉ አጠራጣሪና የፖለቲካ ትኩሳት ያላቸውን መረጃዎች በሚያነቡበት ጊዜ፣ መረጃው የወጣበትን ድረ-ገፅ ታማኝነትና ትክክለኛነት አስቀድመው እንዲያረጋግጡ እና ያልተረጋገጡ መረጃዎችን ከማጋራት እንዲቆጠቡ ይመከራል።
[መረጃው የኢትዮ ቼክ ነው፡፡]

 #ያረጋግጡ!በአሁኑ ወቅት በዓለም አቀፍ ደረጃም ሆነ በሀገራችን በስፋት እየተስተዋለ የመጣው የሳይበር ስጋት "ዲጂታል ምስል እና ድምፅ ማጭበርበር" (Deepfake Technology) ነው፡፡...
07/29/2026

#ያረጋግጡ!

በአሁኑ ወቅት በዓለም አቀፍ ደረጃም ሆነ በሀገራችን በስፋት እየተስተዋለ የመጣው የሳይበር ስጋት "ዲጂታል ምስል እና ድምፅ ማጭበርበር" (Deepfake Technology) ነው፡፡

ዲጂታል ምስል እና ድምፅ ማጭበርበር ማለት የሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) ቴክኖሎጂዎችን በመጠቀም የአንድን ሰው ትክክለኛ ገፅታ፣ ድምፅ ወይም የእንቅስቃሴ ቪዲዮ በከፍተኛ ጥራት አስመስሎ በመስራት፣ ያላላቸውን ንግግሮች እንዳሉ አስመስሎ ማቅረብ ወይም ያልተገበሩትን ድርጊት እንደፈፀሙ አድርጎ ማሳየት ነው።

ቀደም ሲል እንደነዚህ አይነት ሃሰተኛ ምስሎችን ወይም ቪዲዮዎችን በቀላሉ መለየት ይቻል ነበር፤ በአሁኑ ወቅት ግን ቴክኖሎጂው እጅግ በመራቀቁ ምክንያት የተሰራጨው ምስል ወይም ድምፅ እውነተኛ ይሁን ሀሰተኛ ለመለየት አዳጋች ሆኗል።

በሀገራችን የዲጂታል ፋይናንስ እና የማህበራዊ ሚዲያ አጠቃቀም በከፍተኛ ፍጥነት እያደገ ከመጣበት ሁኔታ ጋር ተያይዞ፣ ይህ አሰራር በሶስት ዋና ዋና ዘርፎች ትልቅ ስጋት ደቅኗል፡-

• የፋይናንስ ማጭበርበር፡ የቅርብ ዘመድ ወይም ወዳጅን ድምፅ በ AI አስመስሎ በመስራት (Voice Cloning) "አስቸኳይ ችግር ገጥሞኝ ነው" በሚል በቴሌብር ወይም በሞባይል ባንኪንግ ገንዘብ ማታለል፤

• ማህበራዊ ውጥረት መፍጠር፡ የታዋቂ ሰዎችን ወይም የመንግስት ሀላፊዎችን ገፅታ እና ድምፅ በመጠቀም ህዝብን የሚያጋጩ ሀሰተኛ መረጃዎችን ማሰራጨት፤

• የግለሰቦች ስም ማጥፋት፡ የሰዎችን ፎቶ አግባብ ከሌላቸው ምስሎች ጋር በማቀናጀት ስም የማጥፋት እና የማስፈራራት ድርጊቶችን መፈፀም።

?

1.በስልክ ደውለው ያረጋግጡ፡ በድምፅ መልዕክት ወይም በቪዲዮ ገንዘብ እንዲላክ ከተጠየቁ፣ ወዲያውኑ መደበኛ የስልክ ጥሪ በማድረግ ትክክለኛነቱን ያረጋግጡ፤
2.ምንጭ ያረጋግጡ፡ መረጃዎችን ከይፋዊ የመንግስት እና ከታመኑ የመገናኛ ብዙሃን ገፆች ያረጋግጡ፤

3. ጥንቃቄ ያድርጉ፡ በቪዲዮዎች ላይ ከተፈጥሮ ውጭ የሆኑ የአይን፣ የከንፈር ወይም የድምፅ መዛነቆችን በጥንቃቄ ያስተውሉ፤
4. ከማጋራት ይቆጠቡ፡ ያልተረጋገጡ እና አጠራጣሪ ቪዲዮዎችን ወይም የድምፅ ፋይሎችን ለሌሎች ከመላክ ይታቀቡ።

ወርቃማው ህግ፡ "ያዩትን እና የሰሙትን ሁሉ ወዲያውኑ አይመኑ፤ ከማጋራትዎ በፊት ያረጋግጡ!"
INSA- የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር

  በአሜሪካ የአማራ ማህበር ስም የተሰራጨው መግለጫ ሐሰተኛ መሆኑን ተቋሙ አስታወቀ በማህበራዊ ሚዲያ ገጾች ላይ ከሰሞኑ በስፋት ሲሰራጭ የነበረውንና በአሜሪካ አማራ ማህበርን (AAA) የደብዳ...
07/28/2026

በአሜሪካ የአማራ ማህበር ስም የተሰራጨው መግለጫ ሐሰተኛ መሆኑን ተቋሙ አስታወቀ

በማህበራዊ ሚዲያ ገጾች ላይ ከሰሞኑ በስፋት ሲሰራጭ የነበረውንና በአሜሪካ አማራ ማህበርን (AAA) የደብዳቤ ቅርፅ እና አርማ የያዘውን መግለጫ አስመልክቶ ማህበሩ በዛሬው ዕለት ለኢትዮጵያ ቼክ መረጃ አጋርቷል።

በርካታ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች ሐምሌ 16 ቀን 2018 ዓ.ም. የሚል ቀን የተጻፈበትና የአሜሪካ አማራ ማህበርን ህጋዊ አርማ የያዘ የአቋም መግለጫ በሰፊው ሲያሰራጩ ቆይተዋል። ይህ በስፋት የተሰራጨው መግለጫ ስለ አማራ ሕዝብ የትግል አቅጣጫና የወቅቱ የፖለቲካ ሁኔታዎች ላይ ያተኮሩ የተለያዩ ሀሳቦችን ያካተተ ነው ተብሎ ነበር።

ነገር ግን መረጃው በስፋት መሰራጨቱን ተከትሎ የአሜሪካ አማራ ማህበር በጉዳዩ ላይ አስቸኳይ ይፋዊ ማብራሪያና ማሳሰቢያ ሰጥቷል።

ማህበሩ በላከው መግለጫ መሰረት በማህበራዊ ሚዲያ ላይ እየተዘዋወረ ያለው ሰነድ በማህበሩ ያልተዘጋጀና ሙሉ በሙሉ የተፈበረከ ሐሰተኛ መረጃ መሆኑን ጠቁሟል።

ድርጅቱ ምስሉ ላይ ትልቅ የቀይ “FAKE” (ሐሰተኛ) የሚል ማህተም በማስቀመጥ ደጋፊዎቹ እና የሕዝብ አባላት በተሳሳተ መረጃ እንዳይደናገሩ አሳስቧል።

እንደ ማህበሩ ገለጻ ከሆነ ይህ የተቀናበረ ሐሰተኛ መግለጫ የመነጨውና መጀመሪያ የተሰራጨው ከመንግስት ጋር ግንኙነት ካላቸው አካላት ወይም "የገዥው አካል አፈቀላጤዎች ገጽ ላይ ነው" ብሏል።

በተጨማሪም በአሜሪካ የአማራ ማህበር ማንኛውም አይነት ይፋዊ መግለጫ፣ መረጃና አቋም የሚለቀቀው በድርጅቱ ህጋዊ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች እና በኦፊሴላዊ ድረ-ገጹ ላይ ብቻ መሆኑን አብራርቷል።

በማህበራዊ ሚዲያ ላይ ሲሰራጭ የነበረውና የማህበሩ አርማ ያለበት መግለጫ ሙሉ በሙሉ የተፈበረከ መሆኑን ድርጅቱ በመግለፁ የማህበራዊ ሚድያ ተጠቃሚዎች ያልተረጋገጡ መረጃዎችን ከማሰራጨት እንዲቆጠቡና መረጃዎችን ከተቋማቱ ህጋዊ ገጾች ብቻ እንዲከታተሉ ይመከራል።

ኢትዮጵያ ቼክ!

በመደበኛ የሚዲያ አውታሮች እና በማህበራዊ  ሚዲያ አውታሮች ላይ የህግ ጥሰት፣ የሙያ ስነ-ምግባር ግድፈት፣ የጥላቻ ንግግር እና የሐሰተኛ መረጃ ሲመለከቱ 👉በEMA App በሞባይል መተግበሪያ ...
06/29/2026

በመደበኛ የሚዲያ አውታሮች እና በማህበራዊ ሚዲያ አውታሮች ላይ የህግ ጥሰት፣ የሙያ ስነ-ምግባር ግድፈት፣ የጥላቻ ንግግር እና የሐሰተኛ መረጃ ሲመለከቱ

👉በEMA App በሞባይል መተግበሪያ
👉በhttps://compliant.ema.gov.et/ web port መተግበሪያ
👉በነፃ የጥሪ መስመር በ9192

"በእጅ ስልክዎ፣በታብሌት፣ በዴስክቶፕ፣ በላፕቶፕ እና በሁሉም የዲጂታልና የቋንቋ አማራጮች" ለባለሥልጣኑ በማሳወቅ ሀገራዊ ግዴታዎን ይወጡ!!



 ሀሰተኛ መረጃ ከሚያጋሩ ገፆች መካከል  በመጀመሪያው ምስል ላይ የሚታየው የፌስ ቡከ ገፅ አንዱ ነው።የጋዜጣውን ትክክለኛ መረጃ በተከታዩ ሊንክ ይመልከቱት።https://www.facebook.c...
06/02/2026



ሀሰተኛ መረጃ ከሚያጋሩ ገፆች መካከል በመጀመሪያው ምስል ላይ የሚታየው የፌስ ቡከ ገፅ አንዱ ነው።

የጋዜጣውን ትክክለኛ መረጃ በተከታዩ ሊንክ ይመልከቱት።

https://www.facebook.com/share/193zUt1L9k/?mibextid=wwXIfr

ጄነራል ታደሰ ወረደ ታገቱ በሚል የተሰራጨው መረጃ ሀሰተኛ መሆኑን ተናገሩ የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዚዳንት የነበሩት ጄነራል ታደሰ ወረደ መታገታቸውን ወይም የቁም እስረኛ መደረጋቸውን ...
05/29/2026

ጄነራል ታደሰ ወረደ ታገቱ በሚል የተሰራጨው መረጃ ሀሰተኛ መሆኑን ተናገሩ

የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዚዳንት የነበሩት ጄነራል ታደሰ ወረደ መታገታቸውን ወይም የቁም እስረኛ መደረጋቸውን አስመልክቶ በማህበራዊ ሚዲያ ላይ በስፋት እየተሰራጨ ያለው መረጃ ሀሰተኛ መሆኑን ለኢትዮጵያ ቼክ አረጋግጠዋል።

ይህ መረጃ ባለፉት ጥቂት ቀናት በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ተከታዮች ባፈሩ የፌስቡክ ገጾች እና ግለሰቦች አማካኝነት በከፍተኛ ሁኔታ ሲጋራ ቆይቷል።

ከመረጃው ዋነኛ አሰራጮች መካከል ወደ 480 ሺህ የሚጠጉ ተከታዮች ያሉት "አንዳፍታ" የተሰኘው የፌስቡክ ገጽ እና ከ507 ሺህ በላይ ተከታዮች ያሉት "አባይ ሚዲያ" የፌስቡክ ገጽ ይገኙበታል። በተጨማሪም ከ161 ሺህ በላይ ተከታዮች ያሉት "ኤርሚያስ ለገሰ ዋቅጅራ" የተባለው ግለሰብ የፌስቡክ ገጽ ጄነራል ታደሰ የቁም እስረኛ እንደሆኑ የሚገልጽ ተመሳሳይ ዘገባ ከሌላ ገፅ ወስዶ አጋርቷል።

ኢትዮጵያ ቼክ ጉዳዩ በማህበራዊ ሚዲያ ላይ መነጋገሪያ መሆኑን ተከትሎ እውነተኝነቱን ለማረጋገጥ በቀጥታ ከጄነራል ታደሰ ወረደ ጋር በስልክ ተገናኝቶ የጠየቀ ሲሆን በማጣራቱም ጄነራሉ እንዳልታገቱና የቁም እስረኛም እንዳልተደረጉ ምላሽ ሰጥተዋል።

በርካታ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች ለዘገባቸው ዋቢ ያደረጉት «አፍሪካ ኢንተለጀንስ» (Africa Intelligence) የተሰኘው የዜና ተቋም መሆኑን ቢጠቅሱም ተቋሙ ባወጣው ዘገባ ላይ እሳቸው ስለመታገታቸውም ሆነ የቁም እስረኛ ስለመሆናቸው የጠቀሰው ነገር እንደሌለ አብራርተዋል፣ ይህንን ኢትዮጵያ ቼክም አረጋግጧል።

ጄነራል ታደሰ ወረደ ለኢትዮጵያ ቼክ በሰጡት የቀጥታ ምላሽ "ታግተሃል አልያም የቁም እስረኛ ሆነሃል ለሚለው አሁን እያናገርከኝ ነው፤ እኔ አልታገትኩም፣ የቁም እስረኛም አልተደረግኩም፤ የAfrica Intelligence ያወጣው ዘገባ ላይም እኔ እንደታገትኩም አልያም የቁም እስረኛ እንደሆንኩ አልገለጸም" ብለዋል።

በማህበራዊ ሚዲያ ላይ የታዋቂ ሰዎችን እና የፖለቲካ መሪዎችን ስም በመጠቀም ያልተናገሩትን እንደተናገሩ፣ ያልሆኑትን እንደሆኑ አድርጎ ማሰራጨት የተለመደ የሀሰተኛ መረጃ ስልት መሆኑ ይታወቃል።

የማህበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎች መሰል አጠራጣሪ እና የፖለቲካ ትኩሳት ያላቸውን መረጃዎች ሲያነቡ መረጃው የወጣበትን ድረ-ገጽ ታማኝነት እንዲያረጋግጡ እና ያልተረጋገጡ መረጃዎችን ከማጋራት እንዲቆጠቡ እንመክራለን። via:- ኢትዮጵያ ቼክ!
Fact Check Ethiopia

ዶ/ር አርከበ እቁባይ 'African Pulse' ለተባለ ሚዲያ ሰጡት ተብሎ በስፋት የተሰራጨው ጽሑፍ እና ቃለ-ምልልስ በሀሰት የተፈበረከ ነውየቀድሞው የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ እና የጠቅላይ...
05/25/2026

ዶ/ር አርከበ እቁባይ 'African Pulse' ለተባለ ሚዲያ ሰጡት ተብሎ በስፋት የተሰራጨው ጽሑፍ እና ቃለ-ምልልስ በሀሰት የተፈበረከ ነው

የቀድሞው የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ እና የጠቅላይ ሚኒስትሩ ልዩ አማካሪ የነበሩት ዶ/ር አርከበ እቁባይ “አፍሪካን ፐልስ” (African Pulse) ለተባለ ድረ-ገጽ ሰጡት የተባለው እና በማህበራዊ ሚዲያ በከፍተኛ ሁኔታ እየተሰራጨ ያለው ፖለቲካዊ ትንታኔ እና አስተያየትን በተመለከተ ኢትዮጵያ ቼክ ባደረገው ማጣራት እየተሰራጨ ያለው አስተያየትና ትንታኔ ከእሳቸው ያልወጣ እና በሀሰት የተፈበረከ መሆኑን ማረጋገጣቸውን ይፋ አድርጓል፡፡

'African Pulse' በተሰኘው ድረ-ገጽ ላይ “ስትራቴጂካዊ ራስን ማጥፋት - ዶ/ር አርከበ እቁባይ የህወሓትን አመራር አምርረው ተቹ” በሚል ርዕስ የተጻፈ ጽሑፍ በዛሬው ዕለት ወጥቷል። ይህ የፈጠራ ጽሑፍ ዶ/ር አርከበን በማስመሰል በርካታ ከባድ የፖለቲካ ትችቶችን የቀድሞ ድርጅታቸው ህወሓት ላይ እንደሰነዘሩ አድርጎ ያቀርባል።

ጽሑፉን ይበልጥ እውነተኛ ለማስመሰልም ዶ/ር አርከበ ስለ ጦርነቱ አጀማመር፣ ስለ ፖለቲካዊ ስህተቶች እና ስለ ድርጅቱ መጻኢ ዕጣ ፈንታ ተናግረዋል ያላቸውን የሀሰት ሀሳቦች አካቷል።

በዚህም የቀድሞ የትግል ጓዶቻቸው በስትራቴጂካዊ ድክመት እና በፖለቲካዊ እልህ ውስጥ ወድቀው የትግራይን ህዝብ ህልውና አደጋ ላይ እንደጣሉ እና ጦርነቱ የተጀመረው በስሜት እንጂ በፖለቲካዊ ስሌት እና በበቂ ዝግጅት እንዳልነበረ በጽሑፉ ላይ ተጠቅሷል።

በተጨማሪም አመራሩ የፌደራል መንግስቱን እና የሌሎች ኃይሎችን ጥምረት መገመት አለመቻሉን እንደተቹ፣ እንዲሁም የድርጅቱ አመራሮች ለለውጥ ዝግጁ እንዳልሆኑ እና አሁን ባለበት የዲፕሎማሲ እና የኢኮኖሚ ውድቀት ውስጥ ሆኖ ዳግም ስለ ጦርነት ማሰብ የድርጅቱን ህልውና ሙሉ በሙሉ የሚያጠፋ እንደሆነ አድርጎ አስነብቧል።

ይህ ዶ/ር አርከበ ሰጡት የተባለው የፈጠራ ጽሑፍ በዋናነት ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ተከታዮች ባፈሩ የፌስቡክ ገጾች እና ግለሰቦች አማካኝነት በስፋት ተጋርቷል። ከእነዚህም መካከል ወደ 186 ሺህ የሚጠጉ ተከታዮች ያሉት ጄዚራ አፍሪካ የተባለ ገፅ ይህንኑ ሀሰተኛ መረጃ አጋርቷል።

በተመሳሳይ ከ91 ሺህ በላይ ተከታዮች ያሉት ቬነስ ዜና የተሰኘ የፌስቡክ ገፅ ጽሑፉን ያሰራጨ ሲሆን ከ33 ሺህ በላይ ተከታዮች ያሉት Nebyat Alemu የተባለ ገፅም ይህንኑ መረጃ ተቀብሎ ለተከታዮቹ አጋርቷል።

እነዚህ ገጾች በአጠቃላይ በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ተከታዮች ያሏቸው በመሆኑ ይህ ሀሰተኛ መረጃ ብዙሃን ዘንድ እንዲደርስ እና በአንባቢዎች ዘንድ ከፍተኛ ብዥታ እንዲፈጥር ምክንያት ሆኗል።

ኢትዮጵያ ቼክ ይህ መረጃ በማህበራዊ ሚዲያ ላይ መነጋገሪያ መሆኑን ተከትሎ የጉዳዩን እውነተኛነት ለማረጋገጥ በቀጥታ ዶ/ር አርከበ እቁባይን ጠይቋል። በማጣራቱም ዶ/ር አርከበ 'African Pulse.org' ለሚባለው ድረ-ገጽ ምንም ዓይነት ቃለ-ምልልስም ሆነ የጽሑፍ አስተያየት አለመስጠታቸውን አረጋግጠዋል።

ዶ/ር አርከበ ለኢትዮጵያ ቼክ በላኩት ቀጥተኛ ምላሽ ላይ ለ Pulse.org ቃለ-ምልልስ ሰጥተው እንደሆነ ተጠይቀው እንደነበር ገልጸው ምንም አይነት ቃለ-ምልልስ አለመስጠታቸውን አስረግጠው ተናግረዋል።

በማህበራዊ ሚዲያ ላይ ታዋቂ ሰዎችን እና የፖለቲካ ሰዎችን ስም በመጠቀም ያልተናገሩትን እንደተናገሩ አድርጎ ማሰራጨት የተለመደ የሀሰተኛ መረጃ ስልት ነው።

የማህበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎች እንደዚህ አይነት አጠራጣሪ እና የፖለቲካ ትኩሳት ያላቸውን መረጃዎች ሲያነቡ መረጃው የወጣበትን ድረ-ገጽ ታማኝነት እንዲያረጋግጡ እና ያልተረጋገጡ መረጃዎችን ከማጋራት እንዲቆጠቡ እንመክራለን።

መረጃው ሙሉ ለሙሉ የኢትዮጵያ ቼክ ነው፡፡
Fact Check Ethiopia

  : የገንዘብ ሚኒስቴር የተቋሙን ስምና መለያ በመጠቀም " ለክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች ስለ ስራ ግብር ቅናሽ እና የደመወዝ መጠን መሰረት ያደረገ ማሻሻያ " ተብሎ በማህበራዊ ሚዲያ ላይ እ...
05/21/2026

: የገንዘብ ሚኒስቴር የተቋሙን ስምና መለያ በመጠቀም " ለክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች ስለ ስራ ግብር ቅናሽ እና የደመወዝ መጠን መሰረት ያደረገ ማሻሻያ " ተብሎ በማህበራዊ ሚዲያ ላይ እየተሰራጨ የሚገኘው መረጃ ሀሰተኛ ነው ሲል አሳውቋል።
Fact Check Ethiopia

 #ሀሰተኛ!Fact Check Ethiopiaበኢፌዲሪ የፌዴሬሽን ምክርቤት ስም በወልቃይት ጉዳይ ያወጣው መግለጫ በሚል በማኀበራዊ ሚዲያ የሚዟዟረው ደብዳቤ በተመለከተ ምክር ቤቱ ምላሽ ሰጥቷል፡፡...
05/20/2026

#ሀሰተኛ!
Fact Check Ethiopia
በኢፌዲሪ የፌዴሬሽን ምክርቤት ስም በወልቃይት ጉዳይ ያወጣው መግለጫ በሚል በማኀበራዊ ሚዲያ የሚዟዟረው ደብዳቤ በተመለከተ ምክር ቤቱ ምላሽ ሰጥቷል፡፡

በምክር ቤቱ ስም ወጣ በሚል የተሰራጨው መግለጫ ፍጹም ሐሰት ሲሆን በወልቃይት ጉዳይ የተሰጠ መግለጫ የሌለ መሆኑንም ምክር ቤቱ አስታውቋል፡፡

04/26/2026

#ጥቆማ!

የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት ለምልመላና ለቅጥር፣ የደኅንነት ማስጠንቀቂያ ለመስጠትና ዜጎች መረጃዎችን እንዲያጋሩ የሚያስችል የኮምዩኒኬሽን ፕላትፎርም ይፋ አድርጓል፡፡

ይህን ተከትሎም በርካታ ጥቆማዎች እየደረሱት ነው፡፡

በብሔራዊ ደኅንነት፣ ጥቅምና በሕዝብ ሥነ-ልቦና ላይ ከፍተኛ ጉዳት የሚያስከትሉ የሽብር ወንጀሎች፣ የኢኮኖሚ አሻጥሮች፣በቁልፍ መሠረተ-ልማቶችና የተለያዩ ሁነቶች ዙሪያ ያነጣጠሩ የጥቃት ሙከራዎች፣ከውጭ ኃይሎች ጋር የሚቀናጁ የጥፋት ሴራዎች እንዲሁም የተዛቡ ኢንፎርሜሽኖችን የተመለከቱ ተዓማኒና ተጨባጭ መረጃዎችን niss.gov.et report information ወይም የመረጃ ሪፖርት በሚለው የጥቆማ መስጫ ሳጥን ያጋሩ፡፡

#ለሀገርዎ ብሔራዊ ደኅንነት መረጋገጥ የዜግነት ድርሻዎን ይወጡ፤ለተጨማሪ መረጃዎች የማኅበራዊ ትስስር ገፆቻችን ይጎብኙ!

ኮምዩኒኬሽን ፕላትፎርም፡- https://niss.gov.et

National Intelligence and Security Service -Ethiopia

Address

Toronto, ON
V5A2Z6

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Fact Check Ethiopia posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share