Abenezer Ayele official

Abenezer Ayele official Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Abenezer Ayele official, Digital creator, Whistler, BC.

መሪነት ከፊት መቆም ብቻ አይደለም፤ ብርሃን ሆኖ መንገዱን ማሳየትም እንጂ!በአመራር ዓለም ውስጥ ተቋማዊ ሽግግርንና እውነተኛ ለውጥን (Transformation) ማምጣት የሚቻለው መሪው ሥልጣኑ...
03/26/2026

መሪነት ከፊት መቆም ብቻ አይደለም፤ ብርሃን ሆኖ መንገዱን ማሳየትም እንጂ!

በአመራር ዓለም ውስጥ ተቋማዊ ሽግግርንና እውነተኛ ለውጥን (Transformation) ማምጣት የሚቻለው መሪው ሥልጣኑን እንደ ዱላ ሳይሆን ውስጣዊ ማንነቱን እንደ ብርሃን ሲጠቀምበት ብቻ ነው። ይህ ጉዞ የሚጀምረው መሪው ሌሎች ገና ያላዩትን አድማስ ቀድሞ በሚያይበት ራዕይና ግልጽ ዓላማ ውስጥ ነው። መሪ ማለት "ወዴት እየሄድን ነው?" ለሚለው የብዙኃኑ ጥያቄ ትርጉም ያለውና የሚያነቃቃ ምላሽ መስጠት የሚችል ባለራዕይ ሲሆን ይህ ግልጽ አቅጣጫ በቡድኑ ውስጥ የሚፈጠሩ መዘናጋቶችንና ግጭቶችን በማስወገድ ሁሉም ወደ አንድ ግብ እንዲተም ያደርጋል። ራዕይ የሌለው መሪ እንደ ጨለማ መንገድ መሪ ነው፤ ራዕይ ያለው ግን የተከታዮቹን መንፈስ ቀስቅሶ ወደማይታሰብ ስኬት ይመራቸዋል።

የዚህ ሁሉ ስኬት መሠረትና የአመራር ቋጥኝ ደግሞ ታማኝነትና ሥነ-ምግባር ነው። መሪው የሚናገረውን የሚኖርና ማንም በማያየው ስውር ስፍራ እንኳ ሳይቀር እውነትን የሚከተል ሲሆን በሰዎች ዘንድ የማይናወጥ ተዐማኒነትን (Trust) ይገነባል። የግል ጥቅሙን ከጋራ ዓላማ በታች የሚያደርግ መሪ ተከታዮቹ ለውጡን በሙሉ ልባቸው እንዲደግፉና መስዋዕትነት እንዲከፍሉ የማድረግ ኃይል አለው። ያለ ታማኝነት የሚገነባ አመራር በአሸዋ ላይ እንደቆመ ቤት በመሆኑ ለውጥ አምጪ መሪ መጀመሪያ የራሱን ቃልና ሕይወት በማጽናት የተከታዮቹን ልብ ድል ያደርጋል።

በተጨማሪም በጭንቀትና በግርግር ወቅት የማይደነግጥ፣ የራሱንና የሌሎችን ስሜት በጥልቀት መረዳት የሚችል የስሜት ብልህነት (Emotional Intelligence) ለአንድ መሪ ወሳኝ መሣሪያው ነው። እንዲህ ያለው መሪ የሰዎችን ስጋትና ፍላጎት በአንክሮ የሚያዳምጥ በመሆኑ በቡድኑ ውስጥ ንትርክ ሳይሆን መግባባት የሰፈነበት የተረጋጋ የሥራ ድባብ ይፈጥራል። ይህ ባሕርይ ከውሳኔ ሰጪነት ባለፈ ሰብዓዊ ትስስርን የሚያጠናክር በመሆኑ ለውጥ የሚያመጣው ግፊት ከማስገደድ ሳይሆን ከመረዳዳት እንዲቀዳ ያደርጋል። ስሜቱን የሚገዛ መሪ ተቋሙን ከማዕበል የመታደግ ብቃት ይኖረዋል።

ለውጥ በባሕርይው ፈታኝና መሰናክል የበዛበት በመሆኑ መሪው የማይበገር ስብዕና ወይም ቁርጠኝነትና ጽናት ሊኖረው ይገባል። ከባድ ውሳኔዎችን ለመወሰን የማይፈራና ከውድቀት ተምሮ ዳግም የሚነሳ መሪ ተከታዮቹ ተስፋ በቆረጡበት ወቅት እንደ ዐለት ጸንቶ በመቆም ለቡድኑ ብርታትን ይሰጣል። ይህ ጽናት በችግር ጊዜ ሰዎችን አንድ አድርጎ የሚያቆይ ማጣበቂያ ሲሆን መሪው ለሚቆምለት ዓላማ ማንኛውንም ዋጋ ለመክፈል ዝግጁ መሆኑን በተግባር ሲያሳይ ተከታዮቹም የእርሱን ፈር ተከትለው የማይቻለውን ተራራ ይወጣሉ።

በመጨረሻም እውነተኛ መሪ ሥልጣን የሚቀማ ሳይሆን ሥልጣን የሚያካፍል ሰዎችን የማብቃት ታላቅ ጥበብ ሊኖረው ይገባል። ዋነኛ ሥራው ተከታዮችን ማፍራት ሳይሆን መሪዎችን መቅረጽ በመሆኑ ለሰዎች ውክልና በመስጠትና ችሎታቸውን በማሳደግ ላይ ያተኩራል። መሪው ባይኖር እንኳ ተቋሙ በላቀ ሁኔታ የሚቀጥልበትን ተተኪነት የሚያረጋግጠው ይህ ባሕርይ ነው። ሀብትና ቴክኖሎጂ ተራ ቁሳቁሶች ሲሆኑ እነዚህን አስተባብሮ ታላቅ ውጤት የሚያመጣው ግን የሰዎችን ነፍስ ማንቀሳቀስ የሚችል መሪ ነው።

ዛዲግ አብርሃ
የአፍሌክስ ፕሬዝደንት

የተሰበሩ አጥንቶችን በደቂቃዎች ውስጥ የሚገጥም ግኝት ይፋ ሆነ***********የቻይና ተመራማሪዎች ከአጥንት ስብራት ለማገገም ወራት ይፈጅ የነበረውን ሂደት የሚቀይር በ3 ደቂቃዎች ውስጥ የተ...
10/01/2025

የተሰበሩ አጥንቶችን በደቂቃዎች ውስጥ የሚገጥም ግኝት ይፋ ሆነ
***********

የቻይና ተመራማሪዎች ከአጥንት ስብራት ለማገገም ወራት ይፈጅ የነበረውን ሂደት የሚቀይር በ3 ደቂቃዎች ውስጥ የተሰበረ አጥንትን የሚገጥም ግኝት ይፋ አድርገዋል፡፡

'ቦን -02' የሚል ስያሜ የተሰጠው ይህ ግኝት ተጨማሪ ቀዶ ጥገና ሳያስፈልግ የተሰበሩ አጥንቶችን የሚገጥም ነው፡፡

በሃንግዙ ሰር ሩን ሾው ሆስፒታል የአጥንት ሕክምና ባለሙያ የሆኑት ሊን ዢያንፌንግ እንደገለጹት፤ ሕክምናው በመርፌ መልክ የሚሰጥ እና የተሰበሩ አጥንቶችን በደቂቃዎች ውስጥ አንድ ላይ እንዲጣበቁ የሚያደርግ ነው።

'ቦን 02' በሰው አካል ውስጥ ከገባ በኋላ በተፈጥሮ መንገድ እንዲዋሃድ ተደርጎ መሰራቱም ተመላክቷል።

በመሆኑም ከዚህ በፊት ይደረግ እንደነበረው ማጣበቂያውን ለማስወገድ ሁለተኛ ቀዶ ጥገና ባለማስፈለጉም የኢንፌክሽን አደጋን ይቀንሳል ነው የተባለው።

በ'ዠይጂያንግ' ዩኒቨርሲቲ ተመራማሪዎች በተሰራው በዚህ ግኝትም ከ150 በላይ የሚሆኑ ሰዎች ሕክምና በተሳካ ሁኔታ መካሄዱን ኦዲቲ ሴንትራል ዘግቧል።

በሴራን ታደሰ

Abenezer Ayele
Abenezer Ayele official

Dilla 🇪🇹Ethiopia ....
09/15/2025

Dilla 🇪🇹Ethiopia ....

1.የሰውን ደም የሚያፈስስ ሁሉ ደሙ ይፈስሳልሰውን በእግዚአብሔር መልክ ፈጥሮታልና።ዘፍጥረት 9:6📌.የሰውን ደም አታፍሱ2.ከፀሐይ በታችም የሚደረገውን ግፍ ሁሉ አየሁ፤ እነሆም፥ የተገፉት ሰዎ...
08/27/2025

1.የሰውን ደም የሚያፈስስ ሁሉ ደሙ ይፈስሳል
ሰውን በእግዚአብሔር መልክ ፈጥሮታልና።
ዘፍጥረት 9:6
📌.የሰውን ደም አታፍሱ

2.ከፀሐይ በታችም የሚደረገውን ግፍ ሁሉ አየሁ፤ እነሆም፥ የተገፉት ሰዎች እንባ ነበረ
መክብብ 4:1
📌 ሰውን በግፍ አታስለቅሱ

3.እርሻችሁን ያጨዱት የሠራተኞች ደመወዝ(ላብ) በእናንተ ተቀምቶ ይጮኻል፥ የአጫጆችም ድምፅ
ሁሉን ቻይ ወደ ሆነው ጌታ ጆሮ ገብቶአል።
ያዕቆብ 5:4
📌 የሰውን ደመወዝ (ላብ) አትከልክሉ

'' ሰው ከሰሪው ጋር ካልተገናኘ....በመኖር ብዛት ብቻ የማይሞላው ክፍተት አለ....መገናኘት ይሁንልን .....🙏
08/23/2025

'' ሰው ከሰሪው ጋር ካልተገናኘ....በመኖር ብዛት ብቻ የማይሞላው ክፍተት አለ....

መገናኘት ይሁንልን .....🙏

Address

Whistler, BC

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Abenezer Ayele official posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share