Amhara Plus "አማራ ላይጨርስ አይጀምርም"

የክልሉ የልማት ድርጅቶች በየዘርፋቸው ጎልብተው በመውጣት በጦርነት የደቀቀውን ክልል መልሶ እንዲያገግም የበኩላቸውን ድርሻ መወጣት ይኖርባቸዋል። የልማት ድርጅቶች ሲቋቋሙ ዋና ዓላማቸውም እራሳ...
23/02/2024

የክልሉ የልማት ድርጅቶች በየዘርፋቸው ጎልብተው በመውጣት በጦርነት የደቀቀውን ክልል መልሶ እንዲያገግም የበኩላቸውን ድርሻ መወጣት ይኖርባቸዋል። የልማት ድርጅቶች ሲቋቋሙ ዋና ዓላማቸውም እራሳቸውን እያሳደጉ በተቋቋሙለት ዘርፍ በክልሉ ልማት ማፋጠን ነው። ለዚህ ደግሞ በቂ ድጋፍ እንዲሁም ጥብቅ ክትትል ሊደረግላቸው ይገባል።

ለአማራ ህዝብ እታገላለሁ የሚል ሀይል ሁሉ ግጭትን አስወግዶ በሰላም መወያዬት ይኖርበታል።
20/02/2024

ለአማራ ህዝብ እታገላለሁ የሚል ሀይል ሁሉ ግጭትን አስወግዶ በሰላም መወያዬት ይኖርበታል።

በአማራ ክልል ዘላቂ ሰላም እንዲረጋገጥ አጥፊ ግጭቶች ሊቆሙ ይገባል!

ሰላም ለሁለንተናዊ ለውጥ ቁልፍ ሚና አለው። በክልላችን በተሟላ ደረጃ ሰላም መስፍኑ አማራጭ የሌለዉ የወል ሀሳብ ሊሆን ይገባል፡፡

ዘለቄታ ያለውን ሰላም ለመገንባትም ያጋጠሙ ዝንፈቶችን በዉይይት ማረም አስፈላጊ ነዉ። ይህ እዉን እንዲሆንም የሁሉንም የህብረተሰብ ክፍል ርብርብ ይሻል።

በክልላችን የተፈጠረዉን አንጻራዊ ሰላም ለማጽናት በማህበረሰቡ ውስጥ ግጭት መነሻ የሆኑ መልከዓ ብዙ ምክንያቶችን ለማወቅ አስፈላጊ ዉይይቶች ተደርገዋል፡፡ እየተደረጉም ነዉ። ከዚህ ባሻግር ተጨማሪ ግጭቶች እንዳይከሰቱ መከላከያ ይሆን ዘንድ ስልቶችን መበንደፍ የሀገር የመከላከያ ሰራዊት፣ የክልላችን አመራርና የጸጥታ ሀይል ሌት ተቀን ያለ እረፍት እየሰራ ይገኛል።

ይሁን እንጅ በክልላችን አንዳንድ አካባቢዎች የሚንቀሳቀሱ ጸረ ሰላም ሀይሎች አውዳሚ ረብሻ በመከተል በክልላችን ቀውስ እንዲከሰትና በህዝብ ሀብትና ንብረት ላይም ሊጠገን የማይችል ጉዳት አያደረሱ ይገኛሉ፡፡ ይህ በህዝብ ስም የሚነገድ የፖለቲካ ፍላጎታቸዉ በህዝባችን ዘንድ ከፍተኛ ምሬትና ሮሮ ፈጥሯል።

የዚህ አጥፊ ድርጊት መሪ ተዋናዮች በከፋ ድርጊታቸዉ ከህዝብ በመነጠላቸዉ ከጊዜ ወደጊዜ አቅማቸዉ ተዳክሞ ተራ ዉንብድና ላይ እንዲሰማሩ ሁነዋል። የነዚህ ጸረ-ሰላም ሀይሎች መንገድ መዝጋት፣ ስርቆት፣ ዜጎችን ማገት፣ ተቋማትን እና መሰረተ ልማትን ማዉደም መገለጫቸዉ ከሆነ ሰነባብቷል።

ይህ ድርጊት ያማረረዉ የክልላችን ህዝብም የሰላም መንገድ እንዲከፈትና መንግስት ህግ እንዲያስከብር በተፈጠሩ የህዝብ መድረኮች በተደጋጋሚ ሲያነሳ ቆይቷል። መንግስትም ለህዝብ ጥያቄ መልስ በመስጠት ለሰላም የዘረጋዉ እጁ ሳይታጠፍ ከህዝብ ጋር በጋራ በመሆን ህግ የማስከበር ተግባሩን እየሰራ ነዉ።

ለዚህም ሰላም ወዳዱ ህዝባችን ከመከላከያ ሰራዊታችን እና ከክልላችን የጸጥታ መዋቅር ጋር በጋራ በመሆን እየታገላቸዉ ይገኛል። በዉጤቱም አንጻራዊ ሰላም ተመዝግቧል። የክልላችን ህዝብ ለሰላም መረጋገጥ እያሳየ ያለው ቁርጠኝነት ሊመሠገን የሚገባው ነው።

በመሆኑም እንደህዝብ ለጋራ ሰላማችን በጋራ በመቆም አሁን የተገኘዉን አንጻራዊ ሰላም ወደ ተሟላ ሰላም ለመቀየር ሁሉም የክልላችን ህዝብ የድርሻዉን መወጣቱን አጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል።

የአማራ ክልል መንግስት ኮሚኒኬሽን ቢሮ

ባህርዳር

የአማራ ህዝብ አርቆ አሳቢ እና አስተዋይ ህዝብ ነው። ህዝቡ ፅንፈኛው ቡድን እያደረሰ ያለውን ዘግናኝ ድርጊት በውል እየተገነዘበም ይገኛል። በቀጣይም በአሉባልታ የተደናገረውን ህዝብ መሬት ድረ...
19/02/2024

የአማራ ህዝብ አርቆ አሳቢ እና አስተዋይ ህዝብ ነው። ህዝቡ ፅንፈኛው ቡድን እያደረሰ ያለውን ዘግናኝ ድርጊት በውል እየተገነዘበም ይገኛል። በቀጣይም በአሉባልታ የተደናገረውን ህዝብ መሬት ድረስ ወርዶ ማግኘት እና እውነታውን ማስገንዘብ ይጠይቃል። በተለይም በፅንፈኛው ሀይል እየተዘረፈ ያለው ህዝብ መንግስት እንዲደርስለት እና ፅንፈኛውን አደብ እንዲያስይዝለት አጥብቆ እየጠየቀ በመሆኑ ህዝብን የማወያዬት ተግባሩ ተጠናክሮ ይቀጥል።

"ከህዝባችን ጋር የመከርንባቸው ውይይቶች ዘላቂ ሰላም እና ወንድማማችነትን የሚያረጋግጡ ናቸው"

ክቡር አቶ አረጋ ከበደ
የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር

🕊ሠላም ለሁሉም፤ ሁሉም ለሰላም🕊
•~•~•

"የጣና ቃልኪዳናችን፤ ለዘላቂ ሰላም እና ለሁለንተናዊ ብልጽግናችን"
•~•~•
ለወቅታዊ ፣ ትክክለኛና አዳዲስ መረጃዎች የፓርቲያችንን የማህበራዊ ገፆች ይወዳጁ።
ትዊተር :- twitter.com/AppAmhara?s=09
ዩቲዩብ :- youtube.com/channel/UCxQ5MOnm-YH514Qdta0Kysg
ቴሌግራም:- t.me/amharaapp
ቲክቶክ፡- tiktok.com/

ያሁኑ አመራር ከምንጊዜም የተሻለ መቀናጀትና መናበብ የሚታይበት በመሆኑ አደጋ የተጋረጠበትን ክልል መታደግ ችሏል። በቀጣይም ጥንካሬዎችን እያጎሉና ክፍተቶችን እያረሙ መሄድ ይገባል።
19/02/2024

ያሁኑ አመራር ከምንጊዜም የተሻለ መቀናጀትና መናበብ የሚታይበት በመሆኑ አደጋ የተጋረጠበትን ክልል መታደግ ችሏል። በቀጣይም ጥንካሬዎችን እያጎሉና ክፍተቶችን እያረሙ መሄድ ይገባል።

"በየደረጃው ያለው አመራር የጠራና የጋራ አቋም ይዞ ለክልሉ ዘላቂ ሰላምና ልማት መረጋገጥ በትኩረት መሥራት አለበት"
አቶ አብዱ ሁሴን
የአማራ ክልል ምክትል ርእሰ መሥተዳደር

🕊ሠላም ለሁሉም፤ ሁሉም ለሰላም🕊
•~•~•

"የጣና ቃልኪዳናችን፤ ለዘላቂ ሰላም እና ለሁለንተናዊ ብልጽግናችን"
•~•~•
ለወቅታዊ ፣ ትክክለኛና አዳዲስ መረጃዎች የፓርቲያችንን የማህበራዊ ገፆች ይወዳጁ።
ትዊተር :- twitter.com/AppAmhara?s=09
ዩቲዩብ :- youtube.com/channel/UCxQ5MOnm-YH514Qdta0Kysg
ቴሌግራም:- t.me/amharaapp
ቲክቶክ፡- tiktok.com/

ሰላም እና ልማት የማይነጣጠሉ የአንድ ሳንቲም ሁለት ገፅታዎች ናቸው። የክልላችን መሪዎች ሰላምን በማረጋገጥ  በጦርነት የደቀቀውን ኢኮኖሚ መልሶ እንዲያግም ለማድረግ የምታደርጉትን ትግል እናደ...
18/02/2024

ሰላም እና ልማት የማይነጣጠሉ የአንድ ሳንቲም ሁለት ገፅታዎች ናቸው። የክልላችን መሪዎች ሰላምን በማረጋገጥ በጦርነት የደቀቀውን ኢኮኖሚ መልሶ እንዲያግም ለማድረግ የምታደርጉትን ትግል እናደንቃለን።

"የሚገጥሙንን ፈተናዎች በድል እንሻገራለን እንጂ ለአፍታም ቢሆን ወደ ኋላ አንመለስም፤ በእኛ በኩል የሚያስፈልገው ኃላፊነትን በአግባቡ በመረዳት በቁርጠኝነት መሥራት ብቻ ነዉ ››

ክቡር አቶ ይርጋ ሲሳይ
በአማራ ክልል የብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ

ክቡር አቶ ይርጋ ሲሳይ ያስተላለፉት ሙሉ መልእክት እንደሚከተለዉ ቀርቧል፡፡

የሕዝብ ፍላጎት ሰላም እና ልማት መሆኑ በክልሉ በተካሄዱ ሕዝባዊ ውይይቶች ለማረጋገጥ ችለናል፡፡

አሁን የተገኙትን የፖለቲካና የፀጥታ ድሎች ጥልቀት እንዲኖራቸው ለማስቻልም የአመራር አቅምን በማሳደግ መንግሥታዊ መዋቅርን ማጠንከር፣ የልማት ሥራዎች ላይ ትኩረት ማድረግ ፣ የኑሮ ውድነቱን ለመቀነስ መሥራትና የሥራ ዕድል ፈጠራን ማስፋት ያስፈልጋል፡፡

በዚህ ወቅት ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ በክልሉ ዘላቂ ሰላምን ለማረጋገጥ የምንችልበት አቅም ላይ ነን፡፡ በመሆኑም በእኛ በኩል የሚያስፈልገው ኃላፊነትን በአግባቡ በመረዳት በቁርጠኝነት መሥራት ብቻ ነዉ፡፡

ክልሉን ከችግር ለማውጣትና ሕዝብ የሚያነሳቸውን ጥያቄዎች በጥልቀት መረዳትን ታሳቢ ያደረጉ በርካታ ስራዎች ተሰርተዋል፤ ክልሉን ለማተራመስ የሚሠሩ ሃይሎች ከሕዝብ ተነጥለዋል፤ አመራሩ ከሕዝቡ ጋር ተቀናጅቶ በመሥራቱ የተረጋጋ እና አንጻራዊ ሰላም የሰፈነበት ክልል መፍጠር ተችሏል፡፡

አሁን የክልሉን የሰላም፣ የልማት እና የፖለቲካ ችግር በዘላቂነት በመፍታት ፍጹም የተረጋጋ እና ተወዳዳሪ የሆነ ክልል ለመፍጠር በየደረጃው የሚገኙ የክልሉ መሪዎች በትጋት እየሰሩ ሲሆን በክልሉ እና በሕዝቡ ላይ የታቀደው ሴራ ከሽፎ አንጻራዊ ሰላም ሰፍኗል፡፡

ሕዝባችን ከዚህም በላይ አስተማማኝ ሰላም እና መረጋጋት ያስፈልገዋልና የፖለቲካ አመራሩ፣ የጸጥታ ኀይሉ እና ሕዝቡ ተቀናጅቶ ለህዝብ ተጠቃሚነት በትጋት እንዲሰራ ጥሪዬን ለማቅረብ እወዳለሁ፡፡

የልማት እና መልካም አሥተዳደር ጥያቄን ወደ ጎን ጥሎ ፖለቲካን ማሳመር፣ ሰላምንም ማስፈን አይቻልም። ሰላማችንን እያስከበርን የሕዝብን የልማት እና የመልካም አሥተዳደር ጥያቄዎችንም ለመመለስ በቁርጠኝነት እየሠራን ነው፡፡

በመሆኑም በእኛ በኩል የሚያስፈልገው ኃላፊነትን በአግባቡ በመረዳት በቁርጠኝነት መሥራት ብቻ ነዉና ለዚህ ተግባራዊነት መላዉ የፖለቲካ አመራር በሙሉ አቅማችን ለጋራ ዓላማችን ስኬት እንስራ ለማለት እወዳለሁ፡፡

ወቅቱ ፈታኝና ውስብስብ ቢሆንም ከፊታችን የሚገጥሙንን ተግዳሮቶች ከህዝባችን ጋር በጋራ ተጋግዘን እናልፋቸዋለን፡፡ የአማራ ክልልን ህዝብ ለማገልገልና የተጣለብንን ሃላፊነት ለመወጣት የምናባክነው ጊዜ እንደሌለ በአጽንዖት ለመግለጽ እወዳለሁ፡፡
•~•~•
https://www.facebook.com/profile.php?id=61555230610510

•~•~•
🕊ሠላም ለሁሉም፤ ሁሉም ለሰላም🕊

"የጣና ቃልኪዳናችን፤ ለዘላቂ ሰላም እና ለሁለንተናዊ ብልጽግናችን"
•~•~•
ለወቅታዊ ፣ ትክክለኛና አዳዲስ መረጃዎች የፓርቲያችንን የማህበራዊ ገፆች ይወዳጁ።
ትዊተር :- twitter.com/AppAmhara?s=09
ዩቲዩብ :- youtube.com/channel/UCxQ5MOnm-YH514Qdta0Kysg
ቴሌግራም:- t.me/amharaapp
ቲክቶክ፡- tiktok.com/

የመበታተን አደጋ የተጋረጠበትን ትልቅ ክልል የታደጉ በሳል እና አስተዋይ መሪ🙏
17/02/2024

የመበታተን አደጋ የተጋረጠበትን ትልቅ ክልል የታደጉ በሳል እና አስተዋይ መሪ🙏

‹‹በጊዜ የለንም መንፈስ በሰከነ አመራር ሰጭነት ህዝባችንን ከጎን አሰልፈን ወደ ተሻለ ሰላም እና ልማት እንሸጋገራለን››

ክቡር አቶ አረጋ ከበደ
የአማራ ክልል ርእሰ መስተዳድር

ርእሰ መስተዳድሩ በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ያስተላለፉት መልእክት እንደሚከተለዉ ቀርቧል ፡፡

ከህዝባችን ጋር የመከርንባቸው ውይይቶች ዘላቂ ሰላም እና ወንድማማችነትን የሚያረጋግጡ ናቸው፡፡ ህብረ ብሔራዊ አንድነትን እና ወንድማማችነትንና እህትማማችነትን ለማረጋገጥ በክልሉ ውስጥ በሚገኙ ከተሞች ከህዝብ ጋር ምክክር ያደረግን ሲሆን በውይይቱ የፌደራል እና የክልል አመራሮች የህዝባችንን ፍላጎት ምንነት በአግባቡና በሰከነ መንገድ ማዳመጥ መቻላቸውን እናስታዉሳለን፡፡ በዚህም በወንድማማችነት መንፈስ በበርካታ ጉዳዮች ላይ ውይይት በማድረግ መግባባት ላይ መድረስ ተችሏል፡፡

ይህ ሁለንተናዊ ብልጽግናን አረጋግጠን የሀገራችንን መፃኢ እድል ለመወሰን ሁሉም እድሎች በእጃችን ላይ እንደሚገኙ ማሳያ ነዉ፡፡

በየመድረኮቹ የተነሱ ሃሳቦች ለመንግስትና ለፓርቲያችን በርካታ የውሳኔ ግብዓት ያገኘንባቸው ከመሆኑ ባሻገር የህዝባችንን የሰላም፣ የልማት እና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎችን ለመመለስ የጋራ መግባባት የተደረሰበትና የአንድነት መንፈስ ያጠናከረ ነበር፡፡

በተለይም እነዚህ ዉይይቶች የአማራ ክልልን ህዝብ ጥያቄዎች ምን እንደሆኑ ከመገንዘብ አልፎ የሀገራችንን አንድነት ለማጽናት እና ሁለንተናዊ ብልፅግናን ለማረጋገጥ ዕድል የሚሰጡ ሆነዉ አግኝቻቸዋለሁ፡፡

ክልሉ ዘርፈ ብዙ ሰብዓዊና ቁሳዊ ውድመቶችን ከማስተናገዱ ባለፈ ለወደፊቱ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ዕድገት መዘዝ ያስከተሉ ችግሮች መከሰታቸውን አሁንም የሚያሳዝን እና መሆን ያልነበረበት ክስተት ቢሆንም ይህንን ጊዜ ለመካስ በጊዜ የለንም መንፈስ በሰከነ አመራር ሰጭነት ህዝባችንን ከጎን አሰልፈን ወደ ተሻለ ሰላም እና ልማት እንሸጋገራለን፡፡

ካለንበት ችግር ለመውጣት ህዝባችን ዋነኛ የመፍትሔ ባለቤትና ተሳታፊ መሆን እንደሚገባ አሁንም በድጋሚ ለመጠየቅ እወዳለሁ፡፡

በዚህ በ21ኛው ክፍለ ዘመን ችግሮችን በሰላማዊ መንገድ በውይይትና በድርድር መፍታት ምርጫ የሌለዉ ጉዳይ ሲሆን ፤ በተለይ በህብረተሰብ ዕድገት ውስጥ የሚታዩ ማናቸውም ዓይነት ጥያቄዎች የግድ በጦርነትና በግጭት መፍትሔ ያገኛሉ ተብሎ አይጠበቅምና፤ ይልቁንስ ከሁሉም በላይ ደግሞ ግጭትን እንደገቢ ማስገኛ ምንጭ እና አቋራጭ የመግስት ስልጣን የመቆናጠጫ መንገድ የሚያደርጉ አካላት ድርጊታቸው ህዝብን ማሳነስና የማህበረሰቡን አንጡራ ሃብት ከማውደም ባሻገር ምንም ውጤት እንደማይኖረው ተገንዝበውና ቀልባቸውን ሰብስበው ጉዳዩን በማጤን ለሰላማዊ ትግል እራሳቸውን ማዘጋጀት አለባቸዉ፡፡

ክልላችን ያለበት የሰላም እጦት በእጅጉ የተሻሻለ ቢሆንም ፀረ ሰላም ሃይሎችን ለመጨረሻ ጊዜ የመቆጣጠር እና ፊታችንን ሙሉ በሙሉ ለሁሉም ነገር መሰረት ከሆነው የኢኮኖሚ ልማት ላይ ርብርብ ማድረግ ይኖርብናል፡፡ የህግ የበላይነትን ከማስከበር በተጨማሪ አንፃራዊ ሰላም ባለባቸው የክልሉ አካባቢዎች መደበኛ የልማትና መልካም አስተዳደር ስራዎች እየተከናወኑ ሲሆን በቅርቡም መደበኛ የልማትና መልካም አስተዳደር ስራዎች ተጠናክረው እንደሚሰሩ ለማረጋገጥ እወዳለሁ፡፡

ህዝባዊ ውይይቶቹ በአጎራባች ክልሎችም የተካሄደ መሆኑ እና በተለያዩ ጊዜያት ከመኖሪያቸው የተፈናቀሉ ዜጎችን ለመመለስ እየተሰራ ያለው ስራ አበረታች መሆኑን ለመታዘብ የተቻለ ሲሆን እነዚህ ስራዎች ተናክረው እንደሚቀጥሉ ሙሉ እምነት አለኝ ፡፡

የክልሉ መንግስት በሁለም ረገድ የሚያከናውናቸውን የሰላም፣ የልማት እና የመልካም አስተዳደር ስራዎች ሁሉም አካል በየደረጃው ሊደግፍ የሚገባ ሲሆን በዚህ ሒደት መላ የክልላችን ህዝብ፣ የመንግስት ሰራተኞች፣ መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች፣ የመንግስትና የፓርቲ አመራሮች እንዲሁም ልማት ወዳድ የሆናችሁ አጋር አካላት በሙሉ በክልሉ ውስጥ የሚካሄደውን የሰላም ማስከበር፣ የልማትና መልካም አስተዳደር ስራዎችን በመተግበር ሂደት የበኩላችሁን አስተዋጽ እንድታበረክቱ ጥሪ አቀርባለሁ፡፡

በክልሉ የሚስተዋሉ የፀጥታ ችግሮችን ለአንዴ እና ለመጨረሻ ጊዜ ለመቆጣጠር የፀረ ሰላም ኃይል ትግሉን አጠናክረን የምንቀጥል ሲሆን ለዚህ ተግባር ማህበረሰቡ ከፀጥታ ሃይሎች ጎን በመሰለፍ እያበረከተ ለሚገኘው አስተዋጽዖ ምስጋና ለማቅረብም እወዳለሁ፡፡ ይህን ቅንጅት የህዝባችንን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በምንሰራውና የቅድሚያ ትኩረት በምንሰጠው የኢኮኖሚ ልማትም ንቅናቄ ስራ ሊቀጥል እንደሚገባ ለመጠቆም እፈልጋለሁ፡፡

https://www.facebook.com/profile.php?id=61554415769513

•~•~•
🕊ሠላም ለሁሉም፤ ሁሉም ለሰላም🕊

"የጣና ቃልኪዳናችን፤ ለዘላቂ ሰላም እና ለሁለንተናዊ ብልጽግናችን"
•~•~•
ለወቅታዊ ፣ ትክክለኛና አዳዲስ መረጃዎች የፓርቲያችንን የማህበራዊ ገፆች ይወዳጁ።
ትዊተር :- twitter.com/AppAmhara?s=09
ዩቲዩብ :- youtube.com/channel/UCxQ5MOnm-YH514Qdta0Kysg
ቴሌግራም:- t.me/amharaapp
ቲክቶክ፡- tiktok.com/

“በጦርነት እና ውስብስብ ችግሮች ውስጥ ኾነን በክልሉ ተስፋ ሰጪ የልማት ጅምሮችን ያሳዩን የቀድሞ መሪዎች ምሥጋና ይገባቸዋል” ርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ የአማራ ክልል ምክር ቤት 6ኛ ዙር...
25/08/2023

“በጦርነት እና ውስብስብ ችግሮች ውስጥ ኾነን በክልሉ ተስፋ ሰጪ የልማት ጅምሮችን ያሳዩን የቀድሞ መሪዎች ምሥጋና ይገባቸዋል” ርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ

የአማራ ክልል ምክር ቤት 6ኛ ዙር፤ 2ኛ ዓመት የሥራ ዘመን፤ 1ኛ አስቸኳይ ጉባዔ በባሕር ዳር ሲካሄድ አቶ አረጋ ከበደን ርእሰ መሥተዳድር አድርጎ ሹሟል፡፡

አዲሱ የአማራ ክልል ርእሰ መሥተዳድር ወደ ኅላፊነት የመጡበት ወቅት ፈታኝ እና የጋራ ትብብርን የሚጠይቅ መኾኑን አንስተዋል፡፡

“በጦርነት እና ውስብስብ ችግሮች ውስጥ ኾነን በክልሉ ተስፋ ሰጪ የልማት ጅምሮችን ያሳዩን የቀድሞ መሪዎች ምሥጋና ይገባቸዋል” ያሉት ርእሰ መሥተዳድሩ በተለይም ለቀድሞው ርእሰ መሥተዳድር ይልቃል ከፋለ (ዶ.ር) በሳል፣ የሰከነ እና ሆደ ሰፊ አመራር ሰጭነት ምክር ቤቱ ዕውቅና ሊሰጠው እንደሚገባ አንስተዋል፡፡

ክልሉ አሁን ያለበት ወቅታዊ ኹኔታ ለሁሉም ግልጽ ነው ያሉት ርእሰ መሥተዳድሩ ኅላፊነቱን ከመቀበል ውጭ አማራጭ ባለመኖሩ እንደተቀበሉ አንስተዋል፡፡ በኅላፊነት ዘመናቸው ክልሉ አሁን ካለበት ዘርፈ ብዙ ችግሮች አውጥቶ የተሻለ እና የተረጋጋ ክልል ለማድረግ የሚችሉትን ሁሉ በቅንነት እና በኅላፊነት እንደሚሠሩ አንስተዋል፡፡

የምጣኔ ሃብት፣ ማኅበራዊ፣ ፖለቲካዊ እና ሌሎች ችግሮች አሉብን ያሉት ርእሰ መሥተዳድሩ የአማራ ክልል ከገጠመው ውስብስብ ችግር ለመውጣት የአባቶቻችንን ብስለት እና የሕዝባችንን ስክነት እንደመውጫ መፍትሔ እንጠቀማለን ነው ያሉት፡፡ አሁናዊ ችግሩ ክልሉን የሚጎዳ እና የሕዝቡን ሥነ-ልቦና የሚጎዳ በመኾኑ በፍጥነት ከችግሩ መውጣት ይገባል ብለዋል፡፡

በክልሉ የተፈጠረውን ወቅታዊ ችግር እንደአጋጣሚ በመውሰድ በክልሉ ሕዝብ የዘመናት ጥያቄ እና ጥቅም ላይ ተገቢ ያልኾነ ንግግር የሚሰነዝሩ ቡድኖች ድርጊታቸው ከትንኮሳ የማይለይ መኾኑን ማወቅ ይገባቸዋል ነው ያሉት፡፡

የክልሉ መንግሥት ሕጋዊ የፌዴራል መንግሥት ውሳኔ የሚጠብቅ እንጂ ሕዝብ የጠየቀውን ጥያቄ የሚዘነጋ እንዳልኾነ ሊገነዘቡ ይገባል ብለዋል፡፡

ርእሰ መሥተዳድር አረጋ የክልሉን ሕዝብ ማኅበራዊ እረፍት ለማምጣት በሀገር ውስጥ እና ከሀገር ውጭ ያሉ የክልሉ ተወላጆች፣ ኢትዮጵያዊያን እና የኢትዮጵያ ወዳጆች እንዲረባረቡ ጥያቄ አቅርበዋል፡፡

በየደረጃው የሚገኙ መሪዎች፣ የክልሉ ሕዝብ፣ የሃይማኖት አባቶች፣ የሀገር ሽማግሌዎች እና ወጣቶች ከክልሉ መንግሥት ጎን በመቆም ለሰላም እንዲሠሩ ጥሪ አቀርበዋል፡፡

የብዙሃን መገናኛ ተቋማት፣ የሲቪክ ማኅበራት እና ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች ለሕዝቡ የሚገባውን እና የሚሻለውን ለማድረግ በጋራ እንሥራ ያሉት ርእሰ መሥተዳድሩ የፌዴራል መንግሥት እና ሌሎች ክልሎች የክልሉን ሕዝብ በማገዝ አብረው እንዲቆሙ ጠይቀዋል፡፡

ግብርና ቢሮ የትብብር ጥሪ አቀረበበአማራ ክልል ሰሞኑን በተስፋፋው ግጭት ሳቢያ፣ የ130ሺህ ኩንታል የአፈር ማዳበሪያ ሥርጭት መስተጓጎሉን የገለጸው የክልሉ ግብርና ቢሮ፣ በአፋጣኝ ወደ አርሶ ...
12/08/2023

ግብርና ቢሮ የትብብር ጥሪ አቀረበ

በአማራ ክልል ሰሞኑን በተስፋፋው ግጭት ሳቢያ፣ የ130ሺህ ኩንታል የአፈር ማዳበሪያ ሥርጭት መስተጓጎሉን የገለጸው የክልሉ ግብርና ቢሮ፣ በአፋጣኝ ወደ አርሶ አደሩ ለማድረስ ይቻል ዘንድ የትብብር ጥሪ አቀረበ፡፡

የግብርና ቢሮው ምክትል ሓላፊ አቶ አበጀ ስንሻው፣ ለአሜሪካ ድምፅ እንደተናገሩት፣ በመጪው 10 ቀናት ውስጥ፣ ወደ ክልሉ የገባው 130ሺህ ኩንታል የአፈር ማዳበሪያ፣ ወደ የአርሶ አደሩ ቀዬ ተጓጉዞ ካልደረሰ፣ በቀጣዩ ዓመት ረኀብ ሊከሠት ይችላል፡፡

ያነጋገራቸው አርሶ አደሮች በበኩላቸው፣ አቅርቦቱ እጅግ ዘግይቷል፤ ብለዋል።

ሌሎች ክልሎች ልማት ላይ ናቸው። እኛ ደግሞ የተሰራውንም እያፈረስን ወደኋላ እየሄድን ነው።
11/08/2023

ሌሎች ክልሎች ልማት ላይ ናቸው። እኛ ደግሞ የተሰራውንም እያፈረስን ወደኋላ እየሄድን ነው።

የአፄ ፋሲል ቤተ መንግስት በመድፍ ተመቶ ፈረሰ የሚለው ወሬ ፍፁም ሀሰት ነው መሆኑ ተረጋግጧል።
11/08/2023

የአፄ ፋሲል ቤተ መንግስት በመድፍ ተመቶ ፈረሰ የሚለው ወሬ ፍፁም ሀሰት ነው መሆኑ ተረጋግጧል።

ሰላም የሁሉም ነገር መሰረት በመሆኑ         ሁሉም ስለ ሰላም ሊሠራ ይገባል።                     •~•~•በአንድ ሀገር ውስጥ ሰላም ካልሰፈነ ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ፖለቲ...
11/08/2023

ሰላም የሁሉም ነገር መሰረት በመሆኑ
ሁሉም ስለ ሰላም ሊሠራ ይገባል።
•~•~•
በአንድ ሀገር ውስጥ ሰላም ካልሰፈነ ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ፖለቲካዊ ሁነቶችን ማሳለጥ አይቻልም፡፡ ሰላም በሌለበት አካባቢ ውስጥ የተረጋጋ ህይወት መምራት፣ ሠርቶ መለወጥ እና ይልቁንም በፖለቲካው መስክ ተደራድሮ ማሸነፍ አይቻልም ማለት ነው።

የሰላም ጥቅምና ዋጋ እንዲሁም ፋይዳው የሚታወቀው ደግሞ የሰላም እጦት ሲያጋጥም እና ብዙ ዋጋ ከተከፈለ በኋላ ነው፡፡ ነገር ግን ሁልጊዜም ቢሆን ስለ ሰላም ጥቅም ለማወቅ በቀውስ ውስጥ ማለፍ ተገቢ አይደለም። የቀውሶች መፈጠር እና የሰላም መናጋት ብዙ ያልተገባ ዋጋ የሚያስከፍሉ በመሆናቸው ነው። ሩቅ ሳንሄድ ከሰሞኑ በክልላችን አንድንድ አካባቢዎች የተስተዋሉ ቀውሶች እና ችግሮች እንዲሁም ያስከፈሉት ዋጋ ሁነኛ አስረጂዎች ናቸው።

ሁለንተናዊ ፍላጎቶቻችንን ለማሳካት እና ጥያቄዎቻችንን ለመመለስ ሰላም የማይተካ ሚና ያለው በመሆኑ ሁሉም ስለ ሰላም መስፈን ሊሰራና የበኩሉን ድርሻ ሊወጣ ይገባል። የትኛውም ቡድን እና ግለሰብ በርካታ ፍላጎቶች እና ጥያቄዎች ይኖሩታል። ነገር ግን ጥያቄዎቹ የሚፈቱት በግጭት ሳይሆን በሰከነ መንገድ በውይይት እና ተቀራርቦ በመነጋገር ነው። ግጭቶች እና ብጥብጦች ጥያቄዎቻችንን ይበልጥ በማወሳሰብ ለከፋ ችግር ይከቱናል እንጂ መፍትሄ አያመጡልንም ። ስለሆነም በሰከነ እና በሰለጠነ መንገድ ወደ ውይይቶች መመለስ እና ሰላምን ማስፈን የቅድሚያ ቅድሚያ የሚሰጠው ጉዳይ ነው።

ከሰሞኑ በክልላችን የተለያዩ አካባቢዎች ተከስቶ የነበረው ግጭት እና የሰላም እጦት በህዝባችን አርቆ አሳቢነት እና በፀጥታ ሀይሉ ቅንጅት ታግዞ ሁሉም አካባቢ ወደ ቀደመ ሰላሙ እየተመለሰ ይገኛል። ይሄን አጠናክሮ ለመቀጠል እና የተሟላ ሰላም ለማስፈን ደግሞ የሁሉንም ርብርብ የሚጠይቅ በመሆኑ የሀይማኖት አባቶች፣ የሀገር ሽማግሌዎች፣ ወጣቶች እና መላው የክልላችን ህዝብ በተጀመረው አግባብ ስለ ሰላም አጠናክረው ሊሰሩ ይገባል፡፡

በተለይም የሀይማኖት ተቋማት በውስጣቸው ሁሉንም የህብረተሰብ ክፍል ያቀፉ በመሆናቸው እንዲሁም ሁሉም ሀይማኖቶች ለሰው ልጆች ሁሉ ሰላምና ፍቅርን የሚሰብኩ በመሆናቸው የተጀመረው የሰላም ጭላንጭል ወደተሟላ ሁኔታ እንዲመለስ አጥብቀው በማስተማር እና በመምከር በዚህ ረገድ ያላቸውን አበርክቶ አጠናክረው ሊወጡ ይገባል።

በተጨማሪም በክልላችን ብሎም በሀገራችን ግጭቶችን የምናስወግድባቸው እና ሰላምን የምናሰፍንባቸው በርካታ ዕሴቶች ያሉ በመሆኑ የሀገር ሽማግሌዎች እና አጠቃላይ ህዝባችን ለሰላም መስፈን ቅድሚያ በመስጠት ልዩነቶችን እና ጥያቄዎችን ወደ ውይይት ይዞ መቅረብ እና በውይይት መፍታት እንዲቻል አበክረው ሊሰሩ ይገባል።

ግጭቶች ተወግደው ክልላችን ወደቀደመ ሰላሙ እንዲመለስ የሀይማኖት አባቶች፣ የሀገር ሽማግሌዎች፣ የፀጥታ ሀይሉ እና አጠቃላይ ህዝባችን ያላሰለሰ ጥረት በማድረግ ላበረከታችሁት አስተዋፅዖ ክብርና ምስጋና ይገባችኋል። ይሄም ተጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል።

“ቁጭ ብላችሁ ተወያይታችሁ ይህን ሕዝብ ከመከራ አድኑት” የሃይማኖት አባቶችበኢትዮጵያ እዚህም እዚያም የሚከሰቱ አለመረጋጋቶች ለንጹሀን ዜጎች የደኅንነት ዋስትና እጦት መንስኤ ኾነዋል።ከጊዜ ወ...
11/08/2023

“ቁጭ ብላችሁ ተወያይታችሁ ይህን ሕዝብ ከመከራ አድኑት” የሃይማኖት አባቶች

በኢትዮጵያ እዚህም እዚያም የሚከሰቱ አለመረጋጋቶች ለንጹሀን ዜጎች የደኅንነት ዋስትና እጦት መንስኤ ኾነዋል።

ከጊዜ ወደ ጊዜ ማባሪያ ያጣው የሰላም እጦት ለዜጎች መሞት፣ መቁሰል፣ መሳደድና መንገላታት መንስኤ ሆኖ ቀጥሏል፡፡

በኢትዮጵያ ሰማይ ሥር የተሟላ ሰላም በመጥፋቱ ብዙዎች ሮጠው ሳይጠግቡ ውድ ሕይወታቸውን አጥተዋል፣ እናቶች ያለ ጧሪ ቀርተዋል፣ ሕጻናትም ያለ አሳደጊ ተበትነዋል፡፡ ለዓመታት እንቅልፍ አጥተው፣ ጥረው ግረው ሃብት ያፈሩ ዜጎች ተዘርፈዋል፣ ምንም እንደሌላቸው ባዶ እጃቸውን ቀርተዋል፡፡

ብዙዎች ቤት አልባ ሆነው ተሳድደዋል፡፡ በኢትዮጵያ ሰማይ ሥር ያንዣበበው የሰላም እጦት ዛሬም ብዙዎችን እየቀጠፈ፣ አካል እያጎደለ፣ እያፈናቀለና እያደኸየ ቀጥሏል፡፡ ክፉ ነገርን የሚያዘንበው የሰላም እጦቱ ዛሬም ከዳመነበት አልጠራም፡፡ ዘንቦ ዘንቦም አላባራም፣ በየጊዜው እየዘነበ ብዙዎችን አጥፍቷል፡፡ የቀሩትንም በስጋትና በጭንቅ ውስጥ አስቀምጧል፡፡ ከሰሞኑ በአማራ ክልል በተፈጠረው ችግርም እኖር ባይ ዜጎች አልፈዋል፣ ቆስለዋል፡፡ በኢትዮጵያ ያንዣበበውን ችግርና ሞት የሚያቆመው የተረጋጋ ሰላም ሲኖር ነው፡፡ ሰላም ደግሞ ከሁሉም እጅ ያለች፣ ለሁሉም የተሰጠች እና ለሁሉም የተገባች ናት፡፡ ሁሉም እንደሚፈልጋት እና እንደምታስፈልገው ሁሉ ሁሉም ይጠብቃት ዘንድ ትፈልጋለች፡፡ ይህ ሳይሆን ሲቀር ሰላም ከሁሉም ወጥታ ሁሉንም ታሳጣለች፡፡

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊና የኒዮርክና አካባቢው ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብጹዕ አቡነ ጴጥሮስ ለዘላለም የምንኖረው ኑሮ በምድር የምንሰራው ሥራ ውጤት ነው ይላሉ፡፡ በምድር ስለ ሰላም የምንሠራው ሥራ ለዘላለማዊ ሕይዎት ስንቅ መሆኑን ብፁዕነታቸው ይገልጻሉ፡፡ ሃይማኖት መሠረቱ ሰላም ነው ያሉት ብጹዕ አቡነ ጴጥሮስ የሃይማኖት መሠረቱ ለሰው ልጅ ፍቅርና ሰላም ማምጣት መሆኑንም ተናግረዋል፡፡

ከባለፈው ችግር ለምንድን ነው የማንማረው ? ባለፉት ዓመታት ብዙ ሰው ሞቷል፣ ቆስሏል፣ ብዙ ገንዘብ ወድሟል፣ የተሠራውን አፍርሰን፣ ሌላም እንዳንሠራ አውድመን ለምን እንኖራለን? ለምንድን ነው ከዚህ መማር ያቃተን ሲሉም ይጠይቃሉ ብጹዕ አቡነ ጴጥሮስ፡፡ ጥያቄው ምንድን ነው?፣ የበደልነው በደልስ ምንድን ነው ብሎ መጠየቅና መመለስ እንደሚገባም አስግንዝበዋል፡፡ ማኅበረሰቡ መንግሥትም ሆነ ሌሎች አካላት ሰላምን የሚያናጉ ነገሮች ሲሰሩ አቁሙ በቃን ሊላቸውም ይገባልም ብለዋል፡፡

መግደል ፍትሐዊነት አይደም ያሉት ብጹዕ አቡነ ጴጥሮስ ግጭት ይበቃል፣ ቁጭ ብላችሁ ሀሳባችሁንና ጥያቄያችሁን እርስ በእርሳችሁ ተወያይታችሁ ይሄን ሕዝብ ከመከራ አድኑት፣ ረሃቡ ይበቃዋል፣ መገዳደልን አቁሙት ሲሉም ጥሪ አቅርበዋል፡፡ ብጹዕነታቸው በመልክታቸው የሰውን ልጅ ክብር አታርክሱት ሲሉም ጠይቀዋል፡፡

ሌላኛው የሃይማኖት አባት ፓስተር ቸርነት በላይ ብዙ ሰው የሰላምን ዋጋ የሚያውቀው ሲያጣው መሆኑን ገልጸዋል፡፡ እንዳለመታደል ሆኖ የአንድን ነገር ዋጋ የምናውቀው ስናጣው ነውም ብለዋል፡፡ ሰላም ማለት ችግርና ግጭት አልባ ሕይወት መኖር ማለት ብቻ አለመሆኑን እና ከዚያ በላይ እንደሆነ የገለጹት ፓስተር ቸርነት የሰላም ባለቤት እግዚአብሔር ነው፣ እግዚአብሔር በሰጠን ምድር ላይ ስንኖር ደግሞ ሰላም አስፈላጊ ነው ብለዋል፡፡ ሀገር እንወዳለን ካልን ነገሮችን በልበ ሰፊነት ማየት ይገባል ነው ያሉት፡፡ በእልህ ምንም እንደማይመጣና አሸናፊ እንደማያደርግም ገልጸዋል፡፡ በጦርነት ከመድቀቅ፣ ከመገዳደል እና ከጸጸት የዘለለ ምንም ነገር እንደማይመጣም ተናግረዋል፡፡

በየሥርቻው ቁጭ ብለን ፖለቲካ ከምናነፈንፍ የተሰጠውን የሃይማኖት ነገር ለትውልድ ማስተማር አለብን ነው ያሉት፡፡ ትውልዱ የሚተርፈው በእውቀት መሆኑንም ገልጸዋል፡፡ መስጠት ያለብን ነገር በጊዜ መስጠት አለብን ያሉት ፓስተር ቸርነት በወንድማማቾች መካከል ግጭት ሲፈጠር ተው ወንድምህን አትግደለው፣ በልብህ ያሰብከው ክፋት አይቸዋለሁ ማለት ይገባል ነው ያሉት፡፡ ምክርን መስማት፣ እሺ በማለት መንፈስ መደገፍ ጥሩ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ ሁሉም በየእምነቱ በርከክ ማለትና መስከን ጥሩ ነው ያሉት ፓስተር ቸርነት ከግጭት ትርፍ እንደሌለም አንስተዋል፡፡

ሰው ገድለን ደስታ አናተርፍም፣ ሀዘንና ጭንቀት ነው፣ ስደትና መከራ ነው የምናተረፈውም ብለዋል፡፡

አሚኮ

09/07/2022

"በህይወታችን ዘመን ያከናወናቸው ገንቢም ሆነ አፍራሽ ተግባሮችን ከእኛ መቃብር በላይ ከእኛም በኋላ ለዘላለም ይኖራሉ!" ኮለኔል መንግሥቱ ኃ/ማሪያም

ስለታለመለት ነዳጅ መሸጫ ዋጋ ድጎማ መመሪያ በትንሹም ቢሆን ማወቅ ከፈለጉ ለግንዛቤ ይሔውልዎት  ☞☞ ይነበብ አደራ ይነበብ!!!☜☜✍ አላማው፡-✔በጊዜ ገደብ የታለመ የነዳጅ ዋጋ ድጎማ ስርዓት...
03/07/2022

ስለታለመለት ነዳጅ መሸጫ ዋጋ ድጎማ መመሪያ በትንሹም ቢሆን ማወቅ ከፈለጉ ለግንዛቤ ይሔውልዎት

☞☞ ይነበብ አደራ ይነበብ!!!☜☜

✍ አላማው፡-

✔በጊዜ ገደብ የታለመ የነዳጅ ዋጋ ድጎማ ስርዓት በመዘርጋትና በመተግበር ድጎማን በማስቀረት ወደ ዋጋ ማረጋጊያ ፈንድ አስተዳደር ለመመለስና እዳን ለማስወገድ ነው፡፡

✔ የነዳጅ ውጤቶች ዋጋ ማስተካከያ ሲደረግ አነስተኛ ገቢ ያላቸው የህብረተሰብ ክፍሎች ላይ የጎላ ተፅዕኖ በማያደርስ ሁኔታ እንድፈፀም ለማስቻል ነው፡፡

✔ የአለም የነዳጅ ውጤቶች የገበያ ሁኔታን ያገናዘበ የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ማስተካከያ በማድረግ በነዳጅ ግብይት እየታየ ያለውን ብክነትና ህገወጥነትን ለማስወገድ ነው፡፡

✍ለምን ይህን መመሪያ ማውጣት አስፈለገ

☞ የመጀመሪያው የኢትዮጵያ የነዳጅ መሸጫ ዋጋ ከአለምና ከአፍሪካ አገሮች በጣም በእጅጉ ያነሰ በመሆኑ ማሻሻል በማስፈለጉ

ለምሳሌ፡- ቤንዚን ኢትዮጵያ ውስጥ ከጅቡቲ ወደብ አምጥታ 36.87 ብር ይሸጣት ጎረቤት አገር ጅቡቲ 90 ትሸጣለች
ኬንያ 65 ብር ትሸጣለች፣ ሱዳን = 79 ብር ፣ ናፍጣ ኢትዮጵያ በተመሳሳይ ከጅቡቲ ወደብ አምጥታ 35.43 ብር ትሸጣለች ጅቡቲጰ 60 ብር ኬንያ= 57 ብር፣ ሱዳን= 75 ብር ይሸጣሉ

☞ ሁለተኛው ኢትዮጵያ ውስጥ ከፍተኛ የሆነ የነዳጅ
የኮንትሮ ባንድ ንግድ ስለተስፋፋ ይህን ለመቀነስ ምክንያቱ ደግሞ በከፍተኛ ወጭ መንግስት አስገብቶ በዝቅተኛ ዋጋ በመሸጡ ነዳጁ በህገወጥ ተመልሶ ወደ ውጭ እንድወጣ አድርጎታል

☞ ሶስተኛው በዋጋ ማረጋጋጊያ ፈንድ ከፍተኛ ኪሳራ በማስመዝገቡ ይህም ከ2012 ሰኔ ወር ጀምሮ እስከ 2014 ሚያዚያ ወር ድረስ 124,162,307,477 ብር የነዳጅ ዕዳ ኢትዮጵያ ላይ ተመዝግቧል፡፡ በ2014 በ7 ወር ብቻ 84.7 ቢሊዮን ብር ኪሳራ አስመዝግባለች

☞ አራተኛው የመንግስት ታክስ በተገቢው መጠን አለመመዝገብ በዚህም በአመት 60 ቢሊዮን ብር ገቢ ታጣለች ምክንያቱ ደግሞ በህገወጥ ስለሚዘዋወር

☞ አምስተኛው በፖሊሲ ያልተደገፈ ጥቅል ድጎማ አግባብነት የሌለው መሆኑ ነው፡፡ ይህ ማለት የውጭ ድርጅቱም፣ ኢምባሲዎችም፣ መያዶችም፣ ድሃውም እኩል ነው ሲደጎም የነበረው በዚህ ምክንያት ደግሞ ድጎማው ድሃው ላይ ሳይደርስ በትልልቅ ድርጅቶችና ኢሞባሲዎች እንድሁም በግለሰቦች በህገወጥ ይቸበቸባል ይህም በፖሊሲያችን ላይ የለም ፡፡ በመሆኑም ለድሃው ማህበረሰብ እንድደርስ ለማድረግ ታስቦ የተደረገ ድጎማ ነው፡፡

✍ ለታለመለት የነዳጅ ድጎማ የሚካተቱ የትራንስፖርት አገልግሎት የሚለዩበት መስፈርቶች ምንድን ናቸው?

☞ አነስተኛ ገቢ ላላቸው የህብረተሰብ ክፍል አገልግሎት የሚሰጡ ከሆነ

☞ አገልግሎት አሰጣጣቸው በታሪፍና በስምሪት ቁጥጥር መሆኑን ለተስማሙ

☞ የብዙሃን የትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጡ መሆናቸው

☞ ይህን ለመቆጣጠር ስልጣን ለተሰጠው አካል ተገዥ ለመሆን የተስማሙ ከሆነ

☞ በተለያየ ማህበር ተደራጅተው ለህዝብ ትራንስፖርት ለመስጠት ፍቃደኛ የሆኑ ይካተታሉ

✍ በድጎማው የተካተቱ ተሽከርካሪዎችን ስንመለከት!

☞ የየህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጡ አንበሳፈሸገር፣ፐፕሊክ ባሶች

☞ መደበኛ አገር አቋራጭ ከደረጃ 1 እስከ ደረጃ 3 ባሶች

☞ የመጫን አቅማቸው ከ12 እስከ 47 ያለ መለስተኛ አውቶቢሶች

☞ የኮድ 1 እስከ ኮድ 3 የሚኒባስ ታክሲዎች

☞ ባለ ሶስትና ባለ አራት እግር ባጃጆች ናቸው፡፡

✍ በድጎማው የተካተተሐ የነዳጅ ውጤቶች እነማን ናቸው?
☞ ቤንዚን
☞ ናፍጣ
☞ኬሮሲን(ነጭ ጋዝ) ብቻ ናቸው፡፡

✍ በድጎማው የሚካተቱ የነዳጅ ውጤቶች የድጎማ መጠንና የጊዜ ገደብ እስከ መቼ ነው?

☞ በድጎማው የተካተቱ ተሽከርካሪዎች ቤንዚንና ናፍጣ ስራ ላይ ባለውና በወቅቱ በስሌት በሚደርሰው የችርቻሮ ዋ መካከል ያለውን ልዩነት 10 በመቶ በየስድስት ወሩ እየከፈሉ በአምስት አመት ውስጥ ከድጎማው ሙሉ በሙሉ ይወጣሉ

☞ ከታለመለት ድጎማ ተሽከርካሪዎች ውጭ ያሉት የነዳጅ ተጠቃሚዎች ስራ ላይ ባለውና በወቅቱ በስሌት የተደረሰበት ዋጋ የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ መካከል ያለውን ልዩነት 25 በመቶ በየሶስት ወሩ እየከፈሉ በአንድ አመት ውስጥ ሙሉ በሙሉ ከድጎማው ይወጣሉ

☞በአጠቃላይ ይህ የነዳጅ ድጎማ የመሸጫ ዋጋ በቀጥታ ለድሃው ማህበረሰብ እንድደርስና የህገወጥ ኮንትሮባንድስት መስመሩን ለመቁረጥ የታለመ ነው፡፡

✔ አገራችን ላይ የተጣለባትን የነዳጅ ዕዳ ለመቀነስ ነው

✔ አገራችን እያጣች ያለውን የታክስ ግብር ለማግኘትና ለማዳን ነው፡፡

✍ሁሉም ግንዛቤው ቢኖረው ይጠቀማል እንጂ አይጎዳም ። ይችን አጭር ግንዛቤ ይዞ ለሌሎች ግንዛቤ እንድፈጥርና አሉቧልታዎችን እንድታገል እራሱም ምክኒያታዊ እንዲሆን ይረዳዋል።

14/06/2022

#ፋኖ💪
ጠቅላይ ሚንስትሩ ስለ ፋኖ

ሠበር ዜና//////የአብክመ ጠቅላይ ፍ/ቤት ዛሬ ሰኔ 3/2104 ዓ.ም ብ/ጀኔራል ተፈራ ማሞ በ30 ሺህ ብር ዋስትና ከእስር እንዲለቀቁ ውሳኔ ሰጥቷል።
10/06/2022

ሠበር ዜና
//////

የአብክመ ጠቅላይ ፍ/ቤት ዛሬ ሰኔ 3/2104 ዓ.ም ብ/ጀኔራል ተፈራ ማሞ በ30 ሺህ ብር ዋስትና ከእስር እንዲለቀቁ ውሳኔ ሰጥቷል።

በዚህ ወቅት ሀገሩንና ወገኑን የሚወድ ሁሉ ከመቻቻልና ከመከባበር ውጭ ሌላ አማራጭ የለውም።ጎንደርን የሃይማኖት የግጭት ቀጠና ለማድረግ የምትሯሯጡ በክርስቲያኑም ሆነ በሙስሊሙ ወገን ያላችሁ ማ...
28/04/2022

በዚህ ወቅት ሀገሩንና ወገኑን የሚወድ ሁሉ ከመቻቻልና ከመከባበር ውጭ ሌላ አማራጭ የለውም።

ጎንደርን የሃይማኖት የግጭት ቀጠና ለማድረግ የምትሯሯጡ በክርስቲያኑም ሆነ በሙስሊሙ ወገን ያላችሁ ማንንም የማትወክሉ ቁሞ ቀር ፖለቲከኞች የራሳችሁን ጥቅም ከማሳደድ ውጭ ለሁለቱም ሃይማኖቶች የምትፈይዱት አንድም ነገር የለም። ጎንደር ግጭትን የመከላከልና የማስወገድ ጥበብ ያላቸው ብዙ ሸኮችና ቄሶች የሚፈልቁባት ምድር ነች። አትራፊወች አትጨነቁ ትላልቅ አባቶች እያሉ ምንም የሚፈጠረ ነገር የለም።

ጠላቶቻችን እርስ በእርሳችን እንድንበላላ ብዙ ነገር ቢሞክሩም ሳይሳካላቸው ቀርቷለ። አሁን የተገኘው ክፍት አጀንዳ ለማራገብ የቱንም ያህል ቢጥሩ ያጀግና ህዝብ በጥበቡ እንዴት እንደሚፈታው ታዩታላችሁ። ብዙው ቁሞ ቀርና ሴረኛ የጎንደሬ አማራን አስተዳደግና አኗኗር፣መቻቻልና መከባበር ሚስጢር የሚያውቅ አይመስለኝም።

ሴራው ከሽፎል!!

Adresse

Democratic Republic Of The

Site Web

Notifications

Soyez le premier à savoir et laissez-nous vous envoyer un courriel lorsque Amhara Plus publie des nouvelles et des promotions. Votre adresse e-mail ne sera pas utilisée à d'autres fins, et vous pouvez vous désabonner à tout moment.

Partager