EthioAfro world TV by Abraham

EthioAfro world TV by Abraham 1 Million Followers

Follow our page

One Love Ethiopia
God is Good!
ኢትዮጵያ 🇪🇹 Thank you for following

13/11/2025
13/11/2025

የ2.5 ሚሊዮን ብር ዘራፊዎች ተያዙ!

ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ ከአዲስ አበባ ከተማ አውቶብስ አገልግሎት ድርጅት መካኒሳ ቅርጫፍ ፅ/ቤት የተዘረፈ ከ2.5 ሚሊዮን ብር በላይ በማስመለስ ወንጀል ፈጻሚዎቹን በቁጥጥር ስር አውሏል።

ጥቅምት 6 ቀን 2018 ዓ.ም. ከሌሊቱ 7፡00 ሰዓት ገደማ። ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ወረዳ 13፣ የአውቶብስ አገልግሎት ድርጅት መካኒሳ ቅርንጫፍ ፅ/ቤት። 2,597,635 ብር (ሁለት ሚሊየን አምስት መቶ ዘጠና ሰባት ሺ ስድስት መቶ ሠላሳ አምስት ብር)።

ከድርጅቱ ጥበቃዎች ጋር ተመሳጥረው የድርጅቱን ካዝና በፌሮ ብረት እና በሌሎች መሳሪያዎች በመፈልቀቅ ወንጀሉን ፈጽመዋል።

የተዘረፈውን ገንዘብ በማዳበሪያ ጭነው በሁለት ተሽከርካሪዎች (ኮድ 2C አዲስ አበባ 71417 ቪትዝ እና ኮድ 2A አዲስ አበባ 79207 ሚኒባስ) ተጠቅመው ተሰወሩ።

የንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ የክትትል፣ ኦፕሬሽን እና የወንጀል ምርመራ ክፍሎች ባደረጉት የተቀናጀና እልህ አስጨራሽ ክትትል፣ ወንጀሉ ከተፈጸመ በሁለተኛው ቀን ውስጥ ተይዘዋል።

ስማቸው

1. ቅዱስ ሀይለየሱስ፣
2. ዮናስ ግርማይ፣
3. ኤርምያስ ሰንበት እና ኪሮስ ግርማይ)

ሁለቱ ተሽከርካሪዎች በቁጥጥር ስር ውለዋል።

569,595 ብር (አምስት መቶ ስልሳ ዘጠኝ ሺ አምስት መቶ ዘጠና አምስት ብር) ተመላሽ ተደርጓል።

ፖሊስ አስፈላጊ ማስረጃዎችን በማሰባሰብ በተጠርጣሪዎቹ ላይ በፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ንፋስ ስልክ ላፍቶ ፈጣን ችሎት (RTD) ምድብ ክስ መስርቶ የጉዳያቸው አያያዝ በመታየት ላይ ነው።

ፖሊስ በወንጀሉ ውስጥ የጥበቃ ሰራተኞች ተሳትፎ መኖሩን አስታውቋል። በመሆኑም፣ የጥበቃ አገልግሎት ሰጪ ተቋማት በሚቀጥሯቸው ሰራተኞች በሚፈጸም ወንጀል የፍትሐብሔርና የወንጀል ተጠያቂነት እንደሚከተል ገልጿል።

ይህም የፈቃድ ስረዛን ጨምሮ ከባድ እርምጃዎችን ሊያስከትል ስለሚችል፣ ኤጀንሲዎች ሰራተኞችን ሲቀጥሩ ተገቢውን ጥንቃቄ እንዲያደርጉ አሳስቧል!

የአዲስ አበባ ፖሊስ ወንጀል ፈጽመው የሚሰወሩ ወንጀለኞችን በቁጥጥር ስር የማዋል አቅሙ እየጨመረ መሆኑን ገልጿል።

ህብረተሰቡም ሆነ ግለሰቦች የወንጀል ድርጊት ሲያጋጥማቸው ፈጥነው ለፖሊስ የማሳወቅ ልምድ እንዲያዳብሩ ጥሪ አቅርቧል።

Via አዲስ አበባ ፖሊስ መምሪያ

🌴🌴🌴

13/11/2025
13/11/2025
13/11/2025

20 ሜትር ጥልቀት ካለው የህንፃ ጉድጓድ አፋፍ ላይ በተአምር የተረፈችው ሾፌር!

ዛሬ በአዲስ አበባ ሜክሲኮ ደብረ ወርቅ ህንፃ አካባቢ አስገራሚና ለጥቂት የተረፈ ከባድ አደጋ ተከስቷል!

አንዲት ሴት ሾፌር በድንገት መኪናዋ ፍሬን እምቢ በማለት ከቁጥጥር ውጪ ለመሆን ቢቃረብም፣ ታላቅ ጥፋት ከመድረሱ በፊት ተመልሷል።

በአካባቢው በመሰራት ላይ ባለው ሕንፃ የተቆፈረው ጉድጓድ 20 ሜትር ጥልቀት ካለው አናት ላይ! ሾፌሯ ፣ ተሽከርካሪው ወደ ጥልቁ ከመንሸራተቱ ለጥቂት ሰከንዶች በፊት ማቆም ችላለች!

የታላቅ ጥንቃቄ እና የዕድል ጉዳይ ሆኖ፣ በዚህ አስደንጋጭ ክስተት በሰው ላይ ምንም ዓይነት ጉዳት አልደረሰም።

ነገር ግን አደጋው የጉድጓዱን አስፈሪነት እና የመንገድ ደህንነት ትኩረት እንዲህም መኪናዎቻችን ደህንነት እንደሚያስፈልገው አሳይቷል።

Via አዴ ቡና አብነት ከስፍራው

🙏🙏🙏

🌴🌴🌴

13/11/2025

አስቸኳይ ዜና ከሃዋሳ

የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን እና የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን በሃዋሳ ልዩ የኢኮኖሚ ዞን በሚገኘው ቶዮ ሶላር ኩባንያ ውስጥ በተፈጠረው ግጭት ላይ ያካሄዱትን ማጣራት አጠናቀዋል።

ግጭቱ የተነሳው “በስራ ገበታ ላይ በተደጋጋሚ በሰዓቱ አልተገኘህም” በሚል በተነሳ አለመግባባት ነው። ግጭቱ በአንድ የውጭ ዜግነት ባለው ሱፐርቫይዘርና አንድ ኢትዮጵያዊ ሰራተኛ መካከል የተፈጠረ አምቧጓሮ ነው።

አለመግባባቱ በህግና በኩባንያው ፖሊሲ እንጂ ሰብዓዊ መብትን በጣሰ መልኩ በፀብ መፈታት አልነበረበትም በሚል መግባባት ላይ ተደርሷል። በዚህም መሰረት፣ ኩባንያው በአጠቃላይ 5 ኃላፊዎች ላይ እርምጃ ወስዷል፡

1) ከሥራ የተሰናበቱ ሠራተኞች (2 ሰዎች):

* ድብደባውን የፈፀመው የውጭ ዜጋ ሰራተኛ፡ የድርጅቱን የስነምግባር መመሪያ ባለማክበር ምክንያት ወዲያውኑ ከሥራ ተሰናብቷል።

* ጉዳዩ የሚመለከተው የኩባንያው የስራ ኃላፊ፡ ድርጊቱ በተፈፀመበት ወቅት ተገቢውን አስተዳደራዊ ክትትልና እርምጃ ባለመውሰዱ ምክንያት ከሥራ ተባሯል።

2) የጽሑፍ ማስጠንቀቂያ የተሰጣቸው (3 ሰዎች):

* ተጨማሪ ሶስት መካከለኛ ደረጃ ሥራ አስኪያጆች ኃላፊነታቸውን በአግባቡ ባለመወጣታቸው ከባድ የጽሁፍ ማስጠንቀቂያ ተሰጥቷቸዋል።

እንደዚህ አይነት ችግሮች እንዳይደገሙ ለመከላከል፣ ለኩባንያው ሰራተኞችና አመራሮች ቀጣይነት ያለው ስልጠና የሚሰጥ ይሆናል።

ይህ ውሳኔ ቶዮ ሶላር፣ የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽንና የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ማንኛውንም ዓይነት የስነምግባር ጉድለት፣ አካላዊና ስነልቦናዊ ጥቃት እንደማይታገሱ ግልጽ ማሳያ ነው።
ኮርፖሬሽኑ በሚያስተዳድራቸው ሁሉም የኢኮኖሚ ዞኖች እና ፓርኮች ውስጥ የሠራተኞች ደህንነት፣ ክብር እና እኩልነት ሳይጓደል እንዲጠበቅ ጥረቱን አጠናክሮ እንደሚቀጥል አረጋግጧል።

ቶዮ ሶላር ለ2 ሺህ ሰራተኞች የስራ እድል የፈጠረ ሲሆን፣ በየወሩ ከ15 ሚሊዮን ዶላር በላይ ወደ ውጭ የሚልክ ትልቅ ድርጅት ነው።

ምንጭ፡ የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን

🌴🌴🌴

13/11/2025
13/11/2025

Adresse

Lausanne

Webseite

Benachrichtigungen

Lassen Sie sich von uns eine E-Mail senden und seien Sie der erste der Neuigkeiten und Aktionen von EthioAfro world TV by Abraham erfährt. Ihre E-Mail-Adresse wird nicht für andere Zwecke verwendet und Sie können sich jederzeit abmelden.

Teilen

Kategorie