
21/04/2025
አብይ አህመድ ካድሬዎች ሰብስቦ ጉራጌ ይቅርታ ጠየቀኝ ባለበት ቀን ወልቂጤ ሄዶ ሰባት የተለያዩ አንድ ሆነዉ ጉራጌ ሆኑ ሲል የመስቃን፣የሶዶና የዶቢ ጉራጌዎች ምሥራቅ ብዬ ከፈልኳቸዉ አሁን የምዕራቡ ለመከፋፈል እንደሆነ ገብቶን ነበር ይኸዉ አሁን ደግሞ በመማሪያ መጻፍ ጉራጌ የመከፋፈል ሸፍጥ ከሽኖ ይዞ ብቅ አለ።
በአዲሱ የ11ኛ ክፍል የታሪክ መፅሐፍ ላይ ስለ ጉራጌ ማንነትና ታሪክ የተፃፈውን አጭር ታርክን እቃወማለሁ!!
በመፅሃፉ ውስጥ ከቤተ ጉራጌ አባላቶች 7 ቤት ጉራጌንና ክስታኔ ጉራጌን ብቻ ሰፊውቹ ጉራጌዎች ተደርገው የተንፀባረቁበት መንገድ እጅግ በጣም አደገኛና ጉራጌን የመከፋፈል ተግባር ነው። ጉራጌነት ውስጥ ማንም ትልቅ ማንም ትንሽ ተደርጎ እንዲንፀባረቅ አንፈልግም። ቤዙ ቁስል ስላለብን እባካችሁ አትነካኩን!!
በቤተ ጉራጌ ውስጥ የመስቃን፣ የዶቢ፣ የገደባኖ፣ ጉታዘር፣ ኮኪርና ወለኔ ቤተ ጉራጌዎች ተካተው የባህል ሽምግልናቸውን ፈራገዘኘና የሲናኖ ሴራ አለመካተቱ የጉራጌ አንድነት ላይ የተቃጣ ጥቃት ነው።
ይህንን ጉዳይ የሁሉም ቤተ ጉራጌ ተወላጆች በጋራ ልንቃወመው ይገባል።
👉ከዚህ ወጪ ግን በሁለት ቢላ የምትበሉ ከፋፋዮች እንደለመዳችሁት ሌላ የፖለቲካ አጀንዳ ልታደርጉት አትሞክሩ ያለፈው ይበቃናል።
👉ሁሉም ቤተ ጉራጌዎች ለመማሪያ ያዘጋጇቸው መፃሀፎች በራሳቸው #ጉራጊኛ ተብለው ዘዬው ተጠቅሶ ቢስተካከሉ መልካም ነው። ኩተራ ሂን አዠም ይጨቅም!
👉ጉራጌ እማቱ/ቁናው/