DW Amharic

DW Amharic ዶይቼ ቬለ ርዕሰ ጉዳዮችን በፊስ ቡክ ያወያያል።
Telegram : t.me/dw_amharic
WhatsApp : https://t1p.de/2gg5u

Netiquette: https://www.dw.com/en/dw-netiquette-policy/a-5300954

የጥቅምት 6 ቀን 2018 ቀን አርዕስተ  ዜናበአማራ ክልል ምሥራቅ ጎጃም ዞን የእነማይ ወረዳ ምክትል አስተዳዳሪና የሥራና ክህሎት ጽ/ቤት ኃላፊ የነበሩት አቶ አዲሱ ተሻለ ዛሬ ጠዋት በተተኮሰ...
16/10/2025

የጥቅምት 6 ቀን 2018 ቀን አርዕስተ ዜና

በአማራ ክልል ምሥራቅ ጎጃም ዞን የእነማይ ወረዳ ምክትል አስተዳዳሪና የሥራና ክህሎት ጽ/ቤት ኃላፊ የነበሩት አቶ አዲሱ ተሻለ ዛሬ ጠዋት በተተኮሰባቸው ጥይት ህይወታቸው ማለፉን የወረዳው የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ባሰራጨው ዘገባ አስታውቋል።

የአፍሪቃ ሕብረት ማዳጋስካር ዉስጥ ተደረገ ያለዉን መፈንቅለ መንግሥት አወገዘ።ሕብረቱ ትናንት የማዳጋስካር ጦር ኃይል የሐገሪቱን የመንግሥትነት ሥልጣን መያዙን ተቃዉሟል።

በአሁኑጊዜ በዓለማችን ቁጥሩ 14 ሚሊዮን የሚጠጋ ህዝብ በከባድ ረሀብ እየተሰቃዩ ነው ሲል የዓለም ምግብ ድርጅት አስታወቀ።

የጥቅምት 6 ቀን 2018 ቀን አርዕስተ ዜና በአማራ ክልል ምሥራቅ ጎጃም ዞን የእነማይ ወረዳ ምክትል አስተዳዳሪና የሥራና ክህሎት ጽ/ቤት ኃላፊ የነበሩት አቶ አዲሱ ተሻለ ዛሬ ጠዋት በተተኮሰባ....

የትግራይ ኃይሎች ተቃውሞን ማኅበረሰቡም እንዲቀላቀል ተቃዋሚዎች ጥሪ አስተላለፉበትግራይ ክልል የሚንቀሳቀሱ ተቃዋሚ ፓርቲዎች የትግራይ ኃይሎች አባላት ሰሞኑን የጀመሩትን የተቃውሞ እንቅስቃሴ ሁ...
16/10/2025

የትግራይ ኃይሎች ተቃውሞን ማኅበረሰቡም እንዲቀላቀል ተቃዋሚዎች ጥሪ አስተላለፉ

በትግራይ ክልል የሚንቀሳቀሱ ተቃዋሚ ፓርቲዎች የትግራይ ኃይሎች አባላት ሰሞኑን የጀመሩትን የተቃውሞ እንቅስቃሴ ሁሉም የማኅበረሰብ ክፍል እንዲቀላቀል ጥሪ ጠየቁ ። ዓረና ትግራይ ለሉአላዊነት ዴሞክራሲ የቆየ የትግራይ ሕዝብ የለውጥ ፍላጎት ወደ ጎዳናዎች መፍሰስ ጀምሯል ብሏል ። የትግራይ ኃይሎች ባለፈው ሰኞ የጀመሩት ተቃውሞ ዛሬም ቀጥሎ ውሏል ።

በትግራይ ክልል የሚንቀሳቀሱ ተቃዋሚ ፓርቲዎች የትግራይ ኃይሎች አባላት ሰሞኑን የጀመሩትን የተቃውሞ እንቅስቃሴ ሁሉም የማኅበረሰብ ክፍል እንዲቀላቀል ጥሪ ጠየቁ ። ዓረና ትግራይ ለሉ...

የኦሮሚያ እና ሶማሊ ክልሎች አዋሳኞች ግጭትበኦሮሚያ እና ሶማሊ ክልሎች አዋሳኝ አካባቢ የተፈናቀሉ ነዋሪዎች በድጋፍ እጥረት ችግር ላይ መሆናቸው እየተነገረ ነው ። ደ ቀዬያቸውና ነባሩ ኑሯቸው...
16/10/2025

የኦሮሚያ እና ሶማሊ ክልሎች አዋሳኞች ግጭት

በኦሮሚያ እና ሶማሊ ክልሎች አዋሳኝ አካባቢ የተፈናቀሉ ነዋሪዎች በድጋፍ እጥረት ችግር ላይ መሆናቸው እየተነገረ ነው ። ደ ቀዬያቸውና ነባሩ ኑሯቸው እንዳልተመለሱም ተገልጧል ።

በኦሮሚያ እና ሶማሊ ክልሎች አዋሳኝ አካባቢ የተፈናቀሉ ነዋሪዎች በድጋፍ እጥረት ችግር ላይ መሆናቸው እየተነገረ ነው ። ደ ቀዬያቸውና ነባሩ ኑሯቸው እንዳልተመለሱም ተገልጧል ።

የፓርቲዎች የመንቀሳቀሻ ሜዳ ጠበበ ወይስ ሠፋ?በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በታችኛው የአስተዳደር መዋቅሮች በሚገኙ የማኅበረሰብ ክፍሎች ላይ አማራጭ የፖለቲካ ሐሳባቸውን ለማቅረብ መቸገራቸውን የዐሥ...
16/10/2025

የፓርቲዎች የመንቀሳቀሻ ሜዳ ጠበበ ወይስ ሠፋ?

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በታችኛው የአስተዳደር መዋቅሮች በሚገኙ የማኅበረሰብ ክፍሎች ላይ አማራጭ የፖለቲካ ሐሳባቸውን ለማቅረብ መቸገራቸውን የዐሥራ አንድ ፖለቲካ ፓርቲዎች ስብስብ የሆነው ሰላም ጥምረት አመለከተ፡፡

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በታችኛው የአስተዳደር መዋቅሮች በሚገኙ የማኅበረሰብ ክፍሎች ላይ አማራጭ የፖለቲካ ሐሳባቸውን ለማቅረብ መቸገራቸውን የዐሥራ አንድ ፖለቲካ ፓርቲዎች ስብስብ ....

IOM የኢትዮጵያን የ5 ዓመታት የሥራ ፍኖተ ካርታ ይፋ አደረገበተባበሩት መንግሥታት የፍልሰተኞች ድርጅት (IOM) ኢትዮጵያ ውስጥ በቀጣዮቹ አምስት ዓመታት ሁሉን አቀፍ ልማትና መረጋጋትን በማ...
16/10/2025

IOM የኢትዮጵያን የ5 ዓመታት የሥራ ፍኖተ ካርታ ይፋ አደረገ

በተባበሩት መንግሥታት የፍልሰተኞች ድርጅት (IOM) ኢትዮጵያ ውስጥ በቀጣዮቹ አምስት ዓመታት ሁሉን አቀፍ ልማትና መረጋጋትን በማስፈን «የስደትና መፈናቀል ችግሮችን ለመፍታት የሚያስችል» ያለውን ፍኖተ ካርታ ዛሬ ይፋ አደረገ ።

በተባበሩት መንግሥታት የፍልሰተኞች ድርጅት (IOM) ኢትዮጵያ ውስጥ በቀጣዮቹ አምስት ዓመታት ሁሉን አቀፍ ልማትና መረጋጋትን በማስፈን «የስደትና መፈናቀል ችግሮችን ለመፍታት የሚያስችል....

የወሎ ላሊበላ የባህል ሙዚቃ ቡድን ከትናንት ዛሬየባህል ሙዚቃን ከነሙሉ ክዋኔ እና ባህላዊ አልባሳትን ቱባውን ባህል ለህዝብ በማስተዋወቅ ረገድ በኢትዮጵያ ሙዚቃ ውስጥ የጎላ ሚና የተጫወተው የ...
16/10/2025

የወሎ ላሊበላ የባህል ሙዚቃ ቡድን ከትናንት ዛሬ

የባህል ሙዚቃን ከነሙሉ ክዋኔ እና ባህላዊ አልባሳትን ቱባውን ባህል ለህዝብ በማስተዋወቅ ረገድ በኢትዮጵያ ሙዚቃ ውስጥ የጎላ ሚና የተጫወተው የወሎ ላሊበላ የባህል ሙዚቃ ቡድን በ1960ዎቹ አጋማሽ ነበር፡፡

የባህል ሙዚቃን ከነሙሉ ክዋኔ እና ባህላዊ አልባሳትን ቱባውን ባህል ለህዝብ በማስተዋወቅ ረገድ በኢትዮጵያ ሙዚቃ ውስጥ የጎላ ሚና የተጫወተው የወሎ ላሊበላ የባህል ሙዚቃ ቡድን በ1960ዎቹ...

የማኅበራዊ መገናኛ ዘዴዎች ቅኝትየኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብት ኮሚሽን፤ኢሰመኮ የመዘዋወር ነጻነት አደጋ ላይ ወድቋል ሲል ያወጣው መግለጫ እና የመንግሥት ምላሽ፣ ዶይቸ ቬለ ከአጭር ሞገድ ወደ ሳተ...
16/10/2025

የማኅበራዊ መገናኛ ዘዴዎች ቅኝት

የኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብት ኮሚሽን፤ኢሰመኮ የመዘዋወር ነጻነት አደጋ ላይ ወድቋል ሲል ያወጣው መግለጫ እና የመንግሥት ምላሽ፣ ዶይቸ ቬለ ከአጭር ሞገድ ወደ ሳተላይት ሽግግርን እንዲሁም የኢትዮጵያ የኒዩክሌር ኮሚሽን ኮሚሽነር ሹመትን በዚህ ሳምንት በማኅበራዊ መገናኛ ዘዴዎች ብዙ አስተያየት የተሰጠባቸው ነበሩ።

የኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብት ኮሚሽን፤ኢሰመኮ የመዘዋወር ነጻነት አደጋ ላይ ወድቋል ሲል ያወጣው መግለጫ እና የመንግሥት ምላሽ፣ ዶይቸ ቬለ ከአጭር ሞገድ ወደ ሳተላይት ሽግግርን እንዲሁ.....

ቃለ መጠይቅ፣ የወደብ ጥያቄ፣ የዉጪ ጣልቃ ገብነት፤የኢትዮጵያ፣ የኤርትራና የህወሓት መሪዎች---ግብፅና የተባበሩት አረብ ኤሚሬቶችም የአሥመራና የአዲስ አበባን መሪዎች በመደገፍ ጠቡን እያባባሱ...
16/10/2025

ቃለ መጠይቅ፣ የወደብ ጥያቄ፣ የዉጪ ጣልቃ ገብነት፤የኢትዮጵያ፣ የኤርትራና የህወሓት መሪዎች---

ግብፅና የተባበሩት አረብ ኤሚሬቶችም የአሥመራና የአዲስ አበባን መሪዎች በመደገፍ ጠቡን እያባባሱት መሆናቸዉ እየተነገረ ነዉ።የአፍሪቃና የመካከለኛዉ ምሥራቅ ጉዳይ የፖለቲካ ተንታኝ አብዱረሕማን ሰይድ እንደሚሉት የአዲስ አበባና የአሥመራ መሪዎች ባሕሪም ልዩነቶችን በድርድር ለማስወገድ የሚመች አይመስልም

ግብፅና የተባበሩት አረብ ኤሚሬቶችም የአሥመራና የአዲስ አበባን መሪዎች በመደገፍ ጠቡን እያባባሱት መሆናቸዉ እየተነገረ ነዉ።የአፍሪቃና የመካከለኛዉ ምሥራቅ ጉዳይ የፖለቲካ ተንታኝ...

16/10/2025

ጤና ይስጥልን!
ለአንድ ሰዓት በሚዘልቀው የዕለቱ ሥርጭት ኂሩት መለሰ የዓለም ዜና ታቀርባለች ፤ ማንተጋፍቶት ስለሺ ስርጭቱን ይመራል።
የዶይቼ ቬለ የቀጥታ ሥርጭት ከራዲዮ ሞገድ እና ከሳተላይት በተጨማሪ በቴሌግራም እና በዩቲዩብ ይተላለፋል። ማድመጫውን ለወዳጆቻችሁ እያጋራችሁ አብራችሁን ዝለቁ።
ትክክለኛውን የዶይቼ ቬለ የዩቲዩብ እና የቴሌግራም ቻናሎች በሚከተሉት ማስፈንጠሪያዎች ታገኛላችሁ።
https://www.youtube.com//videos
https://t.me/dw_amharic
dwamharic_newshour

የትግራይ ሐይሎች ተቃዉሞ እንደቀጠለ ነዉ፤ ተቃዋሚዎች ጥሪ አደረጉየትግራይ ኃይሎች የሚባለዉ ወታደራዊ ሥብስብ አባላት የሚያደርጉትን ተቃዉሞ ሌሎች የሕብረተሰብ ክፍሎች እንዲደግፉ ተቃዋሚ ፓርቲ...
16/10/2025

የትግራይ ሐይሎች ተቃዉሞ እንደቀጠለ ነዉ፤ ተቃዋሚዎች ጥሪ አደረጉ

የትግራይ ኃይሎች የሚባለዉ ወታደራዊ ሥብስብ አባላት የሚያደርጉትን ተቃዉሞ ሌሎች የሕብረተሰብ ክፍሎች እንዲደግፉ ተቃዋሚ ፓርቲዎች ጠየቁ።የደሞዝና ሌሎች ጥቅማ ጥቅሞች እንዲከበሩላቸዉ በመጠየቅ ተቃዉሞና የመንገዶች መዝጋት እርምጃ የሚወስዱት የትግራይ ኃይሎች አባላት ዛሬም ተቃዉሟቸዉን እንደቀጠሉ ነዉ።የሠራዊቱ አባላት የተለያዩ ከተሞችን የሚያገናኙ አዉራ ጎዳኖችንና የየከተሞቹን መንገዶች ዘግተዋል።መገዶች በመዘጋታቸዉ የሕዝቡ የዕለት ከዕለት እንቅስቃሴ ተስተጓጉሏል።የትግራይ ሐይሎች የህዝብ ተቃውሞዎች ከማፈን ወጥተው የራሳቸውን ጥያቄዎች ይዘው ወደጎዳናዎች መውጣታቸውን ተቃዋሚዉ የዓረና ትግራይ ለሉአላዊነትና ለዴሞክራሲ እንደሚደግፈው የፓርቲው ሊቀመንበር አቶ ዓምዶም ገብረስላሴ ተናግረዋል።ሌላዉ ተቃዋሚ ፓርቲ የትግራይ ነፃነት ፓርቲ በበኩሉ በትግራይ ያለውን ስርዓት ለመገርሰስ ወጣቶች፣ ሴቶች እና ሌሎች የማሕበረሰብ ክፍሎች ጥያቄዎቻቸውን ይዘው ተቃውሞውን እንዲቀላቀሉ ጠይቋል።የመቀሌዉ ወኪላችን ሚሊዮን ኃይለ ሥላሴ እንደዘገበዉ ዛሬ መቀሌ ዉስጥ የሚገኙ የጦር ጉዳተኞች የተለያዩ ጥያቄዎችን በማንሳት በከተማዋ ሰልፍ አድርገዋል።

የእነማይ ወረዳ ምክትል አስተዳዳሪ ተገደሉበአማራ ክልል ምስራቅ ጎጃም ዞን የእነማይ ወረዳ ምክትል አስተዳዳሪ ዛሬ ጠዋት በታጣቂዎች መገደላቸውን የወረዳው አስተዳደር  አስታወቀ፡፡ የወረዳው የ...
16/10/2025

የእነማይ ወረዳ ምክትል አስተዳዳሪ ተገደሉ

በአማራ ክልል ምስራቅ ጎጃም ዞን የእነማይ ወረዳ ምክትል አስተዳዳሪ ዛሬ ጠዋት በታጣቂዎች መገደላቸውን የወረዳው አስተዳደር አስታወቀ፡፡
የወረዳው የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ባሰራጨው ዘገባ የወረዳው ምክትል አስተዳዳሪና የሥራና ክህሎት ጽ/ቤት ኃላፊ የነበሩት አቶ አዲሱ ተሻለ ዛሬ ጠዋት 12፡30 ከመኖሪያ ቤታቸው ተነስተው ወደ ጽ/ቤታቸው ሲጓዙ በተተኮሰባቸው ጥይት ህይወታቸው አልፏል፡፡
አስተዳደሩ ለግድያው “ጽንፈኛ” ብሎ የጠራውንና በአካባቢው የሚንቀሳቅሰውን ታጣቂ ኃይል ተጠያቂ ነው ሲል በመግለጫው ከስሷል፡፡
የግለሰቦች ህይወት በተለያየ ጊዜና ቦታ እየጠፋ እንደሆነም መግለጫው አመልክቷል፡፡
በጉዳዩ ዙሪያ ተጨማሪ አስተያየት እንዲሰጡን ለወረዳው ዋና አስተዳዳሪ ብንደውልም “መልሼ እደውላልሁ” ካሉ በኋላ ሊደውሉ ባለመቻላቸው ሀሳባቸውን ማካተት አልቻልንም፡፡

ማስታወቂያ ዶይቼ ቬለ የማርኛ አገልግሎት ከ2018 ዓመት መጀመሪያ ጀምሮ የጦማረ-ዜና (Newsletter) አገልግሎት ጀመሯል።በየዕለቱ ከምናሰራጫቸዉ ዝግጅቶች መካካል የጎሉትን ዝግጅቶች በየሳ...
16/10/2025

ማስታወቂያ
ዶይቼ ቬለ የማርኛ አገልግሎት ከ2018 ዓመት መጀመሪያ ጀምሮ የጦማረ-ዜና (Newsletter) አገልግሎት ጀመሯል።በየዕለቱ ከምናሰራጫቸዉ ዝግጅቶች መካካል የጎሉትን ዝግጅቶች በየሳምንቱ ሐሙስ መርጠን የሚጠናቀሩበትን የጦማረ ዜና (Newsletter ) በቀጥታ በኢሜል አድራሻዎ እንልክልዎታለን።የአገልግሎቱ ተጠቃሚ እንዲሆኑ ከታች በተቀመጠዉ ማገናኛ (Link) ውስጥ ባለው ባዶ ቦታ የኢሜል አድራሻዎን ይሙሉ።ቀጥሎ ባለዉ ክፍት ቦታ ደግሞ የአጠቃቀም ደንብ፣ የሚለውን በመጫን «ያስገቡ» የሚለውን ሲነኩ በቀላሉ ተመዘገቡ ማለት ነው ። የአዲሱ አገልግሎታችን ተጠቃሚ እንድትሆኑ ሁላችሁም ተጋብዛችኋል። መልካም ጊዜ።
የዶይቼ ቬለ የጦማረ-ዜና (Newsletter )አገልግሎት
https://system.promio-connect.com/.../single.../83494

Adresse

Kurt-Schumacher-Str. 3
Bonn
53113

Benachrichtigungen

Lassen Sie sich von uns eine E-Mail senden und seien Sie der erste der Neuigkeiten und Aktionen von DW Amharic erfährt. Ihre E-Mail-Adresse wird nicht für andere Zwecke verwendet und Sie können sich jederzeit abmelden.

Service Kontaktieren

Nachricht an DW Amharic senden:

Teilen