Breaking News In Ethiopia " ሰበር ዜና "

Breaking News In Ethiopia "  ሰበር ዜና " Human Rights, Freedom Of Expression & Rule Of Low ln Ethiopia. Big No For War, Enough With ETHNIC FEDERALISM! Ready To Deal ANY Difference's.......

የፌደራል ገቢ ግብር አዋጅ ፀደቀ።የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የፌደራል ገቢ ግብር አዋጅን ለማሻሻል የቀረበውን ረቂቅ አዋጅ አፀደቀ።ረቂቅ አዋጁ በአብላጫ ድምጽ ነው የፀደቀው።ረቂቅ አዋጁ ላይ...
17/07/2025

የፌደራል ገቢ ግብር አዋጅ ፀደቀ።

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የፌደራል ገቢ ግብር አዋጅን ለማሻሻል የቀረበውን ረቂቅ አዋጅ አፀደቀ።

ረቂቅ አዋጁ በአብላጫ ድምጽ ነው የፀደቀው።

ረቂቅ አዋጁ ላይ ሰፊ ክርክር ሲነሳበት እንደነበር ይታወቃል። በተለይ የኢትዮጵያ ሰራተኛ ማሕበራት ኮንፌዴሬሽን (ኢሰማኮ) ረቂቅ አዋጁ ላይ የደመወዝ ገቢ ግብር መነሻ ተብሎ የተቀመጠው 2,000 ብር ወደ 8,324 ብር ከፍ እንዲል ፤ አጠቃላይ አዋጁ የኑሮ ውድነቱንና ጫናውን ታሳቢ ባደረገ መልኩ እንዲታረም ሲወተውት ነበር።

ከ0 ጀምሮ 10% ፣ 15% ፣ 20% ፣ 25% ፣ 30% ፣ 35% ይቀጥል የነበርው የግብር ምጣኔም በረቂቅ አዋጁ 10% ከመሃል ወጥቶ ከ0 ጀምሮ ቀጥታ ባከፍተኛው 15% መጀመሩንም ታቃውሞ ነበር።

ሌላው 14,100 በላይ የሚያገኝ ሰው 35% ግብር ይከፍላል በሚለው ላይም ጥያቄ ተነስቶ ነበር።

በአሁኑ የኑሮ ውድነት ሰራተኛው በእያንዳንዱ ነገር በምግብ ዋጋ፣ በሚገዛው እቃ 15% ይጨምራል ይሄ በ35% ላይ ሲደመር 50% ይመጣል፤ 7% የጡረታ አለ ሲደመር 57% ከደመወዙ ላይ ይሄዳል በቀረችው 43% ልጆች ያስተምራል ፣ ምግብ ይበላል ፣ ልብስ ይገዛል ፣ ቤት ይከራያል ምንድነው የሚያደርገው ? የሚል የሰራተኛውን ጥያቄ በማንሳት ረቂቁ እንዲታረም ጠይቆ ነበር።

ሰበር ዜናበአሁን ሰአት በአፋር ክልል የሚገኘው ኤርታሌ እሳተ ገሞራ እየፈፈነዳ ይገኛልተገቢው ጥንቃቄ ይደረግ
15/07/2025

ሰበር ዜና

በአሁን ሰአት በአፋር ክልል የሚገኘው ኤርታሌ እሳተ ገሞራ እየፈፈነዳ ይገኛል
ተገቢው ጥንቃቄ ይደረግ

“በአፋር ክልል የሚገኙ ታጣቂዎች የሚፈጽሙት ማንኛውም ትንኮሳ የፌደራል ወይንም የአፋር ክልል መንግስት ትነኮሳ አደርገን ነው የምንወስደው” - ሌተናል ጀነራል ታደሰ ወረደበአፋር ክልል የሚገኙ...
15/07/2025

“በአፋር ክልል የሚገኙ ታጣቂዎች የሚፈጽሙት ማንኛውም ትንኮሳ የፌደራል ወይንም የአፋር ክልል መንግስት ትነኮሳ አደርገን ነው የምንወስደው” - ሌተናል ጀነራል ታደሰ ወረደ

በአፋር ክልል የሚገኙ የትግራይ ታጣቂዎች የሚፈጽሙት ማንኛውም ትንኮሳ የፌደራል መንግስት ወይንም የአፋር ክልል መንግስት ትነኮሳ አደርገን ነው የምንወስደው ሲሉ የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት ሌተናል ጀነራል ታደሰ ወረዳ ገለጹ።

የክልሉ የሰማዕታት ኮሚሽን ባዘጋጀው መድረክ ላይ ትላንት ሐምሌ 8 ቀን 2017 ዓ.ም ተገኝተው ንግግር ያደረጉት ሌተናል ጀነራል ታደሰ ወረደ “በዚያ በኩል የሚኖር ምንም አይነት ተነሳሽነት/እንቅስቃሴ እንደ ትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር፣ እዚያ ያሉ ሀይሎች ብቻ አድርጎ አይወስደውም፣ ወይ የፌደራል መንግስት ነው ካልሆነም የአፋር መንግስት ነው ብሎ ነው የሚወስደው” ብለዋል።

“እዛ ካሉት (ነጻ መሬት) ሀይሎች ጋር ያለው ልዩነት መቶ በመቶ መፈታት ያለበት በሰላማዊ መንገድ ነው፤ ነገር ግን ማንኛውም ትንኮሳ ከአፋር ክልል በኩል ከመጣ ወይ የአፋር መንገስት ነው አልያም የፌደራል መንግስቱ ነው ተብሎ የሚወሰድ እንጂ የትግራይ ተወላጆች/ተጋሩ ተደርጎ የሚወሰድ አይደለም” ሲሉም አስታውቀዋል፤ ታጣቂዎች “የውክልና (Proxy) ሀይሎች ሁነው እንዳያገለግሉ የሚቻለንን ሁሉ እናደርጋለን ሲሉ ተደምጠዋል።

22/05/2025

አገዛዙ ሆሮ ጉዱሩ ወለጋ ዞን አሙሩ፣ጃርደጋ ጃርቴ፣ አሙሩና ሆሮ ቡልቅ እንዲሁም ምስራቅ ወለጋ ዞን ኪረሙና ጊዳ አያና ወረዳዎች አማራ በብዛት የሚኖርባቸው አካባቢዎች ካለፉት 3ቀን ጀምሮ ሙሉ በሙሉ ኔትወርክ ተዘግቷል።

በተለያዩ አቅጣጫዎችም የአገዛዙ ጥምር ጦር ወደ ገጠራማው ክፍል እንቅስቃሴ እያደረገ እንደሚገኝና አማራው ላይ የከፋ ጉዳት ሊያደርሱ እንደሚችሉ የደረሰን መረጃ ያመላክታል።መከረኛው የወለጋ ህዝብ ዛሬም ሌላ መከራ አንዣቦበታል።

04/05/2025

የብሪታንያ፣ ፈረንሳይና ኖርዌይን ጨምሮ መቀመጫቸውን በአዲስ አበባ ያደረጉ 14 ኢምባሲዎች፣ በኢትዮጵያ በንግግር ነጻነት ላይ የሚደረገው "ከፍተኛ ተጽዕኖ" እንዳሳሰባቸው ትናንት የተከበረውን ዓለማቀፉን የፕሬስ ነጻነት ቀን አስመልክተው በጋራ ባወጡት መግለጫ አስታውቀዋል። ኢምባሲዎቹ፣ የአገሪቱ ጋዜጠኞች ከለላ እንዲሠጣቸውና የፕሬስ ነጻነት እንዲከበር ጠይቀዋል። አውሮፓ ኅብረት በበኩሉ፣ በአገሪቱ የፕሬስ ነጻነት ከሌለ መረጃ የማግኘት መብትና በነጻነት ማሰብ ችግር ላይ ይወድቃሉ ብሏል። ዓለማቀፉ ድንበር የለሽ የጋዜጠኞች ቡድን በትናንቱ ዓመታዊ የአገራት የፕሬስ ነጻነት ሪፖርት፣ ለኢትዮጵያ ከ180 አገራት 145ኛ ደረጃ የሠጣት ሲኾን፣ በአገሪቱ የፕሬስ ነጻነት "እጅግ አስቸጋሪ" ሁኔታ ውስጥ እንደሚገኝም ገልጧል።

29/04/2025

በኦሮሚያ ክልል በአርሲ ዞን በአርሲ ስሬ ወረዳ ዛሬ ረፋዱ ላይ ታጣቂዎች አንድ ቅጥቅጥ አይሱዙ የሕዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪ አስቁመው ከ50 በላይ ተሳፋሪዎችን አግተው መወሰዳቸውን ምንጮች ገልጸዋል። ታጣቂዎቹ እገታውን የፈጸሙት፣ ተሽከርካሪው ከአርሲ ስሬ ወረዳ ወደ አዳማ ከተማ በመጓዝ ላይ ሳለ እንደሆነ የአካባቢው የዓይን እማኞች ተናግረዋል። እገታው የተፈጸመበት ሥፍራ ከዚህ ቀደም በጸጥታ ኃይሎች ጥበቃ ይደረግለት እንደነበር የገለጹት ምንጮች፣ በዛሬው ዕለት ግን የጸጥታ ኃይሎች ከአካባቢው ተነስተው እንደነበር ገልጸዋል። ታጣቂዎች፣ በዞኑ በአቦምሳ ወረዳ ልዩ ስሙ ከሬቸር በተባለ ሥፍራ ባለፈው እሁድ በተመሳሳይ ወደ አዳማ ከተማ ሲጓዝ ከነበረ ተሽከርካሪ ላይ በርካታ ተሳፋሪዎች እንዳገቱም ምንጮች አስረድተዋል።

22/04/2025

የሰራተኞች የደመዎዝ እርከን ጭማሪ መደረጉን ተከትሎ የተሰሙኝን ሁለት ነጥቦችን ላጋራቹ። ሁለት ያልኳቸውን ነጥቦችንም በቅድሚያ ላስቀምጥና 1ኛ/እርከኑ የተሰጠበት 16% ን በተመለከተ ሲሆን፤2ኛ/ከታችኛው እስከ እስከ ከፍተኛው ደረጃ ባሉ ሰራተኞች መካከል በተመሳሳይ የስራ መደብ ላይ እየሰሩ ነገር ግን የደሞዛቸው ለዩነት እንዴት ተፈጠረ የሚለውን መተንተን የሚሉት ናቸው። እንዴት?እንመለከተዋለነሰ!
ሁላቹም እንደምታውቁት የተከበሩ የተቋሙ ጊዜያዊ ፈላጭ ቆራጭ ባለፈው ሳምንት በጠራው ስብሰባ ላይ በማለት ከግል ኪሳቸው አውጥተው የሚሰጡ ይመስል እንደ ሰበር ዜና የኑኖ ውድነት ተግዳሮት የሆነባቸው ስራተኞች ጆሮ ዘንድ ደርሶ አንዱ "ተመስገን ደሞዝ ሊጨመርልን ነው አሉ!" በማለት ተስፋውን ሲገልፅ፤ሌላኛው ደግሞ "ጭማሪ ቢደረግም ቢደረግም ጨማሪዎቹን ወይም እራሳቸውን ከፍተኛ አመራሩን በሚጠቅም ስልት ያደርጉታል እንጂ መካከለኛና ታችኛውን ሰራተኞችን ታሳቢ አድርገው አይሰሩትም " በማለት ያላቸውን ተስፋቢስ ስሜት በመግለፅ ላይ ነበሩ። በሌላ በኩል ደግሞ "አመራሩን ጨምሮ ከታችኛው እስከ ላይኛው እርከን ያሉትን የፕሬዝዳንቱ ወዳጆችን በሚጠቅም ሁኔታ ሊጨምሩ ካልሆነ በስተቀር፣ሚዛናው የሆነ ስራ ይሰራል ብዬ አልጠብቅም" በማለት ከወዲሁ የሚሆነውን ድርጊት መላ ምታቸውን ያሰቀመጡም ሰራተኞች አልጠፋም ነበር። የሆነ ሆኖ መላምቱ ያም ሆነ ይህ ድርጊት ከሰራተኛው መላምት የተለየ አልሆነም!! እንመልከተው፤ በባንኩ ውስጥ ተቀጥረው በሚሰሩ ሰራተኞች ውስጥ ያለውን የደሞዝ ልዩነት ብንመለከት ዝቅተኛው5000ሺ ሲሆን ከፍተኛው ተከፋዩ ደግሞ ገደብ የለሽ ጥቅማ ጥቅም ሳይጨምር ከ280000-300000ብር ይደርሳል ። በእርግጥ የከፍተኛ አመራሩ ደሞዝ በግልፅ ተጠቅሶ ለሰው ሀይል ፣ለኦዲትና ለፋይናስ ክፍል በደብዳቤ ተገልፆ የተሰጠ መሠጃ የለም በተለይ የፋይናስ ክፍሉ ምን አይቶ ደሞዛቸውን እንደሚከፍላቸው የሚያውቁት ፈጣሪና የተቋሙ 'ጊዜያዊ ፈላጭ ቆራጭ ' ብቻ ናቸው።ለምን የከፍተኛ አመራሩ ወርሀዊ ደሞወዛቸው ብቻ ስንት እንደሆነ እንደማይነገር ግልፅ አይደለም። ከፋዮችን ስንጠይቅ ክፈሉ የተባ
ልነውን ነው የምንከፍለወሰ ከማለት ውጪ ከማብራራት ይቆጠበሉ ።ተከፋዮችን ስንጠይቅ ብቻ መውሰድ እንጂ ደሞዛችን በትክክል ስንት እንደሆነ በቁጥር ተገልፆ አልተሰጠንም።አናቀውም
ይላሉ።እንግዲህ ከላይ እንዳያቹት በታችኛው ና በከፍተኛው ሰራተኛ መካከል ያለውን የደመወዝ ለዩነትን በመገንዘብ ጭማሪው ማንን እንደሚጠቅም መረዳተሰ ይቻላል።እዚህ ላይ ያለውን የደመወዝ ልዩነት ለማሳየት ወይም ትክክል አይደለም ለማለት ሳይሆን፣ ዋናው ነጥብ ተጨመረ የተባለው 16%ለከፍተኛውና ለዝቅተኛው ተከፋይ እኩል መሆን አልነበረበትም።ምክንያቱም 5ሺ ደሞወዝ ተከፋይ የሆነ ሰው 16%ሲሰላ የተጨመረለት 800ብር ብቻ ነው። ባለ 10ሺ ደሞዝተኛ ብንወስድ ደግሞ የተጨመረለት 1600ብር። ወደ ለይ እንውጣና 100ሺ ብር ደመወዝተኛ የሆነ ደግሞ 16000ብር ተጨምሮለታል።እንዲሁም 150ሺ ተከፋይ ደግሞ 24000ብር የተጨመረለት ሲሆን 280ሺሀሰ ተከፋይ የሆነው ግለሰብ ደግሞ 44800ብር ተጨምሮለታል ማለት ነው።እዚህ ላይ ለማስገንዘብ የተፈለገው ዋናውና መሰረታዊ ነጥብ ጭማሪ በተደረገላቸው በታችኛውና በላይኛው እርከን ባሉ ሰራተኞች ውስጥ የጭማሪው ልዩነት በ800ብር እና በ4480 ብር መሆኑ ላይ ብቻ ነው።ይህ ታዲያ ምን ብለን እንለፈው? ለማንኛውም መሆን የነበረበት አሁን ያለውን የኑሮ ውድነትን ታሳቢ በማድረግና የበለጠ የስራ ተነሳሽነትን ለመፍጠር ቢታሰብ ዝቅተኛ ተከፋዩን ሰራተኛ ትርጉም ባለው መልኩ ሊደጉም በሚችል አግባብ መጨመር ነበረበት።ለምሳሌ ከ5-20ሺ ብር ተከፈይ ለሆነ ሰራተኛ 30%ጭማሪ ቢደረግለት፣ከ20-50ሺህ ብር ተከፋይ ለሆነ ሰራተኛ 25%ቢሆን ፣ከ50-100ሺህ ያለ ደግሞ 10%ቢሆንና ከ100ሺህ ብር በላይ ተከፋይ የሆኑትን ደግሞ5%ብቻ በሆነ አግባብ ቢሆን ፍትሃዊ በሆነ ነበር ።በ%ከፋፍዬ ለማሳየት የፈኩት ጭማሪው ከታች ወደ ላይ መሆን ነበረበት የሚለውን ሀሳብ ለማሳየት ነው ።ምክንያቱም ዝቅተኛው ተከፋይ በመሆኑ ለማለት እንጂ%ቱ በትክክል የተሰላ አይደለም። የተቋሙ አሰራር ሁሌ'ውሃ ቢወቅጡት እንቦጭ!'ነውና የተደረገውን ጭማሪ ከፍተኛውን አመራር ተጠቃሚ ያደረገ ብቻ መሆኑን ተረድተናል። ስራ ያለው ታች ቢሆንም የታችኛው ሰራተኛ ልፋት በዜሮ ተባዝቷል።ውዝፍ በማስመለስ እረገድና ቁጠባን በማፈላለግ ስራ ድካም የሚፈራረቅበት የታችኛው ምክኪን ሰራተኛ ግን በአንድ ግለሰብ ሰጪና ነሺ ይሁንታ ምክንያት በእጅጉ አዝኗል። ያለው ይጨመርለታል እንዲሉ የቋሚ ንብረት ግዥ ሲፈቀድ ቅድሚያ ለከፍተኛው አመራር ያለ ዩሉንታ ይቀራመታል።ደመወዝ ሲጨመር ልታጎርሰው እጅህን የላክለት አፍ ሲከፈት

አይተህ መልሰህ ለራስህ ጠቅልሎ የመጉረስ ያህል ከፍተኛ አመራሩ ነው የሚሰለቅጠው።ይሁን እንግዲህ ሁላችንም አንድ እንጀራ ነው በልተን የምናድረው።ጠያቂና ተጠያቂ ተቀራርበው ሲሰሩ እውነታው ይገለጣል።
መግቢያው ላይ የተጠቀሰውን 2ኛውን ነጥብ ሌላጊዜ እንወያይበታለን እያልኩኝ
እሰናበታለው የዚህ ምስኪን ሰራተኛን በደል ፈጣሪ ያስከፍላቹ ከሰው ፍትህ አይገኝም ፈጣሪ ፍትህን ይስጥ።

20/04/2025

ኢትዮጵያ እንደ ሃገር እንድትቀጥል አንድነቷ እንዲጸና በዱር በገደሉ ተዋድቀው አጥንታቸውን ከስክሰው ያቆያትን አገር በታራክ አጋጣሜ ከኢትዮጵያ ጠላቶች ጋር የሚሰሩ ሚስጥር ቅረስ እየሸጡ የነበሩ ሆድ አደሮች ባንዳዎች እጅ በታራክ አጋጣሚ በመውደቃ በለፉት 7 አመታት የህዝቦች መከራ ሞት መፈናቀል ሳይበቃቸው አገራችን የከፈለችው የኢኮኖሚ የበሃል የታራክ ስብራቶችን መጠገን እና በመካስ ተጠያቂ መሆን ሲገባቸው ህዝብንም ይቅርታ መጠየቅ ሲገባቸው እኔ ከምትኩ ሰርዶ አይብቀል እደተባለው እኔ ካልመራው አፋራራሳታለው ወይም ትፈርሳለች በስልጣን ጥማት የሰከረው የብልጽግና እብድ መሪ በእትዮጵያ ከሰራቸው ያፈረሳቸው ከመገባቸው ያስራባቸው ሁሉን ለታራክ አስቀምጦ ለአገራችን ሰላም አንድነት የሙህራን የአገር ሽማግሌ የፖለቲካ ፓርቲ አለም አቀፋ መህበረሰብ የጎላ ሚናቸውን በመወጣት ባለፈው አምስት አመት የአገር መከላከያ ፌደራል ፓሊስ ልዩ ሃይል ለግለሰብ ስልጣን የከፈላቹህትን መሰዋእትነት በተለይ በትግራይ ጦረነት በወለጋ በአማራ የተከፋለው ማሳያ ማስተማሪያ በማድረግ ለአገር እና ለህዝባችን በማሰብ በዱር በገደሉ የምትፋለሙ የምትዋደቁና ውድ ህይወታችሁን የምትሰጡ የመከላክያ ሰራዊት አባላትና መላው የኢትዮጵያ ጸጥታ አስከባሪ የብልጽግና መንግስት በቃህ ይብቃህ በማለት እኛ ለአገር እንጂ ለግለሰብ መሰዋት የምንሆን የትንሣኤ በግ አደለንም የእትዮጵያ ህዝብሞ በግ አደለም በማለት ይብቃህ ለሁሉም ነገርህ ለመላው ክርስትና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለትንሳኤ በዓል በሰላም አደረሳችሁ!

መልካም በዓል ይሁንላችሁ፣ ይሁንልን።

19/04/2025

ከ300 በላይ ወጣቶች በግዳጅ ወደ መከላከያ ማሰልጠኛ ሊላኩ ነው።

እንጀራ በማድረስ፣ሎተሪ በማዞር እና የቀን ስራ በመስራት የሚተዳደሩ ከ300 በላይ የአማራ ወጣቶች ከአዲስ አበባ መንገዶች ታፍሰው ሸገር ሲቲ አለምገና ከተማ በተለምዶ ኬንቴሪ የሚባለው ሰፈር ታግተው ይገኛሉ።

አንዳንድ የታጋች ቤተሰቦች ገንዘብ እንክፈልና ልቀቁልን ብለው ቢማፀኑም የያዝናቸው ወደ መከላከያ ለማስገባት እንጅ ወንጀል ሰርተው አይደለም ከዚህ በኋላ እንዳትጠይቁን በቅርቡ ወደ ማስልጠኛ ካንፕ እንወስዳቸዋለን በማለት አሰናብተዋቸዋል።

16/04/2025

ከውስጥም ከውጭም ትብብር/ ግንባር ጊዜው የሚጠይቀው እውነታ ነው::

ከላይ እንደተጠቀሰው የኦሮሞ ህዝብ ህልውናና ጤናማ ኑሮ የሚረጋገጠው ከሌሎቹ ኢትዮዽያውያን ወገኖቹ ጋር በመሆን ብቻ ስለሆነ ለዚህ ግንባር ወደፊት መምጣት ይኖርበታል:: በስሙ ትጥቅ ያነሳው የኦሮሞ ነጻ አውጭ ድርጅት የግንባሩ አባል በመሆን ትግሉን ወደፊት ለመግፋት መሳተፍ ያዋጣዋል:። በለጻነት ግንባሩ ስም የአብይ አፋኞች ፣ገዳዮች ብዙ ግፍ እንደፈጸሙ እንደሆነ ግንባሩ እራሱ የመሰከረው ነው። ይህን ግፍ ማስቆም የሚቻለው የራሱንም ንጽህና የሚያረጋግጠው የነጻነት ግንባሩ በትብብር ከሌሎች ኢትዮጵያውያን ጋር አብሮ በመስራት ነው።
የትግራይ ህዝብ አሁን ካለበት ቀውስም ሆነ የወደፊት ተስፋው በመነሳት የወያኔን የልዩነትና የግዛት ትርክት አውልቆ ጥሎ የግንባሩ አባል መሆን ዛሬ ለራሱ ደህንነትና እድገት ነገም ለልጆቹ የሚተወው ቅርስ ነው: ዛሬ አብይ የዎያኔን መሪዎች በመከፋፈል ሹመትና ድርጎ የሚሰጠው ለትግራይ ህዝብ ካለው ፍቅር ሳይሆን የስልጣኑን እድሜ ለማራዘም ነው። አማራንና ትግራይን በማናከስ ስልጣን ላይ ሙጭጭ ብሎ ለመቆየት የሚጫወተው ካርድ ነው።
በሃገራችን ብዙ ባለድርሻ አካላት በሰላምም በመሳሪያም የተነሱ ሁሉ ለሃገራቸውና ለራሳቸውም ህልውና ሲሉ በግንባር መሰባሰባቸው አጠያያቂ ሊሆን አይችልም::
በሀገራችን ያሉት ተቃዋሚዎች በዚህ መልክ ወደ አንድ አላማ መምጣት እንዳለባቸው ከውጭም በጊዜያዊም ቢሆን ግንባሩን የሚቀላቀሉ ይኖራሉ: በተለይ አብይ በደነበረ ቁጥር ጣት የሚቀስርባት ኤርትራ የዚህ አካል መሆን እንዳለባት አምናለሁ:: አብይ በስልጣን ላይ እያለ የቀጠናው መተራመስ የማይቀር ነው: ከሃገር ውጭ የመጀመሪያዋ ገፈታ ቀማሽ ደግሞ ኤርትራ ናት: ስለዚህ የአብይ ክመድረኩ መውረድ ለሷም ቀጥተኞ ጥቅም አለው፣ አትራፊ ትሆናለች:: ስለዚህ ታክቲካል ግንኙነት ከኤርትራ ጋር መፍጠር ትክክል ነው::
ሰሜኖች እየመጡ ነው የምትለው ነጠላ ዜማ ለነአብይ እውነትነት አላት: ስጋታቸውን ሊደብቁት ያልቻሉት የፍርሃታቸው መገለጫ ነው:: የሚጠሉትን ያክል ይፈሩታል: እንደነሱ መጥላቱ ላይ ሳይሆን ትኩረቱ ፍርሃታቸውን እውን ማድረጉ ላይ ነው:
እዚህ ላይ ትልቅ በደል እንደደረሰ፣ ትልቅ ቁርሾ እንደለ እረስቸው አይደለም። ያለፈውን ይቅር ብለን የበለጠ እንዳናጣ እንተባበር ነው እንጅ መርሳት የሚባል ነገር አይኖርም። በአግባቡ ታሪክ ያስቀምጠውል የሚል እምነት አለኝ።
በአጭሩ
ከሃገር ቤት
ፋኖ (በአንድ የአመራር ጥላ ስር የተዋቀረ ፋኖ)፣ የኦሮሞ ነፃ አውጭ ሃይል፣ የትግራይ ታጣቂዎች (ከወያኔ መሪዎች ውጭ)እንዲሁም በሌሎች አካባቢዎች ብረት ያነሱ ወገኖች የሚፈጠር ህብረት ወይም ግንባር ሲሆን
በውጭ ደግሞ ከኤርትራ ጋር ይሆናል: ከዚያም ባለፈ ብሄራዊ ጥቅምንና ልዑላዊነትን በማይጻረር መንገድ ከሌሎች ጋር ግንኙነትን መፍጠርና እርዳታዎችን ማግኘት አስፈላጊ ይሆናል::
እዚህ ላይ ትልቁ ስራ ፋኖ ላይ እንደወደቀ ግልጽ ነው። ብዙ የአማራ ግዛቶችን በቁጥጥሩ ስር ማድረጉ፣ በየጊዜው እያስመረቀ የሚያወጣው ተዋጊ ሃይል፣ የትጥቅ ብዛትና ጥራት ያለጥርጥር ግንባር ቀደም ተፋላሚምና አደራ ተሸካሚም ያደርገዋል። ይህን ጉልበቱንና ተቀባይነቱን ይዞ መጀመሪያ እራሱን ወደ አንድነት ማምጣት የድል ማድረጊያው መንገድ ነውና ጊዜ ሳይሰጥ መተግበር ይኖርበታል፣ ቀጥሎም ሌሎችን ተቃዋሚ ሃይሎች የማሰባሰብ ሃላፊነቱን ስራየ ብሎ መስራት ይገባውል።
ፋኖ ከማንም የታጠቀ ሃይል ጋር አንድነቱን ሳይተክል ግንባር ለመፍጠር መሞከር የለበትም፣ ካደረገው ያ ቡድን ብቸኛና የነዚህ ሃይሎች ተከታይ ወይም አገልጋይ (Junior partner)ሆኖ ወያኔ እንደፈለፈላቸው የባዴንና፣ ኦህዴድ እጣ ይገጥመዋል። አንድ የሆነ ፋኖ ድል አድራጊ ብቻ ሳይሆን አሰባሳቢም ይሆናል።
የመንግስት ስልጣን ለመረከብ ሁሉም ባለ ድርሻ አካላት አስቀድመው መዘጋጀትና የመንግስትን አወቃቀር ከወዲሁ በስምምነት ማስቀመጥ ይኖርባቸዋል።
ግንባር ጠላትን ለማሽንፍ ብች አይደለም፣ ካሸነፉም በኋላ ሃገረ መንግስትን ደሞክራሲያዊ በሆነ አሰራር ለማዋቀር ጭምር ነው። ለአንዴና ለመጨርሻ ጊዜ በሃገራችን ጦርነት ለማስቀረት፣ እንደገና እንዳይነሳ ለማድረግ ይህ የመንግስት አወቃቀር ዲሞክራሲያዊ መሆን አለበት።
አንዱ ቡድን በጉልበቱ ስልጣኑን በእጁ ካስገባ በኋላ ሁሉንም ያሳትፋል ማለት ወያኔ ያደረገውን መድገም ነው፣ አንኳር አንኳሩን ጠርንፎ ይዞ እንዳይታማ በሚመስል ትናንሽ ዳረጎት ለአማራም ለኦሮሞም ለሌሎችም እንደቸረው ነው። በመሳሪያ ስልጣን ላይ የወጣ አሁንም እንደወያኔ ደም አፍስሸበታለሁና ትልቁን ድርሻ ቦድሸ እወስዳለሁ ማለቱ የማይቀር ነው። ለዚህ ነው አሁኑኑ የስምምነትና የቃል ኪዳን ሰነድ የሚያስፈልገው። ይህም ሲሆን ቁጭ ብሎ ሌሎች እየሞቱ ስልጣን ያጋሩን ሳይሆን ዛሬውኑ ትግሉን በመቀላቀልም ሆነ ግንባር በመፍጠር የትግሉም የድሉም ባለቤት መሆን ያስፈልጋል።

14/04/2025

ነገረ ብአዴንና ወአፋህድ
የኢህአዴጉ ብአዴን እና የዘመናችን አፋህድ ልዩነት እና አንድንት ምንድን ነው?
በርግጥም ይሄ ቀላል ጥያቄ ቢመስልም ግን የአፋህድን መዳረሻ በሚገባ ለማረጋገጥ ከሚያስችሉ ነገሮች ውስጥ አንዱ ይሄ ነው። አንደኛ ሁለቱም ስማቸው በግርድፉ ሲታይ አማራዊ ይመስላሉ ብአዴን(ብሔር አማራ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ)ም ይሁን አፋህድ(የአማራ ፋኖ ህዝባዊ ድርጅት) ስማቸው አማራዊ ነው። ሁለተኛ ሁለቱም የትጥቅ ትግል አድርገዋል ብአዴን ደርግን ታግሏል ነገር ግን ብአዴን ደርግ አማራ ህዝብ ላይ የተለየ በደል አድርሷል ብሎ አስቦ ሳይሆን ደርግን የታገለው የአማራ ህዝብ እንደ ማንኛውም የኢትዮጵያ ህዝብ በደርግ ተበድሏል ብሎ ስለሚያምን ነበር ደርግን የታገለው እንደዛም ሆኖ በዘመነ ኢህአዴግ ብአዴን የአማራን ሰቆቃ እና መከራ ከደርግ ዘመን በባሰ ሁኔታ አስቀጥሎታል በተመሳሳይ አፋህድ የትጥቅ ትግል አድርጓል ምንም እንኳን በአሁኑ ሰአት አገዛዙን እየታገለ ባይሆንም ነገር ግን መሳሪያ ይዞ ጫካ የተቀመጠን ሀይል ጠርንፎ ይዟል ያም ቢሆን ግን አፋህድ በሚንቀሳቀስባቸው ቦታዎች በሙሉ የአማራን ህዝብ ከአገዛዙ ወታደሮች የማይታደግ ብሎም ህዝቡን ከመጠን በላይ ቀረጥ በመሰብሰብ ያማረረ ድርጅት ነው። ሶስተኛ ሁለቱም ቁርጠኛ የአማራ ታጋዮችን ቀርጥፎ በመብላት ይታወቃሉ። ብአዴንም ሆነ አፋህድ ጠንካራ ጥያቄ የሚያቀርቡ የራሳቸውን ታጋይ በመረሸን ከኋላ በመምታት እና በሴራ ለጠላት አሳልፎ በመስጠት ይታወቃሉ ታምራት ላይኔን አሳልፎ የሰጠው እነ አምባቸውን እና አሳምነውን በሴራ ያስቀረጠፈው ብአዴን ዛሬ ኮረኔል ታደሰን፣ ከፍያለው ደሴን እና ሌሎችም ጠንካራ ታጋዮችን በሴራ ካስቀረጠፈው አፋህድ ጋር ተመሳሳይ አካሂድ ተከትሏል። አራተኛ ሁለቱም ድርጅቶች ዘመኑን የማይዋጅ አካሂድ ይከተላሉ በዘመነ ደርግ እኛ የትግሉም ብቻ ሳይሆን የስልጣኑም ባለቤት መሆን አለብን ያሉትን የብአዴን የያኔው ኢህዴን ጠንካራ ጠንካራ ሰዎችን ራሱ ቀርጥፎ በልቶ አማራን ለዚህ መከራ የዳረገው ብአዴን እንደሆነ ሁሉ አፋህድም ይህንን ትግል ጠልፎ ፀረ አማራ ሀይሎችን አዝሎ ቤተመንግስት ለማስገባት የሚሞክር ሀይል ነበረ አሁንም ትግሉን እየበጠበጠ ይገኛል። በጠቅላላው የብዓዴን እና የአፋህድ ልዩነት ጫካ የገቡበት ዘመን፣ የተደራጁበት ሁኔታ እና የታገሉት አገዛዝ ካልሆነ በቀር ሁለቱም ዘመኑን የማይዋጅ ትግል የሚታገሉ፣ ከፀረ አማራ ሀይሎች ጋር እየሰሩ የአማራን መከራ የሚያራዝሙ፣ አማራን የሚከፋፍሉ፣ እንቁ የአማራ ልጆችን ቀርጥፈው የሚበሉ፣ ለአማራ ህዝብ ብቻ ሳይሆን ለሌላውም ኢትዮጵያዊ የማይጠቅሙ፣ በስልጣን ጥመኞች የሚመሩ ፀረ አማራ አደረጃጀቶች ናቸው። ግን ያኔም በኢህዴን ወይም በአሁኑ ብዓዴን ውስጥ ትክክለኛ ታጋዮች እንዳሉት እና በተለይ የታችኛው ሰራዊት ህዝቡን ብሎ እንደወጣ ሁሉ ዛሬም በአፋህድ ውስጥ ያሉ ፋኖዎች ውስጥ አብዛኛው ሰራዊት እና ጥቂት አመራሮች ወደ ትክክለኛው መስመር ቢገቡ አማራን የሚጠቅሙ ፀረ አማራ እሳቤ እና ፍላጎት የሌላቸው ግን በተለያየ ምክንያት አፋህድን ለቀው መውጣት ያልቻሉ ናቸው። ስለዚህም አፋህድ ማለት ሳልሳዊ ብአዴን መሆኑ ታውቆ ድርጅቱ እንደ ድርጅት መፍረስ ያለበት ስም አጠራሩ መደምሰስ ያለበት ቢሆንም ነገር ግን በውስጡ ያሉ ትክክለኛ ፋኖዎች እንዴት ወደ ሀቀኛ አደረጃጀቶች ሊገቡ እንደሚችሉ በደንብ ማሰብ እና መስራት አለብን።

የኔ ቢጤን መርዳት 10,000 ብር ያስቀጣል። "ይህ ትዕዛዝ ነው፣ ፈጽሙ ተብሏል"አዲስ አበባ ውስጥ ከሆቴሎች የሚወጣ በተለምዶ "ቡሌ" ወይም "ፈዋ" የሚባል የተመጋቢዎች ትርፍራፊ ጎዳና ላይ ...
07/04/2025

የኔ ቢጤን መርዳት 10,000 ብር ያስቀጣል። "ይህ ትዕዛዝ ነው፣ ፈጽሙ ተብሏል"

አዲስ አበባ ውስጥ ከሆቴሎች የሚወጣ በተለምዶ "ቡሌ" ወይም "ፈዋ" የሚባል የተመጋቢዎች ትርፍራፊ ጎዳና ላይ ለወደቁ፣ የዕለት ጉርስ ለራቃቸው ምስኪኖች ይሰጥ ነበር። በዚህ "ቡሌ" ብዙዎች ርሃባቸውን ያስታግሳሉ።

ዛሬ የደረሰኝ መረጃ እንደሚያመለክተው ይህ ትርፍራፊ ሆቴሎች ለድሃ እንዳይሰጡ ተከልክለዋል። ይህን ትዕዛዝ የተላለፈ ባለሆቴል ሶስት ደረጃዎች ያሉት ቅጣት ይጠብቀዋል።

የመጀመሪያ ቅጣት 5000 ብር፣ ሁለተኛ ጊዜ ለድሃ ቡሌ ሲሰጥ የተገኘ 10000 ብር፣ ለሶስተኛ ጊዜ ከተገኘ ሆቴሉ ይታሸጋል፣ ንግድ ፍቃድ ይነጥቃል ባለቤቱም ይታሰራል የሚል ትዕዛዝ ወርዷል። ትዕዛዙ ሁለት ሳምንት ሆኖታል።

የሚላስ የሚቀመስ ሲያጡ ነው ከወለጋ ተፈናቅለው፣ ከአዲስ አበባና ዙሪያው ቤታቸው ፈርሶ፣ ከዋግኽምራና ሌሎችም በድርቅ ተጎድተው አዲስ አበባ የገቡ "ደሃዎች" የሚበተኑት የሚል ግምገማ ነው ለዚህ ትዕዛዝ መነሻ የሆነው ሲሉ ነው ጉዳዩን እንዲያስፈጽሙ ከተመደቡ ሰዎች መካከል የሆኑ የነገሩኝ።

"እኔ መንግስት ሆኜ" ያፈናቀልሁትን፣ ቤቱን ያፈረስሁበትን፣ ያደኸየሁትን መርዳት አትችሉም ነው ነገሩ።

Adresse

Schweinfurt
97424

Webseite

Benachrichtigungen

Lassen Sie sich von uns eine E-Mail senden und seien Sie der erste der Neuigkeiten und Aktionen von Breaking News In Ethiopia " ሰበር ዜና " erfährt. Ihre E-Mail-Adresse wird nicht für andere Zwecke verwendet und Sie können sich jederzeit abmelden.

Service Kontaktieren

Nachricht an Breaking News In Ethiopia " ሰበር ዜና " senden:

Teilen