
21/07/2025
😎😎😎
EBS TV ላይ የበቆሎ አበላል ውዝግብ! 🌽🥄🔪
በየጊዜው በስራዎቹ የምንመሰግነውም ሆነ የምንተቸው EBS TV፣ አሁን ደግሞ በአዲስ ቲክቶክ አቅራቢ ምክንያት አነጋጋሪ ሆኗል!
አዲሱ የዝግጅት አቅራቢ የተጠበሰ በቆሎን እንዴት መብላት እንደሚገባ ሲያስተምሩ ታይተዋል። ይሁን እንጂ፣ በቆሎውን "በማንኪያ ልክ እንደ ፖስታ ነው የሚበላው" በሚል ያሳዩት አበላል ብዙዎችን ግራ አጋብቷል።
የEBS ተከታታዮች ይህን አበላል "ብዙ ልጆች ነገ እኛም እንደ EBS አቅራቢዎች እናድርግ እንዳይሉ እና በቢላ እጃቸውን እንዳይቆርጡ" የሚል ስጋት አሳድሮባቸዋል።
አያይዘውም፣ "EBS አቅራቢዎች ጥርሳቸው እንዳይበላሽ በቆሎ አልግጥም ካሉ አለመጋጥ መብታቸው ነው፤ ይህ ነገር ይታረም" የሚል ጥሪ አቅርበዋል።
እናንተስ ስለ ጉዳዩ ምን ትላላችሁ?
የበቆሎ አበላል በማንኪያ ና በቢ* ይቻላል?
ወይስ አግባብ አይደለም?
ሀሳባችሁን አካፍሉን!
😎😎😎
🌴🌴🌴