የሶስቱ መልአከ መልዕክት Three Angels Message

የሶስቱ መልአከ መልዕክት Three Angels Message አላማችን በራዕይ 14፡6-10 ላይ ያለውን የሶስቱ መልአከ መልዕክት Verified

17/01/2025

መልካም ሰንበት።

11/01/2025

"'I know the plans I have in mind for you, declares the Lord; they are plans for peace, not disaster, to give you a future filled with hope.'"

The Good News: The Lord will make sure there are only good things on your horizon.

Happy Sabbath everyone 😊

06/01/2025

በሃጥያት የጠነከረች ነፍስ ለእግዚአብሔር ቃል ምላሽ አትሰጥም። COL, P44

Send a message to learn more

01/01/2025

=== የእግዚአብሔር ባህሪይ በብሉይ እና በአዲስ ኪዳን ===

በብሉይ ኪዳን እና በአዲስ ኪዳን የተገለፀው የእግዚአብሔር ባህሪይ ለየቅል እንደሆነ በአንዳንድ ክርስቲያኖች ዘንድ ይታመናል። ከዚህም የተነሳ በብሉይ የተገለፀው እግዚአብሔር እንደ ጨካኝ ተደርጐ በአዲስ ኪዳን የተፃፈው ደግሞ አፍቃሪ አምላክ ተደርጐ ይወሰዳል። ይህ አረዳድ ትክክለኛ መሆኑን እና አለመሆኑን በመጽሐፍ ቅዱስ መሰረት እንቃኘው።

እስኪ ከዘፍጥረት እንጀምር እና ወደ ውስጥ እንዝለቅ። አዳም እና ሔዋን ሀጥያትን ከሰሩ በኋላ የተነገራቸው የምስራች ቃል እንዲህ በማለት ይነበባል። “በአንተና በሴቲቱ መካከል፥ በዘርህና በዘርዋም መካከል ጠላትነትን አደርጋለሁ፤ እርሱ ራስህን ይቀጠቅጣል፥ አንተም ሰኰናውን ትቀጠቅጣለህ።” ዘፍ 3፡15። በእባብ የተመሰለው ሰይጣን በአዳም ቤተሰብ ውስጥ የነበረው የጠላትነት ሚና በአቤል እና ቃየል በተግባር ተከናውኖ በዘፍጥረት 4፡8 ላይ ተመዝግቦ እናገኘዋለውን። ከዚያን ጊዜ ጅምሮ ይህ ጠላትነት በብዙ ዘመን ቅብብሎሽ ውስጥ አልፎ በእኛ ዘመን ላይ ደርሷል። ይህም ደግሞ “በዘርህ እና በዘርዋም መካከል ጠላትነትን አደርጋለው” የሚለው የአምላክ ቃል ተግባራዊ እየሆነ እንዳለ ማሳያ ነው።

እስራኤላዊያን ከግብጽ ሀገር ወጥተው ወደ ከነዓን በሚጓዙበት ጊዜ ቁጥራቸው ብዙ ነበር። በጉዞ ላይ እያሉ ከኋላቸው (ምናልባትም በድካም ከኋላ የሚኳትኑት ላይ) ጦርነት የከፈቱባቸው የመጀመሪያው የእስራኤላዊያን ጠላት ተብለው የተገለጹት የአህዛብ (የእስራኤልን አምላክ የማያመልኩ) ህዝብ አማሌቃዊያን ይባላሉ። ይህ ታሪክ በዘፍ 17፡8 ጀምሮ ተፅፏል። ይህ ጦርነት በእስራኤላዊያን አነሳሽነት አልነበረም ነገር ግን በጣም አሰቃቂ እና ብዙ እልቂትን በእስራኤላዊያን ላይ ያስከተለ ነበር። የአማሌቃዊያንን አመጣጥ መጽሐፍ ቅዱስ እንዲህ በማለት ይነግረናል “የዔሳው ልጅ ኤልፋዝ ትምናዕ የምትባል ቁባት ነበረችው፤ እርሷም አማሌቅን ወለደችለት” ዘፍ 36፡12። አማሌቃዊያን በፈፀሙት ጥቃት እግዚአብሔር በሙሴ በኩል የሚከተለውን መልዕክት አስተላለፈ። “ከዚያም እግዚአብሔር ሙሴን፣ ‘ሲታወስ እንዲኖር ይህን በጥቅልል መጽሐፍ ላይ ጻፈው፤ ኢያሱም መስማቱን አረጋግጥ፤ ምክንያቱም የአማሌቃውያንን ዝክር ከሰማይ በታች ፈጽሜ እደመስሳለሁ’ አለው።” ዘፍ 17፡14። ሙሴም ይህንን ቃል ለእስራኤላዊያን በዘዳግም 25፡17-18 ላይ እንዲህ ሲል እያረጋገጠላቸው “ከግብፅ በወጣህ ጊዜ፣ አማሌቅ በመንገድ በአንተ ላይ ያደረገብህን አስታውስ፤ ደክመህና ዝለህ በነበርህበት ጊዜ፣ በጕዞ ላይ አግኝተውህ፣ ከኋላ ያዘግሙ የነበሩትን ሁሉ ገደሉ፤ እግዚአብሔርንም አልፈሩም። አምላክህ እግዚአብሔር ርስት አድርጎ በሚሰጥህ ምድር ዙሪያ ካሉት ጠላቶችህ ሁሉ ባሳረፈህ ጊዜ፣ ከሰማይ በታች ያለውን የአማሌቅን መታሰቢያ ደምስስ፤ ከቶ እንዳትረሳ!”

እግዚአብሔር ይህንን ቃል ለሙሴ ቢናገርም ወዲያው ግን አማሌቃውያንን አላጠፋቸውም። ሙሴም ከእስራኤላዊያን ጋር እስከ ነበረበት ጊዜ ይህ የእግዚአብሔር ቃል አልተፈፀመም (ምክንያቱን በኋላ እንመለስበታለን) ነበር። ከብዙ መቶ ዓመታት የምህረት ጊዜ በኋላ ከጥፋታቸው መመለስ ባለመቻላቸው እግዚአብሔር በንጉስነት የቀባውን ሳኦልን ተጠቅሞ ሊያጠፋቸው ፈለገ። “የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ ‘እስራኤል ከግብፅ በወጣ ጊዜ፣ አማሌቃውያን በመንገድ ላይ ስለ ተቃወሙት እቀጣቸዋለሁ። አሁንም ሂድ፤ አማሌቃውያንን ውጋ፤ ያላቸውንም ሁሉ ፈጽመህ አጥፋ፤ አንዱንም አታስቀር፤ ወንዱንና ሴቱን፣ ልጁንና ሕፃኑን፣ የቀንድ ከብቱንና በጉን፣ ግመሉንና አህያውን ግደል።’ ” 1ሳሙኤል 15፡2-3። በዚያን ጊዜ የአማሌቃዊያን ንጉስ የነበረው አጋግ ነበር።

ከአጋግ ዘር እንደ ሚመዘዝ የሚነገርለት ሐማ የተባለ የአይሁድ ጠላት ታሪክ በአስቴር መጽሐፍ ላይ ተጽፎ ተቀምጧል። “ስለዚህ ንጉሡ የቀለበት ማኅተሙን ከጣቱ አውልቆ የአይሁድ ጠላት ለሆነው ለአጋጋዊው ለሐማዳቱ ልጅ ለሐማ ሰጠው።” አስቴር 3፡10 ሐማም ለንጉሱ እንዲህ አለ “በአሕዛብ መካከል በመንግሥትህ አውራጃዎች ሁሉ ተሠራጭቶና ተበታትኖ የሚኖር አንድ ሕዝብ አለ፤ ይህም ሕዝብ ከሌሎች ሕዝቦች ሁሉ የተለየ ልማድ ያለውና የንጉሡንም ሕግ የማይታዘዝ ነው፤ ታዲያ ይህን ሕዝብ ዝም ማለቱ ለንጉሡ አይበጅም። ነገሩ ንጉሡን ደስ የሚያሰኘው ከሆነ፣ እነርሱን ለማጥፋት ዐዋጅ ይውጣ፤ እኔም ይህን ተግባር ለሚፈጽሙ ሰዎች የሚውል ዐሥር ሺሕ መክሊት ብር ወደ መንግሥት ግምጃ ቤት አስገባለሁ።” አስቴር 3፡8-9

እግዚአብሔር ከሴቲቱ እና ከእባቡ ዘር ጋር ጠላትነት ይሆናል ብሎ ካወጀ በኋላ ስይጣን አማሌቄያዊያንን ተጠቅሞ ክርስቶስ የሚመትጣበትን የዘር ሃረግ ለማጥፋት ተደጋጋሚ ሙከራዎችን አድርጓል። እግዚአብሔርም እነዚህ የአህዛብ ሰዎች ወዲያው አላጠፋቸውም ይልቁንስ ይመለሱ ዘንድ ብዙ የንስሃ ጊዜያትን ሰጣቸው። እነሱ ግን አልተጠቀሙበትም።

እግዚአብሔር የፍቅር አምላክ ነው። ምህረቱ እጅግ የበዛ ለቁጣ የዘገየ ነው። በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የተገለጠ የእግዚአብሔር ተመሳሳይ ነው። የእሱ ባህሪይ እንደ ሰው አይለዋወጥም።

Send a message to learn more

Address

Tallinn

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when የሶስቱ መልአከ መልዕክት Three Angels Message posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to የሶስቱ መልአከ መልዕክት Three Angels Message:

Share