AmharaPress

AmharaPress Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from AmharaPress, News & Media Website, Cairo.

ቴዲ አፍሮ እና ባለቤቱ አምለሰት ሙጬ በአስቴር አወቀ ኮንሰርት ላይ - ሸራተን አዲስአበባዮሽ እየዘፈነላት🌼🌼🌼
12/09/2026

ቴዲ አፍሮ እና ባለቤቱ አምለሰት ሙጬ በአስቴር አወቀ ኮንሰርት ላይ - ሸራተን አዲስ

አበባዮሽ እየዘፈነላት🌼🌼🌼

12/09/2026
 #እንቁጣጣሽ  መልካም አዲስ  ዓመት 🌼🌼🌼2019 ዓ.ም
12/09/2026

#እንቁጣጣሽ መልካም አዲስ ዓመት 🌼🌼🌼
2019 ዓ.ም

06/09/2026

ጳጉሜ 1 የእመርታ ቀን

 ይህ በምስሉ የሚታየው ዘራፊ አጋች ወንበዴ የሆነ እስከ አፍንጫው የታጠቀ ቀማኛ በ30/12/2018 ዓም በአማራ ክልል ከጎንደር ተነስቶ ወደ ዳንሻ ሁመራ እየተጓዘ የነበረን የህዝብ ተሽከርካሪ...
05/09/2026



ይህ በምስሉ የሚታየው ዘራፊ አጋች ወንበዴ የሆነ እስከ አፍንጫው የታጠቀ ቀማኛ በ30/12/2018 ዓም በአማራ ክልል ከጎንደር ተነስቶ ወደ ዳንሻ ሁመራ እየተጓዘ የነበረን የህዝብ ተሽከርካሪ አባዱላ ሚኒባስ ለመዝረፍ አስቦ ላይ አርማጭሆ ትክል ድንጋይ ዝቅ ብሎ በከፈተው ተኩስ አንዲት ተሳፋሪን በመምታት ህይወቷን የቀጠፈ ነው።

ይህንን ዘራፊ ነፍስን አጥፊ ወንበዴ የላይ አርማጭሆ ህዝብ እና ፀጥታ ሀይል በጥምረት ከነገደለበት መሳሪያ ብዙም ሳይርቅ በከበባ በቁጥጥር ስር አውለውታል ለዚህም ለአካባቢው ህዝብ እና የፀጥታ ሀይል ምስጋና ይገባቸዋል።

ይህ ዘራፊ ነፍስ አጥፊ ዛሬ ለእርሱ ከርስ እና ኪስ ሲል ቤተሰብ ደረሰችልን ተመረቀችልን ጧሪ አልባ አትሁኑ የሚለው ምርቃት ሰመረልን በማለት ለፍተው ያስተማሩ ልጃቸውን ከዩኒቨርሲቲ ተመርቃ በአሉን ቤተሰብ ጋር ለመዋል በማሰብ እየሄደች ያለችን እህታችን ነው ነፍስ የነጠቀው።

ይህች እህታችን ሳይማሩ ያስተማሯትን እየተቸገሩ ያጎረሱዋትን እየለፉ ያሳደጉዋትን አስተምረው ለወግ ማእረግ ያበቋትን ወላጆቿን ተምራ በመመረቅ ለፍተው እንዳልቀሩ በማሳየት በቀጣይ ስራ ይዛ ለመጦር ህልምን ሰንቃ በአልን ውላ ልትመለስ ጉዞን ብትጀምርም ለገንዘብ ብሎ የሰው ነፍስን የሚነጥቅ አረመኔ ከመንገድ አስቀርቷታል።

አሁን ላይ በሀገሪቱ መንገዶች ለገንዘብ ብለው ሾፌር የሚያግቱ የሚገሉ የተሳፋሪን ነፍስ የሚነጥቁ ሌቦች እና አረመኔወች ተስፋፍተዋል። እኛም በተደጋጋሚ ችግሩ እንዲቀረፍ ብዙ ብንጮህም በግዝፈቱ ልክ ስራ ባለመሰራቱ ዛሬም እየዘረፉ ነፍስን እየቀጠፉ አሉ።

እንዴት ህዝብ ወደ ጫነ መኪና ጥይት ይተኮሳል ? እንዴት ለገንዘብ ተብሎ ከተሳፋሪ መቶ ሁለት መቶ ተራ ስልክ ለመንጠቅ ህይወት ይጠፋል ? ምን እይነት የእሳቤ ልምሻነት የጭካኔ ጥግ ነው ??

ይህች ተመራቂ በቤተሰቦቿ ተጠባቂ እፎይ ተመረኩ ብላ ሳታርፍ ህይወቷን ለተራ ሳንቲም ብሎ መንጠቅ ምን ቢደደብ ምን ቢጨከን እንዴት ማሰብ ቢቻል ነው ???

ነፍስ ይማር እህታችን እኛ ሾፌሮች ይህን ችግር ብንጮህ ብንናገር ዛሬ ግድያው እንዳንች ያሉትን የቤተሰብ እና የሀገር ተስፋ ያዘሉትን እየቀጠፈ ነው። ማነው ይህንን መሰል ድርጊት ዝርፊያ እና እገታ የሚያስቆመው???

 👇👇ብልጥ የሆኑ ጎረቤት ሀገራት ከኢትዮጵያ ጋር መወዳጀት እንዳይሸከር በጥንቃቄ እየተጓዙ ያሉበት ምክንያት ከኢትዮጵያ የሚያገኙት የጎላ ጥቅም ስላለው እና ሊላላው የማይችል የኢኮኖሚ ትስስር ...
04/09/2026

👇👇
ብልጥ የሆኑ ጎረቤት ሀገራት ከኢትዮጵያ ጋር መወዳጀት እንዳይሸከር በጥንቃቄ እየተጓዙ ያሉበት ምክንያት
ከኢትዮጵያ የሚያገኙት የጎላ ጥቅም ስላለው እና ሊላላው የማይችል የኢኮኖሚ ትስስር ከኢትዮጵያ ጋር ስለነበረው ነው።

የኢትዮጵያ ባሳለፍነው ዓመት ቢቻ በሀገሪቱ 9.73 ጊጋ ዋት ሃይል አመንጭታለች፡፡ ለዚህ ካመነጨችው ሃይል ጎረቤትም ተጠቃሚ ሆኗል።

ከእዚህ ካመነጨችው ሃይል ለጎረቤት ሀገራት ኤሌክትሪክ በመሸጥ 475.7 ሚሊዮን ዶላር ገቢም አግኝታለች።
ካለፈው ዓመት ጋር ሲነጻጸር የ25 በመቶ እድገት

በምስራቅ አፍሪካ የኃይል ፍላጎት እየጨመረ በመምጣቱ ጎረቤት ሀገራት የወደፊት ኢኮኖሚያቸውን ከኢትዮጵያ ታዳሽ ኃይል መረብ ጋር በስፋት እያስተሳሰሩ ይገኛሉ።

የጎቤና ሽኖዬ ባህላዊ አከባበር ስነስርዓት በሸገር ከተማ እየተከበረ ይገኛል
04/09/2026

የጎቤና ሽኖዬ ባህላዊ አከባበር ስነስርዓት በሸገር ከተማ እየተከበረ ይገኛል

ትላንት ገልጬላችሁ ነበር። ጠላት ዐይኑ ዕያየ _ ጆሮው እየሰማ ... ገና እንደ-ማቱሳላ በበረከት፣ ስኬት፣ ተምሣሌትነት ይመራናል። የእድሜ ዘመን ምርጫችን ነው። የፈለገ ይታነቅ እንጂ በዐቢቹ...
03/09/2026

ትላንት ገልጬላችሁ ነበር። ጠላት ዐይኑ ዕያየ _ ጆሮው እየሰማ ... ገና እንደ-ማቱሳላ በበረከት፣ ስኬት፣ ተምሣሌትነት ይመራናል። የእድሜ ዘመን ምርጫችን ነው። የፈለገ ይታነቅ እንጂ በዐቢቹ፣ በሀገርና በመከላከያ ሠራዊታችን ቅንጣት አንደራደርም! 'ሰውዬው' ይለያል።
ወለ - በል ሟርተኛ ሁላ _ ሟርታችሁን ለእናንተ ያድርገው!

ዐቢቹኮ እንወድሀለን፤ የአመራር ዘመንህን በጤና መትረፍረፍ እና በፍቅር የተሞላ ያድርግልን። ለኢትዮጵያውያን ስጦታችን _ ለፀረ - ኢትዮጵያ ባዳና ባንዳ መቅሰፍት ነህ! አባ መላ!

📷 EthioTimes

  🔇🔇የሳዑዲ ዓረብያ የመካ ክልል ፖሊስ የድንበር ደህንነት ህግ በመጣስ እና የሰው ህይወት ማጥፋት ወንጀል የተጠረጠሩ አምስት ኢትዮጵያውያንን በቁጥጥር ስር ማዋሉን ይፋ አድርጓል።ፖሊስ እንደ...
03/09/2026

🔇🔇
የሳዑዲ ዓረብያ የመካ ክልል ፖሊስ የድንበር ደህንነት ህግ በመጣስ እና የሰው ህይወት ማጥፋት ወንጀል የተጠረጠሩ አምስት ኢትዮጵያውያንን በቁጥጥር ስር ማዋሉን ይፋ አድርጓል።

ፖሊስ እንደገለጸው፣ ተጠርጣሪዎቹ በራንያ ግዛት ውስጥ የሀገራቸውን ዜጋ በጭካኔ ሲደበድቡ የሚያሳይ ተንቀሳቃሽ ምስል በቲክቶክ እና በሌሎች የተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች ላይ በስፋት ተሰራጭቶ ነበር።

ተጎጂው ግለሰብ በተሰነዘረበት የኃይል ጥቃት በደረሰበት ከፍተኛና አሰቃቂ የሰውነት ጉዳት ምክንያት ህይወቱ ማለፉ ተረጋግጧል።

በጉዳዩ ላይ የተደረገው የመጀመሪያ ደረጃ የወንጀል ምርመራ እንደሚያመለክተው፣ ይህ አሰቃቂ ክስተት ሊከሰት የቻለው በተጠርጣሪዎቹ እና በተጎጂው መካከል ቀደም ሲል በነበረ የግል አለመግባባት እና ቂም ምክንያት እንደሆነ ታውቋል።

በአሁኑ ወቅት አምስቱም ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ውለው በፖሊስ ጣቢያ የሚገኙ ሲሆን፣ አስፈላጊው የምርመራ ሂደቶች ከተጠናቀቁ በኋላ ጉዳያቸው በህጉ መሰረት የመጨረሻ ውሳኔ እንዲያገኝ እና ተገቢውን የህግ ፍርድ እንዲያገኙ ፋይላቸው ወደ ዓቃቤ ህግ መመራቱ ተገልጿል።

Via Saudi Gazette

እየተጠናቀቀ በሚገኘዉ 2018 ዓ.ም ኢትዮጵያ በማንሰራራት ላይ እንደምትገኝ የሚያመላክቱ ስኬቶችን አስመዘገበች ፡፡ አገልግሎቱ የዘንድሮ የጳጒሜን ቀናት የሚከበሩበትን ዓውድ፣ የቀናቱን ስያሜ ...
03/09/2026

እየተጠናቀቀ በሚገኘዉ 2018 ዓ.ም ኢትዮጵያ በማንሰራራት ላይ እንደምትገኝ የሚያመላክቱ ስኬቶችን አስመዘገበች ፡፡ አገልግሎቱ የዘንድሮ የጳጒሜን ቀናት የሚከበሩበትን ዓውድ፣ የቀናቱን ስያሜ እና መሪ መልእክት ይፋ ያደረገበትን መግለጫ ሰጥቷል፡፡

መግለጫዉን የሰጡት የአገልግሎቱ ሚኒስትር ድኤታ ክቡር አቶ ከበደ ዴሲሳ “ጳጒሜን የኢትዮጵያ ማንሰራራት ወር ብሎ ለማክበር የሚያስችሉ ስኬቶች እየተጠናቀቀ ባለው ዓመት መመዝገባቸውን ገልጸዋል::
የጳጒሜን ቀናት “የኢትዮጵያ ማንሰራራት” በሚል የጋራ መሪ መልእክት ይከበራሉ፡፡
ጳጉሜን 1 - የእመርታ ቀን፣
ጳጉሜን 2 - የማንሰራራት ቀን፣
ጳጉሜን 3 - የጽናት ቀን፣
ጳጉሜን 4- የኅብር ቀን
ጳጉሜን 5- የነገ ቀን በሚሉ ስያሜዎች እንደሚከበሩ ገልፀዋል ።
Via FDRE Government Communication Service-በኢፌዴሪ የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት

Address

Cairo

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when AmharaPress posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share