ጋሞ ደሬ / gamo dere

ጋሞ ደሬ / gamo dere ጋሞ ባይራ ዴሬ

04/11/2025

ጥቂት አመታትን እንታገሳለን ከዛ አለም አቀፉ ስቴዲየማችን ሲጠናቀቅ ውድድሮች ሁላ ወደ ውቢቷ እና ደማቋ አርባምንጭ ይመጣሉ ያኔ ከተማዬ በሌላ ከፍታ🙏🙏🙏🙏

በቶሎ ሊፈታ ሚገባው የቤት ስራ
28/10/2025

በቶሎ ሊፈታ ሚገባው የቤት ስራ

?
👉የአንድ ቡድን የቴክኒክ አማካሪ ሊሆን የሚገባው ሰው ለበርካታ አመታት እግር ኩዋስን በከፍተኛ ደረጃ ተጫውቶ ያለፈ ወይም በአሰልጣኝነት የሠራ ወይም በእግር ኩዋስ ዙሪያ የተለያዩ ስልጠናዎችን የወሰደ ሰው ነው::
❗️የቴክኒክ አማካሪ በእያንዳንዱ ጨዋታ ሊተገበሩ የሚገባውን የጨዋታ ቴክኒክ ከተቃራኒው ቡድን አጨዋወት እና ከያዛቸው ተጫዋቾች ስብስብ እና ከሜዳው ሁኔታ አንፃር የተሻለውን ቴክኒክ እንዲተገበር ለአሠልጣኙ ያማክራል።
❗️እያንዳንዱ ጨዋታዎችን በመከታተል በየጨዋታው የታዩ የቴክኒካል ችግሮችን እየለየ ለአሠልጣኙ ያማክራል፣
ከጨዋታ በፊት (pre match) አሠልጣኙ ይዞ ወደ ሜዳ ሊገባ ስላሰበው ታክቲክ ከውጤታማነቱ አንፃር በቂ መተማመኛ ይሰጣል እንዲህም ከጨዋታ በኃላ(post match) ከመጣው ውጤትና ሜዳ ላይ ከነበረው እንቅስቃሴ አንፃር አሰልጣኙ ከሚያቀርበው የጨዋታ ሪፖርት በመነሳት በጫወታው የታዩ ደካማና ጠንካራ ጎኖችን በመለየት ለቀጣይ መሻሻል ባለበት ነጥሎ በማውጣት የተሻለ ቴክኒካል ሀሳብ ያቀርባል።
❗️በጠቅላላው አንድ ሰው በስፖርት ዶክትሬት ስላለው የቴክኒካል አማካሪነትን በብቃት ይወጣል ማለት አይቻለም። ለእግርኩዋስ ቅርብ የሆነና ተጫውቶ ያለፈ መሆን አለበት
አብዛኞች በአለም ላይ ያሉ ቡድኖች የድሮ ተጫዋቾቻቸውን ነው የቴክኒካል አማካሪ የሚያደርጉት ለምሳሌ የባርሳ የቴክኒክ አማካሪ ዴኮ ነው የአርሰናል እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ ኤዱ ነበር፣
❗️የቴክኒክ አማካሪ አሠልጣኙ ያልታየውን የቴክኒክ ክፍተት ማየት የሚችል መሆን አለበት።
❗️የኛ ቴክኒክ አማካሪ ከዚህ አንፃር ብቁ ነው ብዬ አላስብም ባይሆን ቡድን መሪ ወይም የአካል ብቃት አሠልጣኝ ቢሆን ይሻል ነበር።
ተጫውተው ያለፉ ብዙ ባሉበት ሀገር እሱን ቴክኒክ አማካሪ ማድረግ እውነት ፍትሃዊ ነው ብለን እንመን🤲
❗️አርባምንጭ ከነማ ሚያስፈልገው ሙሉ ጊዜውን ለክለቡ ሰጥቶ ያሉ ክፍተቶችን በጊዜ እየደፈነ ሚሄድ ቴክኒካል ዳይሬክተር እንጂ በትርፍ ሰዓቱ ከመንግስት ስራ ጎን ለጎን ሚሰራ ቴክኒካል ዳይሬክተር አያስፈልገንም ስንት እንቁዎችን የያዘች ከተማ በዚህ ልክ ሰው እንዳጣ ክለብ ማወሳሰቡ አይታየኝም።
መልካም የውድድር ጊዜ 🐊🐊🐊🐊🐊

07/08/2025
14/07/2025


?

👉አሰልጣኝ መኮነን ገላነህ በአሰልጣኝነት በርካታ አመታት ያገለገለ ሲሆን በ 2013 ዓም ጎፋ ባራንቼን ወደ ከፍተኛ ሊግ ለመግባት በተደረገው አዳማ ከተማ ላይ እስከመጨረሻው እልህ አስጨረሽ ውብ እግር ኳስ በማሳየት የስፖርት ወዳዱን ቀልብ መሳብ የቻለበት ቡድን ይዞ መቅረቡ አይዘነጋም። ይህ ታታሪ አሰልጣኝ በተጫዋችነትም በአሰልጣኝነቱም የተሳካለት ነበር።
ይህ ሰው የአርባምንጭ ከተማ ፍሬ የህነው በቅፅል ሱሙ #ዊሀ ይባላል ።
እግር ኳስን በተጫዋችነት 1989 አም እስከ 2001 አም ተጫውቶ ያለፈ ሲሆን በተጫዋችነት ጊዜው በታላላቅ ክለቦች አገልግሎት ሲሰጥ የተጫወተባቸው ክለቦች ደግሞ ከታች ተዘርዝረዋል።
 በክለብ ደረጃ የተጫወተባቸው ቡድኖች
 ሀዋሳ ከተማ
 አርባምንጭ ጨርቃ ጨርቅ
 ወንጂ ስኳር
 ሐረር ቢራ
 አዳማ ከተማ
 ኦሜድላና
 ሻሸመኔ ከተማ ለ 13 አመታት መጫወት የቻለ ሲሆን ለብሄራዊ ቡድን ደግሞ በተለያዩ የእድሜ እርከኖች ተጫውቷል።
 ከ 17 አመት በታች
 ከ 20 አመት በታች
 ከ 23 አመት በታች ለኦሎምፒክ እና ለዋናው ብሄራዊ ቡድን አገልግሏል።
መልካም ዕድል weax 95🙏🙏
👉share
👉follow our page

Dirección

Woliso Ethiopia
Barcelona

Página web

Notificaciones

Sé el primero en enterarse y déjanos enviarle un correo electrónico cuando ጋሞ ደሬ / gamo dere publique noticias y promociones. Su dirección de correo electrónico no se utilizará para ningún otro fin, y puede darse de baja en cualquier momento.

Compartir

Categoría