
07/07/2025
ታማኝ በየነ የሕይወት ዘመን ጀግና የሚባል ሽልማት ሊሰጠው የሚገባ ሰው ነው።
እዚህ አሜሪካ የሚኖሩ "አክቲቪስት ነን" የሚሉ እንከፎች በሆነ ባልሆነው የታማኝን ስም የሚጠሩትን ያህል የፈጣሪን ስም ቢጠሩ በምድርም በሰማይም ተጠቃሚ ይሆኑ ነበር።
"ታማኝ ለተጎዱ ሰዎች ለምን ገንዘብ አይሰበስብም? ታማኝ ለምን ለቤተክርስቲያን gofundme አይከፍትም? ታማኝ ለምን የተቃውሞ ሰልፍ አይጠራም? ታማኝ ለምን የድጋፍ ሰልፍ አይጠራም? ታማኝ ለምን ሰልፍ ላይ አልተገኘም? ታማኝ ለምን ለአማራ አይታገልም? ታማኝ ለምን መንግስትን አልተቸም? ታማኝ ለምን ድምፁን ያጠፋል?" የሚሉ ማለቂያ የሌላቸውን የመሀይም ጥያቄዎች በየጊዜው እያነሱ ሲጃጃሉ እኮ ከታማኝ ጋር ውል የተፈራረሙ ነው የሚመስሉት።
ማይክ ስለያዘ ብቻ የማንም ደንቆሮ እየተነሳ ሲዘባርቅ ማየት እንዴት ያማል! ኸረ ሰው ይታዘበናል በሉ። ታማኝ ለዚች አገር የከፈለው መስዋዕትነትና ያበረከተው አስተዋፅኦ ሀብት ሆኖ ቢመነዘር ኖሮ ለአስር ትውልድ ይበቃ ነበር። ግን ምን ዋጋ አለው አገሪቱ ውለታ ቢስ ትውልድ ነው የፈጠረችው። አድር ባዩና የድል አጥቢያ አርበኛው ሁሉ በአገኘው አጋጣሚ እየተነሳ በእሱ ላይ አፉን ይከፍታል።
አባዬ .. ትልቅን ሰው በመዝለፍ ትልቅነት አይገኝም። የራስህን ስራ ሰርተህ ለመታወቅ ሞክር። ታማኝ የራሱ ህይወት አለው። እሱ ፈጣሪ አይደለም በጠራህው ቦታ ሁሉ የሚገኘው። እንደማንኛውም ሰው ያመነበትንና የተመቸውን ነገር በመረጠው ጊዜ የማድረግ መብት አለው። ምን ማድረግ እንዳለበት አንተ አትነግረውም! ውጤት ላያስገኝልህ ነገር ድድብናህንም አደባባይ አታውጣው!
ይቺ መከረኛ አገር ግን ስንቱን ደነዝ ነው የፈጠረችው? የማይረጥቡ አሳዎች!
በጋዜጠኛ ኃይሌ ሙሉ
ከአመት በፊት የተከተበች ስትሆን ለማስታወስ የተለጠፈ ነው።