Kashif media

Kashif media The source of an authentic news

 #ወልድያየወልድያ ሕዝብ ተረጋግቶ አካባቢውን እንዲጠብቅ መልዕክት ተላለፈ።የወልድያ ከተማ አስተዳደር የከተማው ሕዝብ ተረጋግቶ አካባቢውን እንዲጠብቅ እና ለጥምሩ ጦር ደጀንነቱን አጠናክሮ እን...
28/08/2022

#ወልድያ

የወልድያ ሕዝብ ተረጋግቶ አካባቢውን እንዲጠብቅ መልዕክት ተላለፈ።

የወልድያ ከተማ አስተዳደር የከተማው ሕዝብ ተረጋግቶ አካባቢውን እንዲጠብቅ እና ለጥምሩ ጦር ደጀንነቱን አጠናክሮ እንዲቀጥል ዛሬ ጥሪ አቅርቧል።

" የሀገር መከላከያ ሰራዊት፣ የአማራ ልዩ ኃይል፣ ፋኖ እና ሚኒሻው እየተፋለሙ ነው " ያለው የወልድያ ከተማ " የአካባቢው ማኅበረሰብ አካባቢውን ተረጋግቶ በመጠቅ ለጥምር ጦሩ የተለመደ ሁለተናዊ ደጀንነቱን አጠናክሮ ይቀጥል " ሲል ጥሪውን አቅርቧል።

ከተማ አስተዳደሩ " የጦርነቱ የፍልሚያ ቦታ እስከ አሁኗ ሰዓት ድረስ ከራያ ሚዳ አልዘለለም " ያለ ሲሆን ሾልኮ ለማለፍና በወሬ ለመፍታት የተደረገው ስልትም እስካሁን አልሰመረም ብሏል።

የከተማ አስተዳደሩ ዛሬ መልዕክቱን ያሰራጨው የአካባቢውን ተጨባጭ ሁኔታ በአካላዊ እንቅስቅሴ ጭምር በማጣራት መሆኑን አመልክቷል።

ምንም እንኳን አሁንም መሳሪያ ወርዶ ችግሮች በሰላም እንዲፈቱ የሚቀርቡ የሰላም ጥሪዎች ከሀገር ውስጥ እና ከውጭ እየቀረቡ ቢሆንም በሰሜን ኢትዮጵያ ዳግም ያገረሸው ግጭት ከቀን ወደ ቀን እየተባባሰ መጥቷል። ህወሓት ከዚህ ቀደም ለሰብዓዊነት ሲባል ተኩስ አቁም በታወጀበት ወቅት ከነበረበት ቦታ ወደፊት በመምጣት የአማራ ክልል ቦታዎችን እየያዘ ነው።

በትላንትናው ዕለት በኢትዮጵያ መንግስት እንደተገለፀው የኢትዮጵያ መከላከያ ከቆቦ ከተማ ለቆ ወጥቷል፤ በዚህም ቆቦ በህወሓት ስር ይገኛል።

መንግስት፤ ህወሓት ስልት በመጠቀም ጥቃት እያደረሰ መሆኑን በመግለፅ የህዝብ ከፍተኛ ፍጅት ለማስወገድ መከላከያው " ቆቦ " ን መልቀቁን በትለንትናው መግለጫ አስረድቷል።

Source tikhvah telegram channel

27/08/2022

የትግራይ ሴንትራል ኮማንድ ወቅታዊ መግለጫ

የትግራይ ህዝብ የራስ በራስን የማስተዳደር እና ዴሞክራሲያዊ መብቶቼ ይከበርልኝ በማለቱ ብቻ በፋሽስት አብይ አህመድ እና አጋሮቹ በትግራይ ህዝብ ላይ ግልፅ የህዝብ ማጥፋት ዘመቻ አውጀው በዘመናዊው ዓለም ታይቶ የማይታወቅ ግፍና በደል እንዲደርሰው አድርገዋል።
ከውስጥና ከውጭ አጋሮች ጋበዘው በጥይት ሊያጠፉት የተቻላቸውን ሁሉ አድርገዋል።ሌላው የህብረተሰባችን ክፍል ደግሞ እንዲበታተን እና እግሩ ወደ መራው እንዲሰደድ እና እንዲፈናቀልም አድርገዋል።
ከጥይት እና ከስደት ያመለጠው ህዝባችን ደግሞ በርሀብና በበሽታ እንዲያልቅ ያልፈነቀሉት ድንጋይ የለም።አሁንም ከበባ እና ክልከላ አጠናክረው በማስቀጠል የትግራይ ህዝብ በከባድ ሰቆቃ እንዲኖር በሙሉ አቅማቸው እየተረባረቡ ይገኛሉ።
የትግራይ ህዝብ በላዩ ላይ ለማመን የሚከብዱ ግፍና በደል እየተፈፀመበትም እንኳን ጀኖሳይዳሉን ጦርነት በሰላማዊ መንገድ በድርድር መፍትሔ እንድያገኝና ለሰላም እድል ለመስጠትና እንዲሁም በከበባ እና ክልከላ ውስጥ ሆኖ እየተሰቃየ ያለውን ህዝባችን ሰብአዊ ድጋፍ እንዲያገኝ የሚያስችል ምቹ ሁኔታ ለመፍጠር ብለን ልብ አሳድገን ግዝያዊ ግጭት የማቆም ስምምነቱን ተቀብለን ቆይተናል።
ይህ ውሳኒያችንም በወቅቱ ለህዝባችን እና ለዓለምአቀፉ ማህበረሰብ ግልፅ ማድረጋችን የሚታወቅ ነው።በዚህም የትግራይ ህዝብና መንግስት ለሰላም ያላቸውን ዝግጁነት በተግባር እያረጋገጡ መጥተዋል።
የፋሽስት አብይ አህመድ ቡዱን ደግሞ በማንኛውም መለክያ ቅድመ ሁኔታ ሊቀርብለት የማይገባውን ሰብአዊ ድጋፍ ወደ ትግራይ እንዳይገባ ማለቅያ የሌላቸውን መሰናክሎች እየፈጠረ መግባት የሚገባውን ድጋፍ በወቅቱ እንዳይገባ አድርጓል።ነዳጅ በመከልከልም ከስንት መሰናክል ቡኋላ ወደ ትግራይ የገባውን ድጋፍም ወደ ህዝብ እንዳይዳረስ የተቻለውን ሁሉ አድርጓል።ከዚህ በተጨማሪ እንደ ኤሌክትሪክ ፤ቴሌኮም ፤ባንክ፤ትራንስፖርት ወዘተ ያሉ የህዝብ አገልግሎት ሰጪ ተቋማት በመዝጋት ለሰላም ፋላጎት እንደሌለው በተግባር እያረጋገጠ መጥቷል።
ጠላት እኛ ለሰጠነው የሰላም እድል ረግጦ ሲያበቃ የዓለምአቀፍ ማህበረሰብን ለማደናገር በአፉ ሰላም ድርድር ወዘተ እያለ ዲፕሎማያስዊ እና ፋይናንሳዊ ትርፍና ድጋፍ ለማግኘት ኣልሞ በሙሉ አቅሙ ተንቀሳቅሷል ።በተግባር ግን የትግራይ ህዝብን ከገፀ ምድር ለማጥፋት ያቀደውን የጥፋት ፕሮጀክት በማጠናከር እና ለወረራ ሁሉንአቀፍ ዝግጅት በማድረግ በሰሜን ምዕራብ ትግራይ በድብደባ ጀምሮ በደቡብ ትግራይ ደግሞ ውግያ መጀመሩ የሚታወቅ ነው።በዚህም ከዚህበፊት የተደረገውን ጊዝያዊ ግጭት የማቆም ስምምነት በይፋ እንደጣሰው አረጋግጧል።
ጀግናው የትግራይ ሰራዊት ከጠላት ለታቀደው የህዝብ ማጥፋት ዘመቻ በሚገባ በመመከትና እያመከነ ባለበት ወቅት ጠላት የአየር ሃይሉ በማዝመት ነሓሴ 19ቀን 2014ዓ/ም በራያ ዓዘቦ ወረዳ ነሓሴ 20 ቀን 2014 ዓ/ም ደግሞ በመቐለ ከተማ አሰቃቂ ድብደባ በመፈፀም በንፁሀን ሰዎች እና ንብረት ላይ ከባድ ጉዳት አድርሷል።የትግራይ ሴንትራል ኮማንድ ህፃናትን ጨምሮ በንፁሀን ወገኖች ላይ በደረሰው ግፍ የተሞላበት ግድያ እና የአካል ጉዳት መራር ሀዘን እንደተሰማው ሲገልፅ ለተጎጂ ቤተሰቦችና የትግራይ ህዝብ ፅናቱን ይስጣችሁ ይላል።የንፁሃን ወገኖቻችንም ደም በከንቱ ፈሶ እንደማይቀርም በዚህ አጋጣሚ ማረጋገጥ ይፈልጋል።
የተከበርክ የትግራይ ህዝብ

ከውስጥና ከውጭ አጋሮች ጋብዞ ከገፀ ምድር ሊያጠፋህ ሁሉም ዓይነት ከህደት ከመፈፀም ወደኋላ የማይለው ፋሽስታዊ ሀይል አሁንም ወረራውን አጠናክሮ እየቀጠለበት ይገ

 የኢትዮጵያ መከላከያ " ቆቦ " ን ለቆ መውጣቱን መንግስት ገለፀ።የኢፌዴሪ መንግስት ኮሚኒኬሽን ማምሻውን ባወጣው መግለጫ ፥ " አሻባሪው ህወሓት የሰው ኃይል ማዕበልን በመጠቀም የቆቦ ከተማን...
27/08/2022



የኢትዮጵያ መከላከያ " ቆቦ " ን ለቆ መውጣቱን መንግስት ገለፀ።

የኢፌዴሪ መንግስት ኮሚኒኬሽን ማምሻውን ባወጣው መግለጫ ፥ " አሻባሪው ህወሓት የሰው ኃይል ማዕበልን በመጠቀም የቆቦ ከተማን ከውጭ በብዙ አቅጣጫ እያጠቃ ነው " ብሏል።

በሌላ በኩል ደግሞ በከተማ ውስጥ ሠርጎ ገቦችን በማሥረግ የሕዝቡን ደኅንነት አደጋ ውስጥ በሚያስገባ መልኩ የከተማ ውስጥ ውጊያ ለማድረግ የሚያስችል ሁኔታ እየፈጠረ ይገኛል ብሏል።

በዚህም ፤ " የሕዝብን ከፍተኛ ፍጅት ለማስወገድ የመከላከያ ኃይል የቆቦ ከተማን በመልቀቅ እና ወደ ኋላ መጥቶ ለመከላከል የሚስችለውን ወታደራዊ ይዞታዎችን ለመያዝ ተገዷል " ሲል አሳውቋል።

የኢፌዴሪ መንግስት ኮሚኒኬሽን ፥ " አሸባሪው ኃይል የትግራይን ወጣት እየማገደ በሕዝብ ማዕበል ማጥቃቱን ካላቆመ መከላከያ ሕጋዊ ፣ ሞራላዊና ታሪካዊ ግዴታውን ለመወጣት የሚገደድ ይሆናል " ብሏል።

ምንም እንኳን ከተለያየ አቅጣጫ ሰላም እንዲሰፍን እና መሳሪያ ወርዶ ንግግር እንዲጀመር ጥሪዎች ቢቀርቡም በሰሜን ኢትዮጵያ ዳግም ያገረሸው ግጭት ከዕለት ወደ ዕለት እየተባባሰ መጥቷል።

Source tikhvah telegram channel

27/08/2022

ቤተሰቦች አሰላሙአለይኩም መጥቼያለሁ
ጦርነት አስደንግጦኝ ነው የጠፋሁት እና ከዝህ በኋላ ወደ መደበኛ ሥራ እንገባለን

 #ተመድ  አንቶኒዮ ጉተሬዝ ግጭት እንዲቆም ተማፀኑ።የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ፀሀፊ አንቶኒዮ ጉተሬዥ ፤ በኢትዮጵያ ዳግም ግጭት መቀስቀሱን በመስማታቸው ማዘናቸውንና መደንገጣቸውን ገ...
24/08/2022

#ተመድ

አንቶኒዮ ጉተሬዝ ግጭት እንዲቆም ተማፀኑ።

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ፀሀፊ አንቶኒዮ ጉተሬዥ ፤ በኢትዮጵያ ዳግም ግጭት መቀስቀሱን በመስማታቸው ማዘናቸውንና መደንገጣቸውን ገልፀዋል።

ይህን የገለፁት ፤ ዛሬ ከሚካሄድ የፀጥታው ም/ ቤት ስብሰባ አስቀድሞ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ ላይ ነው።

በኢትዮጵያ ዳግም ግጭት በመቀስቀሱ በጣም ማዘናቸውንና መደንገጣቸውን የገለፁት ጉተሬዥ በአስቸኳይ ግጭት እንዲቆም ተማፅነዋል።

" ኢትዮጵያውያን ትግራዋዮች፣ አማራዎች፣ ኦሮሞዎች ፣ አፋሮች ብዙ መከራ ደርሶባቸዋል " ሲሉ ገልፀዋል።

" አጠንክሬ የምጠይቀው በአስቸኳይ የተኩስ አቁም እንዲደረግና የመንግስትና የህወሓት የሰላም ድርድር እንዲቀጥል ነው " ብለዋል።

ጉተሬዥ የሰብዓዊ እርዳታ አቅርቦት ሙሉ ዋስትና እንዲሰጠው ፤ በተጨማሪ የህዝብ አግልግሎቶች ተመልሰው እንዲቋቋሙ ጠይቀዋል።

በሌላ በኩል ፤ የአፍሪካ ህብረት (AU) ኮሚሽን ሊቀ መንበር ሙሳ ፋኪ በኢትዮጵያ እንደገና ወታደራዊ ግጭት መፈጠሩን የሚገልፁ ሪፖርቶች መስማታቸው እጅግ እንዳሳሰባቸው ገልፀዋል፤ ሁኔታውን እየተከታተሉ መሆኑንም አመልክተዋል።

ሊቀመንበሩ በአስቸኳይ ግጭት እንዲቆም ጥሪ ያቀረቡ ሲሆን ሰላማዊ መፍትሄ ለማምጣት ንግግሩ ሊቀጥል ይገባል ብለዋል።

የአፍሪካ ህብረት መልኩ የጋራ ስምምነት ላይ የተመሰረተ የፖለቲካ ሂደትን ለመደገፍ ከሁሉም ወገን ጋር አብሮ ለመስራት ቁርጠኛ ነው ሲሉ አረጋግጠዋል።

ለዚህም ሁሉም ወገኖች ከአፍሪካ ህብረት የአፍሪካ ቀንድ ከፍተኛ ተወካይ ከሆኑት የቀድሞ የናይጄሪያ ፕሬዚደንት ኦሊሴንጉን ኦባሳንጆ ጋር እንዲሰሩ ጥሪ አቅርበዋል
ምንጭ ቲክቫህ telegram channel

''No plane entered Tigray, nor was an imaginary plane shot-down.'' The government of Ethiopia is just spreading fake inf...
24/08/2022

''No plane entered Tigray, nor was an imaginary plane shot-down.'' The government of Ethiopia is just spreading fake information to lay the groundwork for aerial assaults on Tigray, according to a press statement by TEAO today. ''The international community must prevail on it to refrain from its planned indiscriminate attacks on civilians'', it added.

ሰበር መረጃ!!ለህወሃት የጦር መሳሪያ ጭኖ የኢትዮጵያ የአየር ክልል ጥሶ የገባ አውሮፕላን መምታቱን አየር ኃይሉ አስታወቀየኢትዮጵያን መዳከም የሚፈልጉና ለዚሁም ለዘመናት የሚንቀሳቀሱ ህወሃትን...
24/08/2022

ሰበር መረጃ!!

ለህወሃት የጦር መሳሪያ ጭኖ የኢትዮጵያ የአየር ክልል ጥሶ የገባ አውሮፕላን መምታቱን አየር ኃይሉ አስታወቀ

የኢትዮጵያን መዳከም የሚፈልጉና ለዚሁም ለዘመናት የሚንቀሳቀሱ ህወሃትን በመደገፍ ላይ የሚገኙ ታሪካዊ ጠላቶች ንብረት እንደሆነ የሚታመን አውሮፕላን ለሽብር ቡድኑ የጦር መሳሪያ ጭኖ በሱዳን አልፎ የአየር ክልላችንን ጥሶ ሲገባ በጀግናው አየር ሃይል ተመትቶ ወድቋል::

ሠራዊቱ የሀገሩን ሉዓላዊነት ለማስከበር ከመቼውም ጊዜ በላቀ ሁኔታ ዝግጁ መሆኑም ተገልጿል።

በሀገር መከላከያ ሠራዊት የመከላከያ ህብረት ዘመቻ ዋና መምሪያ የመከላከያ ኃይል ስምሪት ኃላፊ ሜጀር ጀኔራል ተስፋዬ አያሌው ለኢዜአ እንደገለጹት፤ ላለፉት በርካታ ወራት ከፍኛ ወታደራዊ ዝግጅት ሲያደርግ የቆየው አሸባሪው ህወሃት ካለፉት ሁለት ሳምንታት ጀምሮ ኃይሉን ለውጊያ ሲያስጠጋ ነበር።

በየጊዜውም ተኩስ እየከፈተ የሀገር መከላከያን ሲተነኩስ መቆየቱንም ነው ያነሱት።

ቡድኑ መንግስት የዘረጋውን የሰላም አማራጭ ከቁብ ሳይቆጥርና የሰላም ሂደቱ ቴክኒካሊ ፈርሷል ብሎ መግለጫ ባወጣ ማግስት ትናንት ነሐሴ 18 ቀን 2014 ዓ.ም ሌሊት 11 ሰዓት ላይ በቆቦ ግራና ቀኝ ባሉ አካባቢዎች፣ በዞብል ተራራ፣ በቢሶበርና በወትወት ውጊያ መክፈቱን ገልጸዋል። በዚህም የተኩስ አቁም ስምምነቱን ማፍረሱን ጠቅሰው፤ የሽብር ቡድኑ እየላከ ያለው ጀሌ በሀገር መከላከያ ሠራዊትና በጸጥታ ሃይልች እየተለበለበ ነው ብለዋል።

Source BBC Amharic

24/08/2022



ለዜጎች ሰላም እና ከጦርነት ጭንቀት እረፍት ይሰጣል ተብሎ የነበረው የተስፋ ጭላጭል " ሙሉ በሙሉ " ይከስም ይሆን ?

የኢትዮጵያ የፌዴራል መንግስት ዛሬ ፤ ረቡዕ ባወጣው መግለጫ " ህወሓት " በምስራቅ ግንባር በቢሶበር ፣ ዞብል ፣ እና ተኩለሽ በኩል ከለሊት 11 ሰዓት አንስቶ ጥቃት መፈፀሙን ገልጿል።

በዚህ እርምጃውም ተኩስ ማቆሙን በይፋ አፍርሷል ብሏል።

ዜጎችን ከ "ህወሓት" ጥቃት ለመጠበቅም አጠቃላይ የፀጥታ ኃይል በተጠንቀቅ መቆሙን አስገንዝቧል።

የለሊቱ ጥቃት ፤ ከሰሞኑን ከነበረው ትንኮሳ የቀጠለ መሆኑን የገለፀው የኢትዮጵያ መንግስት ፤ የኢትዮጵያ ሀገር መከላከያ ሰራዊትና አጠቃላይ የፀጥታ መዋቅሩ የተሰነዘረውን ጥቃት በድል እየመከቱት ይገኛሉ ብሏል።

ከኢትዮጵያ መንግስት መግለጫ ቀደም ብሎ ህወሓት የፌዴራል መንግስት ከለሊት 11:00 ጀምሮ በጩቤ በር ፣ ጃኖራ ፣ ጉባጋላ እና በያሎው አቅጣጫ ወደ አላማጣ ፣ ባላና ብሶበር መጠነሰፊ ጥቃት ከፍቷል ሲል ክስ አሰምቷል።

ባለፉት ቀናት ፤ በደቡብ ግንባር በየግንባሩ የነበሩትን እና ከሌላ አካባቢ የተሰባሰቡ የአማራ ልዩ ኃይል ክ/ጦሮች ፣ የወሎ ፋኖና ሚሊሻ ወደፊት የማስጠጋት እንቅስቃሴ ነበር በኃላም የፌዴራል መከላከያ ኃይል ተጨምሮ ዛሬ ጥቃት ተከፍቷል የሚል ክስ አቅርቧል።

የኢትዮጵያ የፌዴራል መንግስት ግን ይህ የህወሓት ክስ " ጅራፍ ራሱ ገርፎ እራሱ ይጮሃል " እንደሚባለው ቀድሞ የተካነበት የሀሰት ፕሮፖጋንዳ ነው ብሎታል።

ትንኮሳው በራሱ በ " ህወሓት " መፈፀሙን የገለፀው መንግስት ትንኮሳውን ከፈፀሙ በኃላ " እራሳቸው እየጮሁ " ነው ብሏል።

የዓለም አቀፉ ማህበረሰብ፤ የህወሓት ቡድን የትግራይ የወጣቶችን ለማስጨረስ እያደረገ ያለውን የጦርነት ጉሰማ እንዲያቆም ጠንካራ ግፊት ማድረግ አለበትም ሲል ጥሪ አቅርቧል።

የኢትዮጵያ መንግስት የሁሉም ኢትዮጵያውያን መፍትሄ የሚያገኘው በሰላም ነው ያለ ሲሆን ዛሬም ነገም የሰላም አማራጭ የመጀመሪያ መፍትሄ እንደሆነ በፅኑ እንደሚያምን ገልጿል።

ነገር ግን ህወሓት በትንኮሳው ከቀጠለ ሀገር የማዳን ህጋዊ፣ ታሪካዊ እና ሞራላዊ ግዴታ ስላለበት ህወሓት ወደደም ጠላም ወደ ሰላማዊ አማራጭ እንዲመጣ ለማድረግ እርምጃ እንደሚወስድ አስጠንቅቋል።

በሰሜን ኢትዮጵያ፤ አሁን አሁን ጠንከር ብለው እየታዩ ያሉት ምልክቶች ከዚህ ቀደም እንደነበረው የለየት ደም አፋሳሽ ግጭት እንዳይወልድ ብዙዎችን አስግቷል። የተጀመረው የሰላም ሂደትም እንዳይደናቀፍ ተፈርቷል።

ከወራት በፊት ለሰብዓዊ ድጋፍ ሲባል ግጭት የማቆም ውሳኔ መተላለፉ አይዘነጋም ፤ ይህን ተከትሎ የሰላም ጭላንጭሎች መታየት ችለው ፤ ዜጎችም ከጦርነት እና ግጭት ስጋት ይላቀቃሉ የሚል ተስፋን ሰጥቶ ነበር።

በኃላም ችግሩን በሰላም ድርድር ለመፍታት መወሰኑን ተከትሎ በርካቶች " እፎይ ሰላም ሊገኝ ነው " የሚለው ተስፋቸው እጅግ ተጠናክሮ፤ በዚህም ተደስተው ነበር ነገር ግን ይህ ከሆነ ወራት ሳይቆጠር ዳግም የጦርነት ድባብ አንዣቧል።

ዜጎች የከዚህ ቀደሙ ጉዳት እና ህመማቸው ሳይባባስ ፣ ምንም የማያውቁ ንፁሃን ህፃናት ፤ ሴቶች አረጋዊያን ሳይፈናቀሉ ፣ ምንም የሰው ህይወት ሳይጠፋ ፣ የሀገር ሀብት ከከዚህ ቀደሙ በበለጠ ሳይጎዳ ፤ አሁን እየታዩ ያሉት ምልክቶች ቆመው በፍጥነት ሰላም ወርዶ ፤ ችግሮች ተፈተው በደስታ እንቀበለው ይሆን ? ተስፋ እናደርጋለን ! ለሰላም መቼም ጊዜው አይረፍድም።
Source tikhvah telegram channel

አሜሪካ ለዩክሬን የ3 ቢሊየን ዶላር ወታደራዊ ድጋፍ ልታደርግ ነው ።አሜሪካ ለዩክሬን ተጨማሪ 3 ቢሊየን ዶላር የሚያወጣ ወታደራዊ ድጋፍ ይፋ ልታደርግ መሆኑን አስታውቃለች፡፡ድጋፉ ዩክሬን ከሩ...
24/08/2022

አሜሪካ ለዩክሬን የ3 ቢሊየን ዶላር ወታደራዊ ድጋፍ ልታደርግ ነው ።

አሜሪካ ለዩክሬን ተጨማሪ 3 ቢሊየን ዶላር የሚያወጣ ወታደራዊ ድጋፍ ይፋ ልታደርግ መሆኑን አስታውቃለች፡፡

ድጋፉ ዩክሬን ከሩሲያ ጋር ጦርነት ውስጥ ከገባችበት ጊዜ ወዲህ ዋሺንግተን ለኪዬቭ ካደረገቻቸው ወታደራዊ ድጋፎች ከፍተኛ መጠን ያለው መሆኑ ተጠቁሟል፡፡ወታደራዊ ድጋፉ ከዩክሬንን የነጻነት ቀን ጋር እንዲገጣጠም ለማድርገ መታቀዱንም ሬውተርስ የአሜሪካ ከፍተኛ ባለስልጣናትን ዋቢ አድርጎ ዘግቧል፡፡

የእርዳታ ማዕቀፉ አሜሪካ ለዩክሬን ከመደበችው የዩክሬን ደህንነት እርዳታ ኢኒሼቲቭ በጀት ወጪ የሚደረግ መሆኑም ተመላክቷል፡፡አሜሪካ ከዚህ በፊት ለዩክሬን የተለያየ መጠን ያለው የጦር መሳሪያ ድጋፍ ማድረጓ የሚታወስ ነው፡፡ የአሁኑ ድጋፍ ከጦር መሳሪያ ባለፈ ዩክሬንን የመከላከያ አቅም መገንባት የሚያስችል የመካከለኛ ጊዜ እቅድን ያካተተ መሆኑም ነው
Source BBC Amharic

24/08/2022

" የተሳሳቱ መረጃዎችን በመልቀቅ ተማሪዎች የስነ ልቦና ጫና እንዲደርስባቸው የሚያደርጉ አካላትን ለማድረግ እየተሰራ ነው " - ዶ/ር እሸቱ ከበደ

የ2014 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ቅድመ ዝግጅት ስራ ሙሉ በሙሉ በመጠናቅ ላይ መሆኑን የሀገር አቀፍ ትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር እሸቱ ከበደ (ዶ/ር) ተናግረዋል፡፡

የፈተና ዝግጅቱም የተማሪዎችን ልፋት ሊለካ በሚችል ከደህንነት ስጋት ነፃ እንዲሆን በቴክኖሎጂ በመታገዝ በከፍተኛ ጥንቃቄ እየተሰራ መሆኑንም ገልጸዋል፡፡

ለፈተና አሰጣጡ ውጤታማነት ከመፈተኛ ቦታ መረጣ ጀምሮ የፈተና ኮዶችን ብዛት ከፍ የማድረግ ስራ የተሰራ መሆኑም ተገልጿል።

ይህንን ተከትሎ ተማሪዎች አስፈላጊውን ዝግጅት በማድረግ የራሳቸው ጥረት ውጤት ለማግኘት መስራት እንዳለባቸው አሳስበዋል፡፡

የተሳሳቱ መረጃዎችን በመልቀቅ ተማሪዎች የስነ ልቦና ጫና እንዲደርስባቸው የሚያደርጉ አካላትም ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ ዋና ዳይሬክተሩ ያሳሰቡ ሲሆን ለዚህም የህግ ተጠያቂነት እንዲኖር እየተሰራ እንደሚገኝ ገልፀዋል፡፡

ተማሪዎችና ወላጆችም መረጃዎችን ከተቋሙ እና ከታማኝ የመረጃ ምንጮች ብቻ እንዲከታተሉም ጠይቀዋል።

የ2014 የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ከመስከረም 30 ቀን 2015 ዓ/ም ጀምሮ መሰጠት ይጀምራል።

መረጃው የትምህርት ሚኒስቴር ነው።

Source tikhvah telegram channel

 የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ፌዴሬሽን ም/ቤት አፈ-ጉባዔ ለቦርዱ ያቀረበው የሕዝበ ውሣኔ ማደራጀት ጥያቄ ላይ ውሣኔ አሳለፈ !ነሐሴ 12/2014 የፌዴሬሽን ም/ ቤት ፤ ብሄ...
24/08/2022



የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ፌዴሬሽን ም/ቤት አፈ-ጉባዔ ለቦርዱ ያቀረበው የሕዝበ ውሣኔ ማደራጀት ጥያቄ ላይ ውሣኔ አሳለፈ !

ነሐሴ 12/2014 የፌዴሬሽን ም/ ቤት ፤ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ከ6 ዞኖችን እና 5 ልዩ ወረዳዎችን የክልልነት ጥያቄ ጋር ተያይዞ በ3 ወር ህዝበ ውሳኔ በማድረጃት ውጤቱን ለምክር/ቤቱ እንዲያሳውቅ ብሎ ነበር።

ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ለምክር ቤቱ ምላሹን ሰጥቷል። ምላሹ የህግ አግባብን ተከትሎ የተሰጠ መሆኑ ተገልጿል።

ከቦርዱ ምላሽ ፦

" ... ቦርዱ ለዚህ ጉዳይ አፈፃፀም የሎጂስቲክስ ዝግጅት ለማድረግ፣ የምርጫ አስፈጻሚዎች ምልመላ እና ምደባ ለመተግበር፣ የምርጫ ፀጥታ ጉዳይን ለመገምገም፣ የመራጮች ትምህርት ለመስጠት፣ የምርጫ ጣቢያዎች ለማደራጀት፣ ለታዛቢ ሲቪል ማህበራት ፈቃድ ለመስጠት እና በጉዳዩ ላይ የሚያገባቸውን ባለድርሻ አካላት ለማወያየት የሚያስፈልገውን ጊዜ ታሳቢ ያደረገ የጊዜ ሰሌዳ አውጥቶ ለምክር ቤቱ እንደሚገልፅ ከአክብሮት ጋር እናሳውቃለን። "

(ቦርዱ ያሳለፈው ውሳኔ ከላይ ተያይዟል)

Source tikhvah telegram channel

24/08/2022

Abbootii Aksiyoonaa Baankii Hijraa Kanfaltii Aksiyoonaa hin Kanfalin Hundaaf
ቀሪ የአክስዮን ክፍያ ላልከፈላችሁ የሂጅራ ባንክ አ/ማ ባለአክሲዮኖች በመሉ
🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
የሂጅራ ባንክ አ/ማ ባለአክሲዮኖች ቀሪ የአክሲዮን ክፍያቸውን ባንኩ ሕጋዊ ሰውነት ካገኘበት ቀን ጀምሮ በአንድ ዓመት ጊዜ ዉስጥ ከፍለው ማጠናቀቅ እንዳለባቸው በባንኩ መመስረቻ ጽሁፍ ላይ በግልጽ መቀመጡ ይታወቃል። በዚህም መሰረት ከዚህ ቀደም ቀሪ የአክስዮን ክፍያችሁን ከፍላችሁ እንድታጠናቅቁ በተደጋጋሚ ማሳወቃችን ይታወሳል። ሆኖም የሀገራችንን ወቅታዊና ነባራዊ ሁኔታ ግምት ውስጥ በማስገባት ባንኩ በተደጋጋሚ የመክፈያ ጊዜውን ቢያራዝምም በተቀመጠው የጊዜ ገደብ ውስጥ ቀሪ የአክሲዮን ክፍያቸውን ከፍለው ያላጠናቀቁ ባለአክሲዮኖች መኖራቸውን ማወቅ ተችሏል፡፡

ይህም ባንኩ ተጨማሪ አክሲዮኖችን ወደ ገበያ በማውጣት ለመሸጥ ያለውን እቅድ አስተጓጉሎ ቆይቷል፡፡ በመሆኑም እስካሁን ክፍያችሁን ያላጠናቀቃችሁ የባንኩ ባለአክሲዮኖች ለመጨረሻ ጊዜ እስከ ጳጉሜ 4 ቀን 2014 ድረስ ቀሪ ክፍያችሁን ከፍላችሁ እንድትጨርሱ በአክብሮት እየጠየቅን በተሰጠው የጊዜ ገደብ ውስጥ የሚጠበቅባችሁን ቀሪ ክፍያ ከፍላችሁ በማታጠናቅቁ ባለአክሲዮኖች ላይ ባንኩ በንግድ ህጉ አንቀጽ 289/4፣5፣6/ በተቀመጠው መሰረት አስፈላጊውን ህጋዊ እርምጃ ሁሉ ለመውሰድ፤ ማለትም አክሲዮኖቹን ተመላሽ በማድረግ፣ ለሽያጭ ማቅረብ እንዲሁም መሰረዝ እንደሚገደድ የባንኩ የዳይሬክተሮች ቦርድ በጥብቅ ያሳስባል፡፡ ቀሪ ክፍያችሁን ከዚህ በታች ከተገለጹ የሂሳብ ቁጥሮች በአንዱ ገቢ ማድረግ ያስፈልጋል።

1. ሂጅራ ባንክ አ.ማ. 00011230017001
2. የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 1000438976098
3. አዋሽ ኢንተርናሽናል ባንክ 01410243072601
4. ኦሮሚያ ህብረት ስራ ባንክ 1023500039993
5. ኦሮሚያ ባንክ 1471998800001
6. ንብ ኢንተርናሽናል ባንክ 7000027749618
7. አቢሲኒያ ባንክ 81570302

የከፈላችሁበትን ደረሰኝ በቴሌግራም 0920-33-33-37 ላይ ወይም በኢሜል [email protected] ላይ እንድትልኩልን ወይም ለባንኩ ዋና መ/ቤት ወይም በአቅራቢያችሁ በሚገኝ የሂጅራ ባንክ ቅርንጫፍ በአካል እንድትሰጡ እንጠይቃለን። ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥሮች 011-5584256፣ 0920-33-33-37/38 በመደወል ማግኘት ይችላሉ።

ሂጅራ ባንክ አ.ማ.

Abbootii Aksiyoonaa Baankii Hijraa Kanfaltii Aksiyoonaa hin Kanfalin Hundaaf
🔺🔺🔺🔺🔺🔺🔺🔺🔺🔺🔺🔺🔺🔺🔺

Abbootiin Aksiyoonaa baankii Hijraa kanfaltii aksiyoonaa isaan irratti hafe guyyaa baankichi ulaagaa seeraa guutee dhaabbate irraa kaasee waggaa tokko keessatti kanfalanii xumuuruu akka qaban waraqaa hundeeffama baankichaa irratti ifaan taa’ee jiraachuun isaa ni beekkama. Bu’uuruma kanaan, kanaan dura kanfaltii aksiyoonaa isin irratti hafe kanfaltanii akka xumurtan irra deddeebiidhaan isni beeksisaa turuun keenya ni yaadatama. Haa ta’u malee, haala yeroo biyya keenyaa ilaalcha keessa galchuudhaan baankichi yeroo kanfaltii dheeressaa turus abbootiin aksiyoonaa yeroo jedhame keessatti kanfaltii aksiyoonaa isaan irratti hafe kanfalanii hin xumurree jiraachuun barameera. Kunis kaaroora baankichi aksiyoona haaraa baasee gurguruudhaaf qabu gufachiisaa tureera.

Kanaafuu, abbootiin aksiyoona isinirratti hafe kanfaltanii hin xumuurin yeroo xumuraatiif Hanga Qaammee 4 bara 2014-itt akka xumurtan kabajaadhaan isin gaafachaa, abbootiin aksiyoonaa yeroo kenname keessatti kanfaltii isin irraa eeggamu kanfaltanii hin xumurre baankichi bu’uura seera daldalaa keewwata 289(4), (5), (6) tiin tarkaanfii kan fudhatu, jechuunis aksiyoonota deebisuudhaa hanga gurgurtaadhaaf dhiheesuu akkasumas haquudhaaf akka dirqamu boordiin daayirektaroota baankichaa ciminnaan akeekachiisa.
Kanfaltii Aksiyoonaa karaa lakkoofsa herreegaa armaan gadiitti tarraa’an kessaa tokkon raawwaachuu danddeessu

1. Baankii Hijraa 00011230017001
2. Baankii Daldala Itoophiyaa 1000438976098
3. Baankii Awaash 01410243072601
4. Baankii Hojii Gamtaa Oromiyaa 1023500039993
5. Baankii Oromiyaa 1471998800001
6. Baankii Internaashinaalii Nib. 7000027749618
7. Baankii Abisiiniyaa 81570302
Odeeffannoo Dabalataa karaa laakkoofsa bilbilaa 011-5584256፣0920-33-33-37/38 tiin bilbiluun arggachuu ni danddeessu.

Baankii Hijraa(W.A)
Source ahmedin jabel telegram channel

24/08/2022

የትግራይ ሰራዊት ወታደራዊ ኮማንድ መግለጫ

የተከበርክ የትግራይ ህዝብ

ጠላት በደቡባዊ ግምባር በዛ ግምባር ከቆዩትና ከሌሎች አከባቢዎች ያሰባሰባቸው የአማራ ልዩ ሀይል ክፍለጦሮች፤የወሎ ፋኖ እና ሚሊሻዎችን ባለፉት አምስት ቀናት እያዘጋጀ ከቆዬ በኋላ የፌደራል መከላከያ ሀይል አካላት የሆኑት 6ተኛ እና 8ተኛ እግረኛ እዞችና የ2ተኛ 6ተኛ እና 8ተኛ ሜካናይዝድ ክፍለጦሮችን ጨምሮ ዛሬ ነሓሴ 18 ቀን 2014 ዓ/ም ከማለዳው 11 ሰዓት ጀምሮ በጩቤበር፤ጃኖራ፤ጉባጋላ እና ያሎው አቅጣጫዎች ወደ አላማጣ ባላና ብሶበር ሰፊ የማጥቃት ዘመቻ ጀምርዋል።
ጠላት በዚህ ግምባር የጀመረው የማጥቃት ዘመቻ ደቡብ ትግራይን በቁጥጥሩ ስር ለማስገባት እንዲችል የሚገፋ አጋዥ የማጥቃት አቅጣጫ እንጂ ዋናው የማጥቃት እቅዱ ከምዕራብ ትግራይ እና ምዕራብ ጎንደር ወደ አድያቦ እና አስገደ ፅምብላ መሆኑ ቀድሞ የታወቀ ጉዳይ ነው።
ጠላት በዘመናዊ የዓለም ታሪክ ታይቶ በማይታወቅ መልኩ የትግራይ ህዝብን ሙሉ በሙሉ ዘግቶ ታሪክ የማይረሳው ግፍና ስቃይ እያደረሱ ከቆዩ በኋላ አሁን ተዳክሟልና በጦርነት ሙሉ በሙሉ ልጨርሰው እችላለሁ ባለበት ገዜ ለተወሰኑ ወራት የቆየውን ግጭትን የማቆም ስምምነት በመጣስ ሲያካሂደው ለቆየው ህዝብን የማጥፋት ጦርነት አጠናቅሮ የቀጠለበት መሆኑን በዛሬው ማለዳ በጀመረው ወታደራዊ ጥቃት በይፋ ገሃድ አድርጎታል።

የተከበራችሁ መላው የትግራይ ልጆች

ጠላት ከዚህ ቀደም በሚታወቀው የማጥቃት እቅዱ መነሻ በማድረግ የጀመረው ማጥቃት እንዲቆም ካላደረገው የትግራይ ሰራዊት በአስተማማኝ መልኩ በመመከት ሰብሮ ወደ ፀረ ማጥቃት በማሸጋገር የተወረረው የትግራይ ሉአላዊ መሬት ለመመለስና የተፈናቀለው ህዝባችን ወደ ቦታው እንዲመለስ ለማስቻል ያለው ዝግጁነት ሙሉ መሆኑን የትግራይ ሰራዊት ወታደራዊ ኮማንድ ለመግለፅ ይወዳል።
የተከበራችሁ የኢትዮጵያ ህዝቦች እና የፖለቲካ ሀይሎች
የትግራይ ህዝብ ሀገሬ ለሚላት ሀገር እጅግ ውድስ ዋጋ የከፈለ ጠንካራ ኢትዮጵያዊ እንጂ ጠላት አይደለም።ነገር ግን ጠላቶቻችን ለዚህ ለራሱ ፅኑ ኢትዮጵያዊ አድርጎ ሲያስብ ለነበረው ህዝብ እየፈፀሙት ያሉት ህዝብን የማጥፋት ተግባር ቀጥለውበት እስካሁን ሙሉ በሙሉ ከበው የረሀብ፤የበሽታ እና የጭንቀት ሰለባ አድርገውት ቆይተው ዛሬ ደግሞ ወታደራዊ ጥቃት ጀምረዋል።
ነገር ግን ይህ ፍላጎታቸው በሀይል ሊያሟሉት ፍፁም እንደማይችሉ በመገንዘብ ጦርነቱ እንዲቆምና የትግራይ ህዝብ እንደ ህዝብ ህልውናውና ቀጣይነቱ ለማረጋገጥ ሲል እያደረገው ባለው ያልተቆጠበ ትግል ወገናዊ ድጋፋችሁን እንድታሳዩት የትግራይ ሰራዊት ወታደራዊ ኮማንድ ጥሪውን ያቀርብላቹሀል።

የትግራይ ሰራዊት ወታደራዊ ኮማንድ
ነሓሴ 18 2014 ዓ/ም
ትግራይት

የአዲስ አበባ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት የክፍለ ከተማ የስራ አመራሮች ምስረታና ትውውቅ ፕሮግራም አካሄደ።የአዲስ አበባ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት በዛሬው እለት ከአስራ አ...
23/08/2022

የአዲስ አበባ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት የክፍለ ከተማ የስራ አመራሮች ምስረታና ትውውቅ ፕሮግራም አካሄደ።

የአዲስ አበባ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት በዛሬው እለት ከአስራ አንዱም ክፍለ ከተሞች የተውጣጡ የስራ አመራሮችን በኡማ ሆቴል ባካሄደው ፕሮግራም ላይ ይፋ አደርጓል፡፡

በፕሮግራሙ ላይ ይፋ የተደረጉት የአዲስ አበባ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት የክፍለ ከተማ አመራሮችን በተመለከተ ከዑለሞች ፣ ከምሁራን ፣ከታዋቂና ተፅዕኖ ፈጣሪ ግለሰቦችና ከወጣቶች መካተታቸው ተጠቅሳል፡፡

የአዲስ አበባ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት የክፍለ ከተማ አመራሮች ሰባት አባላት ያሉት ሲሆን ከመካከላቸው ሰብሳቢ፣ምክትል ሰብሳቢ፣ዋና ፀሀፊን መርጠዋል።

ፕሮግራሙ ላይ የአ/አ/እ/ጉ/ከ/ም/ቤት ፕሬዝዳንት ሼህ ሱልጣን ሀጂ አማን ኤባ፣ የአ/አ/እ/ጉ/ከ/ም/ቤት ም/ፕረዝዳንት ሼህ ፈትሁዲን ሀጂ ዘይኑ ሙቅና፣ የአ/አ/እ/ጉ/ከ/ም/ቤት ዋና ፅሀፊ ሼህ ሁሴን በሽር እንዲሁም ከኢትዮጰያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት የስራ አስፈፃሚ አባልና የሀጅና ኡምራ ዘርፍ ሀላፊ ሼህ አብዱልሀሚድ አህመድ ጠቅላይ ምክር ቤቱን በመወከል ተገኝተዋል።

በፕሮግራሙ ላይ የአ/አ/እ/ጉ/ከ/ም/ቤት ፕሬዝዳንት ሼህ ሱልጣን ሀጂ አማን ለክፍለ ከተማ የስራ አመራሮች የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት በማስተላለፍ ከዚህ ቀደም ባሳለፍነው ሶስት አመታት የክፍለ ከተማ አወቃቀር እንዳይዘረጋ ከፍተኛ ጫና እንደነበር በመግለፅ ሀምሌ 11/2014 በሸራተን አዲስ በተደረገው ጉባኤ መሰረት ክልሎች እራሳቸውን ማደራጀት መጀመራቸው የሚታወስ ሲሆን በዚሁ መሰረት የአዲስ አበባ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ከተዋቀረ በኋላ እነሆ ለዛሬው ቀን ክፍለ ከተሞችን ለማዋቀር በቅተናል ብለዋል፡፡አያይዘውም ህዝበ ሙስሊሙ ከዚህ በፊት የነበረው ስርአት ህዝበ ሙስሊሙን ለመለያየት ያደረገው ያልተሳካ ሙከራ በማንሳት በአሁን ሰአት ያለው የለውጥ መንግስት የሙስሊሙን የቆየ አንድነት ከማስጠበቅ አንፃር ያበረከተውን አዎንታዊ ድጋፍ በመጥቀስ ምስጋና አቅርበዋል።

በተጨማሪም ለአዲሶቹ የክፍለ ከተማ አመራሮች የተሰጣቸው ሀላፊነት ከባድ ከመሆኑ አንፃር ሙስሊሙን ማህበረሰብ የማገልገል ሀላፊነታቸውን እንዲወጡ ጥሪ አቅርበዋል፡፡ፕሬዝዳንቱ አክለውም ኢትዮጰያዊያን ሙስሊሞችን የሚመጥን ተቋም ለመገንባት በሚደረገው ጥረት አስተዋፆ ላበረከቱ ባለድረሻ አካለት ምስጋናቸውን ያቀረቡ ሲሆን መንግስትም ለዚህ ተቋም ግንባታ ያሳየውን ቀና ትብብር አመስግነዋል፡፡

ከዚህም ባሻገር የአዲስ አበባ ህዝበ ሙስሊም አሁን ላይ እያሳየ ያለውን ተነሳሽነት በቀጣይ በክፍለ ከተማ ደረጃ ለተዋቀረው መዋቅርም ድጋፍ ያደርግ ዘንድ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡

በክብር እንግድነት የተገኙት የኢ/አ/እ/ጉ/ጠ/ም/ቤት የሀጅና ኡምራ ዘርፍ ሀላፊና የምክር ቤቱ ስራ አስፈፃሚ አባል የሆኑት ሼህ አብዱልሀሚድ አህመድ አዲስ ለተዋቀሩት አመራሮች ከተሸከሙት ሀላፊነት አንፃር መዋቅሩን ከክፍለ ከተማ ባሻገር ወደ ወረዳ ጭምር በማውረድ ማህበረሰቡ በተለያየ ወቅቶች ለሚያነሳቸው ዘርፈ ብዙ ችግሮች አፋጣኝ ምላሽ መስጠት ላይ ትኩረት እንዲሰጡ መልእክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡

የአ/አ/እ/ጉ/ከ/ም/ቤት ም/ፕሬዝዳንት የሆኑት ሼህ ፈትሁዲን ሀጂ ዘይኑ በበኩላቸው አዲስ ለተዋቀሩት የክፍለ ከተማ አመራሮች በሀገር ሰላምና አንድነት ዙሪያ በከፍተኛ ሁኔታ መስራት እንደሚገባቸው ጥሪ አቅርበዋል፡፡

በፕሮግራሙ ላይ ተጨማሪ መልእክት ያስተላለፉት የአ/አ/ከ/ም/ቤት ዋና ፀሀፊ ሼህ ሁሴን በሸር በበኩላቸው በአንድነት ዙሪያ በከፍተኛ ሁኔታ ሊሰራበት እንደሚገባ በመጠቆም በጋራ፣በህብረትና በአንድነት መቆም መለኮታዊ ግዴታ መሆኑን በመጠቆም ከዚህም ባሻገር አንድነታችን በጠንካራ መሰረት ላይ የቆመ እና የተመሰረተ መሆን አለበት ለዚህ ታላቅ እና የተቀደሰ ተግባር ለስኬቱ ሁላችንም ዘብ መቆም አለብን ብለዋል፡፡

አያይዘውም ከሁሉ በላይ ፍትህና ፍትሀዊነት እንዲሁም ሚዛናዊነትን መሰረት ያደረገ አገልግሎት ለማህበረሰባችን ይደረስ ዘንድ ከፍተኛ ሚና መጫወት እንደሚገባቸው በመጥቀስ የተጣለባችው ሀላፊነት ከባድና ውስብስብ ቢሆንም በማዕከል ደረጃ ያለነው የስራ አመራሮች ከክፍለ ከተማዎች ጋር በመተጋገዝ እጅና ጓንት ሆነው ለመስራት ከምንጊዜውም በላይ ዝግጁ መሆናቸውን አብራርተዋል፡፡

በፕሮግራሙ ላይ የአ/አ/እ/ጉ/ከ/ም/ቤት የልማትና አደረጃጀት ዘርፍ ተጠሪ ኡስታዝ መሀመድ ዘይን ከድር መዋቅሩን በተመለከተ ገለፃ ያደረጉ ሲሆን፣ የአ/አ/እ/ጉ/ከ/ም/ቤት የመሳጅድና አውቃፍ ዘርፍ ተጠሪ ኡስታዝ መሀመድ አባተ አዲስ ስለተመደቡት አመራሮች መስፈርትን በሚመለከት ማብራሪያ አቅርበዋል።

የአ/አ/እ/ጉ/ከ/ም/ቤት የህግ ክፍል ተጠሪ ኡስታዝ ሱፊያን ኡስማን አዲሶቹ አመራሮች ከተለያዩ መንግስታዊና መንግስታዊ ካልሆኑ ተቋማት ጋር ሊኖራቸው የሚገባውን የህግ አግባብ አብራርተዋል፡፡

በፕሮግራሙ ላይ የፌደራል ጠቅላይ ሸሪአ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት ሼህ ሙባረክ ሼህ መሀመድአወል ለክፍለ ከተማ አመራሮች የቃለ-መሀላ መርሀ ግብር በማከናውን ፕሮግራሙ ተፈፅሟል፡፡

የአዲስ አበባ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ም/ቤት
ነሃሴ 17/2014ዓ.ም
አዲስ አበባ

Source ahmedin jabel telegram channel

ህወሓት የቅድመ ግጭት ጩኸቱን እያሰማ ነው ሲል የመከላከያ ሚኒስቴር ገለፀ‼️ህወሓቶች "የሰላም ድርድሩ ቴክኒካል ፈርሷል፣ መከላከያ ኃይሉን እያስጠጋ ነው፣ መከላከያ በከባድ መሳሪያ እየደበደበ...
23/08/2022

ህወሓት የቅድመ ግጭት ጩኸቱን እያሰማ ነው ሲል የመከላከያ ሚኒስቴር ገለፀ‼️

ህወሓቶች "የሰላም ድርድሩ ቴክኒካል ፈርሷል፣ መከላከያ ኃይሉን እያስጠጋ ነው፣ መከላከያ በከባድ መሳሪያ እየደበደበን ነው፣ ከላይ እስከታች የዕዝ ሰንሰለቱን ጠብቆ እየተፈፀመ ያለ ጥቃት ነው" ወዘተ በማለት የቅድመ ግጭት ጩኸታቸውን በስሙልኝ ፕሮፖጋንዳቸው እያስተጋቡ ይገኛሉ ሲል መከላከያ ሚኒስቴር ገልጿል።

ሚኒስቴሩ ዛሬ ባወጣው መግለጫ የሠራዊቱን ወቅታዊ ሁኔታ ባልተረጋገጡ፣ ባልተገቡ መረጃዎችና አሉባልታዎች የመዘገብ ወይም የማራገብ አሉታዊ ሙከራዎችም በአስቸኳይ እንዲቆሙ ሲል በጥብቅ አሳስቧል።
ምንጭ ቢቢሳ Amharic

 የ2014 ዓ/ም የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና ከመስከረም 30 እስከ ጥቅምት 11 ቀን 2015 ድረስ በሁለት ዙር እንደሚሰጥ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት አሳውቋል።ለዚህም ተማሪዎች ...
23/08/2022



የ2014 ዓ/ም የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና ከመስከረም 30 እስከ ጥቅምት 11 ቀን 2015 ድረስ በሁለት ዙር እንደሚሰጥ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት አሳውቋል።

ለዚህም ተማሪዎች እራሳቸውን እንዲያዘጋጁ ጥሪ አቅርቧል።

የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት የኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክተር አቶ ረዲ ሽፋ #ለኦቢኤን በሰጡት ቃል ፤ በአጠቃላይ በሁለት ዙር በሚሰጠው ፈተና ከ984,000 በላይ ተማሪዎች ፈተናውን እንደሚወስዱ ገልፀዋል።

ፈተናውን ከሚወስዱት ውስጥ የማህበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች ቁጥር 622,739 መሆኑን አመልክተዋል።

የማህበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች ብዛት ያላቸው በመሆኑ በመጀመሪያው ዙር ከመስከረም 30 እስከ ጥቅምት 3 /2015 አስቀድሞ ፈተናውን እንደሚሰጣቸው አቶ ረዲ ተናግረዋል።

የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች ቁጥር ደግሞ 361,279 ሲሆን በሁለተኛው ዙር ከጥቅምት 8 እስከ 11/2015 ፈተናውን እንደሚወስዱ አስረድተዋል።

ከዚህ ቀደም የነበሩ የፈተና ችግሮችን ለመፍታት ፈተናው በመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች እንደሚሰጥ አረጋግጠዋል ፤ ፈታኞቹ ደግሞ የዩኒቨርሲቲ መምህራን መሆናቸውን አሳውቀዋል።

በተጨማሪም ፤ ፈተናው ከዚህ ቀደም ከነበረው ከ4 ኮድ ከፍ ማለቱን ገልፀዋል።

ፈተናው ተዘጋጅቶ እየታተመ ሲሆን ፈተናው እስከሚሰጥበት ቀን ድረስ ተፈታኞች እራሳቸውን ማዘጋጀት እንዳለባቸውም አሳስበዋል።

Source tikhvah telegram channel

* ቡልቡሎየሀይቅ ቢስቲማ መንገድ " ቡልቡሎ " ላይ በጎርፍ በመቆረጡ ማህበረሰቡ ለእንግልት እየተዳረገ እንደሚገኝ የወረባቦ ኮሚኒኬሽን ገልጿል።የአካባቢው የቲክቫህ ቤተሰብ አባላትም በጉዳዩ ዙ...
23/08/2022

* ቡልቡሎ

የሀይቅ ቢስቲማ መንገድ " ቡልቡሎ " ላይ በጎርፍ በመቆረጡ ማህበረሰቡ ለእንግልት እየተዳረገ እንደሚገኝ የወረባቦ ኮሚኒኬሽን ገልጿል።

የአካባቢው የቲክቫህ ቤተሰብ አባላትም በጉዳዩ ዙሪያ መልዕክት የላኩ ሲሆን መንገዱ በጎርፍ በመቋረጡ ከፍተኛ የሆነ እንግልት እየደረሰባቸው እንደሆነ አስረድተዋል።

የወረባቦ ኮሚኬሽን ያናገራቸው የፖወርኮን መንድ ስራ ተቋራጭ ድርጅት የሀይቅ ቢስቲማ ጭፍራ መንገድ ግንባታ አስተባባሪ አቶ አለሙ አባይነህ ተከታዩን ብለዋል፦

" ድርጅታችን በአጠቃላይ መንገዱን ከመስከረም በኋላ ሙሉ ጥገና ያደርጋል። አሁንም በመንገዱ ላይ የተሰበሩና ለትራንስፖርት መስተጓጉል የሚፈጥሩ ቦታዎች ላይ ጊዜያዊ ጥገና እያደረግን እንገኛለን።

ነገር ግን ጊዜያዊ መፍትሄ ለመስጠት መንገዶቹ የተቆረጡበት ቦታ የወሰን ማስከበርና የሴሌክት ማቴሪያል እጥረት እያጋጠመ ነው "

የወረባቦ ወረዳ መንገድ ትራንስፖርት ኃላፊ አቶ ሁሴን ሰይድ በበኩላቸው ተከታዩን ብለዋል፦

" የሀይቅ ቢስቲማ መንገድ የአስፓልት መንገድ ለመስራት በፌደራል መንግስት ለተቋራጭ የተሰጠ በመሆኑ ወሎ ገጠር መንገድ ከጥገና አገልጎሎቱ ላይ አስወጥቶታል በዚህም መንገዱን እየጠገነ የሚያስተዳድረው ተቋራጭ ድርጅቱ ፖወርኮን ነው።

ፓወርኮን በአሁኑ ሰአት መንገዱን ሙሉ ጥገና ለማድረግ ክረምት ከመሆኑ ጋር ተያይዞ መጠገን ስለማልችል ሙሉ ጥገና ከመስከረም በኋላ ይደረጋል።

ነገር ግን ዛሬ ላይ ቡልቡሎ አውራጎዶና አካባቢ ሙሉ በሙሉ በጎርፍ በመቆረጡ ጊዜያዊ መፍትሄ በመስጠት መኪኖች እንዲተላለፉ ለማድረግ እየተሰራ ይገኛል።

ይህ የተቆረጠበት ቦታ ከወደፊት አንፃር ለጥገና በጣም አስቸጋሪ ስለሆነ በዚህ ሁለት ቀን ውስጥ በጋቢዎን መታሰር ይኖርበታል። "

ፎቶ፦ ወረባቦ ኮሚኒኬሽን፣ ABD
(ቲክቫህ ቤተሰብ)
Source. Tikhvah telegram channel

Address

Adama
NONE

Telephone

+251939902136

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Kashif media posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Kashif media:

Share